ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, January 31, 2012

ኢሳት ( ኢትዮጵያ ሳትከፋ ትኑር)

''ተ ቦርን'' የሚለውን ስም ''ታዲያስ አዲስ'' በተባለው ሸገር ኤፍ ኤም ፕሮግራም ላይ የማያውቀው ያለ አልመስልህ አለኝ:: ''ተ ቦርን'' ቅጥል ስም ነው እንጂ ስሙ ተወልደ በየነ ይባላል:: በኪነቱ አለም በ ሃያሲነትም ሆነ በሙዚቃ ግጥም ቅንብር  ስሙ ይወሳል:: አንድ ጊዚ እንዲያውም በሃገራችን ያሉትን ዘፈኖች ከ ባእዳን ዘፈን ዚማ የተቀዱትን እየለየ አሰምቶን ጉድ አጀብ አስብሎ ነበር::
ለጠቅላላ እውቀት እንዲሆናችሁ ''ተ ቦርን'' ማለትም ተወልደ በየነ የ  ታዋቂው አርቲስት እና አክቲቭስትታማኝ በየነ የ ስጋ ወንድም መሆኑን ሳትነግረን እንዳትሉ ነገርኩዋችሁ አሁን::


ባለፈው ሳምንት በኢሳት  ራድዮ ከ ምድረ አሚሪካ ሃሳቦቹን ለ ወገኑ የ ኢትዮጵያ ህዝብ ሲያካፍል አመሸ:: እናም ብዙ ሃሳቦች ያሉት ወጣት ነው::

በ እዚሁ ኢሳት ( ትርጉሙ ኢትዮጵያ ሳትከፋ ትኑር ብየዋለሁ) ራድዮ ላይ ቀርቦ ከነገረን ቀልድ ላወጋችሁ ነው::
'' አንድ ቀን ጠቅላይ ሚንስትሩ ከልጃችው እና ባለቢታችው ጋር በአይሮፕላን ይጓዛሉ እና በጉዞ መሃል አንድ መቶ ብር አንስቸ ወደ ምድር ልወርውርና አንድ ኢትዮጵያዊ ላስደስት ይላሉ:: ባለቢታችው ታድያ ለምን ሃምሳ ሃምሳ ብር አርገህ ሁለት ኢትዮጵያዊ አታስደስትም አለች ልጂት ደሞ ተነሳችና ለምን ብሩ አስር አስር ተዘርዝሮ አስር ወገናችን አይደሰትም? አለች በ እዚህ ጊዚ የ አይሮፕላኑ አብራሪ ካፒቲን ዘወር አለና ለምን እራስዎ ወርደው ሰማንያ ሚልዮን ህዝብ አይደሰትም?'' አላቸው'' ብሎ አሳቀን
''ተ ቦርን'' ስለ ሃገረ ኢትዮጵያ ገና ብዙ የምነግራችሁ አለ ከ ሆዴ ያለ ስላለ ገና አለ ገና...እያልን ከ ኢሳት ( ኢትዮጵያ ሳትከፋ ትኑር) የ 24 ሰአት ራድዮ እና ቴሊቭዥን መስኮት ብቅ እንደሚል ቃል ገብቶልናል::''ታዲያስ አዲስ'' ''ተ ቦርን'' (ኢሳት-ኢትዮጵያ ሳትከፋ ትኑር)......አበቃሁ::

4 comments:

Anonymous said...

weyne TE BORNYE HEDKBN?

Anonymous said...

ESAT we love you

Anonymous said...

Thanks Gech

Anonymous said...

yigermal weyne TE BORNYE HEDKIBN?

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።