ጉዳያችን/ Gudayachn
ሚያዝያ 29/2011 ዓም (ሜይ 7/2019 ዓም)
በዜግነት ፖለቲካ የሚያምኑ ስድስት የፖለቲካ ድርጅቶች ማለትም የአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ሰማያዊ ፓርቲ፣ኢዴፓ፣የጋምቤላ ክልል ብሔራዊ ንቅናቄ፣የቀድሞው አንድነት ፓርቲ እና መኢአድ ከስመው በውህደት አዲስ ፓርቲ እንደሚመሰርቱ እና የሜመሰረተው ፓርቲ መስራች ጉባኤውን ግንቦት 1 እና 2/2011 ዓም አዲስ አበባ ላይ እንደሚያደርግ የአስተባባሪው ግብረ ኃይል መጋቢት 19/2011 ዓም በሰጠው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።
በእዚህም መሰረት በአይነቱ እና በአደረጃጀቱ ከእዚህ በፊት በኢትዮጵያ ከተመሰረቱት ፓርቲዎች የተለየ ማለትም ከወረዳ ተነስቶ ወደላይ የሚወጣ አደረጃጀት እና ውክልና የያዘ አመሰራረት በመከተል በኢትዮጵያ ካለው 547 የምርጫ ወረዳዎች ውስጥ እስካሁን 312ቱን የሸፈነ እና ቁጥሩ እንደሚጨምር የተነገረ የወረዳ ሥራ አስፈፃሚ እና የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች ምርጫ ተደርጎ 1200 የሚደርሱ የመስራች ጉባኤው ተሰብሳቢዎች በመጪው ሐሙስ ግንቦት 1 እና 2/2011 ዓም በሚመሰረተው አዲሱ ፓርቲ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ይታደማሉ።
አቶ ናትናኤል ፈለቀ እና ሌሎች የመስራች ጉባኤው ግብረ ኃይል አስተባባሪዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ለማወቅ እንደተቻለው በአሁኑ ሐሙስ እና ዓርብ የሚደረገው መስራች ጉባኤ የሚከተሉትን ዓበይት ተግባራት እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል። እነርሱም : -
- የአዲሱን የውሑድ የፖለቲካ ፓርቲ ፕሮግራም እና ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፣
- የአዲሱን ፓርቲ ስያሜ ማውጣት እና ማፅደቅ፣
- የፓርቲውን ዓርማ መወሰን፣
- የፓርቲውን መዝሙር ማፅደቅ፣
- የፓርቲውን ረቂቅ መተዳደርያ ደንብ ማፅደቅ የሚሉት ይገኙበታል።
ኢትዮጵያ በድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment