Wednesday, April 24, 2013

''ህዝብ ለሕዝብ የኪነት ልዑክ'' በደርግ ዘመን ''የአባይ ግድብ ቦንድ ግዥ'' በዘመነ ኢህአዲግ -የሀገሬ አዙሪት(አጭር ማስታወሻ ለሀገሬ ልጅ)

በዘመነ ደርግ በ ፍ 1977 ዓም ኢትዮጵያ ገጥሟት የነበረው የድርቅ አደጋ መላው አለም ከጎኗ በመቆሙ  ኢትዮጵያ የኪነት ቡድኗን በመላው አለም እያዟዟረች ባህላዊ እና ዘመናዊ ሙዚቃዎቿን በማሳየት የምስጋና ቃሏን አሰማች።የኪነት ቡድኑም ሕዝብ ለሕዝብ የኪነጥበብ ልዑክ ተሰኘ።በእዚህ ሃሳቡን ከማመንጨት ጀምሮ ቡድኑን በመምራት በመላው አለም ይዘው የተዟዟሩት አምባሳደር ዶክተር ካሳ ከበደ የቀድሞው መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ነበሩ።

በልዑካን ቡድኑ ውስጥ አንጋፋ የኪነት ሰዎች  ጥላሁን ገሠሠ፣ብዙነሽ በቀለ፣መሐሙድ አህመድ እና ሌሎችም 
የተሳተፉ ሲሆን የዛሬው ተወዳጁ አክቲቪስት ታማኝ በየነም ተካቶበት ነበር።ቡድኑ በአሜሪካ፣አውሮፓ፣መካከለኛው ምስራቅ  ተገኝቶ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከማሳየቱም በላይ በብዙ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የኢትዮጵያን ሌላውን ገፅታ በማሳየት አድናቆትን አትርፏል።ታድያ በወቅቱ ቡድኑ በሄደበት ቦታ ሁሉ እግር በእግር እየተከታተሉ ቡድኑን ይቃወሙ የነበሩ አንዳንድ ቦታ ለዱላ የትጋበዙ ከእዛ ባስ ሲል ደግሞ ግርግር በመፍጠር ዝግጅቱን ለማስቆም የሞከሩ የሻብያ፣የኢህአዲግ፣እና ሌሎች የደርግ ተቃዋሚዎች በእየዝግጅቱ አዳራሽ መግቢያ ላይ ነበሩ።አንዳንዶቹ ቦታዎች እንዲያውም ከያንያኑን አግቶ ለመውሰድ ሴራ ተጠንስሶ ነበር።አዎን በትክክል ለሚያስብ ሰው የሀገርን ገፅታ መቀየር መቃወም  አሳዛኝ ነው። የወቅቱ እሳቤ ግን ''ደርግ ሀገር ሰላም ነው ለማለት ነው----በመጀመርያ ሰብአዊ መብት ይከበር'' የሚል  ነበር።

መሃሙድ አህመድ (ሕዝብ ለሕዝብ ልዑክ አባል)
በዘመናችን ደግሞ ሌላ ሕዝብ ለሕዝብ ቡድን የአባይ ቦንድ ግዥ ሆኖ መጥቷል።አባይን መገደብ ሀገር ያለማል፣ወገን ያኮራል።የያነዎቹ የህዝብ ለሕዝብ ተቃዋሚዎች ሀገርቤት ገቡ እና የአባይ ግድብ ቦንድ ግዥ ይዘው እንደ ሕዝብ ለሕዝብ የኪነት ልዑክ በውጭ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ   ''የሀገር ገፅታ ይቀይራል ወገን ያኮራል ቦንድ ግዙ'' ብለው ጠየቁ።''ከአባይ ግድብ በፊት በመጀመርያ ሰብአዊ መብት ይከበር''ሆነ ጥያቄው።
የወጣው ቢገባም የገባው ቢወጣም ሀገሬ ከማይለቅ አዙሪት አልወጣችም።እውነትነት የሌላቸው ህዝብን ቀርቶ ቤተሰባቸውን በአግባቡ ማሳመን በማይችሉ ቃላት የሚሸነግሉ መሪዎች ተሸክማ ሀገሬ አሁንም አለችበት ቆማለች።
እንደዜጋ ማሰብ ''እሰይ አሳፈርኩት፣ኩም አድርጌ መለስኩ'' ሳይሆን ሃገሬ ከእዚህ አዙሪት የምትወጣው፣በዘረኝነት ላይ ከተመሰረተ አስተሳሰብ የምትላቀቀው ፣አባይንም በሕዝብ ፍቅር ላይ የምትመሰርተው፣''ሕዝብ ለሕዝብ የኪነጥበብ ልዑክ'' ካለአንዳች እረብሻ ለመላው አለም የምታሳየው  መቼ ነው? የሚለው ጥያቄ ነው ጥያቄው።ለእዚህስ የእኔ ድርሻ ምንድንነው? ነው ቀጣዩ ጥያቄ።

ጌታቸው በቀለ 
ኦስሎ 

Monday, April 22, 2013

ትኩረት- ኢትዮጵያ ''አይከን'' የሆኑ ሃገር በቀል መዋለ ንዋይ አፍሳሽ ባለ ሃብቶችዋን በተለያየ ምክንያት ማጣቷን ቀጥላለች።

 ቀደም ብለው እንደ አማልጋሜትድ ኩባንያ፣በያዝነው አመት ብቻ ደግሞ 
-የ አዋሽ ባንክ ስራ አስኪያጅ ሰው ገጭተዋል አልገጨሁም ንትርክ ፣

-የ ሆላንድ ካር ኩባንያ ተጨማሪ ብድር ድጋፍ በመፈለግ ብቻ ለኪሳራ ተዳርጎ ኩባንያው ከስራ ውጭ መሆኑን፣

-  የ አክሰስ ባንክ መስራች እና ኢንቨስተር አቶ አመልጋ ተመሳሳይ መሰል ችግር ገጥሟቸው ነገር ግን ተመልሰው የገጠማቸውን ችግር እንደሚቋቋሙ መግለጻቸው፣
- ሚያዝያ 9 ቀን 2005 ዓ.ም. የ አያት አክስዮን ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አያሌው እና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ከቀረጥ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ቀርበው አቃቢ ህግ የሰባ አመቱን አዛውንት'' ከ ሰባ አመት በላይ እስር ይፈረድልኝ፣ያላቸው መኪናዎች ሁሉ ይወረሱ'' የሚል ጥያቄ አቅርቧል። በነገራችን ላይ አቶ አያሌው ለ አባይ ግድብ የ አንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ብር ቦንድ መግዛታቸው ከግንዛቤ ውስጥ መግባት እንደነበረበት ለፍርድ ቤቱ አሳስበዋል።ፍርድ ቤቱ ግን አልሰማም ፍርዱ ለ ሚያዝያ 29 ተቀጥሯል።
ከሪፖርተር ዕሁድ ሚያዝያ 13/2005 ዓም  ስለ ፍርድቤት ውሎው የተነበበው ዘገባ ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኘበታል።
''አቶ አያሌው ዕድሜያቸው 70 ዓመት መሆኑን፣ ከ15 ዓመታት በላይ በተለያዩ ሕመሞች ማለትም የልብ ቀዶ ሕክምና እንደተደረገላቸው፣ የደም ግፊት፣ የጀርባ ሰረሰር ጉብጠትና የነርቭ ሕመምተኛ መሆናቸውንና ሌሎችንም በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲመለከትላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፀባያቸው መልካም መሆኑን የሚኖሩበት ክፍለ ከተማ ወረዳ ጽሕፈት ቤት በደብዳቤ ማረጋገጡን፣ የ15 ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን፣ ባለቤታቸው የልብና የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን፣ እህታቸው የዓይን ግርዶሽ ታማሚ መሆናቸውንና እርሳቸው እየረዷቸው እንደሚኖሩም አስረድተዋል፡፡

በትምህርት ዘርፍ ከ1974 ዓ.ም. ጀምሮ በግል ተልዕኮ (ርቀት) ትምህርት በመሰማራት ለበርካታ ወገኖች የላቀ ጠቀሜታ ማስገኘታቸውን፣ በሪል ስቴት ልማት ፋና ወጊ መሆናቸውንና የቤት እጥረትን ለማስወገድ የላቀ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን በመዘርዘር፣ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከትላቸው በቅጣት ማቅለያ ሐሳባቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ አያት አክሲዮን ማኅበር 2,468 ቋሚ ሠራተኞችና ጥቃቅን ድርጅቶች በሥሩ እንዳሉ፣ ማኅበሩ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ከ310 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት ገቢ ማድረጉን፣ ለዚህም አስተዋጽኦ እሳቸው ሥራ አስኪያጅ ሆነው በሚሠሩበት ጊዜ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ይኼንንም በማቅለያነት እንዲመለከትላቸው ጠይቀዋል፡፡ 

የውጭ አገር ቤት ገዥዎችን በማፈላለግ በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ሰዎች በውጭ ምንዛሪ እንዲገዙ በማድረግ በድምሩ ከ145 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ እንዲገባ ማድረጋቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ትምህርት ቤቶችን በመሥራት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን፣ የጤና ጣቢያዎችን ከሐኪሞች መኖሪያ ጋር ሠርተው ማስረከባቸውን፣ የገበሬ ማሠልጠኛ ገንብተው ማስረከባቸውን፣ የአትሌቲክስ ስፖርትን ለማጠናከር አሠልጣኝ መቅጠራቸውን በዝርዝር በመግለጽ ባደረጉት አስተዋጽኦ መሠረት ፍርድ ቤቱ በማቅለያነት እንዲወስድላቸው አመልክተዋል፡፡ 

በአዲስ አበባ የወጣቶች ማዕከል መገንባታቸውን፣ በትግራይ ‹‹ከዳስ ወደ ክላስ›› በተሰኘ መፈክር በመማር ማስተማሩ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን፣ በ1998 ዓ.ም. በድሬዳዋ ለደረሰው የጐርፍ አደጋ አንድ ባለአንድ ፎቅ ሕንፃ ገንብተው ማስረከባቸውን፣ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከበር ከፍተኛ ወጪና ቁሳቁስ በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን፣ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርጅቱ የ340 ሺሕ ብር ስጦታና የ980 ሺሕ ብር ቦንድ ግዢ፣ አቶ አያሌው የ100 ሺሕ ብር ስጦታና የ200 ሺሕ ብር የቦንድ ግዢ መፈጸማቸውንና ለአገራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ማስረጃ በማያያዝ ለፍርድ ቤቱ አቅርበው፣ በማቅለያነት እንዲወስድላቸው ጠይቀዋል፡፡ እንዲሁም ለኢሕአዴግ በተለያዩ ጊዜያት ለተከናወኑ ፕሮግራሞች አቶ አያሌው አንድ ሚሊዮን ብር መስጠታቸውንና በማረሚያ ቤት ቆይታቸውም ባላቸው መልካም ፀባይ የተለያዩ የምሥጋና ደብዳቤዎች እንደደረሳቸው በማስረዳት፣ ፍርድ ቤቱ ሁሉንም የቅጣት ማቅለያ ጥያቄዎችንና ማስረጃዎቻቸውን በመመልከት ዝቅተኛ ቅጣት እንዲወስንላቸው ጠይቀዋል፡፡ ''
ኢትዮጵያ ''አይከን'' የሆኑ ሃገር በቀል መዋለ ንዋይ አፍሳሽ ባለ ሃብቶችዋን በተለያየ ምክንያት ማጣቷን ቀጥላለች። 

Saturday, April 20, 2013

ኢህአዲግ የአባይን ግድብ የቦንድ ሽያጭ በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መተንኮሻ አድርጎታል።

ዛሬ እነሆ በኖርዌይ እንዲህ ሆነ

ከኖርዌይ ከተሞች ውስጥ በደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ስታቫንገር ከተማ ዛሬ ሚያዝያ 12/2005 ዓም በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ መብራት በተገኙበት ለአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ የተዘጋጀው ዝግጅት ከኦስሎ ከ ስምንት ሰዓታት በላይ በአውቶቡስ ተጉዘው በስብሰባው በተገኙ ኢትዮጵያውያን በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱ ተሰርዞ አምባሳደሯ በፖሊስ ቦታውን ለቀው  እንዲሄዱ ተመክረው አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።

በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ በሥርዓት ተቀምጠው የተገኙት ኢትዮጵያውያን መርሃግብሩ ከመጀመሩ በፊት ''በዘመነ ኢህአዲግ የተገድሉትን ኢትዮጵያውያን በቅድሚያ በህሊና ፀሎት እናስብ ይህንንም ለማድረግ ሁላችንም ከተቀመጥንበት እንነሳ'' በማለት አምባሳደሯም እንዲነሱ እና አብረው በፀሎት እንዲያስቡ ይጠይቃሉ።አምባሳደሯም ሆኑ አብረዋቸው የመጡት ፈቃደኛ አልሆኑም። በመቀጠል ኢትዮጵያውያኑ እንግዲያው ስለ አባይግድብ አሁን ልንነጋገር አንችልም በማለት ያስታውቃሉ።በእዚህ መሃል ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፅ መሰማት ይጀምራል። 
''ከአባይ በፊት የ ሰብአዊ መብት ጥሰት ይገደብ!''
''የሙስሊሙ ድምፅ ይሰማ!''
''የኢትዮጵያውያን ድምፅ ይሰማ!''
''የዘር መድሎ ይቁም!'' (stop apartheid in Ethiopia!'' ወዘተ የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ላይ ሳሉ የኖርዌይ ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋጋት ሁሉም እንዲቀመጡ ይነገራቸዋል። በእዚህን ጊዜ ግን ኢትዮጵያውያኑ የኮኮብ ምልክት ያለበትን ከአምባሳደሯ ጀርባ ባለው ግድግዳ ላይ የተለጠፈውን ባንዲራ የኢህአዲግ አርማ ኮኮብ በሌለበት በ ኢትዮጵያ ባንዲራ ሸፍነው ጨርሰው ነበር።
ፖሊሱ ኢትዮጵያውያንን ካስቀመጠ በኃላ ቀጥሎም ሁኔታው ደህና መሆኑን ለማስረዳት ይሞክራል።በእዚህ መሃል ኢትዮጵያውያኑ ይብሱን  ቁጣቸውን በዜማ ይቀጥላሉ።

''ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም 
 እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም የደፈረሽ ይውደም''

ይህን የተመለከቱት ፖሊሶች ኢትዮጵያውያኑን ከማስወጣት አምባሳደሯን ማስወጣት ትክክለኛ እርምጃ እንደሆነ ስለተረዱ አንዱ ፖሊስ ወደ አምባሳደሯ ቀርቦ አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ በቃልም በእጁም መውጣት እንዴት እንደሆነ እያሳየ ይነገራቸውል። አምባሳደር መብራት ቦርሳቸውን አንስተው ወደ አዳራሹ ዘወር እያሉ እየተመለከቱ ወደ በሩ አዘገሙ። ኢትዮጵያውያኑ ቀጠሉ።

''ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም 
 እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም የደፈረሽ ይውደም'''
''ሌባ ሌባ አለ ገና አለ ገና!'' አምባሳደሯ ፈጠን ባለ እርምጃ በፖሊስ ታጅበው ወደ መኪናቸው ሄዱ።








ኢህአዲግ የአባይን ግድብ የቦንድ ሽያጭ በባህር ማዶ የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያንን መተንኮሻ አድርጎታል።

ማንም ኢትዮጵያዊ አባይ ቢገደብ ኢትዮጵያ ከድህነት ብትወጣ አይጠላም።ዛሬም  ተቃውሟቸውን የገለፁት ኢትይጵያውያን ለኢትዮጵያ ሞት የሚመኙ ሆነው አይድለም።ኢህአዲግ ግን በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ያሳጣ እየመሰለው ብዙ ተቃዋሚ አለ ብሎ የሚያስበበት ቦታ ሁሉ የ አባይ ግድብ ቦንድን ካርድ እየመዘዘ የልዩነት መስመር በኢትዮጵያውያን መሃከል ይፈጠራል ብሎ ያስባል። ለእዚህም አይነተኛ ማስረጃው የመጀመርያው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ዝግጅት በዋሽግተን ዲሲ  ሲዘጋጅ ብዙ ኢትዮጵያውያን ካርድ ወስደው አክትቪስት ታማኝ በየነን ጨምሮ ወደ ስብሰባው ቦታ ሲሄዱ ''የእንጀራ ልጅ እና የቤት ልጅ'' በሚል መለያ አድርጎት ''አንተ አትገባም አንተ ግባ'' እያለ መለየት ጀመረ። 
''በሀገራችን ጉዳይ ያለንን ሃሳብ መስጠት እንፈልጋለን ካርድ ይዘናል'' ያሉ ታማኝንም ጨምሮ  እንዳይገቡ ተከለከሉ። 

በወቅቱ የሚገቡት ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት ሃሳብ ቢኖራቸው ሃሳባቸውን መስማት እና ምላሽ መስጠት ያን ቀን መግባባት ባይቻል ለቀጣይ ሌላ ስብሰባ አድርጎ መመካከር የጤነኛ መንግስት ልዑክ አሰራር ነበር።ኢህአዲግ ግን ከመጀመርያው የአባይ ግድብን ሲያነሳ በባህርማዶ ያለው ሕዝብ ሲቃወም በሀገር በት ያለው መደገፉ ስለማይቀር ይለያያል። በውጭ ያለውም ብሔራዊ ስሜቱ አይሎ እርስ በርሱ ይከራከራርል የሚል ታሳቢ ያደርገ አቀራረብ ስለነበረው በዋሽግተኑ ስብስባ ላይ እራሱ ኤምባሲው በድብዳቤ የጠራቸውን ሁሉ ተምታተውበት አላስገባም አለ።ኢትዮጵያውያን በገዛ የሀገራቸው ጉዳይ ባይተዋር ሆኑ።


በእንደዚህ አይነት የተጀመረው የ አባይ ጉዳይ ይሄው ኢህአዲግ እስካሁን ድረስ እንደማስይሳካ እያወቀ በባህር ማዶ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች እና የሀገራቸው ጉዳይ የእግር እሳት የሆነባቸውን ኢትዮጵያውይንን መተንኮሻ አድርጎ ይጠቀምበታል።በነገራችን ላይ ይሄው ተመሳሳይ መርሃግብር በኦስሎ ለ አፕሪል 23/2013 መርሃግብር መያዙን ከአምባሲው ድህረገፅ ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ ያስነብባል። ሃገራዊ ህብረት ሳይፈጠር፣ዜጎች ከአንድ ክልል ወደ አንድክልል ካልፈቃድ ለምን ገባችሁ ተብለው እየታሰሩ(የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በ ቤንሻንጉል ክልል ለመታሰር ያበቃቸው)፣ በሺዎች መሬት እና ንብረታቸውን ተነጥቀው ሲንከራተቱ አንዳች ያልተናገረው መንግስት ይህም ከፍተኛ ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በፈጠረበት በእዚህ ጊዜ ስለ አባይ ግድብ ቦንድ ግዙ ብሎ መጠየቅን ምን ስም እንስጠው?

ጉዳያችን Gudayachn