ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ እንዲህ እንዲህ እያለ ዛሬ ላይ ደርሷል።በጎንደር ልዩ ልዩ ስፍራዎች በሕዝብ እና በሕወሓት መካከል ከፍተኛ ውግያ እየተደረገ ነው።ከሱዳን በኩል ዋስትና እስካለኝ ድረስ ምንም አይፈጠርም ብሎ ያስብ የነበረው ስርዓት ከውስጥ የተነሳው አመፅ በኃይል ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት በትትክክልም መክኗል።አመፁ እንደተጀመረ ግጭቱ በአማራ እና ትግራይ መካከል ለማስመሰል ብዙ ጥረት ያደረገውም የሕወሓት ቡድን ነበር።የወልቃይት ኮሚቴ አባላት ¨ችግሩ በአማራ እና ትግራይ አይደለም የኮሚቴ አባላት የሆነው ውስጥም ከትግራይ የምንወለድ አለን ጉዳዩ የማንነት መብት ነው¨ ብለው እየተናገሩም በሕዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር ሙከራው ቀጠለ።ሆኖም አልተሳካም።
በአሁኑ ሰዓት የጎሳ የግጭት ስሜቶች በሙሉ ያነሳሳ የነበረው አካል ተስፋ በመቁረጡ እና ህዝብም እውነቱን እየተረዳ በመጣበት ሰዓት ነው ¨በዜግነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን ግባችን ማድረግ ካልቻልን ትግላችን መና ቀረ ማለት ነው ¨ የሚል ንግግር ባለፈው ዓመት ያሰሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመላው ዓለም ከሰላሳ በላይ ከተሞች በሚደረገው የአርበኞች ግንቦት ሰባት የገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ላይ ካሉበት በኤሌክትሮኒክስ መገናኛ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ንግግር ያደርጋሉ።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአሁኑ ወቅት በፖለቲካው መድረክ ላይ ትግሉን ሳያቆሙ የተለያዩ ስልቶችን በመከተል ከቀጠሉት ጥቂት የሀገራችን አንጋፋ የፖለቲካ ሰዎች ውስጥ ናቸው።
- ሰውዬው ወደ አሲምባ በረሃ ደርግን ለመታገል ብረት ይዘው ሲሄዱ ወቅቱ የሚጠይቀው የሀገር መውደድ እንደሆነ አምነው ነው።
- ሰውዬው ሕወሓት ስልጣን ሲይዝ በሰላማዊ ትግል ሀገር ካዳንኩ እራሴን ዝቅ አድርጌ ወደ ሀገሬ ገብቼ ልግባ ብለው ውሳኔያቸውን ገልፀው ወደ ሀገር ቤት ሲመጡ እና በቅንነት የአቶ መለስን እጅ ሲጨብጡ በወቅቱ ¨ ባንዳ¨የሚል ስም እየሰጠ እንደ እሳት የሚፋጀውን በውጭ የነበረውን ፖለቲከኛ ከኢትዮጵያ ፍቅር አይበልጥም ብለው ነበር።
- ሰውዬው ከምርጫ 97 በኃላ ከሀገር ወጥተው እንደማንም ሰው ማክያቶ ፉት እያሉ ሁሉን ትተው መቀመጥ ሲችሉ ቢሸሹት የማይሸሸውን የእናት ሀገር ፍቅር ይዘው አሁንም እራሳቸውን ዝቅ አድርገው አቶ ኢሳያስ ሀገር የተገኙት ስለ ግል ጥቅም አይደለም።መተኪያ ስለሌላት ስለ ኢትዮጵያ ብለው ነው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑን ዛሬ ማጀገን ካልቻልክ ነገ ሌላ ጀግና እንዲወለድ መጠበቅ አይቻልም።ነገ ፕሮፌሰሩ የፈለጉትን መሆን ይችላሉ።በእዚች ሰዓት ግን የምናየው ጊዜያቸውን እና እውቀታቸውን ለኢትዮጵያ ጉዳይ እንደሰጡ ነው።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጪዎቹ ቅዳሜ እና እሁዶች በሰላሳ የዓለም ከተሞች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ንግግር ያደርጋሉ።ፕሮፌሰሩ ህይወታቸውን ለመስጠት መወሰናቸውን ቢነግሩንም በሕይወት ኖረው ሁላችን የምንናፍቃትን ኢትዮጵያ እንዲመለከቱ ሁል ጊዜ ምኞታችን ነው።ጀግና ማከበር ይልመድብን።
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com