ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, June 21, 2014

የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ሁለተኛ በኖርዌይ የሶስት ቀናት ጉብኝት አደረጉ።ኖርዌይን በመጎብኘት የመጀመርያ የኮፕት ፓትርያሪክ ናቸው (የጉዳያችን ልዩ ጥንቅር -ፎቶዎች ይዘናል (Gudayachn Exclusive)



የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ሁለተኛ በኖርዌይ ከ ሰኔ 12-14/2006 ዓም ባደረጉት ጉብኝት ከፍተኛ አቀባበል በኖርዌይ መንግስት የተደረገላቸው ሲሆን ከኖርዌይ ንጉስ ሃራልድ፣ከጠቅላይ ሚንስትር ወ/ሮ አርና ሱልበርግ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብረንደ ጋር ተወያይተዋል።

የፓትርያርኩ ጉብኝት  በግብፅ ባለው ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳይ ላይ ለመወያየት የኖርዌይ ቤተክርስቲያን ባደረገችላቸው ጥሪ ምክንያት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ካሉት አብያተክርስቲያናት በርካታ ምዕመናንን ያላት የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን በብዙ ወከባ እና ፈተና ላይ መሆኗን የኖርዌይ መንግስት እና የሃይማኖት ድርጅቶች እንደሚረዱ በተወካዮቻቸው አማካይነት ለፓትርያርኩ እና ለልዑካኑ ገልፀዋል።

በአፀፋው ፓትርያርኩ በግብፅ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ማስረዳታቸው እና በተለይ አርብ ሰኔ 13/2006 ዓም በኖርዌይ ከሚገኙ የተለያዩ የክርስቲያናዊ ድርጅቶች ጋር ልዩ ውይይት አድርገዋል።በፓትርያርኩ ለውይይት የቀረበው የመውያያ አርዕስት ''በወቅታዊው የግብፅ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ሁኔታዎች ውስጥ የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የገጠሟት ተግዳሮቶች'' (''Dilemmas and challenges for the Coptic church in the current political and religious situation in Egypt'') የሚል ሲሆን ፅሁፉ የግብፅ ክርስቲያኖችን መፃኢ ፈተና እና ከዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ እና ከኖርዌይ የሚጠበቀውን ድጋፍ ያመላከተ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ፓትርያርክ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ከሁለት ዓመት በፊት ህዳር ወር ላይ በተደረገ ሲመት ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን አቡነ ሺኖዳን ተክተው የተሾሙ መሆናቸው ይታወቃል።

ከእዚህ በታች ፓትርያርክ ቴዎድሮስ ሁለተኛ በኖርዌይ ባደረጉት ጉብኝት በኦስሎ ''ዱም ሺርኬ'' ቅዳሜ ሰኔ 14/2006 ዓም ባደረጉት የፀሎተ-ቅዳሴ ስነ-ስርዓት በጉዳያችን ጡመራ የተነሱ ፎቶውዎችን ነው። 








ጉዳያችን 

ሰኔ 14/2006 ዓም 
(ጁን 21/2014)

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...