Thursday, August 8, 2013

በትልቋ ኢትዮጵያ ውስጥ የእስልምና ተከታዮች ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንም አሉ።


መግቢያ 

ኢትዮጵያ ዛሬ ከሰማንያ ሚልዮን በላይ ሕዝብ ያለባት ነገ ከመቶ ሚልዮኖች በላይ የሚኖሩባት ሀገር ናት።ባለፈው ታሪካችን በባህል፣በቋን እና በሃይማኖት ተከባብረን በመኖራችን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ በሰላም ደርሰናል። አለም የመድን ዋስትና (ኢንሹራንስ) ሳይኖረው ዕድር በመፍትሄነት አስቀምጠን የሞተው ሲቀበር እና ሃዘንተኛ ሲደገፍ ዘመናት አልፈዋል።የባንክ አሰራር ገና ሳይተዋወቅ ዕቁብ በገንዘብ መቆጠብያነት ተጠቅመንበታል። ዕድር እና ዕቁብ አገልግሎታቸው ይህ ብቻ አይደለም።በማኅበራዊ ችግሮች ዙርያ በሚነሱ አለመግባባቶችም የመፍትሄ አካል ሆኖ አገልግሏል።ግጭቶች ለእድር አባላት ቀርቦ መፍትሄ ይፈለግለታል።አቅም ያነሰው እድርተኛ እንዲደጎም ይደረጋል።ህብረተሰቡን የበጠበጠ አጉራ ዘለል ከእድር እንደሚለይ ማስጠንቀቅያ ይሰጠዋል።በጥንቱ አገረ ገዢው በዘመኑ ቀበሌ ወይንም ገበሬ ማህበር የማይፈታው የአካባቢ ችግር በዕድር መፍትሄ ያገኛል። ይህ እንግዲህ የነበርንበት የአኗኗር ዘይቤ መሆኑ ነው።

ባለንበት ዘመን በትልልቅ ከተሞች የዕድር ተቅዋም አቅም እየቀነሰ ቢመጣም በገጠሩ እና መለስተኛ ከተሞች (ከ85% በላይ ሕዝብ በ  ሚኖርበት የሀገራችን ክፍል) ግን ዕድር በሕዝቡ ኑሮ ውስጥ ተደማጭ እና ተፅኖ ፈጣሪ ነው።ዕድርን የመሳሰሉ ማህበራዊ ተማት ለሕዝቡ የአብሮነት አኗኗር  ያላቸው ፋይዳ እጅግ ትልቅ ነው። ዕድር ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አሰራርን ይዞ ቢቻል ከመድን ዋስትና ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ እስከ የጠለፋ ዋስትና አሰጣጥ ድረስ አዘምኖ ግን ማህበራዊ ትስስርን (ጊዜ፣ጉልበት እና ገንዘብን በቆጠበ መልክ) የሚያጎለብት  እንዲሆን ማድረግ  ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ የምትገነባውም ሆነ የምትታወከው  በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ስሜት ብቻ ሳይሆን ትንንሽ በሚመስሉ እንደ እድር ባሉት ተማት ሕልውና እና ሞት ጭምር መሆኑን  መዘንጋት አይገባም።

''የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንኳን እኛ ግመላችን ታውቀዋለች''

ኢትዮጵያን እድር ውስጥ ማየት ከቻልን የእስልምና ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እየደረሰባቸው ያለው የመንግስት በትር ምን ያህል የሚያም መሆኑ ወለል ብሎ ይታየናል።በእድራችን ውስጥ እማማ ዙቤዳ ሲልኩን ተልከን አድገናል። እትዬ ፋጡማ ሲቆጡን እሺ ብለን ሰምተናል።ሃጂ ኑር ከእድሜ እና ከልምድ ሲመክሩን አዳምጠናል። እኛ ያደግንባት ኢትዮጵያ ይህች ነች። ዛሬ ሃጂ ተገልብጠው የሚ ያከብሯትን፣የሚሽቆጠቆጡላትን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ''አጎሳቆሉት'' ብሎ ኢቲቪ ቢነግረኝ የምሰማበት ምን አይነት ሞራል ይኖረኛል? እንዴት ነው በኢትዮጵያ በጎ ዘመን ሲደሰቱ፣ኢትዮጵያ ስትከፋ ያነቡ የሰፈሬ የእድሩ ማገር የነበሩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዛሬ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አዋረዱ ብሎ ኢቲቪ የሚነግረኝ? የአፋሩ ንጉስ አሊቢራ ''የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንኩዋን እኛ ግመላችን ታውቀዋለች'' ተብሎ ሲነገር እየሰማሁ አድጌ  ዛሬ ኢቲቪ ሌላ ታሪክ ሲያወራኝ በየትኛው ልቦናዬ ልስማው? 

ከባህር ውስጥ አንዱ ወይም ሁለቱ አሳ ቢገማ በባህር ውስጥ ያሉትን አሳዎች በሙሉ አይወክልም።

መንግስት ትልን ኢትዮጵያ ማየት ቢችል ኖሮ በቲቪ መነገር የሚገባውን ከማይገባው ለይቶ ማቅረብ በቻለ ነበር።ሆኖም ግን  ከዛሬ አስር አመት ወዲህ በአንዳንድ ቦታዎች ኢትዮጵያዊውን ሙስሊም ከኖረበት አብሮነት ስሜት ለመለየት ሙከራ እያደረጉ ያሉ የሉም ማለት አይደለም። በጅማ ዙርያ፣በአጋሮ ዙርያ፣በአሩሲ አንዳንድ ቦታዎች፣በባሌ ደቡባዊ ክፍል እና በሌሎች ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር  አብረው ለዘመናት በእድር አባልነት የኖሩ የእስልምና ወንድሞች እና እህቶች እንዲሁም አባቶች እና እናቶች በፅንፈኛ ''የሙስሊም ሃይማኖት ተከታዮች'' እንግልት ደርሶባቸዋል፣ተደብድበዋል እንዲሁም ለስደት ተዳርገዋል።ኢቲቪ እና መንግስት ይህንን ያውቃሉ እንድያውም አንዳንድ ቦታዎች ለዘመናት ከኖሩበት የቡና እርሻ ተገፍተዋል።ይህ ተግባር በእስልምና ተከታዮች  ላይ ብቻ ሳይሆን በክርስቲያኖች ላይም ደርሷል። ይህ ማለት ግን እነኚህ እኩይ ተግባር ላይ የተጠመዱ ፅንፈኛ አስተሳሰብ አራማጆች ሌላውን ኢትዮጵያዊ የእስልምና ተከታይ ወንድሞች እና እህቶችን አይወክልም። ከባህር ውስጥ አንዱ ወይም ሁለቱ አሳ ቢገማ በባህር ውስጥ ያሉትን አሳዎች በሙሉ አይወክልም።

የኢህአዲግ ''አጋር'' ተብዬ ድርጅቶች የፅንፈኞች መንፈላሰሻ!

እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን መንግስት ከላይ የጠቀስኩት አይነት የፅንፈኛ ሃሳቦች ሙስሊሙ ሕብረተሰብን እየረበሹ መሆኑን እያወቀ በወቅቱ ቢያንስ ከእድርም ሆነ ከማህበራዊ ኑሮ እንዲባረሩ እና እንዲገፉ የተደረጉትን ወደ ሚድያ ከማቅረብ ይልቅ ሲሸፋፍን ነበር የከረመው።ይልቁንም የእስልምና ተከታይ ወንድሞች እና እህቶች እነኚህን ፅንፈኛ አስተሳሰብ ያላቸውን እንዳይከላከሉ ትልቅ እንቅፋት የሆነባቸው እራሱ መንግስት ነበር። ምክንያቱም እነኚህ ፅንፈኛ ሃሳብ አራማጆች የተጠለሉት ''የኢህአዲግ አጋር '' በተሰኙ የጎሳ ድርጅቶች ስር ነበር። በመሆኑም በምስራቅ፣በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በእነኚሁ ፅንፈኛ አካላት ለደረሱ አደጋዎች (በሙስልሙም ሆነ በክርስቲያኑ ላይ) ተገቢውን ቅጣት መንግስት ሳይሰጥ አጥፊዎቹ እንዲቀጡ የሙስሊሙ ሕብረተሰብም ጭምር መንግስትን እየተማፀነ በጥፋቱ ላይ እጃቸው እንዳለ የታወቁት የኢህአዲግ አጋር ድርጅቶች አባላት ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረው እንዲሰሩ መደረጉ ብዙዎችን ያስቆጨ ጉዳይ እንደሆነ ይሄው አሁንም አለ።ዛሬም ሳላት ሊሰግድ መስግድ የሚገኘው ንፁሁ ሙስሊም ሳይሆን አክራሪነት የተፀናወተው በኢህአዲግ አጋር ድርጅት አባልነት ስር የተኮለኮሉ በርካታ አባላቱ ኢትዮጵያዊ ስሜቱ ያየለበትን ሙስሊም ሳይቀር ቁም ስቅሉን ማሳየታቸውን ተያይዘውታል።ስለሆነም የኢህአዲግ አጋር ተብዬ ድርጅቶች የፅንፈኛ መንፈላሰሻነታቸው እና ለወዳጃቸው ካሮት ለሚቃወማቸው ዱላ እየሰጡ  አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናትን ያልሆነ እርምጃ እንዲወስዱ ሲወተውቱ ይስተዋላሉ።ለምሳሌ በዛሬው የኢድ በዓል ላይ የመግቢያ ካርድ ይዘጋጅ ባዮቹ እኚሁ ''አጋር'' ተብዬዎች ውስጣቸው ፅንፈኛ ከላይ ግን ንፁሃን መስለው ለመቅረብ የሚጥሩቱ አይነተኛ ማሳያዎች ናቸው። 

ባጠቃላይ መንግስት ትልን ኢትዮጵያ በክርስትናም ሆነ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መተሳሰብ፣መፈቃቀር እና አንድነት የኖረች ስለሆነ መንግስት ለችግሮች የሚሰጠው መፍትሄ ከጠበበ አስተሳሰብ ወደ ሰፋ አስተሳሰብ መምጣት መቻል ነበረበት።በተለይ የመገናኛ ብዙሃኑ ፕሮፓጋንዳ አሰራር የዛሬዋን ትንሿን ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደታች ህዝቡ የሚኖርበት የአኗኗር ዘይቤ እንደ እድር በመሳሰሉት የማህበራዊ ተም ውስጥም ትልን ኢትዮጵያ ማየት የሚችል መሆን ይገባዋል።ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አለአግባባ እየተገፉ እድራችን ሰላም ሊሆን አይችልም።ፅንፈኛ የእምነት አራማጆችበኢህአዲግ አጋር ድርጅትነት ስር ተጠልለው መንግስትን እያማከሩ በጎ ምክር አይገኝም።ከእድራችን አባላት ንፁህ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የመለያ ልቦና ያድለን።

አበቃሁ 
ጌታቸው በቀለ 
ኦስሎ 

Wednesday, August 7, 2013

''ትምህርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያዊ እና ወጥ የሆነ ስርዓተ-ትምህርት በመላ ሀገሪቱ እየተሰጠ እንዳልሆነ እያወቀ ለምን እንዳላየ አለፈው?''



የትምህርት ሚኒስቴር ህንፃ አዲስ አበባ 

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  ከትምህርት ጋር በተያያዙ የሚነሱ ጉዳዮች በሁለት ጫፍ እና ጫፍ በያዙ አስተሳሰቦች የተሞሉ ናቸው። አንዱ በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ሽፋን እያደገ ነው የሚለው እና ቀድሞ ወደ ዩንቨርስቲ ይገባ የነበረው የተማሪ ቁጥርን ከአሁኑ ጋር እያነፃፀረ የማቅረብ እይታ ሲሆን ይህ አመለካከት ንግስት የመገናኛ ብዙሃን ጨምሮ የሚስተጋባ ነው። ሁለተኛው አስተሳሰብ ግን ሚዛን የሚደፋ ነው። እርሱም አዎን! የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቁጥር ጨምሯል።ነገር ግን በመረቁት ተማሪዎች ጥራት፣የስራ ብቃት እና የሉላዊው (ግሎባላይዜሽን) አለም ተወዳዳሪነት አንፃር ስናየው ገና ብዙ የሚቀሩ ስራዎች ለመኖራቸው የማይስማማ ወገን የለም።ይህ ጉዳይ በከፍተኛ ትምህርቶችም ሆነ በቀጣሪ ድርጅቶች ጥናት ብዙ የተባለት ስለሆነ ለጊዜው ስለጉዳዩ ከእዚህ የበለጠ ለማውሳት አልፈልግም። 


የዛሬው ''የትምህርታችን ነገር'' እንዳነሳው ያደረገኝ ግን የዛሬ ነሐሴ 1/2005 ዓም ምሽት  በሸገር (አዲስ አበባ) ኤፍ ኤም ራድዮ በተሰማው ዜና  ''ኢትዮጵያ ያለፈው አመትን የትምህርት ሂደት ገመገመች'' በሚለው ዜና ስር የ ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ ለትምህርት ሚኒስትር ዴታው ያነሳው ጥያቄ መሰረታዊ እና የመንግስትን የፖሊሲ ድክመት  የሚያመላክት  ብቻ ሳይሆን ለምን? የሚል ጥያቄን ጥያቄዎች ውስጥ-የሚጭር ሆኖ ስላገኘሁት ነው። 

በመጀመርያ ወቅቱ ክረምቱ ተገባዶ አዲሱ የትምህርት ዘመን የሚጀመርበት ወር- መስከረም እየመጣ ከመሆኑ አንፃር የሸገር ኤፍ ኤም ራድዮ ዛሬ ከዜና ዘገባዎቹ ውስጥ አንዱ መሆኑ ተገቢ እና ወቅታዊ ነው።
በእዚሁ መሰረት በዜና ዘገባው ላይ ትምህርትን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትር ዴታ የተጠየቁት ግን ለእኔ በአግባቡ አለመመለሳቸው ከተሰሙኝ ጥያቄዎች ውስጥ-

ሀ/ መንግስት (ትምህርት ሚኒስቴር) ኢትዮጵያዊ እና ወጥ የሆነ  ስርዓተ ትምህርት በመላ ሀገሪቱ እየተሰጠ እንዳልሆነ እያወቀ ለምን እንዳላየ አለፈው?  

ለ/ በአዲሱ የትምህርት ፖሊስ መሰረት አንዳንድ የትምህርት አይነቶች  ጭራሹን ተዘግተዋል። ለምሳሌ የፍልስፍና እና የታሪክ ትምህርቶች በዲፓርትመንት ከዩንቨርስቲ መሰጠት ቀርተዋል ለምን? የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ።

አንዲት ሀገር ወጥ የሆነ የትምህርት ፖሊሲ የላትም ማለት ምን ማለት ነው?

ከመጀመርያው ጥያቄ (ሀ) ስንነሳ ኢትዮጵያዊ እና ወጥ የሆነ ስርዓተ-ትምህርት በመላ ሀገሪቱ ያለመሰጠቱ ምክንያት እና መንግስት ለምን ይህንን ለማስተካከል እርምጃ አይወስድም? በሚል ሃሳብ ዙርያ ያጠነጥናል። አንዲት ሀገር ወጥ የሆነ የትምህርት ፖሊሲ የላትም ማለት ምን ማለት ነው? ለእኔ የምረዳው የሚከተሉትን ማለት መሆኑን ነው።እነርሱም-

  •  በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች የሚኖሩ ዜጎች የተለያየ የትምህርት አሰጣጥ አላቸው።ይህ ማለት ስለ አንድ ነገር አሰራር በተለያየ መንገድ እንዲመለከቱ የተለያየ አመለካከት ይዘው እንዲወጡ ይደረጋሉ ማለት ነው።እነኚህ ተማሪዎች ወደ ዩንቨርሲቲ ሲመጡ ከስር ወጥ የሆነ ትምህርት ስላልያዙ በነገሮች ላይ የጋራ እና ወጥ ሃሳብ ብሎም ውሳኔ ላይ መድረስ አያስችላቸውም። ለምሳሌ በፖለቲካ፣በታሪክ፣በሀገራችን የምጣኔ ሀብት መሰረታዊ ችግሮች እና መፍትሄዎች ላይ ወዘተ የጋራ የመነሻ ግንዛቤ ስለማይኖራቸው ከመጡበት ክልል ወይም ትምህርት ቤት አልያም መምህር አስተሳሰብ ተነስተው ለነገሮች ድምዳሜ ለመስጠት ይቸኩላሉ ማለት ነው። ይህም ውሎ አድሮ ወደተሳሳተ ግንዛቤ እና ድምዳሜ ላይ ያደርሳቸዋል።

እዚህ ላይ ወጥ የሆነ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ትምህርት በሀገራችን ያለመሰጠቱ መዘዙ በዩንቨርስቲ ብቻ የሚወሰን እንዳልሆነ መገንዘብ አለብን።
  • ከዩንቨርስቲ በኃላ ወደ ስራ አለም የተሰማሩ  ነገ የሀገራችን ፖሊሲ  አውጪዎች በአንድ ጉዳይ ላይ ለመወሰን ስብሰባ ተቀምጠው የማይስማሙ እና በነገሮች ላይ የጋራ ሃሳብ ማመንጨት ያቃታቸው  የካምፓኒ ሥራ አስክያጆች፣ሚኒስትሮች፣መምህራን ወዘተ ይኖሩናል ማለት ነው። ኢትዮጵያዊ እና ወጥ ያልሆነ ትምህርት አለመስጠት ውጤቱ በአጭር አማርኛ ለመግለፅ ሃገርን በጆግራፍያዊ አቀማመጥ እና በብሄር ከመከፋፈል በከፋ መልኩ ትውልድን እንዳይታረቅ አድርጎ የመግደያ 'መርዝ' ነው።
የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ የጠየቀው ጥያቄ እጅግ ወሳኝ እና አንገብጋቢ ነው።የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ከሚያነሷቸው እጅግ አንገብጋቢ ሃገራዊ ጉዳዮች ውስጥ የእዚህ አይነቶቹን የመንግስት  የትምህርት ፖሊስ ጥመቶችን (መንጋደዶችን) በወቅቱ ነቅሰው አውጥተው እንዲስተካከሉ ተፅኖ መፍጠር ይገባቸዋል።ምክንያቱም ችግሩ ጊዜ ከተሰጠው እና ትውልድን ካጣመመ  በኃላ ለመመለስ ሌላ አንድ መቶ አመት ላለመጠየቁ ምንም ዋስትና የለም። 

ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት (የቀድሞ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር) የተናገሩትን እዚህ ላይ መጥቀስ ተገቢ ነው።''ዛፍ ተጣሞ ቢያድግ ሌላ ዛፍ በመትከል  በጥቂት አመታት ታስተካክለው ይሆናል። በተሳሳተ የትምህርት ፖሊስ ምክንያት ትውልድ ተጣሞ ካደገ ግን በምን እና በስንት አመት ታስተካክለዋለህ?'' ነበር ያሉት።

የታሪክ እና የፍልስፍና የትምህርት ክፍሎች(ዲፓርትመንቶች) መዘጋት ጉዳይ 

ሁለተኛውን የጋዜጠኛውን ጥያቄ ማለትም ''ለምን የታሪክ እና የፍልስፍና ትምህርት ክፍሎች ከዩንቨርስቲ ተዘጉ?'' ለሚለው ጥያቄ እንደተባለው  የትምህርት ክፍሎቹ ከዩንቨርስቲ ውስጥ ከተባረሩ ጉዳዩን በአሳዛኝነት በማለፍ ብቻ ሳይሆን ተያያዥ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ለመሆኑ እማኝ እንደማይፈልግ እርግጠኛ ነኝ። ጥያቄዎቹም - 
  • ፍልስፍና የሌለው ኅብረተሰ እንዴት ማደግ ይችላል? 
  • ኢትዮጵያዊ ፍልስፍናዎቻችንን ትውልዱ እንዳይማር እና እንዳይመራመር ማድረግ ብሎም ከዩንቨርስቲ የትምህርት ክፍልነት መሰረዝ እና ተማሪዎች እንዳይማሩ ማድረግ ምን አይነት ሃገራዊ  የትምህርት ፖሊሲ ነው? 
  • ፍልስፍና የሌለው ፖለቲካ፣ፍልስፍና የሌለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ፍልስፍና የሌለው የማህበረሰብ ፖሊሲ ይዘን እስከመቼ እንኖራለን? በምን ያህል እርቀት ሀገራችንን ያስጉዛል? 

የታሪክን ትምህርት ክፍል መዘጋትን በተመለከተ ግን ጥያቄዬ አንድ እና አንድ ነው። ባለታሪክ ሀገር ኢትዮጵያ የታሪክ ተመራማሪ እና ተማሪ ከሌላት የትኛዋ ሀገር ናት ሊኖራት የሚገባትና የሚታሰብላት?

አበቃሁ 
ጌታቸው 
ኦስሎ  

Saturday, August 3, 2013

''የኢትዮጵያ ቀን'' በ ኦስሎ፣ኖርዌይ የመከበሩ ጥቅም እና ዝግጅቱን የበለጠ ለማሳመር መከናወን የሚገባቸው ተግባራት (አጭር ማስታወሻ)

በኖርዌይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ) ''የኢትዮጵያ ቀን'' የተሰኘ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች እና የቡና ማፍላት ስነ-ርአት ያካተተ መርሃ ግብር ዛሬ ሐምሌ 27፣2005 ዓም በኦስሎ ከተማ ''ግሩን ላንድ'' መናፈሻ አካሂዶ ነበር።በቅድምያ ዝግጅቱን ለማዘጋጀት ለተነሳሱት እና ለዝግጅቱ ደፋ ቀና ያሉትን ሁሉ ማመስገን ተገቢ ይመስለኛል።በመሆኑም በጎ ተግባራትን ማበርታት እና ማጎልበት ከሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ኃላፊነት መስሎ ስለተሰማኝ ይህችን አጭር ማስታወሻ ለመፃፍ ወደድኩ። 


ሀ/  የመርሃብሩ ጥቅም 

 የእዚህ አይነቱ መርሃግብር  ለእኛ ለኢትዮጵያያን  የሚሰጠው ጥቅም እጅግ ከፍ ያለ ነው። ከጠቀሜታዎቹ ውስጥ ጥቂቶቹ -
1/ የኢትዮጵያውያንን ተሰሚነት በሚኖሩበት ሀገር ውስጥ በሚደረጉት ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ክንውኖች ውስጥ የጎላ ሚና እንዲኖረው ያደርጋል። ይሄውም በምንኖርበት ሀገር ማኅበረሰብ ውስጥ ውሎ አድሮ የተሰሚነት እና የተፅኖ ፈጣሪነት ሚናችንን ከፍ ማድረጉ አይቀርም፣

2/ የኢትዮጵያን ባህል ማለትም አመጋገብ፣አለባበስ፣ወዘተ  በውጭው ማኅበረሰብ ዘንድ ያስተዋውቃል። ይህም የሀገራችንን ሌላውን በጎ ጎን ማለትም በባህላችን፣በታሪካችን እና በማንነታችን ዙርያ የሀገራችንን በጎ ገፅታ ለምንኖርበት ሀገር ለማሳየት ይረዳል። 

3/ በውጭ ለተወለዱ ኢትዮጵያውያን ስለሀገራቸው የበለጠ እንዲያውቁ እና ፍቅር እንዲያድርባቸው ያደርጋል።

 ለ/ በመጪው አመት ዝግጅቱን ይበልጥ ለማሳመር ምን ቢደረግ ጥሩ ነው?


''የኢትዮጵያ ቀን'' ዝግጅት ይበል የሚያሰኝ እና ለወደፊቱም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአግባቡ ሊሳተፉበት እና የእኔነት ስሜትን ልያጎለብቱበት የሚገባ መሆን ይኖርበታል።ለእዚህም እንዲረዳ በመጪው አመት እነኚህ ተግባራት ቢከወኑ ዝግጅቱን የበለጠ ያስውበዋል እነርሱም-
1/ ''የኢትዮጵያ ቀን'' መርሃግብር የማስታወቅያ ሥራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሰራ ማበረታታ፣

2/ ከኦስሎ ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ቀኑን አስበው ቀድመው ኦስሎ እንዲመጡ ማድረግ እና የማረፍያ ቦታዎችን የኦስሎ ነዋሪዎች እንዲያግዙ ማነሳሳት፣

3/ በመላዋ ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የንግድ ድርጅቶች የሚተዋወቁበት እና ስፖንሰር የሚያደርጉበት ሁኔታ ማመቻቸት፣

4/ በወጣቶች የሚዘጋጁ የተውኔት (ድራማ) መርሃግብሮችን በበዓሉ ወቅት ማቅረብ፣

5/ በዓመቱ ውስጥ በኖርዌይ ውስጥ ልዩ ልዩ ተግባራት የሰሩ ለምሳሌ በትምህርታቸው ላቅ ያለ ውጤት ያመጡ፣የኖርዌይ መገናኛ ብዙሃንን የሳበ ተግባር የሰሩ ወይንም ሀገራቸውን በተለያዩ በጎ ጎኖች ያስጠሩ ኢትዮጵያውያንን በኮሚቴ አስጠንቶ እና አወዳድሮ ለሽልማት ማብቃት እና 

6/ ለኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ በጎ ያደረጉ ኖርወጅያናውያን የሚሸለሙበት መርሃግብር እና የመሳሰሉት ቢካተቱ ዝግጅቱን የደመቀ እንደሚያደርገው እሙን ነው።

በመጨረሻም  በኖርዌይ፣ኦስሎ የተደረገው የኢትዮጵያ ቀን ዝግጅት ጥሩ ተግባር በመሆኑ አዘጋጁ ኮሚቴ ለመጪው አመትም በበለጠ አቀራረብ እንደሚያዘጋጅ ተስፋ በማድረግ የእዚህ አይነት ዝግጅቶች  ሃይማኖት፣ትውልድ፣ወዘተ የማይለዩ ስለሆኑ ኢትዮጵያውያንን በአንድ ህብረት የማስተሳሰር እና የማስተሳሰብ ኃይላቸው ከፍተኛ ነው።በመሆኑም  ሁሉም በያገባኛል ስሜት ይሆናል የሚለውን ሃሳብ በመስጠት ያጎለብተው ጠቀሜታው ለእራሳችን፣ለልጆቻችን ከፍ ሲል ደግሞ  ለጋራ ቤታችን-ኢትዮጵያችን መሆኑ እሙን ነው።

የኢትዮጵያ ቀን አከባበር በኦስሎ ግሩንላንድ መናፈሻ ፎቶዎች ይመልከቱ። ፎቶ(ጌታቸው)












ጌታቸው በቀለ 
ኦስሎ 

Wednesday, July 31, 2013

''እያበበ'' ነው የተባለው ዲሞክራሲ ለእዚች ትንሽ ጥያቄ ካልሰራ የት ይሆን የሚሰራው?




አቶ መለስ ካረፉ አንደኛ አመታቸው አልፏል።አንዳንዶች ቀለል አድርገው ለማየት ይሞክራሉ።ጉዳዩ ግን የዲሞክራሲ መታፈንን ደረጃ የሚያሳይ ነው። ለእኔ ግን የብዙ ነገር አመላካች ነው።ከአንድ አመት በኃላም እንዳስገረመኝ አለ። አቶ መለስ-
 እንዴት እንደሞቱ?

በምን ህመም እንደሞቱ?

የህመሙ ምክንያት ምን እንደነበር?
የት ሆስፒታል እንደሞቱ?

የት ሀገር እንደሞቱ?

እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የሀገራችን ቴሌቭዥንም ሆነ መንግስት አልነገረንም።

 በድፍኑ ''በውጭ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው'' ከመባል ውጭ። ይህንን የመጠየቅ መብት እንዳላቸው በቅጡ የተገነዘቡ ቁጥራቸው ስንት ደርሶ ይሆን? 
አንድ የውጭ ዜጋ  ''መሪያችሁ በምን ህመም እንደታመመ፣የት እንደታከመ ሌላው ቀርቶ አስከሬን ከየት ሀገር እንደገባ ያልተነገራችሁ...ምስኪን ጭቁን ህዝቦች፣የህወሓት አባላት፣የኦህዴድ አባላት፣የብአዴን አባላት ሆይ!  እስኪ መልሱልኝ? '' ብሎ  ቢጠይቅ መልስ ያለው አለ? ይህ የሚያመላክተን አንድ እና አንድ ነገር ብቻ ነው። ይሄውም  የነፃነታችንን እና የመብታችንን ባዶነትን ነው የሚያሳየው። ''እያበበ'' ነው የተባለው ዲሞክራሲ ለእዚች ትንሽ ጥያቄ ካልሰራ የት ይሆን የሚሰራው?

ጌታቸው
ኦስሎ  

Monday, July 22, 2013

ከአምባሳደር፣ጋዜጠኛ እና ደራሲ ዘውዴ ረታ ጋር ቃለመጠይቅ (ቪድዮ)

ዛሬ ሐምሌ 15፣2005 ዓም የሲ ኤን ኤን እና ቢቢሲ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ትልቅ ዜናቸው ሆኖ የዋለው የእንግሊዝ ልዑላውያን ቤተሰብ  ልጅ መውለዳቸው ነበር።በማግስቱ ሐምሌ 16 ቀን ደግሞ የቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ የልደት በዓል በተለይ በጀማይካውያን ዘንድ ኢትዮጵያ እና ጀማይካ ውስጥ ይከበራል።
አምባሳደር፣ጋዜጠኛ እና ደራሲ ዘውዴ ረታ ''የኤርትራ ጉዳይ'' የተሰኘውን ትልቅ ጥራዝ መፅሐፍ ጨምሮ ሌሎችንም መፃህፍት በመፃፍ ይታወቃሉ። የኢሳት ጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ትህትና በተላበሰ ጥያቄው አምባሳደርን አናግሯል።
አምባሳደር፣ጋዜጠኛ እና ደራሲ ዘውዴ ረታ ባለፉት ኩነቶች ላይ ሲፅፉ ምርመራዊ (investigation) መንገድን መከተላቸው የፅሁፎቻቸው ልዩ መታወቅያዎች ናቸው።
በሁለት ክፍል የተከፈሉትን ቃለ መጠይቆችን ቪድዮ ይመልከቱ።

ክፍል 1
ምንጭ - ኢሳት ቴሌቭዥን



ክፍል 2
ምንጭ - ኢሳት ቴሌቭዥን







Tuesday, July 9, 2013

አምባሳደር ብርሃኑ ዲንቃ አረፉ

አምባሳደር ብርሃኑ ዲንቃ 


  • በዲፕሎማሲው አለም ከእሩብ ክፍለዘመን በላይ አገልግለዋል።  
  • በካይሮ፣በዋሽግተን፣ነውዮርክ፣ጅቡቲ የሀገራቸው አምባሳደር ሆነው ሰርተዋል፣
  • በካምቦድያ፣ደቡብ አፍሪካ፣ሱማልያ በተባበሩት መንግሥታት ወኪልነት ሰርተዋል፣
  • በደቡብ ሱዳን የዳርፉር ግጭት በአፍሪካ አንድነት ድርጅት  ስር የነበረውን ''የስልጣን መጋራት ኮሚሽንን'' እስከ ስምምነቱ ፊርማ ድረስ በሊቀመንበርነት መርተዋል፣
  • የ ቀድሞው የተ.መ.ድ. ዋና ፀሐፊ ልዩ አማካሪም ሆነው ሰርተዋል፣
  • አሁን በቅርቡ ሕይወታቸው እስካለፈበት ድረስ በኬንያ በቀድሞው የምርጫ ወቅት ተነስቶ በነበረው ግጭት ''የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽን'' ውስጥ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኪባኪ ተሾመው  በአለምአቀፍ ኤክስፐርትነት እና የኮሚሽኑ የሪፖርት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆነው እያገለገሉ ነበር።

አምባሳደር ብርሃኑ ዲንቃ በኒውዮርክ በነበረባቸው የካንሰር ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሰኞ ሰኔ 1፣2005 ዓም ሕይወታቸው ማለፉን የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል።እረፍተ ነፍስ ይስጥልን።
source- Daily Nation,July 9,2013
            - The standard Digital news, July 8,2013

Monday, July 8, 2013

የግብፅ ኦርቶዶክስ (ኮፕቲክ) ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ፕሬዝዳንት ሞርሲን ከስልጣን ለማውረድ በተቃዋሚዎች በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ አንፃር እንዲህ ብሎ ነበር

የግብፅ ኦርቶዶክስ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ ፕሬዝዳንት ሞርሲን ከስልጣን ለማውረድ በተቃዋሚዎች  በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ አንፃር እንዲህ ብሎ ነበር-
''በሰኔ 30/2013 ዓም ፕሬዝዳንት ሞርሲን ለማውረድ በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ምዕመናን  የመሳተፍም ሆነ ያለመሳተፍ መብታቸው የተጠበቀ ነው።'' 
አንድመቶ ሃያ ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት የያዘው የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል ይህንን መግለፁን ያሳወቀው  ''አህራም ኦንላይን'' የተሰኘው የድህረ- ገፅ ጋዜጣ ነበር።
ሙሉ የ ''አህራም ኦንላይን'' የተሰኘው የድህረ- ገፅ ጋዜጣ የእንግሊዝኛ ንባብ ''ጉዳያችን ጡመራ'' ላይ ያንብቡ።



Copts free to join 30 June anti-govt protests: Egypt's Coptic Church
Coptic Church's Holy Synod says Coptic Christians are free to join planned 30 June protests against President Morsi and Egypt's Muslim Brotherhood
Ahram Online , Friday 21 Jun 2013
Egyptian Copts are free to decide for themselves whether or not to take part in planned 30 June anti-government rallies, the Holy Synod of Egypt's Coptic Orthodox Church has stated.
Synod members issued the statement at a Thursday meeting, where they also announced that a new church spokesman would soon be appointed by Coptic Orthodox Pope Tawadros II.
The Holy Synod, which is comprised of 120 archbishops, represents the church's most authoritative decision-making body.
Opposition parties and groups have issued calls for mass protests on 30 June, which will mark the end of President Mohamed Morsi's first year in office, to demand Morsi's ouster and snap presidential elections.
The protest calls were initially made by the anti-Morsi 'Rebel' campaign, which on Thursday announced that it had met its target of 15 million citizens' signatures in support of its demands.
In April, Pope Tawdros criticised President Morsi for failing to protect Cairo's main Coptic Orthodox cathedral during sectarian clashes that left two dead and dozens injured.
Later the same month, the pope told Reuters that Egypt's Coptic Christians were facing increased marginalisation.
Egypt's Christian community, accounting for an estimated 10 percent of the national population of 84 million, have long complained of discrimination in the Muslim-majority countr
y

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የሰሞኑ ከራሞት ልዩ ሪፖርታዥ

የ2018 ዓም የጥምቀት በዓል አከባባር በአቴንስ ኪዳነምሕረት  በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ፡  በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱን እና ምእመናንን  የሚያምሷት እነማን ናቸው? እራሱን ''የሲ...