Pages

Pages

Saturday, September 22, 2012

የ ኢትዮጵያን መጪ ዘመን የሚያመላክቱ ያለፉት የ 24 ሰዓታት ክስተቶች

ትናንት መስከረም 11 እና ዛሬ መስከረም 12/2005 ዓም ሀገራችን ፖለቲካ መድረክ ላይ መጪውን ዘመን የሚያመላክቱ ሶስት ሁኔታዎች ታይተዋል። ነገን በደንብ የሚያመላክቱ ኢትዮጵያውያን በውል ልንመለከተው የሚገባም ይመስለኛል።ኢህ አዲ ወደቀደመው መዝሙሩ አቶ መለስ ሞት በኋላ ሙሉ በሙሉ መመለሱን፣ ለለውጥ ዝግጁ አለመሆኑን በደንብ አረጋግጧል።በነገራችን ላይ አቶ ሃይለማርያም '' በመተካካት ኢህአዲግ ባህል መሰረት ወደ ስልጣን መጡ'' የሚለው ፈፅሞ ሐሰት ነው።መተካካት የሚባለው አቶ መለስ ፈቃዳቸው ስልጣን ለቀው ቢሆን ነበር እንጂ ሞት ሲለዩ በቦታቸው ሌላ ሰው ማስቀመጥ መተካካት አይባልም።
መጪውን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች  

መጪውን አመላካች 1 :-  ''አሁንም አጨብጭቡ!''
መስከረም 11/2004 ዓም  (Sep.21/2012)  አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በ ኢህአዲግ ምክርቤት ለማፀደቅ አቶ አባ ዱላ ምክርቤቱን እንዲያፀድቅ ሲጠይቁ ዝምታ ሰፈነ ቀጠሉና አባ ዱላ እንዴት እንደሚጨበጨብ ለማሳየት እጃቸውን እንደማጨብጨብ ሲያደርጉ የ ምክርቤቱ አባላት ማጨብጨብ ጀመሩ።
መጪውን አመላካች 2 - ''ጉድጓድ እስኪገባ?''
''መተካካት ማለት አዲሱን መሪ  በ ሩቅ  ሆኖ መታዘብ ማለት አደለም----- በሕይወት እስካለን ጉድጓድ እስኪገባ ድረስ ድጋፍ መስጠት አለብን---- የትም አንሄድም።----ህዝቡ እስካለ ድረስ አዲሱ አመራር ወለም ዘለም የሚልበት ዕድል አይኖረውም'' አቶ ስዩም መስፍን መስከረም 12/2005 ዓም  (Sep.22.2012) ለ ኢ ቴ ቪ  ከሰጡት መግለጫ።
መጪውን አመላካች 3 - ''ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ------!!!''
''ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ'' በማለት ከ 20 ጊዜ በላይ የጠራው የ ህዋሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ መስከረም 12/2005 (Sep.22.2012) ዓም በ ኢ ቴ ቪ ያስነበበው መግለጫ። በመጨረሻ እንዲህ አለ:-
''በተግባር የተፈተነው የድርጅታችን መስመሮች  ጓድ መለስ እንዳለው በድርጅታችን መቃብር ላይ ካልሆነ በቀር  በማንኛውም መንገድ ለ ድርድር እንደማይቀርብ ደግሞ ደጋግሞ ያረጋግጣል''
አሁንም አሳዛኝ ''ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ'' ነገር ገባን። ኢህአዲግ እራሱን ለማረም አልቻለም። ሁሉ ነገር እንደነበረ ይቀጥላል፣ ፖለቲካዊም፣ማህበራዊም ምጣኔ ሃብታዊም  ሽግርግር የለም።በ ኢህአዲግ  በ ክልል እና በ ቋንቋ የተከፋፈለ ትውልድ ነው የምንወርሰው? ይች ነች በ ኢህአዲግ  ቅኝት ውስጥ የምትኖረው ኢትዮጵያ?
 







 

3 comments:

  1. mikerew mikerew kalsema mekera ymkerew new weyane.

    ReplyDelete
  2. እራስ የሚያም ነገር ነው። አሁንስ በዛ ቤተክርስቲያንን የዘረፈው መንግስት ብሎ ብሎ በቀደም እለት በ አቦይ ስብሃት በኩል ''ኦርቶዶክስ ስልጣን ባለመያዙ ተደስተናል'' ተባልን። ይህን ክላሲካል ስሰማ ውስጤ ደማ። ለ እራሴም ለሃገሬም አለቀስኩ። እመብርሃን አንቺ አጽናኚን።ጎረቤቶቸም እኩል ቁጭ ብለው አብረውኝ አለቀሱ።ቀጥለን ለምን አለቀስን? ብለን የቀረበውን ቡና ሳንጠጣ ተነጋገርን።የሚገርም ቅዳሜ አሳለፍኩ።መብታችን በ እጃችን ነው የሁላችንም ቃል ነበር።የ ዛሬን ቅዳሜ አልረሳትም።ክላሲካሏም ከ ውስጤ ተቀበረች። ይህን አስተያየት እንድጽፍ ያዘዙኝ አብሮ አደግ ጎረቤቶቸ ናቸው።

    ReplyDelete
  3. WEYNE HAGERE
    MEQELEJA HONSH???
    ENGA AHUN SEW ENBALALEN? WSHETAMOCH NEN.HAGEREEEEEEEEEEEE

    OOOOOO!!! LBEL?

    ReplyDelete

አስተያየትዎን እዚህ ላይ ይስጡ