ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, February 16, 2017

ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በ90 ዓመታቸው አረፉ ቀብራቸው በመጪው ሰኞ ቅድስት ስላሴ ቤ/ክርስቲያን በ9 ሰዓት ይፈፀማልእናታቸው እንግሊዛዊቷ ሲልቭያ ፓንክረስት ኢትዮጵያ በጣልያን ስትወረር በእንግሊዝ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በማቀጣጠል ተቃውመዋል።ንጉሡ በስደት በነበሩበት ወቅት አብረው ወጥተዋል ወርደዋል። በኃላም ከልጃቸው ሪቻርድ ፓንክረስት ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በኢትዮጵያ እስከ ሕይወታቸው ፍፃሜ ድረስ ኖረዋል።

ወ/ሮ ስልቭያ ፓንክረስት ዕረፍታቸውም ቀብራቸውም በኢትዮጵያ ነበር።የተቀበሩት በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው በመጪው ሰኞ የካቲት 13፣2009 ዓም ልጃቸው በሚቀበሩበት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ነበር።

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት እናት የኢትዮጵያ ወዳጅ ወ/ሮ ስልቭያ ፓንክረስ 


ሲልቭያ ፓንክረስት መቃብር ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ 

የስልቭያ ፓንክረስት ልጅ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል እንዲመሰረት ያደረጉ ስለ ኢትዮጵያ ሲፅፉ እና ሲመራመሩ የኖሩ ምሁር ናቸው።ፕሮፌሰሩ ከ1940ዎቹ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መውረድ ድረስ በኢትዮጵያ ከኖሩ በኃላ በ1970ዎቹ መጨረሻ እንደገና ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምርምራቸውን ቀጥለዋል።ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ በ90 አመታቸው ማረፋቸው እና በመጪው ሰኞ አዲስ አበባ በሚገኘው ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን የቀብራቸው ስነ ስርዓት እንደሚፈፀም ተነግሯል።

እረፍተ ነፍስ ለፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት መፅናናትን ለቤተሰቦቻቸው ይስጥልን።

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ ፕሮፌሰር አሉላ ፓንክረስ ግጥም ከእዚህ በታች ይመልከቱ።ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com