ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, June 25, 2014

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ለሀገሩ የሚያደርገው አስተዋፆ ታላቅ አብነት-የኢትዮ-አሜሪካ የሕክምና ዶክተሮች ቡድን በአዲስ አበባ ለአፍሪካ ሞደል የሆነ ከፍተኛ ሆስፒታል በሁለት ቢልዮን ብር ወጪ ሊገነባ ነው የመሰረት ድንጋዩ በመጪው ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ ይጣላል

ኢትዮ-አሜሪካ የሕክምና ዶክተሮች ቡድን አባላት በከፊል 

ኢትዮ-አሜሪካ የሕክምና ዶክተሮች ቡድን በአሜሪካን ሀገር በህክምና ሙያ ላይ በተሰማሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተመሰረተ ቡድን ነው። ቡድኑ በድረ-ገፁ ላይ ተልዕኮውን እና ራዕዩን አስቀምጧል።
የቡድኑ ተልኮ '' በኢትዮጵያና አካባቢዋ እንዲሁም በአፍሪካ ደረጃውን የጠበቀ፣ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሰጪዎች የተመሰከረለት እና የጤና ዕውቀት ማስመስከርያ የሆነ ሆስፒታል መገንባት ነው'' ይላል።
'' To build an economically sustainable, center of excellence hospital that will deliver internationally accredited standard of care and become the catalyst for change in how health care is delivered in the region and Africa.
ራዕዩ ደግሞ እንዲህ ይነበባል - '' እኛ ከ 200 በላይ የሆንን ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ከፍተኛ ጥራት እና ደረጃ ያለው በዕውቀት እና በምርምር ላይ የተመሰረተ የሕክምና አገልግሎት ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ለአፍሪካ እና ለመላው ዓለም ሕዝብ መስጠት ራዕያችን ነው''' ይላል።
  • ''We are more than 200 physicians of Ethiopian origin coming together to develop and deliver high quality medical care through education and research for the people of Ethiopia, Africa and beyond.''
ቡድኑ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ለሀገሩ የሚያደርገው አስተዋፆ መገልጫ የሆነውን እና  በታላቅ አብነት የሚጠቀሰውን ተግባር በመጪው ቅዳሜ ሰኔ 21/2006 ዓም በሁለት ቢልዮን ብር ለሚገነባውን ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ በመጣል ይጀምራል።
ሆስፒታሉ በዓለማችን ካሉት ምርጥ ሆስፒታሎች ተርታ የሚመደብ ሲሆን ደረጃውን ''ጆይንት ኮሚሽን ኢንተርናሽናል'' በተሰኘ የሆስፒታሎችን ደረጃ በሚያወጣ ድርጅት በሚሰጠው ሰርተፍኬት ዓለም አቀፍ ተወዳዳርነቱን የሚያስመሰክር እንደሚሆን ይጠበቃል።ሆስፒታሉ የማስተማርያ እና ከፍተኛ የሕክምና ምርምር የሚደረግበት መሆኑን እና ከ200 በላይ የሆኑትን የቡድኑ  አባላት ውስጥ የተወሰኑትን  ስፔሻሊስቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አገልግሎት እንደሚሰጡ የቡድኑ አመራር  አባል  ዶ/ር ግርማ ተፈራ አስረድተዋል።
በ 2011 እ ኤ አ በ አስራ ሁለት አባላት የተጀመረው የኢትዮ-አሜሪካ የሕክምና ዶክትሮች ቡድን ዛሬ 200 አባላትን ይዟል።
የዜናው ምንጮች -
                  የቡድኑ ድረ-ገፅ  http://ethioamericandoctors.com/
                  ቪኦኤ የአማርኛ አገልግሎት ሰኔ18/2006 ዓም ዘገባ 

ጉዳያችን 
ሰኔ 18/2006 ዓም (ጁን 25/2014)

No comments: