ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, August 30, 2019

በሁለት ትውልዶች ውስጥ ለመስዋዕትነት የተዘጋጀ የዘመናችን ምሳሌ - አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የአሁኑ ቅዳሜ በኦስሎ፣ኖርዌይ የምስጋና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ።ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተጋብዘዋል።

በ1960ዎቹ  መጨረሻ እና የ1970ዎቹ የፖለቲካ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፈዋል።በ1984 ዓም በተፈጠረው የመንግስት ለውጥ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለውጡን ለማስተካከል ከዳር ሆኖ ከመመልከት ከውስጥ ሆኖ መስራት ይገባል በማለት ለመስራት ሞከሩ።ለውጡ በለየለት የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ እየተዘፈቀ በመምጣቱ  መቀጠል አልቻሉም።በ1997 ዓም ምርጫውን ተከትሎ የቅንጅት መሪዎች ሲታሰሩ የማስፈታቱን ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ካስተባበሩት ውስጥ ነበሩ። በመቀጠል የግንቦት 7 በኃላም የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ፀሐፊ በመሆን ከየመን እስከተጠለፉበት ጊዜ ድረስ በኤርትራ በረሃ ወርደው የትጥቅ ትግል አስተባብረዋል።በቅርቡ ለአርት ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለ መጠይቅ የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን እንደ ሶርያ እና ሊብያ ሊከፋፍል እንደሚችል ከየመን ከመጠለፋቸው በፊትም ድምዳሜ ላይ እንደደረሱ አስታውቀዋል።

አቶ አንዳርጋቸው የተሰማቸውን በግልጥ በመናገር ይታወቃሉ።በ1984 ዓም ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ በወቅቱ የነበረው የዲያስፖራ ስብስብ ለምን? በሚል ሞግቷቸው ነበር።ሆኖም ግን ለኢትዮጵያ እስከጠቀመ ከሩቅ ሆነን ከምናበላሽ ገብተን ሊስተካከል የሚችለውን መስራቱ ይሻላል ብለው ሞግተዋል። በኃላም የግንቦት 7 ንቅናቄ ወደ ኤርትራ ሲገባ እንዲሁ ቀላል ያልተባለ ሙግት ቀርቦባቸው ይህንንም ተጋፍተው በማስረዳት እስከለውጡ ድረስ ገፍተውበታል። አቶ አንዳርጋቸው በሁለቱም ትውልድ ውስጥ ሆነው ሲታገሉ ያመኑበትን በግልጥ በመናገር የሚታወቁ ናቸው።

እኝህ ሰው በአሁኑ ቅዳሜ ጳጉሜን 2/2011 ዓም  (ሴፕቴምበር 7/2019 ዓም) በኦስሎ፣ ኖርዌይ የምስጋና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ።ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ።በዝግጅቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተጋብዘዋል። ቦታው ''አንቲራስስት ሰንተር'' ፣ አድራሻ Storgata 25, 0184 Oslo ነው።

አንዳርጋቸው ማለት አንተ ከቤትህ የሞቀ አልጋ ላይ ሆነህ ለኢትዮጵያ እና ላንተ ሊሞትልህ በረሃ የገባ ጀግና ባለውለታህ ነው።ቢያንስ በዝግጅቱ ላይ አለመገኘት ውለታ ቢስነት ነው። ኢትዮጵያውያን ባለውለታዎቻንንን ስናጥላላ ወደር የለንም። አፄ ኃይለሥላሴን በመግደል የተመፃደቅን፣የራሳችን የሆኑትን ጀግኖች አንዳንድ ሳር እየመዘዝን ክምር የሆነውን ታላላቅ ስራዎቻቸውን እየሸሸግን በማዋረድ እና ኢትዮጵያ ነገ ሌላ ጀግና እንዳይወጣላት በእዚህ እኩይ ስራችን አዲሱን ትውልድ ስሜት ለመግደል ቀን ከሌት የምንሰራ አሳዛኝ ሕዝብ መሆናችን እንቆቅልሻችን ነው። 


አንዳርጋቸው ለመሞት ለተዘጋጀለት የመፃፍ መብት ተጠቅሞ የመሰለውን  ፅፏል፣ወደፊትም ይፅፋል።ይህ ማለት ባቀረባቸው ነጥቦች ላይ ትከራከራለህ እንጂ የሰራቸውን መልካም ስራዎች 100 % አውርዶ ማጣጣል ግን የተለመደው አዙሪት ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? አቶ አንዳርጋቸው በአዲስ  ስታድዮም ያደረጉት ንግግር ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...