Friday, May 4, 2012

አርበኞቻችንን እናስታውስ።


                                           ሚያዝያ 27 የ ድል አደባባይ

ሚያዝያ 27  የ ኢትዮዽያ አርበኞች የፋሺሽት ኢጣልያን ያሸነፉበት ቀን። የ ኢትዮዽያ ሰንደቅ ዓላማ ዳግም የተሰቀለበት ቀን ።

የ ኢትዮዽያ ገበሬ ሚስቱን፣ልጁን፣ንብረቱን ትቶ ፋኖ ተሰማራ ብሎ ያቆያት ሃገር:- ኢትዮዽያ!

ሚያዝያ 27/1935 ዓ ም ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ሃይለስላሴ የ ኢትዮዽያን ሰንደቅ ዓላማ በ ቤተ መንግስት ከሰቀሉ በሁዋላ ለ መላው ዓለም ካስተላለፉት መልዕክት

የመልክቱ ግርድፍ ትርጉም
''አዲስ አበባ ከሚገኘው  ቤተ መንግስቴ  የ አትክልት ስፍራ ተገኝታችሁ ይህን ፊልም መቅረጻችሁ መልካም ነው :: በመላው ዓለም  ይህን የሚመለከቱ ሁሉ በ ዕምነት እና በጀግንነት አማካኝነት በ ሃያኛው ክፍለ ዘመንም ዳዊት ጎልድያን እንደመታ ይገነዘባሉ ።'' ሚያዝያ 27/1935 ዓ. ም. ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ  ሃይለስላሴ::

                                                                 
                             አርበኞቻችንን እናስታውስ


ቁርጥ ቀን ባይመጣ ሁሉም ጀግና ነበር

ቁርጥ ቀን ባይመጣ ሁሉም ጀግና ነበር፣
የ ውሎ ገድሉን ሲኖር የሚናገር።
እስኪመጣ ድረስ ቁርጥ ቀን በቶሎ፣
ፈሪም ያውቅበታል መኖር ተመሳስሎ።
ጌታቸው በቀለ
ሚያዝያ 27/2004 ዓ.ም
ኦስሎ

2 comments:

Anonymous said...

cheers all!!!! Enquan aderesachihu!!!

Anonymous said...

I am happy with full confidence approach of Haileselassie I. Africa has missed such courage full leader.God bless Ethiopia

በግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ዛሬም ከምንጊዜውም በላይ የቅዱስ ሲኖዶስን የአፈጻጸም ጥብቅ ክትትል ትፈልጋለች።በሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን ችግር ላይ ናቸው።

በጥንታውቷ ግሪክ ዋና ከተማ ከአቴንስ ወጣ ብሎ  ከስድስት ሺህ ካሬ በላይ ስፋት ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም የተገዛው ገዳም ============= ጉዳያችን ልዩ ሪፖርት ============= ኢት...