Friday, September 2, 2016

PLEASE SIGN THE PETITION TO UN SECURITY COUNCIL ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት የሚቀርብ ፔቲሽን እንፈርም

I just signed the petition "UN SECURITY COUNCIL: STOP KILLING IN ETHIOPIA BY TPLF 

DICTATORIAL REGIME" and wanted to see if you could help by adding your name.Our goal is to 

reach over 1000 signatures and we need more support. You can read more and sign the petition 


Thanks!

Gudayachn

ሰላም ለሁላችሁም፣
እባካችሁ ከእዚህ በታች ያለውን ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት የሚቀርብ ፔቲሽን እንፈርም።በኢትዮጵያ ሁኔታ መናደድ ብቻውን ምንም ውጤት አያመጣም። 
በእጃችን ባለው ኮምፕዩተር ግን አንድ ነገር ማድረግ እንችላለን።ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይክፈቱ፣በፌስ ቡክ እና ትዊተር ያካፍሉ። 

https://www.change.org/p/un-security-council-stop-killing-in-ethiopia-by-tplf-dictatorial-regime  


ጉዳያችን / GUDAYACHN   www.gudayachn.com

Thursday, September 1, 2016

ህወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ አዲስ ቁማር ጀምራለች።ከመተማ እና ከጎንደር የትግራይን ሕዝብ ለማስደንበር ሞከረች።


ስደተኛ መሆን ምን ማለት ነው?

ስደተኝነት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ላለፉት አርባ አመታት ልብሳችን አድርገነው የኖርነው ክፉ ዕጣችን ነው። አንድ ሰው ከአገሩ የሚሰደደው በሚደርስበት የመንግስት ወይንም የሌላ አካል ጥቃት ሳቢያ ሊሆን ይችላል።በኢትዮጵያ በተለይ በአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ስደት ማለት ከአገር ውጭ ብቻ ሳይሆን እዚያው በአገራቸው እና በገዛ መሬታቸው ሲሆን ተመልክተናል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በጎንደር እና ጎጃም በተነሳው ሕዝባዊ አመፅ ሳብያ  የስርዓቱ አገልጋይ ሆነው ይልቁንም በሕዝብ ላይ ግፍ የፈፀሙት ላይ በተለየ ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።ይሄውም በጎሳ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን አማራም ሆነ ቤንሻንጉል እያለ ሳይለይ በኢህአዴግ ጋር ባላቸው ተሳትፎ እና በሕዝብ ላይ ባደረሱት በደል መጠን  ከህዝብ ጋር አይጥ እና ድመት ´የሆኑ ባለስልጣናት ንብረት ላይ አደጋ መድረሱ ተሰምቷል።በጎሳ ላይ የተመሰረተ ጥቃት ግን አልተፈፀመም።ለእዚህ አብነት የሚሆነው የወልቃይት ኮሚቴ አባል አንድ ወቅት የተናገሩት ነው።እንዲህ ነበር ያሉት 

´´ጎንደር ቀበሌ 18 ያለውን ፎቅ የሚያህል የለም ባለቤቱ የትግራይ ሰው ናቸው።እርሳቸው ለፍተው ጥረው ነው ያገኙት አንድ የነካባቸው ሰው የለም።እኔ እራሴ የወልቃይት ኮሚቴ አባል ነኝ አያቴ ትግራይ ናቸው።ይህንን ወሬ የሚያወራው እራሱ ወያኔ ነው።ሕዝብ ማጣላት ልማዳቸው ነው´´ ነበር ያሉት።

ይህ ብቻ አይደለም ጉዳዩን ያጣራው የክልሉ ቃል አቀባይም ምንም አይነት ዘርን እና  ቋንቋን ያማከለ ጥቃት አለመፈፀሙን እና በጎንደር ከተደረሰው አደጋ ከ80% ያማያንሰው በእራሱ በክልሉ ተወላጅ ላይ የደረሰ መሆኑን  ለአሜሪካ ራድዮ በሰጠው መግለጫ ገልጧል።

በጎንደር  ዩንቨርስቲ የሚማሩ የትግራይ ተወላጆችን ማን በግድ ጠራቸው? 

ህወሓት ግን የትግራይ ተወላጆችን ማስደንበር ቀጥላለች ለእዚህም ማስረጃ የሚሆነው የጎንደር ዩንቨርስቲ የሚማሩ የትግራይ ተወላጆችን በድንገት ዩንቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ በሚስጥር በመንገር እና ልዩ ትራንስፖርት በመመደብ እንዲሄዱ ያደረገችው ሥራ ነው። ተማሪዎቹ  ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው በሚስጥር ከመሆኑም በላይ የዩንቨርስቲ መልቀቅያ ሳይወስዱ በቀጥታ ትግራይ እንዲገቡ እና ትምህርት እንዲቀጥሉ ነው የተደረገው።ይህ በእራሱ ለተማሪዎቹም ግራ ያጋባ እና ለምን ትሄዳላችሁ ሲባሉ ´´እኛ ምን እናድርግ ኑ ተብለን ነው ´´ የሚል ምላሽ ሲሰጡ ለእራሳቸውም እየገረማቸው ነበር።ምክንያቱም የዩንቨርስቲው ማኅበረሰብ በእራሱ ምንም አይነት ችግር የሌለበት  ይልቁንም የእራሱ የሆነ ልዩ የአብሮነት መንፈስ ያዳበረ ግቢ ነውና ምንም የሚያሰጋቸው ጉዳይ የለም።በእዚህ ጉዳይ የጎንደርም ሆነ የመቀሌ ሕዝብ አይታማም።የሁለቱም ከተሞች ሕዝብ እንግዳ እግር አጥቦ ያለውን አብልቶ የእራሱን አልብሶ የሚያሳድር እንጂ እንደ አራሙቻ የህወሓት ካድሬ ነገር ሲያጠነጥን የሚኖር ሕዝብ አደለም።ህወሓት ግን ወጣቶቹን በለጋ አእምሯቸው ልክ ትልቅ ችግር እንደተፈጠረ ወደ ትግራይ እንዲመጡ ልዩ ትዛዝ አስተላለፈ። 

በመቀጠል በመተማ ሕዝብ ላይ ከትናትን በስትያ ጥቃት ለመፈፀም ሲዘጋጅ በመጀመርያ ያደረገው ነገር ቢኖር የትግራይ ተወላጆችን ማስደንበር ነበር።ህወሓት ቀድሞ ሲቪሉን ሕዝብ ለመፍጀት ስላሰበ  እና ጅምላ ጨራሽ  ሂደቱን በሚስጥር በተደረገ ስብስባ ስለወሰነ ትግርኛ ስለተናገሩ ብቻ ከውልደታቸው ጀምሮ  የሚያውቁትን መተማን ለቀው እንዲወጡ በመዋቅሩ አደረገ።በነገራችን ላይ በመተማ እና በጎንደር ትግርኛ ተናጋሪዎች ህወሓት እራሷ ገና በረሃ ሳትገባ የተወለዱ የተከበሩ የአገር ሽማግሌዎች የሚኖሩባቸው ቦታዎች ናቸው። ይህ ብቻ አይደለም ትግርኛ ተናጋሪ የኤርትራ ተወላጆችም አሁንም በፍቅር የሚኖሩባቸው ከተሞች ናቸው። ከእዚህ በላቀ ቁጥር ደግሞ ባህርዳር ከተማ  ከአነስተኛ ንግድ እስከ ከፍተኛ ሆቴሎች ድረስ አሁንም ትግርኛ ተናጋሪዎች ከሕዝቡ ጋር ተከባብረው የሚኖሩባት ሌላዋ ከተማ ነች። ነገር ግን ሕዝብ እንደ ሕዝብ አልተባረረባቸውም።

የሰሜን ጎንደሩ የተለየ ጉዳይ 

ከእዚህ ሁሉ በተለየ የህዝብ መገፋፋት የታየው በሰሜን ጎንደር ሁመራ እና ወልቃይት ነው።እነኝህ ከተሞች ላይ ከጥንት ጀምሮ ትግርኛ ተናጋሪ እና አማርኛ ተናጋሪው ተከባብሮ የኖረበት ይልቁንም የሰሊጥ ምርት ሲደርስ ከደቡብ ኢትዮጵያ ጭምር ለሰልሊጥ ምርት ለቀማ የሚሄዱበት እና የአዝመራ ጊዜው ሲያልፍ ሕዝብ ወደቦታው የምመለስባቸው ቦታዎች ናቸው።ህወሓት በረሃ እያለችም የምዕራባዊው ትግራይ ሕዝብ የሽሬ ከተማን ጨምሮ ህወሓት ´´አማራ ጠላታችን´´እያለች ስታወራ የትግራይ ሕዝብ በስብሰባ ´´ከጎንደር ሕዝብ ጋር አታጣሉን እናንተ ካድሬዎች ዛሬ ለፍልፋቹ  ወደ ጉረኗቹ ትመለሳላችሁ እኛ ቅዳሜ ገበያችን ጎንደር ሐሙሲት ነው።በፍቅር እንደኖርን ተዉን ´´ ማለቱን አሁን ድረስ የአካባቢው ሰው ደጋግሞ የሚያነሳው ወግ ነው። 

ይህ የሰሜን ጎንደር አካባቢን ግን ህወሓት የአዝመራ ወቅት ብቻ የመጡ የነበሩ ገበሬዎች ሳይሆኑ ከህወሓት የተቀነሱ ወታደሮች እና ከምዕራብ ትግራይ መሬታቸው የተራቆተባቸው ገበሬዎችን ወደ ሁመራ እና ወልቃይት እየወሰደ ማስፈር ሲጀምር እና ነባር ነዋሪው ግን አገሩን መልቀቁ የግጭቶች መነሻ ሆን።ስለሆነም የወልቃይት ግጭት ሲነሳ እነኝህ ከሰፈሩ ብዙ አመታት ያላስቆተሩ ገበሬዎች በእራሳቸው ስጋት  አካባቢውን እየለቀቁ መሄዳቸው ተሰምቷል። ይህ ትግግል ነው ማለት አይደለም። ለችግሩ ግን ዋነኛ  መነሻ የህዝቡ ተግባብቶ የመኖር አቅም ማጣት ሳይሆን ህወሓት በነባራዊው የህዝቡ የጋራ አኗኗር ስርዓት ውስጥ ታልቃ በመግባት ፖለቲካዊ ቃና ስለፈጠረችበት ነው። ምክንያቱም ህዝቡ ግጭት ቢፈጠር እንዴት በሽማግሌ እና በሃይማኖታዊ መንገድ እንዴት እንደሚፈታ ያውቅበታል።

ባጠቃላይ ህወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ ቁማር መጫወቷን ማቆም አለባት።የትግራይ ህዝብም ይህንን ቁማር ቀድሞ ተረድቶ ያልተፈጠረ ነገር እያራገቡ ለዘለቄታ የህዝቡ ጥቅም ላይ የምቀልዱትን ካድሬዎች በቃችሁ ሊላቸው ይገባል።አሁንም በጎንደር፣ባባህርዳር፣በመተማ፣ደባርቅ በርካታ የትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን  የህወሓትን ማስደንበር አጣጥለው በማህበራዊ፣ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች  ከተሳሰሩት  ሕዝብ ጋር አብረው እየኖሩ ነው።  ህወሓት ዘለቄታው ውርደት ወደሆነው የውርደት ገደል ለሚከታት ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ በቆሙ ካድሬዎች ሕዝቡን ማስደንበሯን ቀጥላለች።ዛሬ በማኅበራዊ ድረ ገፅ ላይ የምናየው ድራማም የእዚሁ የህወሓት የማስደንበር አካል ነው።ይህ ማለት ግን አንዳንድ በስሜታዊነት እየተገፉ ህዝብን የሚጎዳ ሥራ የሚሰሩ ይጠፋሉ ማለት አይደለም።እነርሱን ግን በሽማግሌ እያስመከሩ ሕዝብ ዘለቄታውን ከህወሓት ውድቀት በኃላ የምትኖረውን ኢትዮጵያ  አሻግሮ መመልከት አለበት።መንግስት በከፋፋይነት የቆመባት አገር ሆነን እስካሁን ሕዝብ እንደ ሕዝብ አለመጫረሱ አገሩ ኢትዮጵያ ስለሆነ ነው እንጂ እንደ ህወሓት መርዛማ ሥራ ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ ተባልተን ባለቅን ነበር።

ህወሓት ሕዝብ ለመከፋፈል ቢሮ ከፍቶ ባለሙያ ቀጥሮ የሚሰራ የእኩይ እኩይ የሆነ መንግስት ነው።ስለሆነም የትግራይ ሕዝብ በህወሓት የማስደንበር ወጥመድ ሳትገባ እራሱ ህወሓትን በመቃወም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አጋርነትህን ማሳየት የወቅቱ ጥያቄ ነው። ደግሞስ በአንዳንድ ቦታዎች ጎረቤት ከጎረቤት በጎሳ ምክንያት ግጭት ቢነሳ ማነው መወቀስ ያለበት።የኢትዮጵያ ሕዝብ የእዚህ አይነት ጠባይ ነበረው? የትግራይ ህዝብስ በፓርላማ ደረጃ የጎሳ ፖለቲካ በማወጅ ሕዝብ ከህዝብ የለያየውን ህወሓትን መታገል እና መውቀስ ነው ያለበት ወይንስ የጎሳ አባት የሆነውን ህወሓትን እሹሩሩ ማለት አለበት? የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚኖር የጋራ አብሮነት ጥቅም ይበልጣል? ወይንስ ነገ ብል የሚበላው የህወሓት የዛገ ታንክ ነው የሚበልጠው? በደንብ መታሰብ ያለበት ጉዳይ ነው። 


ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

“ጠላታችን ህወሃት እንጂ የትግራይ ህዝብ አይደለም”


ይህ ፅሑፍ ለምን በሚገባው በእየድረ ገፁ ላይ  በሚገባ እንዳልተዳረሰ ይገርመኛል።በአሁኑ ወቅት ህወሓት በስልጣን ለመቆየት ብቸኛ የመንጠላጠያ ምሰሶው የትግራይን ሕዝብ እያስደነበረ ከሌላው ወገኑ ጋር እያጋጨ የስልጣኑ መጠበቅያ ሊያደርገው ይፈልጋል።ለእዚህም እንዲረዳው አንዳንድ ፀሐፊዎችን የውሸት ፅሁፎች እንዲያሰራጩ እያደረጉ ነው።እውነታውን ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ አለበት።
ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍ ነሐሴ 5፣2008 ዓም በአርበኞች ግንቦት 7 ኦፊሻል ድረ ገፅ ላይ የወጣ ግልፅ መልዕክት ነው።የትግራይ ማኅበረሰብም (አውቀው የሚያራግቡትን ትተን) ኢትዮጵያ ከሶስት ሺህ ዓመት በላይ በመንግስት ስርዓት ለመኖሯ አክሱም ያለውን ሐውልት ብቻ መመልከት ምስክር ነው።ዛሬም ነገም ለችግር ደራሽ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ በዘር የተቧደነው ህወሓት አይደለም።ህወሓት በማንኛውም ሰዓት ፈራሽ ነውና። መልካም ምንባብ። 
////////////:::::::::///////:::::::::///////////:::::::::///////////
“ጠላታችን ህወሃት እንጂ የትግራይ ህዝብ አይደለም”

የህወሃትን አገዛዝ ለመቃወም ባለፈው ዕሁድ አደባባይ የወጣው የጎንደር ህዝብ ከፍ አድርጎ ሲያስተጋባቸው ከዋለው መፈክሮች አንዱ “ጠላታችን ህወሃት እንጂ የትግራይ ህዝብ አይደለም” የሚል ነበር።

ይህ መፈክር ህወሃት ባለፉት 25 አመታት የሥልጣን ዘመኑ ከትግራይ ውጪ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ህዝብንና ህወሃትን አንድ አድርጎ እንዲመለከት በዘረኝነትና በጥቅም በሰከሩ ጥቂት ተከታዮቹ አማካኝነት ሲቀነቀን የኖረውን ቅስቀሳ ዋጋ ያሳጣ ብቻ ሳይሆን ህወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ አይኖርም ተብሎ በጭፍን ሲነዛ የሰነበተውን መሠረተ ቢስ ፕሮፖጋንዳ አከርካሪ የሰበረ ነው። ህወሃት ስልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ በህዝባችንና በአገራችን ላይ የፈጸማቸው ወንጀሎች የትግራይን ህዝብ በጅምላ ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችልበት ህጋዊም ሆነ ሞራላዊ አመክንዖ እንደሌለ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። “እኔ ከሌለሁ አማራው ወይም ኦሮሞው በጠራራ ጸሃይ ያጠፋሃል ወይም ይበቀልሃል” በሚል ቅስቀሳ የትግራይን ህዝብ መደበቂያ ዋሻ ለማድረግ የሚደረገው ሙከራ ህወሃት በመሣሪያ ትግል ላይ በነበረበት 17 አመታት በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸማቸውን ወንጀሎች ለማድበስበስና ለማዘናጋት ካልሆነ በቀር ለምንም ፍጆታ ሊውል የሚችል ነገር አይደለም። በዚያ የ1977 ደርቅ ወቅት አለም አቀፍ ለጋሾች በህወሃት ቁጥጥር ሥር ለነበሩ የትግራይ ወረዳዎች እንዲከፋፈል የሰጡትን የነፍስ አድን እርዳታ እህል እነ መለስ ዜናዊ፤ ስዩም መስፍን፤ ስብሃት ነጋ እና ብርሃኔ ገብረኪርስቶስ የመሳሰሉ የህወሃት መሪዎች በምን አይነት ማጭበርበር ከረሃብተኛው ጉሮሮ በመቀማት በአንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር በሱዳን በኩል ወደውጪ ልከው እንደሸጡና ድርጅታቸውን በመሳሪያና በሎጄስቲክ እንዳጠናከሩበት በዚህም የተነሳ በተላከላቸው የምግብ ዕርዳታ ህይወታቸው ይድን የነበሩ ብዙ ሺህ የትግራይ ተወላጆች በረሃብ እንደቅጠል እንደረገፉ የትግራይ ህዝብም ሆነ የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚረሳው ጉዳይ አይደለም። ለርካሽ የፖለቲካ ዓላማ የትግራይን ህዝብ ለማነሳሳትና ከጎኑ ለማሰለፍ ሲባል ብቻ ለደርግ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ገበያ የወጣ ሠላማዊ የሃውዜን ነዋሪዎች በአገሪቱ አየር ሃይል በግፍ እንዲጨፈጨፉ ህወሃት የተጫወተው ሚና በፕሮፖጋንዳ መሣሪያዎች ብዛትና የካድሬዎች ጋጋታ ከታሪክ ማህደር የሚፋቅ አይሆንም። ሌላው ህወሃት በትግራይ ህዝብ ላይ ከፈጸማቸው መልከ ብዙ ክህደቶች ሳይገለጽ መታለፍ የሌለበት “ከደርግ ጋር አብራችኋል” የተባሉ የትግራይ ተወላጆች ቤተሰቦች የደረሰባቸው ስቃይና እንግልት ፤ እንዲሁም ህወሃት በኢትዮጵያና በታሪኳ በተለይም በአማራው ህዝብ ላይ ያለውን የጥላቻ ፖለቲካ የተቃወሙ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች የራሳቸውን መቀበሪያ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ ተደርገው የተፈጸመባቸው ዘግናኝ ጭፍጨፋ አንዱ ነው። እንዲህ አይነት ኢሰብአዊና ዘግናኝ እርምጃዎችን በትግራይ ተወላጆች ላይ እየፈጸመ ለሥልጣን የበቃ ሃይል ዛሬ የፖለቲካ አላማውንና ከመንግሥት ሥልጣን የተገኘ ጥቅሙን እንዲያስከብሩለት ትግሪኛ ተናጋሪዎችን እየፈለገ በመንግሥት ሥልጣንና በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሃላፊነት ቦታዎች ላይ በብዛት ስለመደበ ወይም ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎችን እንዲቆጣጠሩት ስለአደረገ የትግራይ ጥቅም አስከባሪ ወኪል ተደርጎ ሊቆጠር አይችልም ። ህወሃት እራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ነኝ ስላለ ብቻ የትግራይ ህዝብ ተወካይ የሚያደርገው ህጋዊ ወይም ፖለቲካዊ ድንጋጌ እንደሌለ ማንም አይዘነጋም ። የኢትዮጵያ ህዝብ በጠባብ አላማ የተሰባሰቡ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች በህወሃት ሥም ተደራጅተው የአገራችንን በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ በህዝባችንና በአገራችን ላይ ለፈጸሟቸው ወንጀሎችም ሆኑ በትግሉ ወቅት በትግራይ ወገኖቻችን ላይ ላደረሱት ጥቃት የጊዜ ጉዳይ ካልሆን በቀር በህግ ይፋረዳቸዋል። ያን ጊዜ ተጠያቂ የሚሆኑት ድርጅቱን እንመራለን የሚሉና በተዋረድ የመንግሥትን ሥልጣን የተቆጣጠሩ ህግ አውጭዎች ህግ አስከባሪዎችና በአስፈጻሚነት ላይ ያሉት ብቻ ይሆናሉ። ህወሃት ዛሬ የሚመካበት የሠራዊት ብዛትና የመሳሪያ ጋጋታ በምንም ተአምር ያንን የፍርድ ቀን የሚያስቀር አይሆንም ።

ህዝባችንን ለመግዛት መለኮታዊ ሥልጣን እንዳላቸው ቤቴ እምነቶች ሳይቀሩ ሲያስተምሩላቸው የነበሩ የቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ መንግሥት ከአመት ባነሰ ዕድሜ እንዴት እንደተንኮታኮተ እናስታውሳለን። በሠራዊትና በመሳሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን በወታደራዊ ሳይንስ ብቃቱ በአፍሪካ ተወዳዳሪ ያልነበረው የደርግ ዘመን ሠራዊትም በምን ፍጥነት እንደተበተነ እናውቃለን። ከዚህ ሁሉ ልምድ ትምህርት ለመቅሰም ያልታደለው ህወሃትም አወዳደቁ ከዚህ ያልተለየ ምናልባትም የከፋ ሊሆን እንደሚችል ለመናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። ድርጅቱን ከምሥረታው ጀምሮ ያቋቋሙና ለድል ያበቁት ተሰናባች የህወሃት መሪዎቹ በግለሰብ ደረጃ እየመሰከሩ ያለው ሃቅም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው ።

“ጠላታችን ህወሃት እንጂ የትግራይ ህዝብ አይደለም” በማለት የጎንደር ህዝብ ሃምሌ 24 ከፍ ብሎ ሲያስተጋባ የዋለው መፈክር የመላው ኢትዮጵያዊያን መፈክር እንደሆነ ህወሃት በከፈተው የጥቅም ቦይ ያልተወሰደ የትግራይ ህዝብ ሁሉ በሚገባ ይገነዘባል። የዚህን መፈክር እውነታነት የሚጠራጠሩ በመንግሥትና የህዝብ ሃብት ዘረፋ የከበሩና የሰረቁትን ገንዘብ ማሸሺያ የሚጨንቃቸው ከትግራይ ሰፊው ህዝብ የተገነጠሉ የትግራይ ተወላጆችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ብቻ ናቸው። መላው የትግራይ ህዝብ እንደተቀረው ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ የህወሃት አገዛዝ ይብቃ እያለ መሆኑን በነአብረሃ ደስታ ላይ የተፈጸመው ግፍ ማስረጃ ነው

አርበኞች ግንቦት 7 የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ያነሳውን የማንነት ጥያቄ አስመልክቶ ጎንደር ላይ የተደረገው ሠላማዊ ሰልፍ በመላው አገራችን ላይ ከፈጠረው መነቃቃት በተጨማሪ ለህወሃት መሪዎች ያስተላለፈው ትልቅ መልዕክት እንዳለ ያምናል። ይህ መልዕክት ትዕግሥት እውቀት እንጂ ፍርሃት አለመሆኑን የሚገልጽ መልዕከት ነው። ህወሃት ሺ ጊዜ የሚመካበት የጦር መሳሪያና የሠራዊት ብዛት ህዝብ ለነጻነቱ የሚያደርገውን ተጋድሎ ሊያስቆም እንደማይችል ከራሱ ተሞክሮ ማወቅ ነበረበት ። ህዝብ በሠላማዊ መንገድ ነጻነቱን ለማስከበር የሚያቀርበውን ጥያቄ ህወሃት በለመደው እብሪት በሃይል ለመቀልበስ በሚያደርገው እርምጃ በሰው ህይወትም ሆነ በንብረት ላይ ሊደርስ በሚችለው ጉዳት ተጠያቂው ህወሃት ብቻ እንደሆነ አርበኞች ግንቦት 7 ያስጠነቅቃል። በዚህም ምክንያት በኦሮሚያ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግዲያ በአስቸኳይ እንዲቆምና በጎንደርና በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እየቀረበ ያለው የመብት ጥያቄ በአስቸኳይ ምላሽ እንዲያገኝና አገራችን ከገባቺበት የፖለቲካ አጣብቂኝ እንድትወጣ የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት 7 ለመላው የአገራችን ህዝብ የትግል ጥሪ ያቀርባል። የህወሃት የአፈና አገዛዝ ላለፉት 25 አመታት በህዝባችን ጫንቃ ላይ እንዲንሰራፋ ፖለቲካዊ ፤ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ሲያደርጉ የኖሩ ምዕራባዊያን መንግሥታትና የወይኔ ደጋፊዎች ድጋፋቸው በአገሪቱ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት ቆም ብለው እንዲያስቡና አሰላለፋቸውን እንዲያስተካክሉ በዚህ አጋጣሚ ንቅናቄያችን ያሳስባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!


ምንጭ = አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ 
                  ነሐሴ 5፣2008 ዓም 

Tuesday, August 30, 2016

በኢትዮጵያ ከገጠር እስከ ከተማ በከፍተኛ ደረጃ በድብቅ እየተደመጠ እና እየተሰራጨ ያለ ወኔ ቀስቃሽ ሙዚቃ





ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

በኢትዮጵያ አሁን ያሉት አማራጮች (በቀጣይ የሚሆኑት) ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው።ምርጫው በእያንዳንዳችን ውጤት ይወሰናል። (የጉዳያችን ማስታወሻ)


ሀ/ ነባራዊ ሁኔታው 

1/ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ በቃኝ ብሏል። 
2/ ወያኔ ለእውነተኛ የፖለቲካ መፍትሄ ዝግጁ አይደለም።
3/ ወያኔ ፋሽሽት መንግስት መሆኑን በሚያፈሰው የንፁሃን ደም አስመስክሯል።
4/ የወያኔ ደጋፊዎች  ወያኔ በሕዝቡ ላይ መዝመቱን ሲሰሙ ´´እሰይ ይበለው!´´ ሲሉ እየተሰሙ  ነው።በእዚህም የበለጠ የህዝብ ልብ አድምተዋል።እነኝህ ነባራዊ ሁኔታዎች ናቸው።
5/ አቶ ኃይለ ማርያም ድምፁን ያሰማው ሕዝብ እንዲገደል ፈርምያለሁ ብለው በይፋ ተናግረዋል።

ለ/ ሁለቱ ብቸኛ አማራጮች 

አማራጭ አንድ 

ወያኔ በሕዝቡ ላይ የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥሏል።ትናንት ነሐሴ 23/2008 ዓም ጀምሮ ተጨማሪ ከባድ መሣርያዎች እየገቡ ነው።ስለሆነም ወያኔ ይህንን አመፅ ከጨፈለቀ በሰልፍ ላይ የታዩትወጣት፣ሽማግሌ  ሁሉ የሱዳን እና የአረብ አገር ስደተኛ ይሆናሉ።በበረሃ ያልቃሉ።የቀሩት እስር ቤት ገብተው ይማቅቃሉ።የአንድ ጎጥ ፖለቲካ በባሰ ፋሽሽታዊ መልኩ ይቀጥላል።ትግሉ ግን አይቆምም።የጎጥ በደል የደረሰበት ሕዝብ ደግሞ በማንኛውም መልኩ በደሉ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የአንድ አካባቢ ሕዝብ መሆኑን አምኖ ባገኘበት ቦታ ሁሉ ጥቃቱን ይፈፅማል።በእየቦታው በማናቸውም ጊዜ እና ሰዓት ለምሳሌ በስፖርት ውድድር፣ሆቴል፣ ሆስፒታል ሁሉ ሕዝብ አመፁን በመግደል ሊያሳይ ይችላል።

አማራጭ ሁለት  

አማራጭ ሁለት በስሩ ሶስት ክፍሎች ይዟል።ይሄውም ወያኔ በሕዝቡ ላይ የጀመረውን ወታደራዊ ዘመቻ ሲቀጥል የሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ሊከሰት  ይችላል። ወደድንም ጠላንም እነኝህ ሁኔታዎች በአጭር (በጥቂት ቀናት እስከ ጥቅምት)  ወይንም በመካከለኛ ጊዜ (እስከ የካቲት፣2009 ዓም ) ይፈጠራሉ ብሎ ማሰብ ይቻላላ።

እነርሱም -

1ኛ/ በጦር ሰራዊቱ ውስጥ ትግሪኛ ተናጋሪ ያልሆነው እራሱን ከእነ መሳርያው ይለያል።በአንዱ የአገራችን ክፍል ተቆርጦ ባለበት ይታኮሳል።አንዳንድ ቦታዎች ላይ የጎበዝ አለቃውን  ከበታች መኮንኖች መርጦ እረዘም ላለ ጊዜ ይዋጋል።ምናልባትም ሕዝብ እየተቀላቀለው የሚሄድ ያልታወቀ አለቃ ሊነሳ ይችላል። ይህ በአፍሪካ የተለመደ ነው።

2ኛ/ በሰሞኑ ሰልፍ የተሳተፈው ወጣት ተመልሶ እቤቱ ቢገባ ወያኔ እንደሚያደርገው እንደሚታፈስ ስለሚያውቅ ያለውን መሳርያ ይዞ ወደ ገጠሩ ክፍል ይገባል። ለእለት የሚሆነውን ከወያኔ ካምዮኞች ላይ እየዘረፈ አንዳንዴም ወደ ከተማ የተቀናበረ ዘመቻ እያደረገ ወያኔን መቆምያ መቀመጫ ያሳጣል። ይህ ሁኔታ በተደራጀ መልኩ ማለትም በፖለቲካ ኃይሎች አደረጃጀት ከታገዘ አጠቃላይ ለውጥ በኢትዮጵያ ያመጣል።የሰው ሕይወት እና የንብረት አደጋ ማጥፋቱ አይቀርም።በአዲስ አበባም በማናቸውም ሰዓት በህወሓት ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ሊፈፅም ይችላል። 

3ኛ/ ሁኔታዎች ከእጃቸው መውጣቱን የተረዱት ወያኔዎች በግብፅ እንደተደረገው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት (በጀነራል ፃድቃን ሃሳብ መሰረት) አንድ ቀን ማለዳ የተወሰኑ የህወሓት ባለስልጣናት መታሰራቸውን ይነግሩን እና የፖለቲካ ኃይሎች ለውይይት ይምጡ ሊሉ ይችላሉ።ይህ ለህወሓት ሁለት ጥቅም አለው።አንዱ  የዘረፉትን ንብረት እንደማይወሰድባቸው ዋስትና ከመጪው ወታደራቸው ያገኛሉ።ሁለተኛ በተዘዋዋሪ የተቃውሞውን ጎማ ሽክርክሪት ያበርዱበት እና ከአንድ እና ሁለት ዓመት በኃላ መልሰው የህወሓት አስተዳደርን ቀለም ቀብተው አግባብተው ይመልሱታል።

መፍትሄው 

ፀረ ወያኔ ትግሉ መቆም የለበትም።ከላይ የጠቀስኩት ሁሉ ከመምጣቱ በፊት የትግራይ ኤሊት ህወሓት የሚሄድበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን በግልፅ  ተረድቶ የትግሉ አካል መሆን ብቸኛ አማራጩ ነው።ኤሊቱ ወደ እዚህ ትግል በግልፅ መግባቱ ለጊዜው የሚያሳጣው ነገር ያለ ይመስለዋል። ሆኖም ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የሚያጣው የከፋ እና ለብዙ አመታት ቁስል ጥሎ የሚሄድ ነው እና አያዋጣም።ይህንን የትግራይ ኤሊት አያደርገውም ምቾት ቀጠና (comfort zone) ስለሆነ መንቀሳቀስ አይፈልግም የሚሉ ብዙዎች አሉ።ነገሩ አያሳምንም ማለት አይቻልም።

ከእዚህ በተለየ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ምርጫ ተሳተፈ ውጤቱ ድምፁ ተነጠቀ።ሰላማዊ ሰልፍ ፍቀዱልኝ አለ።ምላሹ ዱላ ሆነ።በኃይል ተነስቶ እጁን እያጣመረ  በቃኝ አለ።በምላሹ በጥይት ተገደለ።አሁን ደግሞ በታንክ እየዘመቱበት ነው።ስለሆነም ከእዚህ በኃላ የሽምቅ ውግያ በየትኛውም ቦታ ቢደረግ ተጠያቂው ህወሓት እና አይዞህ ባዮቹ ብቻ ናቸው።እንደ እኔ አስተያየት ከላይ ከጠቀስኩት ውጭ ታምር ይፈጠራል ብዬ አላስብም። እርግጥ ነው ከላይ የተፃፉት ስፃፉ እንጂ ሆነው ስናያቸው ታምር መሆናቸው አይቀርም።መሆናቸው ግን አይቀርም።


ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Sunday, August 28, 2016

ህወሓት ምንም አዲስ መልዕክት የሌለው መግለጫ ዛሬ ሰጠ።ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው EPRDF press release is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years


የአማርኛ ፅሁፍ ከስር ይመልከቱ።
EPRDF press release of August 28,2016 is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years. It is  full of empty words. There is no single word of ´´excuse´´ for over 1000 Ethiopians killed in last seven months by the regime. The press release is expected to invite more people to protest  TPLF. Because it did´t even reason out the real situation of the country plus the possible solutions suppose to be proposed by this particular press release. In addition to that the press release, at the last statement conclusion, warns peaceful protestors and appreciate the regime´s security personnels. Such a kind of approaches of TPLF is very common for Ethiopians in the last 25 years. In short it is possible to say that this is another confirmation as dictators will make fast their last days by following poor minded advisers. The same is happening in TPLF. For your easy information about the press release, please read the below Amharic version of Gudayachn´s view and full press release of TPLF video at the end of article.

የኢትዮጵያ ሕዝብ እያገባደድነው ባለው የ2008 ዓም ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል በአዲስ መልክ ያቀጣጠለበት ዓመት ነው።በእዚህ ዓመት ብቻ እስካሁን ትክክለኛ ቁጥሩ ባይታወቅም በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች ብቻ በሰላማዊ ሰልፍ መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን በጥይት አረር ተገድለዋል። በአስር ሺዎች ወደ እስር ቤት ተግዘዋል።ሌሎች አስር ሺዎች ካሉበት ቀዬ ወደ ሌላ ቦታ ተሰደዋል።

ሕዝባዊ አመፁ እያየለ መጥቶ ይህ ፅሁፍ በምፃፍበት በእዚህ ቅፅበት በጎንደር እና ጎጃም ሕዝብ የህወሓት መዋቅር የሆኑ የአስተዳደር እርከኖችን አፍርሶ እራሱን በእራሱ ጊዝያዊ የአስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ እና መሪውን እየመረጠ መሆኑ እየተዘገበ ነው።በእዚህ ሁኔታ እያለ ነው እንግዲህ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከስብሰባ በኃላ ደረሰበት የተባለውን ውሳኔ ዛሬ ነሐሴ 22፣2008 ዓም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተነበበው።

መግለጫው በእራሱ የኢህአዴግ ነው ወይ? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው።ምክንያቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብአዴን እና ኦህዴድ ቀድሞም በህወሓት መዋቅር የመታዘዛቸው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ በእዚህ ዓመት ይብሱን በሕዝባዊ አመፁ ሳብያ ሕልውናቸው ማክተሙን በግልፅ የታየበት ነው።ስለሆነም የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲባል ህወሓት እና ህወሓት ብቻውን ያሰበውን መግለጫ በሚል ስም እንዳወጣው መረዳት ተገቢ ነው።

በተሰጠው መግለጫ ላይ በመጀመርያ ክፍል ላይ ´´ውዳሴ ህወሓት´´ የተሞሉ ቃላት ብቻ ሲገኙበት።በሚልዮን የሚበሉት እና የሚጠጡት ባጡባት አገር ውስጥ ይልቁንም ረሃብ እንደ አዲስ አበባ ያሉ ታላላቅ ከተሞች ውስጥ ተማሪዎች የምግብ ድጋፍ ካልተደረገላቸው ትምህርታቸውን መቀጠል እንደማይችሉ እነዩኒሴፍ የመሳሰሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በገለፁበት ሁኔታ ሁሉ የኢህአዴግ መግለጫ ኢትዮጵያ እንዳደገች ለመስበክ መሞከሩ አሁንም በአስራአንደኛው ሰዓት ላይ ቆመውም ህወሓቶች ለለውጥ ሳይሆን ለበለጠ ግድያ መነሳታቸውን አመላካች ነው።

የመግለጫው ዋና እና ቁልፍ ምክንያት የኢትዮጵያን ሕዝብ አዘናግቶ የበለጠ ጦር ሕዝባዊ አመፁ ወደተነሳባቸው ቦታዎች አዝምቶ ለመጨፍለቅ እና የምዕራባውያንን ውትወታ በሆነች ለውጥ በምትመስል መግለጫ ይሄው እየሰራን ነው ለማለት የታሰበ ነው።ለእዚህም ነው የህወሓት የማኅበራዊ ሚድያ አፈቀላጤዎች  መግለጫውን በተመለከተ በእንግሊዝኛ ለመፃፍ የሚደክሙት።ሌላው አስቂኝ የመግለጫው ሂደት አሁን ኢህአዴግ የሚያደርገው ለውጥ ከአስራ አምስት ዓመት በፊት የተጀመረው አካል ነው ሲል መደመጡ ነው።ይህ ´´ ሃያ አምስት ዓመት በጥይት ስገድሉን ኖረው አሁን ደግሞ በሳቅ ገደሉን ´´የምትለዋን አባባል ያስታውሳል። ስህተት ተሰርቷል ለውጥ ያስፈልጋል ብሎ በድፍረት የለውጥ አስፈላጊነትን አፍን ሞልቶ ለመናገርም ያፈረ ስርዓት ዛሬ በህዝባዊ አመፅ ለለውጥ ተገደድኩ ይሉኛል በሚል ጭንቀት ለውጡን ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ባቀጣጠልነው መሰረት ነው ብሎ መግለጫ ማውጣት ለምንም አይነት እርምጃ አለመዘጋጀታቹን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል። 

ህወሓት በእዚህ መግለጫ ላይ ለችግሩ መነሻ ብሎ ያቀረባቸው ነጥቦች በእራሳቸው ደካማ እና መሰረታዊ የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ ያገለለ ነው።በዛሬው መግለጫ ህወሓት የአገራችን ችግር ብሎ ያቀረባቸው ችግሮች ያሉ ችግሮች ቢሆኑም ዋናው እና መሰረታዊው ችግር ከላይ እንደተጠቀሰው የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት፣ጎጠኛ እና አድሏዊ ስርዓት መስፈን እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ የሚሉት ዋነኛ ናቸው።ለእነኝህ መፍትሄዎቹ ደግሞ በዋናነት ህወሓት ስልጣኑን በፍጥነት እንዲለቅ ማድረግ እና ሕዝባዊ እና የሽግግር መንግስት መመስረት ነው።ከእዚህ ያነሰ መፍትሄ ቁስል የበለጠ እንዲመረቅዝ እና ኢትዮጵያን ወደ ባሰ ማጥ ውስጥ የመክተት ግልፅ ፍላጎትን ብቻ ያመለክታል።ህወሓት በዛሬው መግለጫው ግን ችግሮች ብሎ ጉዳዩን በጥገናዊ ለውጥ ለማለፍ የሞከረበት መንገድ ችግሮቹን  የህዝብ መብዛት፣የሕዝብ ፍላጎት መጨመር፣ስልጣንን የሀብት ማከማቻ የማድረግ ሂደት በኢህአዴግ ውስጥ በመስረፁ ወዘተ ናቸው በሚሉ ቃላት ለማድበስበስ ሞክሯል።

ባጠቃላይ መግለጫውን በሶስት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን።የመጀመርያው ክፍል ህወሓት እራሱን ያሞገሰበት እና ኢትዮጵያውያን ´´ምግብ በልታችሁ ያደራችሁት እኔ ስልጣን ከያዝኩ በኃላ ነው´´ ቀረሽ ሐተታ ሲሆን ሁለተኛው ችግሩን ከህወሓት የስልጣን ጥማት እና አገሪቱን በተሳሳተ የጎጥ ፖለቲካ  መከፋፈል የመጣ መሆኑን ሸሽጎ የችግሩን መነሻ በገሃድ ካሉ ግን ብቸኛ ችግሮች ካልሆኑት የስልጣን መባለግ፣የህዝብ ብዛት መብዛት እና የህዝብ አዳዲስ ፍላጎቶች በሚሉ ቃላት ሊያድበሰብስ የሞከረበት ነው።በመግለጫው የመጨረሻ ክፍል ላይ ደግሞ ሕዝባዊ አመፁን የጥፋት ኃይሎች መሆኑን ሊሰብክ ይሞክርና ከጎኑ ቆመው ሕዝብ የገደሉትን ሲያሞግስ እና አይዟችሁ በርቱ ሲል ታገኙታላችሁ። መግለጫው ባጭሩ ይሄው ነው።ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው።ህወሓት ማር ሊያመነጭ አይችልም።ማር የንብ ሥራ እንጂ የዝንብ ሊሆን እንደማይችል ሁሉ።

ሙሉ መግለጫውን ለመመልከት  ይህንን ይጫኑ።

ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Friday, August 26, 2016

ጥልቅ ሐዘን / Our deep condolences



==============
OUR DEEP CONDOLENCES FOR ALL ETHIOPIANS KILLED IN -OROMIA,AMHARA,GAMBLE,BENISHANGUL,KONSO,AFAR,ASOSA, HARER AND OTHER PLACES BY TPLF SOLDIERS.

በኢትዮጵያ፣በኦሮምያ፣አማራ፣ጋምቤላ፣አፋር፣አሶሳ፣ኮንሶ፣ቤንሻንጉል ሐረር እና ሌሎች ቦታዎች በህወሓት ወታደሮች ለተገደሉት እና አሁንም እየተገደሉት ላሉት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሃዘናችን የጠለቀ ነው።
=========================




ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com