ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, December 6, 2015

ሰበር ይህን ያውቁ ኖሯል? ህወሃት እንግሊዛውያንን ጠልፎ አንድ ሚልዮን ዶላር ካልተከፈለኝ አለቅም ማለቱን!

ዛሬ ንፁሃን ኢትዮጵያውያንን ''ሽብርተኛ'' እያለ የሚከሰው በአንድ ወቅት አውሮፓውያንን እየጠለፈ ገንዘብ ካልተከፈለኝ አለቅም የሚል ድርጅት ነበር።ይለናል  የሰብአዊ መብት ተመልካች የአፍሪካ ክፍል ሪፖርት  ገፅ 139 ላይ ነው የተገለፀው ''ወደው አይስቁ'' ያለው ማን ነበር? ህወሃት እንግሊዛውያንን ጠልፎ 1 ሚልዮን ዶላር ይከፈለኝ ብሎ እንደነበር እና ታጋቾቹን 8 ወራት አግቶ እንደነበር፣ በኃላም በሱዳን መንግስት አደራዳሪነት ከስምንት ወራት እንግልት በኃላ ጋዜጠኛው እና አራት የቤተሰቡ አባላት ጋር እንደተፈቱ ያውቃሉ?  ዳሩ ማን ይነግርዎታል። የያኔ ጠላፊዎች አሁን ፈራጆች ናቸው።


እንደ! ይህ እኮ ዓለም አቀፍ አሸባሪነት ነው። ለመሆኑ አሜሪካ ከማን ጋር ነው የምትሰራው? ጎበዝ! እየደጋገሙ  ''ሽብር ሽብር'' የሚሉን የተካኑበትን ነው እንዴ? ብለን እንጠይቅ እንዴ?  ከሰሞኑ በወቅቱ የነበራችሁ የህወሃት ባለስልጣናት መልስ እንደምትሰጡበት ተስፋ እናደርጋለን። ጉዳዩ ቆየት ስላለ የሚመለከታቸው ጠና ጠና ያሉትን የድርጅቱን አባላት ነው። ስምአልጠራም። 

የኤፈርትን ገንዘብ አንዱ የአመጣጥ መንገድ ባሰብን ጊዜ አለቀስን።ጉዳዩ ወጣት  አባላትን አይመለክትም።ወጣቶቹ ሲሆን ጠና ያሉትን የህወሃት አባላት ''እውነት አውሮፓውያንን እየጠለፋችሁ ገንዘብ አምጡ ትሉ ነበር እንዴ?'' ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። እኔ ግን ዛሬ ለሆነ ወረቀት መፃህፍት ሳገላብጥ አገኘሁት።አይን ደግሞ አይከለከል።እንዲህ አይነት ተራ የዝርፍያ ተግባር የተሰማራ ግለሰብ የአገር መሪ ሲሆን በምናባችሁ አስቡት።ምኑን ታስቡታላችሁ ያለፉትን 24 ዓመታት ተግባራት አስታውሱ ማለቱ ይሻላል።የብሔራዊ ባንክ ወርቅ መዳብ ሆኖ ተገኘ የሚለውን ዜና እያስታወስንም አለቀስን። 

''እነሆ ኢየሩሳሌምን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን'' እንዲል። 
ለማንኛውም ማስረጃው ይሄው

''ክፉ ቀኖች: ሰላሳ የጦርነት እና የረሃብ አመታት'' በሚል በእንግሊዝኛ በቀረበ ''የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተመልካች'' የአፍሪካ ክፍል በአውሮፓውያን አቆጣጠር 1991 ባወጣው ባለ 379 ገፅ ሪፖርት ላይ  በገፅ 139 ላይ ነው ጉዱን ያወጣው።ከስር ፅሁፉ ተለጥፏል።

''Evil Days: Thirty Years of War and Famine in Ethiopia''
 By Alexander De Waal
page 139 








ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:

የተወካዮች ምክርቤት (ፓርላማው) አሰራሩ እና ውሳኔ አሰጣጡ የ21ኛውን ክ/ዘመን የሚመጥን፣ ኢትዮጵያ የመጀመርያ ፓርላማዋን ከከፈተች ከ80 ዓመታት በላይ እንደሆናት በሚያሳይ ልክ አይደለም።

አሁን በአራት ኪሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፓርላማ ህንጻ በ1928 ዓም  =========== ጉዳያችን ========== የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በድረገጹ ላይ የኢትዮጵያ ፓርላማ ታሪክ በሚለው ርዕሱ ስር እንዲህ የ...