ትናንት መስከረም
11 እና ዛሬ
መስከረም 12/2005 ዓም በ
ሀገራችን የ
ፖለቲካ መድረክ
ላይ መጪውን
ዘመን የሚያመላክቱ
ሶስት ሁኔታዎች
ታይተዋል። ነገን
በደንብ የሚያመላክቱ
ኢትዮጵያውያን በውል
ልንመለከተው የሚገባም
ይመስለኛል።ኢህ አዲ
ግ ወደቀደመው
መዝሙሩ ከ
አቶ መለስ
ሞት በኋላ
ሙሉ በሙሉ
መመለሱን፣ ለለውጥ
ዝግጁ አለመሆኑን
በደንብ አረጋግጧል።በነገራችን
ላይ አቶ
ሃይለማርያም '' በመተካካት
የ ኢህአዲግ
ባህል መሰረት
ወደ ስልጣን
መጡ'' የሚለው
ፈፅሞ ሐሰት
ነው።መተካካት የሚባለው
አቶ መለስ
በ ፈቃዳቸው
ስልጣን ለቀው
ቢሆን ነበር
እንጂ በ
ሞት ሲለዩ
በቦታቸው ሌላ
ሰው ማስቀመጥ
መተካካት አይባልም።
መጪውን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች
መጪውን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች
መጪውን አመላካች 1 :- ''አሁንም አጨብጭቡ!''
መስከረም 11/2004 ዓም (Sep.21/2012) አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በ ኢህአዲግ ምክርቤት ለማፀደቅ አቶ አባ ዱላ ምክርቤቱን እንዲያፀድቅ ሲጠይቁ ዝምታ ሰፈነ ቀጠሉና አባ ዱላ እንዴት እንደሚጨበጨብ ለማሳየት እጃቸውን እንደማጨብጨብ ሲያደርጉ የ ምክርቤቱ አባላት ማጨብጨብ ጀመሩ።
መጪውን አመላካች 2 - ''ጉድጓድ እስኪገባ?''
''መተካካት ማለት አዲሱን መሪ በ ሩቅ ሆኖ መታዘብ ማለት አደለም----- በሕይወት እስካለን ጉድጓድ እስኪገባ ድረስ ድጋፍ መስጠት አለብን---- የትም አንሄድም።----ህዝቡ እስካለ ድረስ አዲሱ አመራር ወለም ዘለም የሚልበት ዕድል አይኖረውም'' አቶ ስዩም መስፍን መስከረም 12/2005 ዓም (Sep.22.2012) ለ ኢ ቴ ቪ ከሰጡት መግለጫ።
መጪውን አመላካች 3 - ''ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ------!!!''
''ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ ፣ ጓድ መለስ'' በማለት ከ 20 ጊዜ በላይ የጠራው የ ህዋሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ መስከረም 12/2005 (Sep.22.2012) ዓም በ ኢ ቴ ቪ ያስነበበው መግለጫ። በመጨረሻ እንዲህ አለ:-
''በተግባር የተፈተነው የድርጅታችን መስመሮች ጓድ መለስ እንዳለው በድርጅታችን መቃብር ላይ ካልሆነ በቀር በማንኛውም መንገድ ለ ድርድር እንደማይቀርብ ደግሞ ደጋግሞ ያረጋግጣል''
አሁንም አሳዛኝ ''ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ'' ነገር ገባን። ኢህአዲግ እራሱን ለማረም አልቻለም። ሁሉ ነገር እንደነበረ ይቀጥላል፣ ፖለቲካዊም፣ማህበራዊም ምጣኔ ሃብታዊም ሽግርግር የለም።በ ኢህአዲግ በ ክልል እና በ ቋንቋ የተከፋፈለ ትውልድ ነው የምንወርሰው? ይች ነች በ ኢህአዲግ ቅኝት ውስጥ የምትኖረው ኢትዮጵያ?
3 comments:
mikerew mikerew kalsema mekera ymkerew new weyane.
እራስ የሚያም ነገር ነው። አሁንስ በዛ ቤተክርስቲያንን የዘረፈው መንግስት ብሎ ብሎ በቀደም እለት በ አቦይ ስብሃት በኩል ''ኦርቶዶክስ ስልጣን ባለመያዙ ተደስተናል'' ተባልን። ይህን ክላሲካል ስሰማ ውስጤ ደማ። ለ እራሴም ለሃገሬም አለቀስኩ። እመብርሃን አንቺ አጽናኚን።ጎረቤቶቸም እኩል ቁጭ ብለው አብረውኝ አለቀሱ።ቀጥለን ለምን አለቀስን? ብለን የቀረበውን ቡና ሳንጠጣ ተነጋገርን።የሚገርም ቅዳሜ አሳለፍኩ።መብታችን በ እጃችን ነው የሁላችንም ቃል ነበር።የ ዛሬን ቅዳሜ አልረሳትም።ክላሲካሏም ከ ውስጤ ተቀበረች። ይህን አስተያየት እንድጽፍ ያዘዙኝ አብሮ አደግ ጎረቤቶቸ ናቸው።
WEYNE HAGERE
MEQELEJA HONSH???
ENGA AHUN SEW ENBALALEN? WSHETAMOCH NEN.HAGEREEEEEEEEEEEE
OOOOOO!!! LBEL?
Post a Comment