ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, July 30, 2022

በእዚህ ሳምንት ውስጥ በውጭው ዓለም የተዘገቡ አገርቤት ትኩረት ያላገኙ ኢትዮጵያን የተመለከቱ 8 መልካም ዜናዎች

የለገዳዲ የመጠጥ ውሃ ግድብ ዕድሳት ስምምነት ሲፈረም 

ከ50 ዓመታት በላይ እድሳት ያልተደረገለት የአዲስ አበባ ለገዳዲ የመጠጥ ውሃ ግድብ በንጉሱ ጊዜ በሰራው የጣልያን ኩባንያ ለመጪዎቹ 50 ዓመታት እንዲያገለግል ተደርጎ ሊስፋፋ ነው።

የዓለም ባንክ በሰጠው 11 ሚልዮን ዶላር በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ጊዜ የተገነባው እና ለ50 ዓመታት እንዲያገለግል ተደርጎ የተሰራው የለገዳዴ የመጠጥ ውሃ ግድብ ቀድሞም በሰራው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ በሚደረግለት ዕድሳት ለቀጣይ 50 ዓመታት በተጨማሪ እንዲያገለግል ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ግድቡ አዳዲስ የማስተንፈሻ እና ዘመናዊ የማጣርያ መሳርያዎች የሚገቡለት ይሆናል።የግድቡ እድሳት በ18 ወራት የሚጠናቀቅ ሲሆን ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሳሊኒ (አዲሱ ስሙ እንገነባለን ''ዊ ብዩልድ'' ብሎ ቀይሯል) ጋር ስምምነቱን ሲፈራረም የአዲስ አበባ ውሃናፍሳሽ ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን አባተ እንዳሉት ይህ እድሳት የግድቡ የውሃ የማቅረብ  አቅሙን በቀን በሠላሳ ሺህ ኩቢክ ሜትር ያሳድገዋል።

''ኢትዮጵያ ታሪክ እየሰራች ነው።አየርመንገዷ በአፍሪካ ያልገባ ኤር ባስ ኤ 350-1000  (Airbus’ A350-1000 aircraft) ገዝታለች '' ትራቭልራዳር
ኤር ባስ ኤ 350-1000

ሓሙስ ዕለት ትራቭል ራዳር ኢትዮጵያ ታሪክ እየሰራች ነው በሚል ርዕስ ያወጣው ዜና ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእዚህ ግዢው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከፈረንሳይ እና ከቻይና አየር መንገድ ጋር ከስድስቱ ግዙፍ አየርመንገዶች ተርታ ያሰልፈዋል ይላል።ዜናው አክሎም የኤርባስ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክተር ሚካኤል ሆአሪ  (Mikail Houari) ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ጠንካራ አጋርነት መፍጠራቸው እንዳስደሰታቸው መግለጻቸውን ጠቅሶ አየር መንገዱ በቴክኖሎጂ የተራቀቀውን ኤር ባስ ኤ 350 በመግዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ አየርመንገድ ያደርገዋል ብለዋል ብሏል።

ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የዓባይ ግድብ በያዝነው ክረምት እንደምትሞላ ለግብጽ መልዕክት ልካለች

ኢትዮጵያ በእየዓመቱ የዓባይን ግድብ ስትሞላ ኦፊሽያላዊ ደብዳቤ ለታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች ማለትም ለግብጽ እና ለሱዳን በደብዳቤ እያሳወቀች ነበር። ዘንድሮም ሦስተኛውን የዓንባይ ግድብ እንደምትሞላ ግልጽ ደብዳቤ ከኢትዮጵያ እንደደረሳት ግብጽ መግለጿን  የዘገበው ''ኢጂፕት ኢንዲፐንዳንት '' የተሰኘው ጋዜጣ በያዝነው ሳምንት ውስጥ ነው።ይህንኑ የገለጹት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሽኩሪን ኢትዮጵያን ለተባበሩት መንግስታት ለመክሰስ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ኢትዮጵያ ውሃውን እንደምትሞላ በግልጽ ነግራናለች ብለዋል። ሚኒስትሩ የመንገሯን ጨዋነት ግን ማድነቅ አልፈለጉም።

የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ለኬንያ ሁለተኛው ግዙፍ የመብራት ኃይል አቅራቢ ሆነይህንን የዘገበው የኬንያው ስታር ጋዜጣ በያዝነው ሳምንት ነው።ጋዜጣው ኬንያ ከኢትዮጵያ የመብራት ኃይል ለመግዛት ውል መፈራረሟን ገልጾ ባለፈው ሓሙስ በስቲማ ፕላዛ የተደረገው የኢትዮጵያ እና የኬንያ የመብራት ኃይል ውል መሰረት በኪሎዋት በአንድ ሰዓት ከስድስት እስከ ሰባት የኬንያ ሽልንግ እንደሚቆጥር ጋዜጣው ያብራራ ሲሆን የመስመር ዝርጋታው የተጠናቀቀው የመብራት ኃይል አገልግሎቱ ኬንያ ከኢትዮጵያ 600 ሜጋዋት ያህል የምታገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ አገልግሎቱን ከመጪው ህዳር ወር ጀምሮ እንደምትሰጥ ዜናው ያትታል።በሓሙሱ የውል ስምምነት ላይ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ እንደተገኙ የኬንያው ስታር ጋዜጣ ዘግቧል።


የኢትዮጵያ አየር ኃይል የአልሸባብን ይዞታ ዛሬ ቅዳሜ በድንገት አደባይቶታል

የቱርክ ዜና አገልግሎት አናዶሊ ዛሬ ቅዳሜ እንደዘገበው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የአልሸባብ ይዞታዎችን ዛሬ ድንገት ደርሰው አደባይተውታል።አየር ኃይሉ ያጠቃበት ቦታ በደቡብ ምዕራብ ሱማልያ ጋራስዋይነ በተባለ ቦታ መሆኑም ገልጾ የአናዶል ዘጋቢ ከስፍራው በስልክ የነገረውን ገልጾ የቱርክ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው አራት ሚሳኤሎች ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ተወንጭፈው ኢላማቸውን መምታታቸውን ገልጿል።

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የስበት ኃይልነቷ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልጽ እየሆነ ነው። 

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ የስበት ማዕከል እየሆነች እንደመጣች ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልጽ ሆኗል።ይህንን ለማረጋገጥ የሃያላኑ መንግስታት የእዚህ ሳምንት አዲስ አበባ መክተም ብቻ በመመልከት መረዳት ይቻላል።
እያሳለፍነው ባለነው ሳምንት ብቻ 
  • ቻይና ከስድስት የምስራቅ አፍሪካ አገራት ጋር ጸጥታን በተመለከተ አዲስ አበባ ላይ ልዩ ስብሰባ አድርጋለች፣
  • አሜሪካ ልዩ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ዓርብ ዕለት ልካለች፣
  • የሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በእዚሁ ሳምንት አዲስ አበባ ከትመዋል።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ 488 ሚልዮን ዶላር ለሰብዓዊ ዕርዳታ ለኢትዮጵያ ህዝብ መስጠቷን በዩኤስ ኤይድ ጋዜጣዊ መግለጫ የገለጠችው በእዚህ ሳምንት ነበር።

በጋዜጣዊ መግለጫው (ፕሬስ ሪሊዝ) ላይ የአሜሪካ ተራዶ ድርጅት እንደገለጸው ድጋፉ ወደ 8 ሚልዮን ለሚሆን ህዝብ የሚዳረስ ሲሆን ከምግብ ዕርዳታ በተጨማሪ ለገበሪዎች ለመጪ ዓመት ምርት ድጋፍ፣ለንጹህ መጠጥ ውሃ እና ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ድጋፍ ጭምር እንደሚውል ያብራራል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ4ነጥብ 3 ሚልዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉ የተገለጸው በእዚህ ሳምንት ነበር።

የአፍሪካ ልማት ባንክ በድረገጹ ላይ ከአቢጃን ረቡዕ እለት እንደገለጸው የባንኩ ቦርድ 4ነጥብ3 ሚልዮን ዶላር ለኢትዮጵያ ስጦታ የሰጠ ሲሆን ገንዘቡ ኢትዮጵያ በተለይ የገንዘብ ሚኒስትር ለሚያካሂደው የአቅም ግንባታ እንደሚውል ባንኩ በዘገባው ላይ አብራርቷል።
============///===========
No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...