ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, February 1, 2012

'' እያከበሩ ማፍረስ'' ጠቅላይ ሚንስትሩ የተናገሩት

'' እያከበሩ ማፍረስ''  ጠቅላይ ሚንስትሩ  የተናገሩት

'' እያከበሩ ማፍረስ'' የምትለው አባባል  የ  ዛሬ ሶስት  ዓመት ገደማ ጠቅላይ ሚንስትሩ  የተናገሩት ትዝ ይለኛል።
ወቅቱ ዝናብ በመጠኑ የሚጥልበት ወቅት ነበር። ።እለቱ ቅዳሜ ነበር ከረፋዱ አራት ሰዓት አካባቢ ቦሌ መንገድ የሚገኘው የ ''ሚሊንየም'' አዳራሽ ውስጥጠቅላይ ሚንስትሩ የ ቀን አበል የተከፈላቸውንም ጭምር ይዘው  አልፎ አልፎ እንደሚአደርጉት የ ፓርትያቸውን ደጋፊ ወጣቶች ሰብስበው ንግግር እያረጉ ነው።የለበሱት ጃኬት እና ያረጉት የወጣት ኮፍያ ከ ወጣቶቹ ጋር አመሳስሏቸዋል።


ፕሮግራሙ በቀጥታ ይተላለፍ  ስለነበር ቴሌቪዥኔን ከፈትኩ እና አህቴ ያቀረበችልኝን ቡና ፉት ማለት ጀመርኩ
ጥያቄዎች ይጠየቃሉ ይመልሳሉ። ከተጠየቁት ጥያቄ ውስጥ እና ከመለሱት መልስ ውስጥ ሁሌ ጆሮዬ ላይ የምትቾህብኝ አንድ ጥያቄ እና መልስ አለች።ጀባ ልበላችሁ። የምትገርም መልስ ይዛለችና።

ጥያቄ- ''---በ ትግል ልምድ፣በ ኑሮም፣በኃላፊነትም ፣ብዙ ተሞክሮ አለዎት እና ለ አኛ ለውጣቶች ምን ይመክሩናል?''
የ አትዮጵያ ከፍተኛው ባለስልጣን መልስ- ትልቁ መማር እንዳለባቸው አንክሮ ከሰጡ በሁአላ እንዲህ አሉ '' በወጣትነት ጊዜዬ ብዙ ነገሮች ዛሬውኑ ካልተሰሩ ብዬ የሄድኩባቸው ነገሮች እንዳሉ አስታውሳለሁ ይሄ ደሞ ማንም ወጣት ውስጥ ያለ ስሜት ነው።እናንተ ቢቀየሩ ቢጠፉ የምትሏቸው ነገሮች ይኖራሉ ግን ባንድ ቀን ለመቀየር አትሞክሩ ብዬ ነው የምመክራችሁ ።እያከበራችሁ ማፍረስ ማወቅ አለባችሁ ባንድ ቀን ላፍርስ ብትሉ ብዙ ነገር ይበላሻል እና ጎጂ የምትሉትን ነገር እያከበራችሁ አፍርሱት ''

የ ቡና ስንዬን እንደያዝኩ ቀረሁ። ፕሮግራሙ ቀጥታ ይተላለፍ ስለነበር ልክ እንደ ቡናው እንደወረደ ነው የሰማሁት።በምሽቱ ፕሮግራም ላይ ይህ አነጋገር  ከ ንግግራቸው ውስጥ ወጥቶ መቅረቡንም አልዘነጋውም::የ ቡና ስንየን  ወደ ረከቦቱ አየመለስኩ ሃሳብ ገባኝ:: የሆነ የተደበቀ ነገር ያገኘሁ ያህል ተሰማኝ።በቀጥታ የሚተላለፍ የ ቴሌቭዝን ፕሮግራም አንዴት ጥሩ ነው ለካ! አልኩ አሁንም ለራሴ ቀጥየም   ''እያከበሩ ከማፍረስ'' ስህተትን ነግሮ ፊት ለፊት መተማመን ይሻላል እኮ አልኩት  ለ ቴሌቪዥኑ ።ምክንያቱም እየተከበረ እየፈረሰ ያለው ሃሳብም ሆነ ተቁአም ሁሌ የተወደደ፣ጥሩ የሰራ አየመሰለው ወዳጅ አና ጠላቱን ሳይለይ መጉዓዙ በ አጅጉ ይጎዳዋል። ምናልባት ጠባቂ መላክ ካለው ቀድሞ ያድነው እንደሆነ ነው አንጂ።
አትዮጵያ ውስጥ ላለፉት አመታት እየተከበሩ የፈረሱ ብዙ ነገሮችን አይተናል:: መጀመርያ ተከበሩ: ቀጥለው አቃቂር ወጣላቸው  በሁአላ ግን እየተከበሩ ፈረሱ::

No comments:

መንግስት ከዲፕሎማሲያዊ መፋዘዝ ይውጣ! የአረብ ሊግ በአባይ ግድብ አንጻር የወሰነውን የጸብጫሪነት ተግባር በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የምላሽ መግለጫ ብቻ የሚበቃ ሊሆን አይገባም።መንግስት ያልሰራው ግዙፍ ስራ ኢትዮጵያን ለአደጋ እንዳያጋልጣት ያሰጋል።

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያቤት መንግስት በፍጥነት ሊሰራቸው የሚገቡት አምስት ወሳኝ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት ========= ጉዳያችን አለርት ========= የአረብሊግ አንዱ የሚታወቅበት መለያው እንደባዶ ቆር...