Saturday, November 20, 2021

አስቸኳይ መረጃ Breaking News ( Read in English under the Amharic version) የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነትህ ተነስ! አሜሪካ ኢትዮጵያን ለመውረር ዝግጅት ላይ መሆኗ ተሰምቷል። Breaking News - The Biden Administration is making the century’s Mistake. The US army is preparing to attack Ethiopia.



•••••••••••••••
=================
ጉዳያችን / Gudayachn News
=================
አሜሪካኖች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተን ኢትዮጵያን ካልወጋን ብለዋል። ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ወታደሮችን ወደ እሥራኤል በብዛት እያስገቡ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ለማዝመት ልዩ ልምምድ እያደረጉ ነው የሚል መረጃም አለ።
ጀርመን የሚገኘው የአሜሪካ ጦርም ወደ ኢትዮጵያ ሊሄድ ስለሚችል በተጠንቀቅ እንዲቆም መታዘዙን መረጃዎች ያሳያሉ። ዩኤስ ኤይድም ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ትእዛዝ ደርሶታል። በልዩ ልዩ ፕሮፓጋንዳ ስላልተሳካውን መንግሥትን የማንበርከክ ተልዕኮ "ኢትዮጵያ ውስጥ ሰብአዊ ቀውስ ተፈጥሯል" በሚል ምክንያት ጦር ለማስገባት ሙከራ መኖሩ አሁን በትክክል እየተሰማ ነው።
ሰሞኑን የአሜሪካ ጦር እንዲገባ የተለያዩ ወዳጅ መሳይ አካላት ያቀረቡትን ሐሳብ የኢትዮጵያ መንግሥትና የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች አጥብቀው ተቃውመውታል።የስቴት ዲፓርትመንት ብሊንከን ጉብኝትም ይህንኑ ለመወትወት ነበር:

Breaking News - The Biden Administration is making the century’s Mistake. The US army is preparing to attack Ethiopia.

===================

There is reliable Information Gudayachn Received as the US Army is preparing to attack Ethiopia

There are reports that large numbers of Ethiopian-born soldiers are entering Israel and are undergoing special training to deploy to Ethiopian sovereign territory.


Evidence suggests that US troops in Germany may be heading to Ethiopia and that a precautionary measure has been issued to the army. USAID Ethiopia has also been ordered to leave Ethiopia as soon as possible. The Biden Administration attempts to wage war on Ethiopia in the cause of the "failed humanitarian crisis".


The Ethiopian government and East African countries have strongly opposed the recent proposal by the United States to invade Ethiopia. This week US Secretary of state Antoni Blinken was on a visit to Kenya, Senegal, and Nigeria. There are reports that he was trying to convince these countries to invade Ethiopia. However, strong opposition was the African country's response.


Ethiopia is a country never colonized by any foreign power. It has over 3000 years of statehood history. If the Biden Administration decides to invade Ethiopia, this will be the mistake of the century to the US, and the resistance from over 100 million Ethiopians will be so strong and the United States will lose not only over a century of diplomatic and historical relations with Ethiopia but with Africa too.


Friday, November 19, 2021

ከዛሬ ጀምሮ በመጪው ሳምንት ድረስ ጁንታው የመጨረሻ የሽብር ሥራ ለመስራት እያሰበ ነው። በሁሉም መስክ መንግስት እና እያንዳንዱ ሰው ሊተገብራቸው የሚገቧቸው ተግባራት




===============
ጉዳያችን /Gudayachn
===============

አሁን ያለው ሁኔታ 

👉 የሽብርተኛው ህወሓት ወራሪ ከሰሜን ወሎ ይዞ ወደ አፋር ሚሌ ይንደረደርበት የነበረው ምሽግ በመሰበሩ እና በአስር ሺዎች የሚቆጠር ጀሌ ስላለቀበት የተረፈውን እና የሸሸውን ጀሌ በቻለው ወደ ሰሜን ሸዋ ለመላክ እየሞከረ ቢሆንም የሰሜን ሸዋ ገበሬ ጨምሮ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል።

ጁንታው የመጨረሻ የሽብር ሥራ ለመስራት እያሰበ ነው።የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ አካባቢዎች 

👉 በእዚህ ሳምንት መጨረሻ እና በመጪው ሳምንት ላይ ጁንታው የመጨረሻ እንጥፍጣፊ ሙከራውን በተለይ በዲጂታል ወሬ ለመዝመት የውስጥ እና የውጭ ኃይላቸውን ከምንጊዜም በላይ እንዲዘምቱ ተነግሯቸዋል።በእዚህ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በቀጣዩ ሳምንት በዋናነት አጠናክረው ሊያደርጉ ያሰቡት -
  •  በሁሉም ማኅበራዊ ሚድያ የጁንታው ጀሌ ገና ያልያዟቸው ከተሞች እንደ ደብረብርሃን ያሉት በሙሉ እንደተያዙ ተደርጎ በሰፊው ለማውራት፣
  • ለእዚህ ዘመቻ የሚታወቁት ሚድያዎች በተጨማሪ ሁሉም በራሱ አዳዲስ የማኅበራዊ ሚድያ እየከፈተ የወሬ ዘመቻ ላይ እንዲዘምት፣
  • የውስጥ ወኪሎቻቸው ከእዚህ በፊት ከነበረው በተለየ በከተሞች ውስጥ በቻሉት የወሬ ዘመቻ ላይ እንዲሰማሩ።የጁንታው ሰራዊት ብዙ እንደሆነ ማውራት፣ የስነ ልቦና ጦርነት ማድረግ 
 👉 አሁን በአዲስ አበባ የሽብርተኛው ህወሓት ሴል እየተበጣጠሰ ስለሆነ ሁሉም መዋቅሩ ተበጣጥሶ ሳያላቅ የቀረው ቡድን በቶሎ አንድ አይነት ሽብር በአዲስ አበባ እና ደብረ ብርሃን ላይ እንዲፈፅም።በእዚህም በሰፊው በአዲስ መልክ ከሚደረገው ዘመቻ ጋር ትንሹን የሽብር ጥቃት ተጋኖ እንዲወራ በውጭም ሆነ በውስጥ እንዲዘመት።ለእዚህም የቀረው የሸኔ ሴል በትልልቅ ከተሞች ሰላማዊ ሕዝብ ላይ ጥቃት እንዲፈፅም እና የመንግስት የፀጥታ መዋቅር የተዳከመ አስመስሎ እንዲቀርብ ማድረግ።

 👉 የኃላ ረድፍ ሆነው በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የጁንታው ጠላት ነን የሚሉ ግን ለአማራ የሚቆረቆሩ መስለው መንግስትን ከህዝብ ጋር የሚያጣሉት ዩቱበሮች እና የማኅበራዊ ሚድያ አንቀሳቃሾች አዳዲስ የማጣያ አጀንዳዎች እንዲፈጥሩ እና በተለይ መንግስት በአማራው ላይ ሴራ ሰራ የሚል አጀንዳ ማናፈስ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲሰሩ እና  ለእዚህ ሥራ ደግሞ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ነገር ግን በተግባር በሕዝብ ላይ ለሽብርተኛው ቡድን የፕሮፓጋንዳ ተኩስ  ዩቱበሮች ትኩረት ተደርጎባቸዋል።

 👉 የተቀናጀ የዲጂታል ጥቃት ለመፈፀም መሞከር።በተለይ ይህ ጥቃት በመንግስት ድርጅቶች እና የህዝብ አገልግሎት ሰጪ አካላት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ለማድረግ 

መንግስት እና ሕዝብ ምን ያድርጉ?

መንግስት ምን ያድርግ?

👉 መንግስት የውጭ ለምሳሌ እንደ አሜሪካ ያሉ ልዑክ ጋጋታ የመንግስት ቁልፍ ሰዎችን ሥራ አስፈትቶ የሚወጥር አጀንዳ መስጠት መሆኑን እና የልዑኩ ምልልስ የመንግስትን ስሜት ለመለካት እና የማደናገርያ የተኩስ ሽፋን ለሽብርተኛው መስጠት በመሆኑ። እነኝህ ልዑካን የሚያመጡትን አጀንዳዎች ለጊዜው  ኃይሉ ጦርነቱ ላይ ማትኮር አለበት።

👉 መንግስት ራሱ ለውጭ ኃይሎች አጀንዳ መስጠት አለበት።ለምሳሌ የምዕራባውያን ለሽብርተኛው ቡድን እየሰጡ ያሉትን መንግሥታት  በግልጥ በተባበሩት መንግሥታት መድረክ መክሰስ እና ግልጥ ደብዳቤ ለተባበሩት መንግሥታት በመፃፍ ማስጠንቀቅ አለበት።በእዚህም 

1) መንግስት አጀንዳ ሊሰጡ የሚፈልጉ አካላትን ለራሳቸው አጀንዳ መስጠት ይችላል።

2) የኢትዮጵያ ወዳጆች የትኞቹ ሀገሮች ወይንም ሀገር በቀጥታ ጣልቃ እየገባ መሆኑን እንዲረዱ ያደርጋል።የችግሩን ዲግሪም እንዲረዱት ያደርጋል።

👉 መንግስት የኢትዮጵያን ህልውና የማስከበር አንቀሳቃሽ ሞተር እና አስተባባሪ በመሆኑ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የገቡ ኤምባሲዎች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲሄዱ ማድረግ፣በሀገር ውስጥ እየተተገበረ ያለው አዋጅ ጠንከር ብሎ እንዲቀጥል ማድረግ አለበት።የለሰለሱ አካሄዶች ፈፅሞ አያስኬድም።እዚህ ላይ ''ጠላትህን ለማሸነፍ ጠላትህ እየሄደ ባለበት መንገድ ካልሄድክ አታሸንፍም'' የሚለው አባባል ማሰብ ያስፈልጋል።

👉 መንግስት አንድ ልዑክ ለምሳሌ በክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የሚመራ ልዑክ ወይንም የተለያዩ ልዑካን በተለያየ አቅጣጫ በተመረጡ የአፍሪካ፣የአውሮፓ እና ጃፓን ጭምር ሄደው በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ማስረዳት እና ዲፕሎማሲያዊ ጦርነቱን መመከት አለባቸው።ልዑኩ በአሜሪካ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ወዳጅ የምክር ቤት አባላትን ለማናገር ሁሉ መሄድ አለበት።በእዚህም ከንግድ ሰዎች ጋር እና ከእየሃገራቱ ሚድያዎች ጋር የመነጋገር እና የማስረዳት ዕድል ሁሉ መጠቀም ይችላሉ።የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት ወይንም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አፍሪካ በአካል እየተገኙ በኢትዮጵያ ላይ ለመዝመት ያደረጉት  ጥረት ኢትዮጵያ መማር አለባት።በአካል መሄድ አስፈላጊ ነው።

👉 መንግስት የፕሬስ መግለጫዎቹን መቀጠል እና የዲጂታል ጥንቃቄውን እያደረገው እንዳለው ማጠናከር።

ሕዝብ ምን ያድርግ?

ትልቁ ኃላፊነት የህዝብ ነው።ሕዝብ ማለት ከሀገር ቤት እስከ ውጭ ያለው ሁሉ ያጠቃልላል።በቀጣይ ቀናት በተለየ 

👉 በቀዳሚነት ስነልቦናውን ያጠንክር።ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።በእዚህ መጠራጠር አይቻልም።የጠላት ዋና ኢላማ የሕዝብ ስነ ልቦና መምታት ነው።ለእዚህም ዋና መንገዱ በውሸት ወሬ የስነ ልቦና ጦርነት ማድረግ ነው።ስለሆነም ለስነ ልቦና ጦርነት ላለመጋለጥ መስማት የሌለበትን አለመስማት።ይልቁንም አፀፋዊ ጥቃት መፈፀም የህዝብ ኃላፊነት ነው።

👉 እያንዳንዱ በእያንዳንዱ ቦታ እና በሚኖርበት ቦታ ከማናቸውም የሽብርተኛ ጥቃት የመጠበቅ ኃላፊነቱ የራሱ መሆኑን ማመን።

👉 እያንዳንዱ ሰው በቤተሰብ ደረጃ አጀንዳ አድርጎ መወያየት አለበት።ይህ የሽብርተኛው ሥራ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ቤተስቡን ለማፍረስ መሆኑን ባልና ሚስት እንዲሁም ልጆች ሊያምኑበት ይገባል።በእዚህ መሰረት በውጭ ያለው በገንዘብ የተፈናቀሉትን በመርዳት፣በሀገር ቤት ያለው በዘመቻው እና በሁሉም መስክ ለሚያደርገው ሥራ ቤተሰቡ ጭምር ድርሻውን እንዲያውቅ ያደርገዋል።

 👉 በቅርቡ ያሉት በጥቅም፣በመዋለል እና በቸልተኛነት አሁን ኢትዮጵያ የገጠማት የህልውና ጉዳይ ዝቅ አድርገው በማሳየት ሕዝብ ሊያዘናጉ የሚሞክሩትን በማስተማር፣ ሆን ብለው ለጠላት ያደሩትን ደግሞ ለፍርድ በማቅረብ እና በማኅበራዊ ቅጣት ጭምር የራሱን ውሳኔ መወሰን አለበት።

ማጠቃለያ 

አሁን ኢትዮጵያ የገጠማት ፈተና የማታሸንፈው አይደለም።የፈተናው አመጣጥ በአንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እና ከውስጥ የተነሱባት ከሃዲዎች ጋር በአንድነት መሆኑ ብቻ ነው የፈተናው ክብደት ያመጣው።ሕዝብ ወስኗል።ይህ በራሱ በቂ ነው። ይህም ሆኖ ግን ከዛሬ ጀምሮ በተለይ በቀጣይ ሳምንት ላይ ሽብርተኞቹ ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ የከተማ መዋቅራቸው እየታደነ በመሆኑ የቀራቸውን ሴል ከመያዙ በፊት አጥፍቶ ለማጥፋት ምንም አያደርግም ማለት አይቻልም። አይሆንም ከማለት ይሆናል ብሎ በስነ ልቦናም በተግባርም የበለጠ ዝግጁ መሆኑ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም።የሽብርተኛው ህወሓት ቡድን ቀሪ መጠቀምያዎቹ ሁለት ናቸው። እነርሱም የውሸት ፕሮፓጋንዳ በማድረ የህዝብ ስነልቦና ለመጉዳት መሞከር እና የሽብር ጥቃት በሰላማዊ ሕዝብ ላይ መፈፀም ናቸው።ሁለቱም የሚከሽፉት ለሁለቱም ጥቃት ላለመጋለጥ በሚደረግ የተቀናጀ የህዝብ ሥራ እና የውስጥ አሾክሿኪን ለይቶ በመቅጣት ነው።

=========////===========

Thursday, November 18, 2021

ኢትዮጵያ አንገት ላይ እንዲጠመጠም በህወሓት ታቅዶ የተጻፈው አንቀጽ 39 አድፍጦ ቆይቶ ህወሃት አንገት ላይ ይጠመጠማል ብሎ ማን ገመተ?

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 

===============
ጉዳያችን / Gudayachn
===============
''ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፣
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም።'' ታላቁ ፀሐፊ ከበደ ሚካኤል 

በሀገራችን የሚባል አባባል አለ።''ጉድጓድ አርቀህ አትቆፍር።ከቆፈርክ ደግሞ አታርቀው።ማን ኢንደሚገባበት አይታወቅምና'' ይላል።
ዘንድሮ አለመሳቅ አይቻልም።አንዷ የጁንታው ደጋፊ በፈረደበት ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ብቅ ብላ እንዲህ አለች '' የኢትዮጵያ አንድነት የሚሉት አንቀጽ 39 ይፈልጉታል።ምክያቱም ትግራይ እንድትገነጠልላቸው'' ብላው አረፈች። እርሷ የተነገረችውን እንደ ቧንቧ ማስተላለፍ ነው። እንድታስተላልፍ የተነገራት ግን አንድ የሚያሳየው ስዕል አለ።  ኢትዮጵያ አንገት ላይ እንዲጠመጠም ታቅዶ የተጻፈው አንቀጽ 39 አድፍጦ ቆይቶ እራሱ ህወሃት አንገት ላይ ተጠምጥሟል።

ትግራይ በሪፈረንደም መገጠሉን እያሰበችበት መሆኑን የሚገልጥ መግለጫ ደብረፅዮንና ጌታቸው ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ስንቴ በትግራይ ቴሌቭዥን፣ሮይተርና ቢቢሲ ላይ እንደተናገሩ ገባ ብሎ መቁጠር ነው::መገንጠል በሕገመንግስቱ አስገብቶ አትንኩብኝ ያለውስ ማነው? እራሱ ህወሓት ነው::የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ኢትዮጵያን የሚገነጣጥለው አንቀጽ 39 እንዲወገድ ብዙ ለፍቷል። ይህንኑ አንቀጽ በመቃወም ሰዎች ታስረዋል፣ተገድለዋል፣ተሰደዋል። አንቀጹ ኢትዮጵያን ለማፈንዳት በሰዓት ተሞልቶ የተቀመጠ ''የጊዜ ቦንብ '' ነው በሚል ኢትዮጵያውያን ተቃውመዋል። ህወሃት ግን አንቀጹ ዋስትናዬ ነው እያለ ሲቀልድ ነበር። የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ግን አንቀጹ ለትግራይም አደጋ ስላለው ለማንም አይበጅም ብለው በቅንነት ነበር ሲቃወሙት የኖሩት።

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ''ቀይ መስመር'' በተሰኘው የኢቲቪ መርሃግብር ላይ ቀርበው ይህንኑ አንቀጽ 39 አንስተው ነበር።ከንቲባዋ የጠየቁት ህጋዊ ጥያቄ ነው። ጥያቄያቸው ህወሃት ለዘመናት ሲያቀነቅነው የነበረው በኋላ ስዩም መስፍንና አባይ ጸሃዪ በቴሌቭዥን መስኮት ቀርበው ሲያስፈራሩበት የነበረው።ከላይ እንደተገለጠው ደግሞ ደብረጽዮን፣ጌታቸው ረዳ እና ጻድቃን በትግራይ ቴሌቭዥን፣ቢቢሲ እና ሮይተርስ ላይ የትግራይ ህዝብ ለመገንጠል ድምጽ እንዲሰጥ እንደሚያስገድዱት ደጋግመው ገልጠዋል።እንደሚያስገድዱት ያልኩት ህዝቡ ፈቅዶ እና ወዶ አያደርገም የሚለውን ሃሳብ መነሻ በማድረግ ነው።

ይህንን በአደባባይ የተነገረ በህገ መንግስቱ ውስጥ እንዲገባ ህወሃት የተሟሟተበት አንቀጽ 39 ተከትሎ የክብርት ከንቲባዋ ጥያቄ  ትግራይ መገንጠል ከፈለገች ለምን ከ20 ዓመታት በላይ አብሯቸው የተጋደለው መከላከያን በሌሊት መግደል ለምን አስፈለገ? በህጋዊ መንገድ ጠይቀው ጉዳያቸው መታየት አይችልም ወይ? የሚል አጭር እና ግልጥ ነበር። ይህንን መሰረታዊ ጥያቄ የጁንታው አፈቀላጤዎች መመለስ አልቻሉም።ዝም ብለው አድበስብሰው ሊያልፉት ይሞክራሉ። 

እውነታው ግልጥ ነው። ህወሃት አንቀጽ 39 ያስቀመጠችው ለመገንጠል አቅዳ ነው። ነገር ግን መገንጠሉ የታሰበው እስከ ቤኒሻንጉል ያለውን ቦታ ከሱዳን አዋሳኝ ግዛቶች ከአማራ ክልል ቆርሶ ትልቋ ትግራይ የሚሏትን ከፈጠሩ በኋላ የታቀደ ነበር።የሰሞኑ ወደ አማራ እና አፋር የተደረገው ዘመቻም የተወሰኑ የአማራ እና የአፋር እንዲሁም የቤኒሻንጉል ክልል መሬት ከያዙ በኋላ በመደራደር አሜሪካንን ከጀርባ አሰልፎ መገንጠሉን ለማሳካት ነበር።ሆኖም ጉድጓድ አጥልቀህ አትቆፍር ማን እንደሚገባበት አይታወቅምና።አሁን ህወሃት በአፋር እና አማራ ክልል ተመትቶ ለመገንጠል ከሆነ ለምን በህጋዊ መንገድ አትጠይቁም? ይሄ ሁሉ ህዝብ ለምን እንዲያልቅ ተደረገ? የሚለው ጥያቄ አሁንም መላሽ ካለ እንጠይቃለን።

 የከንቲባ አዳነችን መሰረታዊ አና ተገቢ ጥያቄ ተከትሎ የህወሓት ዩቱበሮች እጃቸውን እያወራጩ ሰሞኑን እንደማበድም ሲያደርጋቸው ታይቷል። ስታሊን ለመቀወስ እሩብ ጉዳይ በሆነ መልኩ ቃል በቃል '' እናቷ ሆድ ብትገባ አታመልጠንም'' የሚል ቃል ተናግሮ ስሜቱን መቆጣጠር አንዳቃተው እያሳየ በከንቲባዋ ላይ ዝቷል።የርዮት ሚድያ ቴዎድሮስ እርሱም ቃል በቃል '' ኢትዮጵያዊነት በቅጂ የደረሰው ሁሉ፣ ኢትዮጵያዊነት በደብዳቤ የደረሰው ሁሉ'' እያለ ለመዝለፍ ሞክሯል። ኢትዮጵያ ልጆቿን ታውቃለች። የክብርት ከንቲባዋን ኢትዮጵያዊነት የህወሓት ግልገሎች ዛሬም ለክተው ሊሰጧት ይፈልጋሉ።አዳነች ብዙ ጊዜ ተናግራለች።ስለ ኢትዮጵያዊነቷ የምትመሰክርላት እራሷ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን ጀግንነቷን ለኢትዮጵያ ያላትን ጥልቅ ፍቅር አይቶ ነው ዳግማዊት ጣይቱ ያላት።የጣይቱ እና የኢትዮጵያ አባቶች እነ ፊታውራሪ ገበየሁ፣ጀነራል ጃጋማ ኬሎ እና ኮለኔል አብዲሳ አጋ ደማቸውን አፍስሰው ባቆዩት ሀገር ስታሊን እና ቴዎድሮስ ዛሬም ኢትዮጵያዊነት በችርቻሮ ሊሰጡን ይፈልጋሉ።

ለማንኛውም  ኢትዮጵያ አንገት ላይ እንዲጠመጠም በህወሓት ታቅዶ የተጻፈው አንቀጽ 39 አድፍጦ ቆይቶ ህወሃት አንገት ላይ ይጠመጠማል ብሎ ማን ገመተ? ሆኗል!

 ===================///========


 


Tuesday, November 16, 2021

The distributors of Fake News on their tweeters are also 'analysts' on Ethiopian current issues on the western media.

Kjetil Tronvol,William Davison Rashid Abdi and Marin Plaut
(from Top - round Clockwise)

👉 Non-academic and Irrational but pure biased,pro-TPLF and war promotors on Ethiopia commentators will not deserve the International media.

👉የህሰት ትዊት አድራጊዎቹ የምዕራብ ሚድያዎች ተንታኞች ናቸው። ግለሰቦቹ በኢትዮጵያ እና በምዕራቡ ዓለም ያለውን ግንኙነት እየመረዙት ነው።

👉They are spoiling Ethio-US and Europe's Historical relationships.


==========
Gudayachn
==========

As an active follower of the Ethiopian and the Horn of Africa Political, Economical and Social Affairs and blogger of Gudayachn, I read the above posted four individual's tweets on Ethiopia. Many Ethiopians know them well with their flow of tweeters which focuses on Ethiopia's current issues. Marin Plaut, Kjetil Tronvol, Rashid Abdi, and William Davison are the four known Fake News Tweeters regarding Ethiopia. I think it is possible to say that they are also spoiling Ethio-US and Europe's historical relationship.


Many Ethiopians are seeing them as the ‘faces of sabotage’ that reflects the US and European Foreign Policy formulators. Due to their non-responsible tweets and analysis on the Western media, the Political, Economic, and Social environment of Africa is misinterpreted. It is quite clear that People-to -people historical relations need great care. However such Individuals misbehave and characters for some sort of individualistic interest could have a huge catastrophic danger on the relationship between the North and South. Here it is possible to present a deep-rooted analysis of how can it happen. But it is not an objective of this particular article.


These people are well-known Pro-TPLF (Tigray Peoples Liberation Front), biased to its ethnocentric ideology, attempting to advise TPLF on their tweets and continue to tweet fake news on Ethiopia and Africa. The bad thing is that the western media's views and analysis programs are referring to them to share their biased ideas. The ways they analyze the Political, Economic, and Social environment and current issues of Ethiopia are ‘square one’. That means non-academic, full of hate, and only observed from the TPLF point of view.


Here below I share some of their tweets in the past few months.



Not only BBC but Aljazeera and France International are using him as ''analysts''




Sometimes, his bare wishes were posted as news. This had never happened. It is pure Fake News

Fake News for Martin is as simple as drinking a cup of coffee. There is no road cut.

 Africa as a continent is also targeted. 



Rashid even call TPLF spokesperson as his 'Uncle'


To magnify and multiple ethnic politics 


Strategic expert? or advisor for TPLF?


Is he an independent analyst or an advisor and 'master mind' for TPLF operation in Ethiopia?


From the above sample tweets, anyone can understand how far they are going to assist the Terrorist group of TPLF by pure propaganda, Fake News, and sometimes by providing some tips to make sabotage against Ethiopia and Africa.

Now here is the message to the Western world as a whole. The long-aged historical relationship between Ethiopia and Africa on one side and the USA and Europe on the other side is spoiling due to the above-mentioned individuals Fake News and negativity hidden under the name of analysts. Currently, Ethiopians and Africans are looking at the Western world in the eyes of these individuals. Here I am trying to be softer as if there is no driving power behind the back of the mentioned individuals. However, it is not bad to say - let us give a chance for the investigators and historians to disclose in the future the unknown reasons that are driving them to spoil the North-South relationships. But for a time being, it is possible to say, if the western world has a plan to improve its relation with Ethiopia and Africa as a whole, it is vital to cease from giving any chance to the above-mentioned individuals in any International media to comment on any issue of Ethiopia and Africa. Non-academic and Irrational but pure biased,pro-TPLF and war promotors on Ethiopia commentators will not deserve the International media. In fact, the choice is yours. If you ignore this notice, no doubt that Africans' grand revolution to resist the western provocation of indigenous Political, cultural and Economic heritage of Africans or Ethiopians will come soon.

===================///===========






Saturday, November 13, 2021

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሌላ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወኑ ነው።

ኖርዌይ 

Voluntary Ethiopians and Norwegians agreed to assist Internally Displaced People (IDP) in Ethiopia with out any discrimination of ethnicity and Language..

  • በዘንድሮ የገና በዓል ለልጆቻችን ልንሰጥ ያሰብነው ስጦታ ከልጆች ጋር በመነጋገር በማስቀረት የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ እንደሚገባ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
  • በዓይነቱ ለየት ያለ አደረጃጀት ዛሬ ተመስርቷል።

=====================

ጉዳያችን ዜና /Gudayachn News

=====================

በመላዋ ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው አሁን ባለችበት ፈታኝ ጊዜ በምን መልኩ መርዳት አንዳለባቸው ሲያወጡ ሲያወርዱ ነበር የከረሙት።በእዚህም መሰረት ሁሉንም የሲቪክ ድርጅቶች፣በተለያዩ የኖርዌይ ግዛቶች የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ስብስቦችን እና ማኅበራዊ አደረጃጀቶችን ማዕከል ባደረገ መልኩ የጋራ አደረጃጀት ማስፈለጉ ላይ ተስማምተው ይህ አደረጃጀት እና ድርጅት ምን መምሰል እንዳለበት፣መተዳደርያ ደንቡን እና በዋናነት ምን መስራት ይችላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ ላለፉት አምስት ወራት በአስተባባሪ ኮሚቴ ሲያዘጋጅ ቆይቶ ዛሬ ከመላዋ ኖርዌይ በዙም በተደረገ ስብሰባ ''ለኢትዮጵያ እንቁም በኖርዌይ'' የተባለ ድርጅት የመተዳደርያ ደንቡን እና ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚያስተባብሩ ሰባት አባላት ያሉት የአመራር አካላትን እና ሁለት የውስጥ ኦዲት እና ቁጥጥር መርጧል።በተለይ አመራሮቹ ሲመረጡ በመላዋ ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ለመወከልበተቻለ መጠን በኖርዌይ ካሉት ትላልቅ ከተሞች ለመወከል  በሚል የአመራሮቹን ስብጥር ለመጠበቅ ጥረት ተደርጎ ነበር።

በእዚህ መሰረት የሚከተሉት ለስራ አስፈፃሚነት ዕጩ ቀርበው የነበሩ ሲሆን 9ኙ ለስራ አስፈፃሚነት እና ለኦዲት እና ኢንስፔክሽን መርቷል።በእጩነት የቀረቡት የ11ዱ ስም ከእዚህ በታች ያገኛሉ። -

1) ዶ/ር ኃይሉ ከበደ ከስታቫንገር ከተማ 

2) ዶ/ር ነፃነት ግዛው ከትሮምሶ ከተማ 

3) አቶ አስማማው ተሻማሁ ከትሮንዳይም ከተማ 

4) ዶ/ር ፋሲል እጅጉ ከኦስሎ ከተማ 

5) ወ/ሮ ኢትዮጵያ ብሮተን ከኦስሎ ከተማ 

6) ኢንጅነር ስምዖን ጴጥሮስ ከኦስሎ ከተማ 

7) አቶ ሳምሶን ደረጀ ከበርገን ከተማ 

8) ኢንጅነር ክፍሌ አሰፋ ከበርገን ከተማ 

9) ወ/ሮ ገነት በቀለ ከበርገን ከተማ 

10) ፓስተር ዮሐንስ ከበርገን ከተማ 

11) ኢንጂነር ካሳሁን ገድሉ ከኦስሎ ከተማ 

በዛሬው የምስረታ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያውያን ኮምዩኒቲ ሥራ አስፈፃሚዎች እና አባላት፣የሲቪክ ድርጅቶች ሥራ አስፈፃሚዎች እና አባላት እንዲሁም የሃይማኖት ድርጅቶች ተወካዮች እና አባላቶቻቸው የተሳተፉ ሲሆን በቅርቡ በኖርዌይ ሕግ ምዝገባውን የሚያካሂድ ሲሆን አሁን በአፋጣኝ በሀገራችን በጦርነቱ ችግር የደረሰባቸው ወገኖቻችንን ዘር፣ሃይማኖት እና ቋንቋ ሳይለይ ድጋፍ ለማድረግ እንዲችል በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን የገንዘብ ማሰባስብ ሥራ እንዲጀምሩ ጥሪውን አስተላልፏል።

በመጨረሻም በተለይ አሁን የተቸገሩ ወገኖች ካሉበት አፋጣኝ ችግር አንፃር ከመደበኛ ድጋፍ በተጨማሪ በዘንድሮ የገና በዓል ለልጆቻችን ልንሰጥ ያሰብነው ስጦታ ከልጆች ጋር በመነጋገር በማስቀረት የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።በመጨረሻም ድርጅቱ የኢትዮጵያ ችግር እስኪቀረፍ ድረስ በቀጣይነት የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራ እና ወደ ሀገር ቤት በሕጋዊ መስመር እንዲላክ እንደሚያደርግ ተብራርቷል።የህ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተግባር በሌላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በናሙናነት ሊጠቀሙበት የሚችሉት መሆኑን ጉዳያችን ለማስገንዘብ ትፈልጋለች።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ከክፉ ሁሉ ይጠብቃት!


==========///==========


Friday, November 12, 2021

The U.S. Wants To Turn Ethiopia Into Bosnia

Andrew Korybko

👉The American hybrid war on Ethiopia aims to turn the country into Yugoslavia

By Andrew Korybko

It was earlier feared that the American hybrid war on Ethiopia aims to turn the country into Yugoslavia, which implies its full dissolution along regional lines. Arminka Helić, member of the British House of Lords and served as special adviser to Foreign Secretary William Hague from 2010 to 2014, deceitfully claimed that Prime Minister Abiy Ahmed risked advancing this scenario through the Ethiopian National Defense Forces’ (ENDF) ongoing anti-terrorist operation in the northern Tigray Region in an article that she published at Politico in August titled “In Ethiopia, Echoes Of Yugoslavia”. In reality, it is those U.S.-backed foreign forces, including corrupt UN officials, that are meddling in the Horn of Africa country who are the ones pushing this outcome. PM Abiy is, in fact, counteracting their efforts to advance the Yugoslav scenario in Ethiopia.

Her article was rebutted by Ethiopia’s Ambassador to Belgium, Luxembourg, and EU institutions Hirut Zemene a few days later at the same outlet in a response titled “Ethiopia Is Not Yugoslavia”. She convincingly debunked Helić’s false comparison, chastising her for “calling for unwarranted action” on that basis. Politico is back at it again—however, this time publishing a similarly provocative piece titled “Ethiopia Is Plunging into Chaos. It’s Time for A New Dayton Peace Process”. This article is authored by Alex Rondos and Mark Medish. The former is described as having served until July 2021 as EU Special Representative to the Horn of Africa while the latter served on the Dayton Peace implementation team and at the U.S. Treasury and National Security Council in the Clinton Administration. Their article reveals the intended end game for Ethiopia and deserves to be analyzed.

The U.S. no longer believes that it can formally partition Ethiopia through a hybrid war after its TPLF proxies failed to inspire other terrorist groups elsewhere across the country to support their anti-state campaign in other regions. The grand strategy objective has thus been comparatively scaled back to the de facto partition of the country through its “Bosnification”. Judging by what the Dayton Peace Process resulted in for that Balkan state, it implies a radical constitutional reform intended to grant large degrees of independence to the warring regions. In the Ethiopian context, this would likely be weaponized by pressuring Addis Ababa to devolve such powers not just to the Tigray Region but to every other one as well. The Dayton Peace Process also led to a foreign military intervention under the guise of peacekeepers and a formal UN control of the country.

Suffice it to say, the impact of this scenario on Ethiopia would be completely destabilizing and dysfunctional. It would basically divide-and-rule the country by carving out identity-centric statelets across its diverse ethno-regional checkerboard that could potentially expand to become almost countless in number, depending on how radically this process is imposed. There would almost certainly be a regime change, too, since there is no way that PM Abiy would surrender control of Ethiopia to any foreign power or entity, let alone one that has already been proven as corrupt and hostile to his country as the U.S. presently is. Furthermore, the ENDF and the patriotic population that they represent would never accept an invasion under the cover of a peacekeeping mission. Ethiopia would essentially cease to exist in any meaningful sense if this happened.

There is even more at risk than just the de facto erasure of Ethiopia from the map under that dark scenario. If one of the proudest, historically independent and most powerful countries in Africa failed to stop this “regime reboot” scheme (which is what externally provoked radical constitutional reform in the direction of “Bosnification” can be referred to in the context of Hybrid War theory), then there is no doubt that it will be replicated elsewhere across the continent through a similar hybrid war means against other rising powers like Nigeria to usher in another so-called “Scramble for Africa”. The U.S. and its allies would strategically benefit from this outcome since it would enable them to more effectively divide and rule Africa in a way that could reduce the influence of Russia, China, and other multipolar countries there across the ongoing New Cold War.

In other words, Ethiopia isn't just defending its own sovereignty by pushing back against America's Hybrid War, but also all of Africa's. The US feels threatened not only by PM Abiy's pragmatic attempts to balance between it, China, Russia, Turkey, and others in the New Cold War, but increasingly by the possibility that his government could revive the Pan-African movement in modern-day geopolitical conditions building upon Ethiopia's historical leadership of it in the past. Since the Yugoslav scenario is no longer seriously pursued due to the ENDF's success in containing the TPLF's terrorist threats, the Bosnian one is now being advanced as “Plan B”. The US hopes to leverage the latest intensification of its Hybrid War on Ethiopia towards that end, but so long as the targeted country is aware of what's being advanced, then this latest scheme also stands to fail too.

==========================

Andrew Korybko is American Moscow-based political analyst specializing in the relationship between the US strategy in Afro-Eurasia, China's One Belt One Road global vision of New Silk Road connectivity, and Hybrid Warfare.

Source = RIAC

Thursday, November 11, 2021

የአሜሪካው አድሚራል ኢትዮጵያን እንውረር ድንፋታ በተመለከተ ኢትዮጵያውያን ልናውቃቸው የሚገቡ ሦስት ጉዳዮች።


አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን


===============
ጉዳያችን /Gudayachn
===============

ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ  በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵያን መውረር አለበት በሚል (በሰላም አስከባሪ ስም ነው የጠቀሱት) የፃፉትን በተመለከተ በብዙዎች ዘንድ እንደ ድንገት ደራሽ እያዩት ነው። ይህን እንደሚያደርጉ ሊብያን፣ሶርያን፣ዩጎዝላቭያን እና የመንን አየን።አሁን እኛ የማይሸነፍ ሃገር ህዝብ ነን እና ካለፉት የመማር እድልም ስላለን እራሳችንን አድነን አፍሪካን እንዴት እናድን? ነው ጥያቀው።ኢትዮጵያን በአድዋ ወረራ ጊዜ በ1928 ዓም ጣልያን ተመልሶ ሲመጣ ተመልሳ እንዳትነሳ ብትደረግ ኖሮ አፍሪካ ነጻ ባልወጣ።የአፍሪካ አንድነት ድርጅትም ባልተመሰረተ ነበር።አሁን አፍሪካን ሊበሏት ሲፈልጉ ካለፈው ትምህርት ወስደው ቅድምያ ኢትዮጵያን መምታት ነው ዕቅዱ።
እዚህ ላይ  ሶስት ነጥቦችን  ማስታወስ አለብን - 

1) ያልጠበቅነው እና ከእዚህ በፊት በኢትዮጵያ ያልተሞከረ ድንገቴ ጉዳይ አይደለም።

ኢትዮጵያን ባዕዳን ሊወሯት እንደሚፈልጉ ከልጅነታችን አልሰማንም? ቀድሞስ ኢትዮጵያን ወርረው ለመቆጣጠር የሞከሩ ሀገሮች እንደነበሩ አላነበብንም?  ሁሉንም የምናውቀው ነው።ዛሬ የአሜሪካ አድሚራል የፃፉት ውሸት ነው ብለን ማጣጣል ፈፅሞ የለብንም። ጦርነት የሚፈጠረው ሜዳ ላይ ሳይሆን አዕምሮ ላይ ነው። ሂትለር ዓለምን ከመውረሩ በፊት ወረራውን ያቀደው አዕምሮው ላይ ነው። አዕምሮው ላይ ያለውን ሃሳብ በአንድበቱ አውጥቶ ሌሎችን አማከረ ቀጥሎ ሰራዊት አሰልጥኖ ወደ ሥራ ቀየረው።

የአሜሪካው አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስ በሃሳቡ ያለውን በፅሁፍ ላይ ሲያሰፍር ከማንም የአሜሪካ ባለስልጣን ጋር ሳይወያይ፣ሳያብላላ እና በመፃፉ የሚያመጣውን መዘዝ ሳያውቅ የፃፈው አይደለም።በእዚህ ደረጃ ላይ ያለ ሰው የፃፈው ድንገቴ አይደለም።ስለዚህ ቀድሞ መተንፈሱ እና የፍላጎታቸውን ልክ መተንፈሱ መልካም ነው።ስለሆነም  የማናውቀው አልሆነም እና የመጀመርያው መጀመርያ አንደነግጥም! አንፈራም! ለሀገር የመጨረሻው ስጦታችን መሞት መሆኑን እያንዳንዱ ሰው በአዕምሮው ማስቀመጥ አለበት።አድሚራሉ በእዚህ ፅሁፉ ሞሶሎኒ፣ሞሶሎኒን ሸቶናል፣ገምቶናል።አሟሟቱም እንደ አድሚራል ወይንም እንደ ግራዚያ እንዲሆን መምረጥ የራሱ የአድምራሉ ነው።

2) ''ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው።አስቀድሞ ማለት አሾክሿኪውን ነው።''

ጠላት ኢትዮጵያን አይጥላትም።ሊያደማት፣ሊያንገላታት በጊዜያዊ ድል ሊፈነጥዝ ይችላል።ሆኖም ግን ፈፅሞ ጠላት አሸንፎን አያውቅም ወደፊትም አያሸንፈንም። እኛን የሚገዳደረን የውስጥ ባንዳ ነው።በጣልያን ወረራ ጊዜ የኢትዮጵያ አርበኞች ዋና ፈተና ባንዳ እንጂ ሰላቶ ፋሽሽት ጣልያን አልነበረም። አሁንም ቀድሞ ለጠላት መንገድ ጠራጊ ባንዳ እና አሾክሿኪ ነው።ኢትዮጵያ አሁን ከሽብርተኛው ህወሓት ጋር የገጠምነው ጦርነት ከአሾክሿኪው ጋር ነው።አሁን አሜሪካን ጋር ሆኖ እያሾከሾከ ኢትዮጵያን ከሸጣት ውስጥ አንዱ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ነው።ይህ ሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ኢትዮጵያን ለባዕዳን ከሸጣት ውስጥ ከቀንደኞቹ ውስጥ ሆኖ በመጪው ትውልድ የኢትዮጵያ ታሪክ መፅሐፍ ላይ ከእነ ፎቶው ተሰቅሎ ትውልድ ሲረግመው የሚኖር ሰው ነው።ዛሬ አድሚራሉ በኢትዮጵያ ላይ የድፍረት ቃል እንዲናገር መንገድ የጠረገው እና አብልታ አጠጥታ ያሳደገችው እናቱን ከባዕድ ጋር እየዶለተ ካራ ከሚስሉት ውስጥ ይህ ሰው አንዱ ነው።

ሆኖም ግን አሾክሿኪው ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ብቻ አይደለም።ዛሬ ኢትዮጵያውያንን በጎሳ ለመከፋፈል ከሚድያ እስከ መሳርያ አንስተው እየወጉ ያሉ ሁሉ በባንዳነት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሱ ናቸው።እነኝህን ሁሉ በማስተባበር ኢትዮጵያን ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ያህል  ያቆሰላት፣የከፋፈላት እና የባዕዳን ፈረስ የሆነው ህወሓት ነው።የባዕዳንን ፈረስ ሳይመቱ ባዕዳንን መምታት አይቻልም።ስለሆነም አሁን ኢትዮጵያ የገጠማት የጠላት ጥያቄ ፋሽሽት የጠየቀው ነገ አሜሪካ ኢትዮጵያን ለመውረር እመጣለሁ የሚለው ጥያቄ አንድ ነው።ስለሆነም ''ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው። አስቀድሞ ማለት አሾክሿኪውን ነው።'' 

3) ሃገር ወዳድ የነቁ እና የሰሉ አነቃቂዎች በመላዋ ኢትዮጵያ ማሰማራት 

አነቃቂዎች በኢትዮጵያ የጥንት ታሪክ ውስጥ አሸናፊ እንድትሆን ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።አንዳንዶች የማኅበራዊ ሚድያ ከመጣ ወዲህ አንቂዎች የተፈጠሩ አድርገው ያስባሉ።ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ከባእዳን ጋር ያደረገችው ጦርነት በአሸናፊነት እንድትወጣ ካደረጉት ውስጥ አነቃቂዎች ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።አዝማሪ በግጥም እና በዜማ፣እረኛው በዋሽንት፣ባለቅኔው በቅኔ፣ሸሁ በስብከት፣ካህኑ በምክር፣ፎካሪው በፉከራ ሁሉም ኢትዮጵያ ጠላት ሲገጥማት ለሕዝቡ የሞራል ልዕልና ስንቅ ያስታተቁ ናቸው።ሰው በተፈጥሮው ስሜቱ እንደጊዜው ይቀያየራል።አነቃቂዎች ግን ይህን ሁሉ ጠብቀው የሀገር ፍቅር ስሜቱን ያንሩታል፣የነቁታል፣ከመከራ በኃላ ያለውን መልካም ጊዜ በተስፋ ያሳዩታል፣ሞት ምንም አለመሆኑን እና ክብሩን ያመለክቱታል። 

ስለሆነም ዛሬም ኢትዮጵያ አንቂዎች፣በገበያ ላይ፣በከተሞች አደባባይ ላይ የሚናገሩ፣በየቤቱ እየሄዱ የሚያስረዱ ሰዎች ያስፈልጋሉ።በወታደራዊው መንግስት ዘመን  የህዝብ አንቂዎች ካድሬ በሚል ስም ተሰጥቷቸው የኢትዮጵያ የነበረው ባህል ተረሳ።አሁን ግን እንደ አዲስ ማነቃቃት ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ህዝብን 79% ያህል የገጠር ነዋሪ ነው። ይህ ሕዝብ ስንቱ ራድዮ እና ቴሌቭዥን ወይንም ስልክ ይጠቀማል? ደግሞስ አንቂ በራድዮ ከሚሰማ ይልቅ በአካል የሚያቀርበው የበለጠ ኃይል አለው።ይህ ማለት ዘመናዊ መገናኛ መጠቀም አያስፈልግም ማለት አይደለም። ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያ ከተሞች ባልተስፋፉባት ሀገር የህዝብ አንቂዎች አደባባይ መውጣት አስፈላጊ ነው። እኛ የአደባባይ አንቂነቱን ከስልጣኔ ጋር አገናኝተን ተውነው እንጂ እንደ እንግሊዝ ያሉ ሀገሮች ከተሞቻቸው መናፈሻ ቦታ ላይ  ማንም ሰው ንግግር የሚያደርግባቸው ክፍት መድረኮች ሁሌ አሉ።በእዚህም ብዙ ዕውቀት አሁን ድረስ ይገበይበታል። ይህ ህዝብን ማንቃት ከጥንት የግሪክ ዘመን ጀምሮ እነ አርስቶትልን፣በዘመናዊው ዘመን ደግሞ እንደ እነ በርናንድ ሾውን የመሰሉ ተናጋሪዎች አፍርቷል። 

ሕዝብ ያወቀ ቢመስለንም ያላወቀ፣በልዩ ልዩ ወሬ ግራ የተጋባ ወይንም በደካማ የምኞት መናወዝ ለሀገሩ ከመቆም ሊዘናጋ ይችላል።በእዚህ ጊዜ አነቃቂዎች የሚነግሩት ያፀናዋል።ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ከዘማቹ ጋር በታዳጊ ወጣትነታቸው ደራሲ አዲስ ዓለማየሁ ጣልያን ከመግባቱ በፊት ከወዳጆቻቸው ጋር ሕዝቡን ለማንቃት ኃላፊነት የወሰዱት በእየገበያው እየዞሩ ህዝቡ ለጦርነት እንዲዘጋጅ በማድረግ ነበር። በእዚህም ብዙ ሕዝብ ቆርጦ እንዲገባ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።የህዝብ አንቂዎች ለጦርነት ብቻ አይደለም። ሰላም መጥቶ ሕዝብ ወደ ልማት ሲዞር የልማት ስራውን ተረድቶት እና ወዶት እንዲሰራ መቀስቀስ ይፈልጋል።እዚህ ላይ በቀላሉ ሕዝብ በመገናኛ በመንገር ሊረዳው ይችላል ተብሎ ሊታሰ ይችላል።ነገር ግን እንዲህ በብዙ ማማለል ሁሉ በማታለል ሀገር ለመውረር የሚፈልግ እንደ አሜሪካ ያለ ሀገር በተመለከተ  ነገሩን ከስር የማስረዳት እና የቆረጠ ሕዝብ ዝግጅት ይፈልጋል።

ባጠቃላይ ይህ ትውልድ ልደናገጥ አይገባውም።ይልቁንም ሞትም ቢመጣ ዕድለኛ ትውልድ እንደሆነ ማሰብ አለበት።ኢትዮጵያን በደማቸው አስከብረው ለእኛ ያስተላለፉት የአባቶቻችን ዕድል እኔ ደረሰኝ።ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ኃላፊነቱ ከአምላክ ተሰጠኝ ብሎ በሃዘን ሳይሆን በደስታ፣በማማረር ሳይሆን በሀገሩ ውድነት እና ብርቅነት ምክንያት አባቶቻችን የገጠማቸው ጠላት ዛሬም እጃችን ላይ ልጥልልን  እንደመጣ ማሰብ አለብን።ዛሬ ኢትዮጵያውያን አቅማችንን አናስተውለውም እንጂ ግዙፍ ነን።በመላው ሀገር ያለው ስርጭታችን፣የተማረ የሰው ኃይል፣እምቅ የተፈጥሮ ሀብት እና ከሁሉም ጋር ኢትዮጵያን ስጠብቅ የነበረ ወደፊትም የሚጠብቅ የአባቶቻችን አምላክ ከእኛ ጋር ለዘላለም አለ።ተወረርን እንጂ አልወረርንም።መጡብን እንጂ አልመጣንባቸውም። ይህ ብቻ በራሱ ለሀገራችን ለመሞት በሞራል ልዕልና እና በአሸናፊነት መንፈስ እንድንነሳ የሚያደርግ ታላቅ ስንቅ ነው።
====================///==============

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...