ጉዳያችን / Gudayachn
ነሐሴ 23/2011 ዓም (ኦገስት 29/2019 ዓም
ኢትዮጵያ በዘገምተኛ ለውጥ ውስጥ ከምር መግባት ከጀመረች አንድ ዓመት አልፏታል።ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ ፈፅማ ወደ አደገኛ መንገድ ውስጥ ከመግባት ድና የተሻለ የመፃፍ፣የመናገር እና የመደራጀት መብት እንዲሁም ሁሉም የተቃዋሚ ኃይሎች ወደ አገር ቤት የመግባት እና የመስራት ዕድል አግኝተዋል።ከእዚህ በተጨማሪ በህወሓት መራሹ ኢህአዴግ የነቀዙ ፕሮጀክቶች ለምሳሌ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ሜቴክ እና የ70 ቢልዮን ብር በላይ የአገር ሀብት የበላው የስኳር ፕሮጀክት ጨምሮ የማከም እና ፕሮጀክቶቹን በተሻለ ደረጃ ለማንቀሳቀስ በተደረጉ ጥረቶች ፕሮጀክቶቹ በተሻለ መንገድ እንዲቀጥሉ የማድረግ ሥራ በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘቱ የአንድ ዓመት ተኩል የለውጡ ሂደት ውጤት ነው።
የለውጥ ሂደቱ በትምህርት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት፣የሕግ ማሻሻያዎችን ለምሳሌ ከመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መመርያ፣ የሲቪል ሰርቪስ እና ሌሎች ሕጎች ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል።ከእዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ከጎረቤት ሀገሮች እስከ መካከለኛው ምስራቅ፣ከአውሮፓ እስከ ሩቅ ምስራቅ ያላት የዲፕሎማሲ ግንኙነት መሻሻል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ እየተከበረች እና የመደመጥ አቅሟን ያሳደጉ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተከናወኑት የመንግስት መልካም ስራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እያለ የለውጡን ሂደት ለማደናቀፍ ያለሙ ኃይሎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ላይ ያነጣጠረ መሰረት የለሽ የስም ማጥፋት ስራዎች በሰፊው ሲሰሩ ሰንብተዋል።የስም ማጥፋት ዘመቻዎቹ ከከተማ እስከ ገጠር የተዘረጉ እና በቀድሞ የህወሓት-መር የደህንነት መዋቅር ስር የተሰራ ተራ አሉባልታ ሁሉ ያጠቃለለ ነው። አብዛኞቹ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ቀድመው የቀድሞው ስርዓት አድናቂ ነገር ግን በተቃዋሚነት የሚታወቁ ሁሉ በጭንቅ ሰዓት በአምስተኛ ረድፈኝነት በተቃዋሚ ካባ፣ ነገር ግን በጎሳ ስም ተለብደው በተቃዋሚነት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲያደርጉ በተሰጣቸው የቤት ሥራ መሰረት በማኅበራዊ ሚድያ እና ሰው ለሰው በመሄድ የስም ማጥፋት ዘመቻቸውን ስያጧጡፉ ሰንብተዋል።
ይህ ሁሉ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከጦርነት በፊት እንደተከፈተ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተልዕኮውን እንደተወጣ የስም አጥፊ ቡድኖቹ አባላት ያስባሉ። እዚህ ላይ ተገቢ ወቀሳ ወይንም ሃሳብ መስጠትተገቢ ሆኖ ሳለ፣ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከፋሺሽቶች ጋር እያመሳሰሉ የሚዋሹንን ግን ለምን በእዚህ ደረጃ ስም ለማጥፋት ተነሱ? ብሎ አለመጠየቅ እና አሰላለፋቸውን አለመረዳት በራሱ የሞኝነት የመጨረሻው ደረጃ ነው።
አሁን ላይ ላይ ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ የእነማን ዕቅድ እንደሆነ በግልጥ እየታየ ነው።መቀሌ ላይ ነሐሴ 21 እና 22/2011 ዓም በሕገ መንግስት እና ፌድራላዊ አስተዳደር ስም የተደረገው ስብሰባ ለውጡን ተፃሮ ያወጣው መግለጫ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ሲደረጉ የነበሩ ዘመቻዎች ዓላማ ያለፈው ስርዓት ወደ ፊት እንዲመጣ የሚደረግ ስልታዊ ሥራ አካል እንደሆነ በትክክል አሳይቷል። ለውጡ እንደመጣ ሕዝብ እንዲፈናቀል፣የኑሮ ውድነቱ እንዲንር፣አለመረጋጋት እንዲኖር የሰሩ፣የግድያ ሙከራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ላይ የሞከሩት ሁሉ አለማዋጣቱን የተመለከቱ ኃይሎች ሙሉ ኃይላቸውን ወደ ስም ማጥፋት ካዞሩ በኃላ በመጨረሻ የመንግስትን ህልውና በምንድ መልኩ መግለጫ በማውጣት ጉባኤውን ጨርሰናል ሲሉ ተደምጠዋል።
ኢትዮጵያ በታሪክ ካገኘቻቸው ከአብዮት እና ጦርነት ውጭ በሆነ መልካም የጀመረቸው ለውጥ ፈፅሞ ሊደናቀፍ አይችልም።አሁን ብዙው ነገር ግልጥ ሆኗል።ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ የለውጡ ኃይል የጀመረውን የለውጥ ሂደት በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መቀጠል፣ሕዝቡ ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሚደረጉ የስም ማጥፋት ስራዎችን መቃወም እና ምክንያታዊ የሆኑ ጨዋ አገላለጦችን ብቻ ማበረታታት ብቻ ሳይሆን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን በመቆም የለውጡን ሂደት ለማደናቀፍ የሚጥሩትን መቃወም አለበት።ኢትዮጵያ በያዘችው የለውጥ ሂደት መቀጠል አለባት።ስትቀጥል ደግሞ ላለፈው አንድ ዓመት ከተሄድበት ሂደት ወንጀል የሰሩትን ከፅንፈኛ የኦሮሞ አክትቪስቶች እስከ ህወሓት ተፈላጊ ሙሰኞች፣ ከአድር ባይ ድርጎ ለቃሚዎች እስከ የባዕዳንን እጅ የሚማፀኑ ላይ ሁሉ የተጠያቂነት አጀንዳ በመክፈት መሆን አለበት።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱት በረጅም ጊዜ ውትወታ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በበጎ የሚያነሳ ሁሉ ለማሸማቀቅ ደጋግመው ሰፊ ዘመቻ ከፍተው ሰንብተዋል።ባስ ሲል የለውጡ አራማጆች ፎቶ ሲመለክቱ አጋንንት የመላዕክትን ስዕል ሲያይ እንደሚያንቀጠቅጠው ሁሉ የጥላቻ አይናቸው ተጎልጉሎ ሲወጣ ይታያል። አዎን! በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱ ማንነት እየቆየ እየለየ ነው።የመቀሌው ጉባኤ የድሕረ ስም ማጥፋት ዘመቻው አካል ነበር።ሕዝብ በእንዲህ አይነቱ እኩይ አካሄድ ላይ በጊዜው እርምጃ መውሰድ ካልቻለ ውጤቱ የከፋ ይሆናል።ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከለውጥ ኃይሉ ጎን ዛሬም እንቆማለን!
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
ነሐሴ 23/2011 ዓም (ኦገስት 29/2019 ዓም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ

No comments:
Post a Comment