- የ አርባ ዓመቱ (ከ 1965 እስከ 2005 ዓም) የኢትዮዽያ የ መከራ ዘመን ያበቃል !
- በ ኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የ አስራ አራት ቀናት ሱባዔ ታወጀ፤
- የዛሬዋ ቀን ለመድረስ አርባ አመት ፈጀብን። በ አርባ ቀን የሚያልቀው ስራ በ እኛው ትዕቢት አርባ አመት አደረግነው። የ እስራኤላውያን ከ ግብጽ ወደ ከነአን ጉዞ የ አርባ ቀኑ አርባ አመት መሆኑን ልብ በሉ።ኢትዮዽያ በደስታዋም ሆነ በሃዘንዋ ከ አምላኳ በቀር የምታማክረው፣የምታለቅስበት ቦታ የላትም ፤
- ባለፉት አርባ አመታት ወደ ዋይት ሃውስ ማልቀስ ለምደናል፤
- ባለፉት አርባ አመታት ተፈጥሮን እንቆጣጠራለን (በስራ ለመትጋት የተጠቀምንበት ቢሆን ባማረ) ብለን ከ ፈጣሪ ጋር መገዳደር ለምደናል፤
- ባለፉት አርባ አመታት ከ መገናኛ ብዙሃኖቻችን ጀምሮ ሁለት ጸጉር ያወጣው ሁሉ ከ ቤተ እምነቱ እስከ ቤተ መንግስቱ ድረስ ውሸት ለምዶብን ካልተዋሸ አይኖርም የምንል ደፋሮች ሆነናል፤
- ባለፉት አርባ አመታት ኢትዮዽያውያን የምንታወቅበት ስርዓታችን፣እምነታችን፣ሰው አክባሪነታችን፣መልካም እሴቶቻችን ሁሉ ሙዜም ሊገቡ ዳር ዳር ብለዋል።
አሁን እነሆ አርባ የመከራ እና የ ጉድለት ዘመናችን ሊያልፍ የደረሰ መሰለ። እንዴት? በሉኝ።
በ አርባ አመት ለመጀመርያ ጊዜ በ ኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የ አስራ አራት ቀናት ሱባዔ ታወጀ።ከ እዚህ በፊት አልታወጀም ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። እንደ እዚህ አምላክ በፈቃዱ ከ ቤተመንግስትም ከ ቤተ ክህነትም ሰው ወስዶ ምልክት ያሳየበት ዘመን የለንም:: ከ ሊቅ እስከ ደቂቅ የሚሳተፍበት፤ አምላክ ቢያንስ ከ አንድ በላይ ጻድቅ የሚያገኝበት፤ በትክክል ቤተመንግስቱን እና ቤተ ክህነቱን አንኳኩቶ የመጣ አምላክ ወደ እርሱ ከ አርባ አመታት መታተር በኋላ አቅማችንን አውቀን ከፊቱ ልንንበረከክ ነው እና በትክክል የሚሰማን ብሎም ህዝቡን በፍቅር፤ሃገራችንን በክብር፤ ለ ሁለት የተከፈለችውን ቤተ ክርስቲያን በቃልኪዳኑ ወደ አንድነት እንደሚመልስ እርግጠኛ እንሁን።
ቅዱስ ሲኖዶስ ሱባዔ ማወጅ አይደለም አንድ ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ¨ልዩ ምህላ ስለ ሃገር እንያዝ¨ ብለው ገና ሲያስቡ ¨ሃገር አማን ነው ምን አስባችሁ? ነው¨ ተብለው በ ፖሊስ የተበተኑበትን አጋጣሚ (በ ጅማ ሰማዕታት ጊዜ) የነበረ መሆኑን ካልረሳን አሁን አምላክ በረቂቅ ጥበቡ ብሔራዊ የ ምህላ ጊዜ መታወጁ እጹብ ድንቅ ነው።
ይህንን ሱባዔ የምንችል ¨መታዘዝ ከመስዋዕትነት ይበልጣል¨ እንዳለን ቅዱስ መጽሃፍ ታዘን የተባለውን በስርዓት እንከውን።ይህ ካቃተን ግን ከመተቸት ተቆጥበን አንደበታችንን እንግታ። ዛሬ ምህላ ለምን? እያልን አንመራመር። የታወጀው አስራ አምስት አመት አደለም አስራ አምስት ቀን ነው።
ቦሌ ደብረ ሳሌም መድሃኔ ዓለም፣መጥምቀ መለኮት ዮሃንስ ወ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን
ይህ ሱባዔ የ ቤተ ክርስቲያን የ አንድነት ተምሳሌትም ነውና ከውይይቱ በፊት ሱባዔ ያወጀው ቅዱስ ሲኖዶስን በመደገፍ በውጭ የሚኖሩ አባቶቻችንም በስራቸው ላሉት ካህናት ቢያሳስቡ እና አብሮ ሁሉም ለሃገር፣ለቤተ ክርስቲያን ብሎም ለ መላው አለም ከሁሉም በላይ ስለ እያንዳንዳችን በደል ¨ይቅር በለን!¨ ማለት ምን ሃጢያት አለው? እናም አባቶች በልጅነት አንደበት የምንጠይቃች ሁን ቸል ሳትሉ ብታሳስቡልን እንለምናችኋለን(እኔ ማለቴ ነው የሁሉም ምዕመን ሃሳብ እንደሚሆን እየገመትኩ)።
በፈቃዳችን ሳይሆን ፈቅዶልን፤ በችሎታችን ሳይሆን በደካማነታችን ደግፎን ከ ሊቅ እስከ ደቂቅ የሚጮህበት¨አምላከ ሙሴ ወአሮን ወ አምላከ ዕዝራ!¨ ብለን እንለምነው በ አርባ አመት የፈተና ዘመናችን የምናገኘው ነውና የ አርባ ዓመቱ የኢትዮዽያ የ መከራ ዘመን ያበቃል (ከ 1965 እስከ 2005 ዓም)::
መልካም አዲስ ዘመን ይሁንልን።
ጌታቸው በቀለ
ኦስሎ፣ ኖርዌይ
Read also http://www.dejeselam.org/2012/09/blog-post_5.html#more
በፈቃዳችን ሳይሆን ፈቅዶልን፤ በችሎታችን ሳይሆን በደካማነታችን ደግፎን ከ ሊቅ እስከ ደቂቅ የሚጮህበት¨አምላከ ሙሴ ወአሮን ወ አምላከ ዕዝራ!¨ ብለን እንለምነው በ አርባ አመት የፈተና ዘመናችን የምናገኘው ነውና የ አርባ ዓመቱ የኢትዮዽያ የ መከራ ዘመን ያበቃል (ከ 1965 እስከ 2005 ዓም)::
መልካም አዲስ ዘመን ይሁንልን።
ጌታቸው በቀለ
ኦስሎ፣ ኖርዌይ
Read also http://www.dejeselam.org/2012/09/blog-post_5.html#more