ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, October 19, 2023

ኢትዮጵያ ባነሳችው የባሕር በር ጉዳይ ላይ አንድም የአውሮፓ፣የሰሜን አሜሪካ፣ደቡብ አሜሪካ፣እስያና አውስትራልያ ሀገር ትክክል አይደለም ያለ መንግስት የለም።

  • የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የተባበሩት መንግስታት በጉዳዩ ላይ ምንም አለማለት፣ሁለቱም በኢትዮጵያ የወደብ ባለቤትነት ጉዳይ ላይ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ እንደሌላቸው በትክክል ያሳያል።
============
ጉዳያችን
============


ኢትዮጵያ ባነሳችው የባሕር በር ጉዳይ ላይ አንድም የአውሮፓ፣የሰሜን አሜሪካ፣ደቡብ አሜሪካ፣እስያና አውስትራልያ ሀገር ትክክል አይደለም ያለ አንድም መንግስት የለም።ለወትሮው አንዲት ሀገር የእዚህ ዓይነት ጉዳዮችን ስታነሳ በቶሎ አስተያየት ለመስጠት እና ለመቃረን የሚጋፉ መንግስታትም ሆኑ ባለስልጣናት የሞሉባት ዓለማችን በኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ አልተፈጠረባቸውም። ይህ ማለት በርካታ የዓለማችን ሀገሮች፣ በጉዳዩ ላይ የሚስማሙበት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ የራሱ የሆነ የኃይል ሚዛን የሚፈጥር እና የቀይ ባሕርና የሜዴትራንያ ባሕር ፀጥታም የሚያረጋጋ ለመሆኑ አንዳችም ጥርጣሬ አልፈጠረባቸውም። ከእዚህ ውጪ ከኤርትራ፣ጂቡቲና የሱማልያ የፓርላማ አባላት፣ጋዜጠኞች የተሰጡ ምላሾች የሚጠበቁ እና ተፈጥሯዊ ምላሾች ናቸው። ከኤርትራ ተሰጠ የተባለውም ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ ለመርሳት ለመሞከር የሚደረግ እራስን የማታለል ዓይነት መግለጫ ነው። ይህም ሆኖ መግለጫው የዓለምን ትኩረት አልሳበም።

በሌላ በኩል በጉዳዩ ላይ ''ያዙኝ ልቀቁኝ '' ትላለች ተብላ የምትጠበቀው ግብፅ በጋዛ እስራኤል ጉዳይ ተወጥራ ''ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ'' ላይ ነች።ከሰሜናዊ ጋዛ እንዲወጡ የተደረጉ ፍልስጤማውያን ጎርፍ እንዳያጥለቀልቃት ጭንቀት ውስጥ ነች።

ዓለም የኢትዮጵያን እውነት በእንዲህ ዓይነት ደረጃ ሲመለከት እራሳቸው የኢትዮጵያ የሆነው ሰፌድና የባዕድ የሆነ ድስት በመልክ መለየት አቅቷቸው እዚህ እና እዝያ እየዘለሉ ግራ ተጋብተው የኢትዮጵያን ሕዝብ ግራ ለማጋባት የሚሞክሩት ዩቱበር ወገኖቻችን ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የኤርትራ ህዝብ ዛሬ ነቅቷል።ከኢትዮጵያም ከኤርትራም ሰው በከንቱ እንዳይወድቅ ካለፈው ተምሯል። ይህም ሆኖ ግን ኢትዮጵያን ካለወደብ አስቀርቶ በሰላም ውሎ ማደር እንደማይኖር ይህም ለማንም እንደማይበጅ ሁሉም በየቤቱ ገብቶታል።ጸብ ብሎ ነገር የለም። ኢትዮጵያም ካለወደብ ውላ ለማደር አትችልም።ይህንን እውነታ ማስታረቅ የግድ ነው።
============////==================

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...