ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, July 23, 2022

በግብጽ እና ሱዳን ጓዳ ሲቋጠሩና ሲፈቱ የከረሙት ጉዳዮች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ያለፉት ሦስት ሳምንታት አክራሞት


===========
ጉዳያችን ልዩ ዘገባ
===========
በግብጽ እና ሱዳን ጓዳ ሲቋጠሩና ሲፈቱ የከረሙት ጉዳዮች

ኢትዮጵያና ሱዳንን ወደየለየለት ጦርነት ለመክተት በሱዳን ውስጥ በተሰገሰጉ የግብጽ ወኪሎች እና በግብጽ በራሷ ሲገፋ የነበረው ጥረት መጨረሻ ደረጃ ይሳካል ተብሎ የታሰበው በቅርቡ በሁለቱ አገሮች ድንበር አካባቢ በአልፋሻጋ አካባቢ የሱዳን ወታደሮች ተገደሉ የሚል ዜና በመንዛት ነበር። እነኝሁ በሱዳን የግብጽ ወኪሎች እና ግብጽ እራሷ ከፍተኛ የሚድያ ዘመቻ ከማድረግ አልፈው የግብጹ ፕሬዝዳንት አድርገው የማያውቁትን የሃዘን መግለጫ በኢትዮጵያ ለተገደሉት የሱዳን ወታደሮች ሃዘን በሚል አወጡ።በኢትዮጵያ በኩል ጉዳዩ ቀድሞ የታወቀ ስለሆነ እና ዓላማው በኢትዮጵያ እና ሱዳን መሃል ጦርነት ማስነሳት እና ግብጽ በመሃል የመግብያ ቀዳዳ እንድታገኝ በእዚህም በያዝነው ክረምት የሚሞላው ሦስተኛው ዙር የዓባይ ግድብ ማስተጓጎል ነበር። ከእዚህ ባለፈ የሱዳን መንግስት በውስጡ የተነሳው የህዝብ አመጽ ለመግታት እና አቅጣጫ ለማስቀየር የታሰበም ነበር።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ አቋም ጉዳዩን በንግግር መፍታት ላይ ማትኮሯን የሚገልጽ መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአረብኛ በትዊተር ገጻቸው መለጠፋቸው ብቻ ሳይሆን የሱዳንን ባለስልጣናት ናይሮቢ በተደረገው የኢጋድ ስብሰባ ላይ አግኝተው ማስረዳታቸው ሱዳኖች ሳይወዱም በግድ በህዝባቸው ግፊትም ቢሆን ከግብጽ ግፊት ለማፈግፈግ ተገደው ነበር።

አሁን በቅርብ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ የሱዳን ጦር በአልፋሻጋ እና አልሱቅራ በተባሉ ቦታዎች ገለዓሉባን ተራራ እና ሉግዲ በረከት በተባሉ ቦታዎች የሱዳን ኃይሎች በአካባቢው ያሉትን ሚሊሻዎች እየገፉ ቦታዎች እየያዙ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

ሱዳን እና ግብጽ ጓዳ ምን እየተደረገ ነው?

በኢትዮጵያ አንጻር የሱዳን መንግስት በሚከተለው የግብጽን ፍላጎት የማሟላት ሂደት በሱዳን በራሷ በተለይ በባለስልጣናቱ መሃልም ጭምር ክፍፍል ፈጥሯል። የመጀመርያው ክፍፍል ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካይነት ናይሮቢ ላይ  ለሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌ/ጀነራል አብዱል ፋታህ በግልጽ ያስተላለፈችው መልዕክት ግልጽ ስለሆነ ሱዳን ለምን የራሷን ችግር በመፍታት ላይ አታተኩርም? የሚሉ የሱዳን ባለስልጣናት መንግስታቸውን ወጥረው መያዛቸው ነው። ይህንን ሃሳብ ከሚደግፉት ውስጥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ውይይት ያደረጉት እራሳቸው ጀነራል አብዱል ፈታህ መሆናቸው እና ይህንንም አቋም ይዘው በመመለሳቸው ነበር በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር መከፈት ላይ እና የታጠቁ ኃይሎች በድንበር አካባቢ መንቀሳቀስ አይችሉም የሚል መግለጫ የሉዓላዊ ምክር ቤቱ እንዲያወጣ ያደረጉት።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን ለሱዳን መንግስት ቅርበት ያላቸው የሱዳን መገናኛ ብዙኃን የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ እርምጃ እንደወሰደ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደተማረኩ እያስመሰሉ የበለጠ ብዥታ ለመፍጠር ሲሞክሩ የግብጽ ወኪል የሱዳን ባለስልጣናት በበኩላቸው ደግሞ የሱዳንን ህዝብ ስሜት ለመቀስቀስ የሱዳን ህዝብ በኢትዮጵያ እንደተዋረደ እያስመሰሉ ማቅረብ ጀመሩ።ይህ በእንዲህ እያለ ግን በኢትዮጵያ ድንበር ልዩ ቦታው ''በረከት ኑር በተባለ ቦታ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው የገቡ የሱዳን ታጣቂዎች የኢትዮጵያ የእርሻ ካምፖችን፣መጋዘኖች እና 16 ትራክተሮችን እና በበርሜል የተከማቸ ነዳጅ ዘርፈዋል።እስካሁን ባለው መረጃም አስር የሚሆኑ የኢትዮጵያ ባለሃብቶች አፍነው ወስደው በረከት ኑር በተሰኘው አካባቢ ካምፕ ውስጥ መሸሸጋቸውን ለማወቅ ተችሏል። ይህ በእንዲህ እያለ ሱዳን አሁንም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ከገፋ እስከ አየርኃይሏ ለመጠቀም በውስጥ መወሰናቸው ተሰምቷል። 


ይህ በእንዲህ እያለ ግብጽ በሱዳን ወታደራዊ መንግስት ላይ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ እንዲያደርግ እስከ ማስራራት የደረሰ ጫና እያሳየች ነው። ወደእዚህ ዓይነት እርምጃ ግብጽን የመራት ደግሞ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ መሃል በናይሮቢ የተደረገው ውይይት ከግብጽ ቁጥጥር ውጪ የሆነ እና ምህዋሩን የሚያስታት በመሆኑ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሮባት ሰንብቷል። ይህንን ውይይት ተከትሎ ካይሮ ልዩ የደህንነት ልዑክ ወደ ካርቱም የላከች እና የጸረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ እንዳይቆም የተቻላትን ለማድረግ  ሞክራለች።በተጨማሪም ግብጽ ቦይንግ 737 የመንገደኞች አይሮፕላን  የግብጽ አለስከንደርያ ኩባኛ ንብረት የሆነ አይሮፕላን በሱዳን የከሰላ አይሮፕላን ማረፍያ እንዳረፈ እና ሌሎችየካርጎ አውሮፕላኖች በገዳሪፍ አዘዛ በተባለው የሱዳን ወታደራዊ ካምፕ እና በገዳሪፍ አልፋው በተባለው የሱዳን 2ኛው ክፍለ ጦር ካምፕ የተለያዩ የህክምና መሳርያዎች እና መድሃኒቶች አራግፈው መሄዳቸውን የኢትዮጵያ መረጃ ቢሮ እጁ ገብቷል።

በሌላ በኩል ግብጽ በከፍተኛ ሁኔታ እየሮጠችበት ያለው ጉዳይ በኢትዮጵያ ፌድራል መንግስት እና በህወሃት መሃል ሊደረግ የታሰበው ውይይት በፍጥነት እንዲቀጭ የተቻላትን ሁሉ በማድረግ ላይ ነች።ለእዚህም እንዲረዳቸው ከህወሃት በኩል በድርድሩ የሚሳተፉትን አባላት እና ሌሎች የቡድኑ ወታደራዊ አመራሮች ወደ ካይሮ ለመውሰድ ወይንም በሱዳን የደህንነት ማሰልጠኛ ውስጥ ገብተው ስልጠና እንዲወስዱ ለማድረግ ዕቅድ እንዳላት የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።


የኢትዮጵያ መከላከያ ባለፉት ሦስት ሳምንታት አክራሞት

በሸኔ፣ጋምቤላ፣ጉሙዝ እና በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በቅርብ እና የሩቅ የኢትዮጵያ ጠላቶች የተሰጣቸው ተልዕኮ ያሉበትን ክልል ከማተራመስ ባለፈ ወደ ሌሎች ክልሎች በፍጥነት እንዲሰርጉ ነበር። ሆኖም ግን መከላከያ ባሳለፍናቸው ሦስት ሳምንታት የወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኖቹ አከርካሪ ተመቷል።በእዚህም በአዝማቾቻቸው መንደር ከፍተኛ መበሳጨት ፈጥሯል።
በሸኔ ላይ የተወሰደው እርምጃ 
  • በመቶዎች የሚቆጠሩ የሸኔ ቡድን አባላት ተገድለዋል።
  • ከሁለት መቶ በላይ ቀላል እና መካከለኛ የጦር መሳርያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል
  • ከውጭ የነበረው የግንኙነት መረብ ከጠበቀው በላይ ተቋርጦበታል፣በእዚህም ከፍተኛ መደናበር በቀሩት አባላት ውስጥ ተፈጥሯል
  • ጥቃቱ በአራቱም የወለጋ እና የሸዋ ዞኖች እንዲሁም በጉጂ ዞን በተወሰደበት እርምጃ የተበታተነው የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በአንዳንድ ቦታዎች የሚታየው ባልተደራጀ እና ሰንሰለቱ በተበጣጠሰ ደረጃ ሆኖ ነው
  • ይህም ሆኖ የተበታተነው ኃይል አልፎ አልፎ በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ መሞከሩ እንደማይቀር ይገመታል
በተመሳሳይ በጋምቤላ፣ጉሙዝ እና ቅማንት ስም የሚነግዱ የሽብር ቡድኖች ላይም በተወሰደው በተለይ በዓባይ ግድብ ላይ ለማድረስ የታቀደው ሁከት ከመከላከል ባለፈ የሽብር ቡድኖች ስጋት የመሆናቸውን አደጋ በእጅጉ ለመቀነስ መቻሉ ቢታወቅም አሁንም ከባዕዳን ጀምሮ እስከ የውስጥ አደራጆቻቸው እንደገና ለማወክ መሞከራቸው ስለማይቀር ዛሬም በንቃት የመጠበቅ ስራው ሊቀጥል ይገባል።

ባጠቃላይ አሁን የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያ የአባይን ግድብ ሦስተኛ ዙር ሳትሞላ አንዳች ዓይነት ሁከት ለመፍጠር እና የውስጡ ማወክ ካልተሳካ ቀጥታ ወረራ ለመፈጸም አያሰላስሉም ብሎ ማሰብ አይቻልም። በእርግጥ ማንም አገር በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያሰበ አገር የሚያገኘው ምላሽ ምን እንደሆነ ያውቀዋል።በተለይ የሱዳን እና የግብጽ የጥቃት ሙከራ ከኢትዮጵያ ይልቅ ሁለቱን አገሮች የማፍረስ ደረጃ የማድረስ አደጋ አለው።ለእዚህም አንዱ ምክንያት ኢትዮጵያ ለሚሰነዘርባት ማናቸውም ጥቃት ከአየር ኃይል እስከ የእርቀት ሚሳኤሎች የአጸፋ ምላሽ መስጠቷ ስለማይቀር እና በሱዳንም ሆነ በካይሮ የህዝባቸው ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ቁጥር ተከማችቶ የሚገኘው በተወሰኑ ከተሞች በመሆኑ የሁለቱ አገራት የተወሰነ መሰረተ ልማት ላይ ኢትዮጵያ ለምትወስደው እርምጃ በአስር ሚልዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ይበተናል። ይህም ከፍተኛ ቀውስ ለመካከለኛውም ሆነ ለአውሮፓ ይዞ መምጣቱ አይቀርም። በመሆኑም ግብጽም ሆነች ሱዳን ኢትዮጵያን ከውስጥ በራሷ ከሃዲዎች ለማተራመስ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚከፍሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ማወቅ አለበት።ከእዚህ በተረፈ ክውጭ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች አይኖሩም ብሎ ተዘናግቶ የሚቀመጡበት ጊዜ እንዳልሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልጽ ነው።በቅርቡ በሳውዲ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ከግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ጨምሮ የአባይ ግድብ ጉዳይ በአጀንዳነት እንዲቀርብ ግብጽ ብዙ መጋጋጥ አድርጋ ሄዳበታለች።አሁን ጥያቄው በእዚህ ስብሰባ ላይ ምን ነበር ንግግሩ? የውስጥ የሴራ ንግግር ነበር ወይንስ ግልጽ ውይይት ነበር? ለሚሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሾች ስናገኝ ብዙ ነገሮች ግልጽ ይሆኑልናል።ባጭሩ ግን ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ከውስጥም ከውጭም ነቅተው እና ተግተው የሚጠብቁበት ጊዜ አሁን ነው።
==============//////==================


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...