ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, February 8, 2012

''ቡና ጠጡ'' የኢትዮጵያውያን የመረጃ ምንጭ

''ቡና ጠጡ'' የኢትዮጵያውያን የመረጃ ምንጭ 
በ እኛ  ኢትዮጵያውያን ዘንድ ''ቡና ጠጡ'' የምትለው ጥሪ የማናውቅ የለንም።ቢያንስ ልጅ ሆነን ''ሂድ ማሙሽ አልያም ሚሚ እገን ቡና ጠጡ በል ወይም በይ'' ተብለን  ስንላክ አድገናል።እኛም  አድገን '' ካፈ'' ቤት ጎራ ብለን ቡና  እየቀመስን  የ ልባችንን ከ ወዳጅ ዘመድ  ጋር ያላወጋን  ማን ነን? ሰሞኑን አንድ ወዳጀ  ቡና እየጠጣ የተነሳውን  ፎቶ  አየሁ እና ብዙ ነገር ስለ ቡና ትዝ አለኝ። በመቀጠል  ግን ስለ ቡና ያነበብኩትን እና ያስተዋልኩትን ትንሽ ማለት ፈለግሁ።

ቡና  ለ እኛ ለ ኢትዮጵያውያን ከ ገጠር እስከ ከተማ   የሚጠጣ ትኩስ መጠጣችን ነው። ስለ ቡና አመጣጥ ስረ መሰረት የ እንግሊዝኛው ''አንሳይክሎፕድያ'' በ አንድ ሲኒ ቡና ስእል ስር እንዲህ የሚል ፅሁፍ በ ማብራርያነት ያስነብበናል :- 
''ቡና መልኩ ጥቁር አልያም ቡናማ ሲሆን የተገኘው ከ ኢትዮጵያ ነው '' ይላል ( http://en.wikipedia.org/wiki/Coffee)
አዎን ቡና አሁን ላለችው ዓለም የራሱ  ድርሻ  አንዳለው ብዙዎቻችን ልብ ያልነው አይመስልም:: ለ እንዱስትሪው አብዮት ዋነኛ የ አዳዲስ ሳይንሳዊ፣ፖለቲካዊ፣አና ምጣነሃብታዊ ሃሳቦች መፍለቅያነት ምክንያት ከነበሩት አንዱ  የ ኢንዱስትሪ አብዮት መጠንሰሻ የነበረችው  የ እንግሊዝ የቡና መጎንጫ ቤቶች ''ኮፊ ሃውስ '' ይባሉ የነበሩት ቤቶች ሚና ቀላል አንድልነበር ታሪክ ያስረዳናል:: 



ለ አዲሱ ዘመን እሳቤ የመወያያ መድረክ እና ሃሳብ ማፍለቂያ ቦታ ሁሉ የ  ''ኮፊ ሃውስ ''ድርሻ በ አገናኝነት የማይናቅ ነበር ::ይሄው ሂደት አድጎም አለማቀፍ የ ቡና  መጎንጫ ''ስታርባግስ '' በ ሶስቱ ተማሪዎች በ ጃሪ ባልድውን፣ጎርደን ቦውከር እና ዘፍ ዘይግል የዛሬ ፬፪ ዓመት በ ሞቀው የ ሲያትል ገበያ ስፍራ ተከፈተ።(http://en.wikipedia.org/wiki/Coffee#Coffeehouses)
 ይህ ብቻ አደለም በዛሬው የሰለጠነው ዓለም ከ ሳይቲስት አስከ ተራው ሰው፣ ከ ፕሬዝዳንት አስከ ቢልገት (የ ማይክሮ ሶፍት አስገኚ) ቡና ሳይጠጡ ለ እዚህ ሁሉ ስኬት አንዳልበቁ አንዳንዴ ሳስበው የ ቡና አምራች ሀገሮች የ ኤኮኖሚ  እቀባ አድርገናል ቢሉ(ደግነቱ ለማለት አቅምም ልብም ይጠይቃል እንጂ) አለምን የማተራመስ አቅም ያለው የ ብዙ ሀገሮች የ ካቢኔ ሚኒስትሮች ስብሰባ እና የ ዓለም አንቱ የተባሉ ኩባንያዎች የ ቦርድ ስብሰባ ባግባቡ ላለመደረጉ ምክንያቱ ቡና በሆነ ነበር። ይህ ብቻ አደለም የ እቀባው የ ህመም ደረጃ  የሚታወቀው ከ እረጅም ጊዜ በሁአላ ሳይሆን  በሚቀጥለው ቀን ያውም ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ መሆኑ  እና ማዛጋቱም በ እለቱ ስለሚጀምር እቀባው አደገኛ እና በ ፈረንጆቹ አባባል ''ታርገት ፉል '' የሚባል እንደሚሆን ለማወቅ ብዙም ሳይንቲስት መሆን አያስፈልግም:: እንድያውም የነዳጅ እቀባ ጊዜ እና የማሰብያ ወቅት አለው:: ቡና ግን ቡና ግን ስለ እቀባው ለማውራት እራሱ ቡና መጠጣት ይፈልጋል::  የ አዚህ አይነት ትብብር አምራቾቹ አንዳይኖራቸው አንደደሄዩ አንደኖሩ መፀለይ ወይም  አውጣን  ማለት ብቻ ነው የ አደገው ዓለም ሥራ መሆን ያለበት:: 
ቡና በሀገራችን አጠጣጡ   አንደ አውሮፓውያን አና አሜሪካውያን ለብቻ ጨልጦ  መሮጥ አይነት አይደለም።በ ቀጠሮ፣በ እርጋታ ለ ሀገራዊውም ሆነ ሰፈራዊ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች ላይ እየተወያዩ  ብሎም ውሳኔ እያሳለፉ  እንደሆነ ልብ ይሏል ። ኢትዮጵያውያን ቡና እየጠጡ ብዙ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ በመረሻም ውሳኔ ያሳልፋሉ። ልብ አላልነው እንደሆነ እንጂ ወላጆቻችን  ሳያስቡት ቡና እየጠጡ፣ያልተወያዩበት፣ያላበጠሩት፣ያልዳሰሱት ፣አንድ አም ያልያዙበት እና በጋራ ያልወሰኑትጉዳይ ምን አለ?  ( ራድዮ እና ቴሌቪዥኑ ውሳንያቸውን ባያነብላቸውም)  አስኪ ልብ በሉት።ኢትዮጵያን ቡና እየጠጡ የወሰኑትን   ነገር ማን ይፈታዋል?
፩/ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ

ቡና ሲጠጡ ጎረቤቱ ይሰበሰብና አቦል ላይ አንዲህ ይወራል:-
-ዛሬ ዜና ሰማሽ?
-አዎ ሰማሁ።
-አይገርምሽም
-ምን ይገርማል ጉዳዩ አኮ ምን መሰለሽ-?-----እገለ አንደነገረኝ ታድያ  በ ''ዲሽ'' ቲቪ  አይቶ ነው  የነገረኝ እና ------ነው አሉ።
አቦል ጀባ ተብሏል ቡናው--- አንዲህ ይወያያሉ-----ነገ ሌላ ቡና አለ ትናንት የተነሳው ሃሳብ መረጃ ተሰብስቦበት ዳብሮ ውይይት እንደገና  ይደረግበታል። ከ ዛሬ ፲ ዓመት በፊት አንዲት የ ብሪታንያ ጋዜጠኛ ''ፎከስ ኦን አፍሪካ'' በተሰኘው የ ቢቢሲ ፕሮግራም ላይ በወቅቱ በነበረው የ ኢትዮ-ኤርትራ የ ድንበር ውዝግብ ላይ ህዝቡ ምን ይላል እንዴት እየተወያየ ነው ተብላ ስትጠየቅ  እንዳለቺው
'' አትዮጵያውያን በድንበር ውዝግቡ ጉዳይ ላይ በ ራድዮ እና ቲቪ ከሚሰሙት በተሻለ   የተውያዩትም ሆነ የወሰኑት ቡና ላይ ነው ።ብዙ መረጃዎችን የሚቀያየሩት አዚሁ ላይ ነው::ቡና ላይ አትዮጵያውያን ይወያያሉ፣መረጃ ይቀያየራሉ፣ያልተፃፉ ትልልቅ ውሳኔዎችንም  ያሳልፋሉ'' ብላ የተናገረችውን አስታውሳለሁ::

፪/ ማህበራዊ ጉዳዮች
ቡና ላይ እናቶች ይሰበሰቡ አና አንዲህ ይላሉ-
-አንቺ  እገሊትን ለምን ተጣላሻት?
- ተይኝ የ አሷን ነገር----አርጋኝ------ከዛም አንዲህ አርጋኝ----ከዛም----
-በይ ''ይቅር በሉ ይቅር እላለሁ'' ብሏል አምላክ። አሁን ጠርቼ ይቅር አባብላለሁ----አንቺም ይቅር በያት። እርቅ ይከወናል።
- አንቺ ልጅሽን ለምን አትመክርያትም ከ እገሊት ጋር አየሁአት አሱ አኮ ስርዓት የለውም------ምከር
-እውነትሽን ነው። እንኩዓን ነገርሺኝ።አላቅም ነበር።ዛሬውኑ እመክራለሁ።
 ----እዚህ ቦኖ ውያ ዝቅ ብሎ አዲስ የተከራዬ ሰው አለ ታቁታላቺሁ?
-አረ አላቅም ግን የሚሰራው----ነው አሉ-----
-አይመስለኚም ሥራ የለውም ሌሊት ነው የሚገባው----ምን እንደሚሰራ አይታወቅም -----።
የ ቀድሞውን የ ግብፅ ፕሬዝዳንት ሙባረክን አዲስ አበባ ሊገሉ የሞከሩት ''እስላማዊ ወንድማማች'' ህብረት ሰዎች (ዛሬ  የ ግብፅን ምክርቤት አየተንጎራደዱበት አንደሆነ ቢነገርም) ያን ጊዜ የተያዙት አዲስ አበባ ላይ በሰሩት ወንጀል ተከራይተውበት ከነበሩበት ቦታ በ ፀጉረ ልውነታቸው የ ሰፈሩ ሰዎች  ቡና ላይ መረጃ በተቀያየሩ እናቶች ውይይት  መሆኑን የ ወቅቱ የ ፖሊስ ፕሮግራም ዘገባ ላይ ሕብረተስቡን ሲያመሰግን  መጠርጠር ክፋት የለውም::
፫/ ምጣኔ ሃብታዊ

-እናንተየ ጤፍ ስንት ገባ?
- ዛሬ አህል በረንዳ ሄጄ------ይሄን ያህል ሆኗል።
-በርበረ ግን ቀንሷል
-ስንት ገባ? ለነገሩ ታህሳስ አደል ወሩ መቀየር አለበት
-ቅቤ ስትገዙ ግን ከ-------ግዙ።
የ ወቅቱ ገበያ ይዳሰሳል:: ሁሉም ከ ውሎው እና ከ ሰማው ለሌላው ያካፍላል:: የ ዋጋ መውጣት እና መውረድ ይታወቃል::የት ቦታ ጥሩ ገበያ በ እንዴት ያለ ሁኔታ እንደሚገኝ ይወሳል:: በ እርግጥ በ ''ሞባይል'' ስልክ ዘመን እንዲህ ይወራል የሚሉኝ እንደሚኖሩ እገምታለሁ:: መልሱ ግን ስለ ፹ ከመቶው ሕዝብ ነው ያወራሁት ነው።

ቡና አንዲህ በ ፖለቲካው፣በምጣኔ ሃብቱ፣በ ማህበራዊ ጉዳይ ሁሉ ውይይት አንድደረግ ይረዳል ፣መረጃ ይፈሳል፣ ይጣራል፣ ውሳኔ ይሰጣል። ዘመናዊ የ መረጃ ማግኛ ለሌላት ሀገር ቡና ከ ገጠር እስከ ከተማ አወያይ፣የ መረጃ መገኛ፣ግራ ለተጋባ ብሔራዊም ሆነ ሰፈራዊ ጉዳይ የማያዳግም ያልተፃፈ ግን ማንም ሊቀይረው የማይችለው ውሳኔ ይተላለፍበታል- ቡና ::  እ ናም የቀደሙት እንዲህ  ተወያይተው፣ ወስነው ብሎም  አንድ ልብ ሆነው ብዙ ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸው ሥራ ሰርተዋል ወደፊትም ይሰራሉ :: ዘመናዊ የ መረጃ ማግኛ ለሌላት ሀገር ቡና ከ ገጠር እስከ ከተማ አወያይ፣የ መረጃ መገኛ፣ግራ ለተጋባ ብሔራዊም ሆነ ሰፈራዊ ጉዳይ የማያዳግም ፣ያልተፃፈ ግን ማንም ሊቀይረው የማይችለው ውሳኔ ይተላለፍበታል- ቡና ::ከ ጥቂት አመታት በፊት በ እምነት ስም እያስመሰሉ ''ቡና አትጠጡ'' የሚሉን ሰዎች የማንን አጀንዳ ይዘው ነው? አያልኩ ሃሳብ የገባኝ ስለ ቡና እና አጠጣጡ  እንዲህ ካሰብኩ በኋላ ነው ። በ አርግጥ ቡና  በሀገራችን ያያዘው ልማዳዊ ጎጂ ጎን አለው ::ሰዎች የራሳቸውን ሥራ ትተው ስለ ሌሎች ሃሜት፣ወግ መጠረቅ፣ወዘተ ምክንያት  ሥራ ያስፈታቸዋል የሚለውን ሃሳብ አልንቀውም:: ግን ቡና ሲጠጡ ብዙ አታውሩ ስንል ሌላ የ መረጃ፣የ መቀራረብያ መንገድ ፈጥረን ቢሆን ያምርብናል:: አልያም  ጎበዝ ከሆናቺሁ ''ፈስቡክ'' በ እየበታችን  ይግባልን።''ፌስ ቡክ'' ደሞ ሌላ ሀገር መብዛቱ ሕዝቡን አነቃው:: የ እኛ ''ፈስ ቡክ'' ''ኢንተር'' ማረግ የለ፣''ፓስ ዎርድ'' የማይጠይቀውን  -ቡናችንን ሌላን ሳናማ፣ሥራ ሳንፈታ ለመረጃ እና ለ ማደግ እንጠቀምበታለን ጎበዝ! 
ጌታቸው በቀለ
ኦስሎ

1 comment:

Anonymous said...

Nice view. Keep it up.