- የአሁኑ የፍልስጤም እስራኤልን ጦርነት ለዓለማችን የከፋ ከሚያደርጉት ውስጥ ስድስቱ ምክንያቶች
=========
ጉዳያችን ምጥን
=========
በዓለማችን ላይ ሁሉንም ሀገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይነካል የተባለው ''እምብርት'' የፍልስጤም- እስራኤል ጦርነት ተቀስቅሷል።የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ የአሚሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ለእስራኤል የጦር መሳርያ መላካቸውን እና መንገድ ላይ መሆኑን መግለጻቸው ማምሻውን ተገልጿል። ኢራን ከፍልስጤም ጎን እንግሊዝና ኔቶ ከእስራኤል ጎን መሰለፋቸውን አሳውቀዋል።የተባበሩት አረብ ኢምሬት በተለየ ሁኔታ የገለልተኛነት ቦታ መያዟ ሲሰማ፣ በግብጽ የእስራኤል ቱሪስቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ሲገለጽ አጠቃላይ ክስተቱ በቋፍ ላይ የነበረውን የተከፋፈለ ዓለም ''ጠብ ያለሽ በዳቦ'' ዓይነት ትርጉም የለሽ ግጭት ውስጥ እንዳያስገባ ተፈርቷል። የአሁኑ የሀማስ በእስራኤል ላይ የጀመረው ጥቃት ከቀደሙት የሚለየው እስራኤል በኃይል ይዛቸዋለች ባላቸው ግዛቶች ላይ ሳይሆን ጥቃቱ የፍልስጤም ግዛት ባልሆነው የእስራኤል መሬት ላይም መሆኑ የነገሩ ሰፋ ብሎ መጀመር ያሳያል፣ይህ በቀላሉ በዲፕሎማሲ የሚፈታ እንደማይሆን በራሱ አመላካች ነው።
የአሁኑ የፍልስጤም እስራኤልን ጦርነት ለዓለማችን የከፋ ከሚያደርጉት ውስጥ ስድስቱ ምክንያቶች :
- የሩስያ ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በምዕራቡና ሩስያ፣ቻይና መሃል ያለው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ላይ መሆኑ፣
- የተባበሩት መንግስታት በተዳከመበት እና የዓለምን ጸጥታ ችግር የመፍታት አቅሙ በተደጋጋሚ ተፈትኖ በወደቀበት ጊዜ መሆኑ፣
- የጸጥታው ምክር ቤት አምስቱ አባላት በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጋራ አጀንዳቸው በሳሳበት እና ለእዚህም አንድ ዓይነት መፍትሄ ገና ባላገኙበት ወቅት መሆኑ፣
- የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ሀገሮች ውስጥ አባል የሆነችው ቱርክ በፍልስጤም እስራኤል ጉዳይ የምትወስደው አቋም ለድርጅቱ የራሱ የሆነ ጥላ ማጥላቱ፣
- ከኮቪድ በኋላ የተጎዳው የብዙ ሀገሮች ምጣኔ ሀብት በፈጠረው የኑሮ ውድነት ሳብያ በብዙ ሀገሮች ያለው የውስጥ ቅራኔ በተባባሰበት ጊዜ መሆኑና ይህም በብዙ ቦታዎች ''ግልገል ጦርነቶች'' የመፍጠር አደጋ መኖሩና
- የምዕራቡን ዓለም በማስተባበር የመሪነቱ ሚና የነበራት አሜሪካ በአሁኑ ጊዜ ያላት ፕሬዝዳንት የነቃና የተጋ አለመሆን ብቻ ሳይሆን ሰላማዊ መፍትሄ የማምጣት አቅሙ ያነሰ መሆኑ የሚሉት ይጠቀሳሉ።
================//////============
ኢትዮጵያ በቴዎድሮስ ካሣሁን
No comments:
Post a Comment