ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, July 3, 2022

ሽብርተኛው ህወሓት የአፄ ዮሐንስን ራስ ደግሞ ቆረጠው።


=====
ጉዳያችን 
=====
በአባታቸው ከተንቤን በእናታቸው ከእንደርታ የሚወለዱት አጼ ዮሐንስ 4ኛ የነገሱት በቀድሞ ስማቸው ደጃች በዝብዝ ካሣ ተብለው በሚጠሩት ዘመን  ነበር ከአፄ ተክለጊዮርጊስ ጋር አድዋ አካባቢ ተዋግተው ካሸነፉ ብኋላ ጥር 13/1864 ዓም  አፄ ዮሐንስ ተባሉ። አፄ ዮሐንስ የመጨረሻ የንግስና ዘመናቸው ያበቃው በወቅቱ ደርቡሾች ዛሬ ሱዳን የሚባለው አገር የመጣ ሰራዊት ጋር ባደረጉት ውጊያ ነበር።ውጊያው መተማ አካባቢሲሆን በመጨረሻም በእዚሁ ቦታ ህይወታቸው አልፏል።በጦርነቱ ወቅት መጀመርያ የኢትዮጵያ ሰራዊት የበላይነቱን ይዞ ነበር። በጦርነቱ መሃከል ግን የአፄ ዮሐንስ መቁሰል ተሰማ።ይህም ለሱዳን ጦር የልብ ልብ ስለተሰማው አፄ ዮሐንስ ከቆሰሉበት ቦታ ደርሶ አንገታቸውን ቆርጦ ወደ ሱዳን በመውሰድ ካርቱም ገበያ ለገበያ እያዞረ በንጉሱ አንገት ቀልደዋል።

ይህንኑ አስመልክቶ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ፣የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983 ዓም በሚለው መጽሓፋቸው ላይ የሚከተለውን 
ብለዋል 

ሽብርተኛው ህወሓት የአፄ ዮሐንስን ራስ ደግሞ ቆረጠው

የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን ኢትዮጵያን በትነን ሲዖል እግባለሁ በሚል መግለጫ የሰጠው የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ትናንት በሰጠው መግለጫ ላይ ደግሞ የአፄ ዮሐንስ አንገት ከተቆረጠባት ዛሬም ታሪካዊ ጠላት ለመሆን የሚጥር መንግስት ካላት ከሱዳን ጎን ሆኖ ኢትዮጵያን እንደሚወጋ በግልጽ ተናግሯል። በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ በከፍተኛ የስልጣን ዕርከን ላይ አስቀምጣው የነበረው በኢትዮጵያ እንጀራ ፊቱ የወዛው ጌታቸው ረዳ የሱዳንን ጦር የኢትዮጵያ መከላከያ ሊያስፈራራው አይችልም፣ሱዳን እንድትነካ አንፈልግም፣ከሱዳን ጎን ነው የምንቆመው፣ውለታ ውለውልናል እና ሌላም ሌላም ብሏል። የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የተናገረው ሁሉ በህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ተወስኖ እንዲነገር የተወሰነ በመሆኑ ህወሃት በግልጽ ከሱዳን ጎን መቆሟን በእዚህ መግለጫ አረጋግጣለች።

ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ሌላው የህወሃት ጥቁር ታሪክ ብቻ ሳይሆን መጪው ትውልድ የህወሃትን ፍጹም ኢትዮጵያን መክዳት እና ከባዕዳን ጋር የመተባበር አሳፋሪ ታሪክ ተመዝግቧል። እዚህ ላይ ታሪካዊ ጥያቄ ለትግራይ ህዝብ ይቀርባል። ህወሃት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከአክሱም እስከ ሽሬ እና በሌላው ህወሃት በሚቆጣጠረው የትግራይ ክልል ሁሉ ወርዶ የህወሃት ዓርማ ሲሰቀል፣አሁን ደግሞ የአፄ ዮሐንስን አንገት የቆረጠው የደርቡሽ አገር ኢትዮጵያን ሲወር አብረን እንቆማለን፣ዛሬም ኢትዮጵያን እኛ መበተን ስላቃተን ኢትዮጵያን ለመበተን የሚመጣ ጠላት የትግራይን ህዝብ እናሰልፋለን ሲል ሁሉ የትግራይ ህዝብ ምላሽ ምን መሆን አለበት? የሚለው ጥያቄ ነው።ይህ ጥያቄ በኢትዮጵያ የታሪክ መዝገብ ላይ የሚጻፍበት መንገድ በጥቁር እና አሳፋሪ ታሪክ ነው ወይንስ ስህተትን በሚያርም መልኩ ነው የሚለው የሚመለሰው የትግራይ ህዝብ ለህወሃት አሳፋሪ ተግባር በሚሰጠው ምላሽ ይወሰናል።

አሁን ያለው አሳፋሪው እና መጪው ትውልድ በጥቁር ቀለም የሚጽፈው ታሪክ ሽብርተኛው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማወክ ከንቱ ድካም ከሚደክመው ከደርቡሽ አገር ሱዳን ጋር አብሮ በመቆም  የአፄ ዮሐንስን ራስ ደግሞ መቁረጡን ነው።
===========////=========


No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...