ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት፣ሪታ ፓንክረስት፣ሲልቭያ ፓንክረስት፣ ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ፣ ገጣሚ እና ደራሲ መንግስቱ ለማ (ፎቶ:-pinterest.com)
ባለፈው ሐሙስ የካቲት 9፣2009 ዓም ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ቀብር ሰኞ ታስቦ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅፅር ግቢ የሚቀብረው የቤተ ክርስቲያኒቱ እምነት ተከታይ መሆን ስለሚገባው ይሄው ጥያቄ ተነስቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በክርስትና ስማቸው ገብረ ሐና በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባል መሆናቸው መረጋገጡን ሐራ ዘተዋህዶ ድረ- ገፅ ማምሻውን ባወጣው ዘገባ ገልጧል። ፕሮፌሰሩ ካቶሊክ ናቸው የሚል ዜና ወደ ቤተ ክህነት ይዘው የሄዱት የፕሮፌሰሩ የቅርብ ወዳጅ ነኝ ያሉ ግለሰብ መረጃ ሐሰት መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ከፕሮፌሰሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደብተር ጋር ማረጋገጥ መቻላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ሐራ ዘተዋሕዶ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣውን ዘገባ ይህንን በመጫን ያንብቡ።
ከቶ አይቀርም ሞቱ
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com