ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, June 18, 2014

የመካከለኛው ምስራቅ ሃይማኖታዊ እና ስልታዊ አቀማመጥን መሰረት ያደረጉ ታሪካዊ ግጭቶች ወደ አፍሪካ በተለይ ወደ አፍሪካ ቀንድ እንዳይዛመቱ ስጋቱ አይሏል።(የጉዳያችን ማስታወሻ)

የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቪግዶር ሊበርማን¨

¨እስራኤል በአፍሪካ የነበራትን  ቦታ ማስመለስ ትፈልጋለች። የ አፍሪካ መሪዎች ከፅንፈኛ እስልምና እንቅስቃሴ ጋር የሚደረገውን ትግል ይቀላቀሉን።¨ የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቪግዶር ሊበርማን
ያለፉት ሁለት ዓመታት ለመካከለኛው ምስራቅ የምጥ አመታት ነበሩ።ሶርያ ማባርያ በሌላው ጦርነት ውስጥ ተነክራለች።ኢራቅ ¨ከድጡ ወደ ማጡ¨ እንዲሉ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ነውጠኛ እንቅስቃሴ የያዙ ቡድኖች (አይ ኤስ አይ ኤስ-ISIS) ዛሬ ዋናውን የነዳጅ ማምረቻ ቦታ ይዘዋል።በጉዳዩ ላይ ኢራን ሥጋቷን ብቻ ሳይሆን የጦር ኃይሏን ከኢራቅ መንግስት ጎን ላማሰለፍ ዝግጁ መሆኗን ገልፃለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ የፀጥታ ሁኔታዎች ከጊዜ ወደጊዜ አሳሳቢነታቸው እየባሰ መምጣቱ እየተስተዋለ ነው።የሱማሊያው አልሸባብ ከመዳከም ባለፈ በተከታታይ የአፍሪካ ሕብረት ሰራዊት ዘመቻ ሊጠፋ አልቻለም።ይልቁንም በኬንያ በሚፈፅማቸው የሽብር ጥቃቶች ከ አርባ አምስት ሰዎች በላይ መሞታቸው የያዝነው ሳምንት ዜና ነበር።ሁኔታዎቹ ለጊዜው አይቀጣጠሉ እንጂ በአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ተመሳሳይ አደጋዎች አንዣበዋል።
ሱዳን የውስጥ ችግሯን ለመፍታት ጥረት ስታደርግ ብትታይም የጦር መሳርያ   ግዥዋን ግን ቀጥላበታለች።የደቡብ ሱዳን ግጭት እንደቀጠለ ነው።ኢትዮጵያን በጎሳ ፖለቲካ የሚመራው ኢህአዲግ/ወያኔ ከእስልምና ተከታዮች ጋር የገባው ውዝግብ መድረሻው ገና አልታወቀም።ኤርትራ ቆላው ክፍል አልፎ አልፎ የሚሰሙ የፅንፈኛ እስልምና አራማጆች እንቅስቃሴ በመሳርያ ኃይል የተደገፈ እንቅስቃሴ የመኖሩ ከመሰማቱ በላይ የወታደራዊ መፈንቅል እንቅስቃሴ ከተደረገ ገና አንድ ዓመት ማስቆጠሩ ነው።የእንቅስቃሴው መሪዎች በአቶ ኢሳያስ ፈላጭ ቆራጭ አመራር የተማረሩ ብቻ ሳይሆኑ የፅንፈኛ እስልምና አራማጆች እንደተገኙበት የሚገልፁ ዘገባዎች ተደምጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ እስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ልካ የአፍሪካ ሃገራትን ለመጎብኘት የተነሳችው። ጉዳዩ ከተራ ጉብኝት ጋር የተያያዘ አይመስልም።ይልቁንም ከፀጥታ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ውሎችን ማድረግዋ ጉዳዮቹን የበለጠ የማወሳሰብ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ችግር ጋር የማዛመዱ ዕድል ከፍተኛ ነው።
እስራኤል በራሷ በአፍካ ቀንድ መገኘት ከአልቃይዳ የአፍሪካን ቀንድ ለማመስ መንቀሳቀስ ጋር ተዳምሮ ጉዳዩን እሳትና ጭድ እንዳያደርገው ነው ስጋቱ። የእስራኤሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ሰሞኑን አዲስ አበባ ሲገቡ የተከተላቸው የልዑካን ቡድን አባላት ብዛት ከ50 በላይ ነበሩ።

ጉዳያችን
ሰኔ 12/2006 ዓም  (ጁን 19/2006) 

No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...