Monday, January 11, 2021

ለሁለት ወራት የሚቆይ ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያ የሆኑትን መልካም ነገሮች ሁሉ ለቀሪው ዓለም የማጉላት (Rising Ethiopia) የዲጂታል ዘመቻ ተጀምሯል።ኢትዮጵያውያን በያሉበት መተባበር አለባቸው።



ከስር የዘመቻው ትውተር፣ዩቱብ እና ፌስ ቡክ ሊንኮች እንዲሁም  የሦስት ወራት ፕሮግራም ያገኛሉ።
ማሳሰቢያ - ይህ ዜና ተጨማሪ መረጃዎች (updates) አሁን ተካተውበታል።

በእንግሊዝ ሀገር ነዋሪ በሆኑት ዶ/ር በላቸው ጨከነ ተስፋ በተባሉ ኢትዮጵያዊ ሃሳብ አፍላቂነት እና አስተባባሪነት ፣በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ባሕል እና ቱሪዝም ዕውቅና የተጀመረው የኢትዮጵያን ስም ለቀረው ዓለም የማጉላት (Rising Ethiopia) ዘመቻ የተጀመረው ባለፈው እኤአ ዴሴምበር 30 ሲሆን እስከ መጪው እስከ የካቲት 21/2021 ዓም እኤአ የሚቆይ ዘመቻ ነው።በዘመቻው የዌብነር መክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ክብርት / ጽዮን ተክሉ በኢትዮጵያ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር  የዲያስፖራ እና ኢኮኖሚ ዲፒሎማሲ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ክቡር  አምባሳደር ተፊሪ መለሰ በዩኬ እና አይርላንድ  የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር፣ክብሩ አቶ ስለሺ ግርማ የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስክያጅ እና የኢትዮጵያ ባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ፣መቀመጫቸውን በአፍሪካ እና እስያ ያደረጉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች፣የቱሪዝም እና አስጎብኚ ድርጅት ባለቤቶች እና ሌሎች ከ100 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን በእዚሁ መክፈቻ መርሃግብር ላይ የመርሃግብሩ ሃሳብ አመንጪ እና አስተባባሪ ዶ/ር በላቸው ጨከነ ተስፋ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እምቅ የሆነ  የቱሪዝም መዳረሻ፣ የኢንቨስትመንት አማርጫ፣ የተማረ የሰው ሃይል ሀብት በሀገረ  ውስጥ እና 3.5 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያው በመላው ዓለም ያላት ሀገር መሆኗን አብራርተዋል።

ዶ/ር በላቸው ጨከነ በእዚሁ ንግግራቸው በተጨማሪም የዘመቻው ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ የሚገኘውን  ይህን ሀብት በውጪ የሚገኘውን ኢትዮጵያው እና ትውለድ ኢትይጵያዊ በመጠቀም ለዓለም ለማሳውቅ እና በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እደገት ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ያለመ መሆኑንና ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ የንግድ ድርጅቶችን በየአካባቢያቸው  በማስተዋወቅ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አቅማቸውን ማጠናከረም ዘመቻው አካል መሆኑን አብራርተዋል።በመቀጠልም ዶ/ር በላቸው ኢትዮያን የማጉላት ዘመቻው አራት ዋና ዋና ክፍሎችን የያዘ መሆኑን ገልጠዋል።እነርሱም -

በመጀመሪያው ክፍል ማለትም ከታህሳስ 21(Dec 30) - ጥር 14(Jan 24)  እምቅ የኢትዮጵያን የቱሪዝም  መዳረሻነት እና ድንቅ የሆነውን ባህላችን  የምናስተዋውቅበት ጊዜ ሲሆን  በእነዚህ ሶስት ሳምንታት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቦታዎች፣ መንፈሳዊ በዓላት፣ ወንዞች እና ሐይቆች፣ ተራሮች፣ የዱር እንሰሳት፣ ሙዚየሞች፣ ኪነ ጥበባችን፣ አለባበሳችን እና አመጋገባችንን ለዓለም በማሕበራዊ ሚድያዎች በሰፈው የምናስተዋውቅበት ይሆናል በእነዚህ ሳምንታት ኢትዮጵያዊያን የባህል ልብሳቸውን እንደአመቺነቱ በሥራ ቦታቸው ለአንድ ቀን በመልበስ እና ፎቶአቸውን በማጋራት፣   ትናንሽ ስጦታዎችን ለሌው ማህብረሰብ በመሰጠት ኢትዮጵያን በቀላሉ የሚያስተዋውቁበት ነው። በዚህ ሳምንት የኢትዮጵያ አየር መንገድም በሰፊው ይተዋወቃል። ኢትዮጵያ የጎብኚዎች አማርጭ እንድትሆነ በሰፈው ይሰራል።


በሁለተኛ  ክፍል  ከጥር 15 (25 Jan) - ጥር 22 (31 Jan) ድረስ  ከኢትዮጵያ ውጪ በየሀገሩ ያሉ የንግድ ድርጅቶችን በየአካባባያቸው ባሉ ኢትዮጵያዊያን የሚተዋወቁበት ሳምንት ነው ይሄውም ኢትዮጵያዊን በዓለም አቀፍ ደረጃ በያሉበት ብቁ እና ተወዳዳሪ ድርጅቶች እንዲኖራቸው ያግዛል  


የኢትዮጵያዊያን ተወዳዳሪ መሆን ወደ ሀገር ቤትም ኢንቨስት ለማደረግ እና ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ ለመላክ (Export) ትልቅ አቅም ይፈጥራል።  በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያዊያን በየአሉበት ሀገር የሚያውቃቸውን  የኢትዮጵያውን የሒሳብ አማካሪዎች፣ ሱቆች፣ የሕግ ባለሞያዎች፤ ምግብ ቤቶች፣  የኢንፎርሚሸን ቴክኖሎጂ ተቋማት፣ ኮሌጆች፣ የመኪና መሸጫዎች፣ የሕክምና ተቅዋማት  አድራሻ እና ስለአገልግሎታቸው  በማኅበራዊ ሚድያ ይተዋወቃል።


ሶስተኛው ክፍል ከጥር 23 (Feb 1 ) - ይካቲት 7 (Feb 14) የኢትዮጵያ እንቨስትመንት ሳምንት ነው። በዚህ ሳምንት የኢትዮጵያን እምቅ የእንቨስትመንት አቅም በኢንዱስትሪው፣ በእርሻ በኃይል አቅርቦት፣ በማዕድን ፍለጋ ዙርያ የሚተዋውቅበት ነው። በኤምባሲዎች በኩል ውይይቶችን፣ በኢንቨስትመንት ቢሮ በኩል ደግሞ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚያሳዩ ዶክምነትሪዎች ለሌሎች እንዲጋሩ ይደረጋል በኢትዮጵያም እስካሁን ኢንቨስት ያደርጉ በጎ ልምዳቸውን እንዲያጋሩ ይደረጋል። የታወቁ ኢትዮጵያዊያን  የኢንቨስት አማራጮቻችንን እንዲያስተዋውቁ ይሆናል።


የመጨረሻው እና አራተኛው ክፍል ከየካቲት 8 (Feb 15) - የካቲት 14 (Feb 21) የመስጠት ሳምንት (Giving weeks) ነው - በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያውያን በእያሉበት በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ መልካም ፕሮጀክቶች ማለትም  ሕዳሴ ግድብ፣ ኮቪድን ለመከላከል፣ ለበጎ አድራጊ ድርጅቶች  እና ለሌላም ፕሮጀችክቶች የገንዘብ ደጋፍ የሚያደርጉበት እና ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ መልካም ግንኙነቶችን የሚፈጥሩበት ሳምንት እንደሚሆን ዶ/ር በላቸው አብራርተዋል።


የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት የውጭ ሚድያዎች ሳይቀሩ በተረባረቡበት በእዚህ ጊዜ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይህንን ዘመቻ በትዊተር፣በፌስ ቡክ፣ዩቱብ እና ሌሎችም መንገዶች ሁሉ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል። 

ከእዚህ በታች የዘመቻው ትውተር፣ዩቱብ፣ፌስ ቡክ ሊንኮች እና የሦስት ወሮች ፕሮግራም ያግኙ።

የትውተር ሊንክ = https://twitter.com/RisingEthiopia  

የፌስ ቡክ ሊንክ= https://www.facebook.com/RisingEthiopia1/


የዘመቻው የሦስት ወሮች ፕሮግራም 

============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Sunday, January 10, 2021

የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የስድስት ዓመት ስልታዊ (ስትራቴጂ) ዕቅድ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት አቀረበች


በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ ቤ/ክርስቲያን የሰሜን አውሮፓ (ስካንዲንቭያን እና አካባቢው) ሀገረ ስብከት  የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የስድስት ዓመት ስልታዊ (ስትራቴጂ) ዕቅድ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የኢጣልያን እና አካባቢው  ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ የበላይ ጠባቂ  በተገኙበት አቀረበች።ላለፉት ስድስት ወራት ሰባት የኮሚቴ አባላት ያሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ ስልታዊ ዕቅድ አዘጋጅ ኮሚቴ በስልታዊ ዕቅዱ ዝግጅት ላይ ሲሰራ የነበረ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍሎች ጋር ውይይት አድርጎ ሃሳብ ከተቀበለ በኃላ፣ዛሬ ጥር 2፣2013 ዓም ደግሞ በቀጥታ የዩቱብ ስርጭት ለአጥቢያ ቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን በስልታዊ ዕቅዱ ዙርያ ማብራርያ ሰጥቷል። 

በዛሬው የስልታዊ ዕቅድ ዙርያ ማብራርያ ያቀረቡት የአዘጋጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ዳዊት ሻወል አስፈላጊነቱን ሲያብራሩ በቀዳሚነት ያስቀመጡት የቤተ ክርስቲያንን ግቦች እና ርዕይ ለማሳካት መሰረት የሚሆን ሰነድ መኖሩ አስፈላጊ በመሆኑ መሆኑን የገለጡ ሲሆን በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኒቱ  ለምታቅዳቸው ዕቅዶች እና ተግባራት ፍኖተ ካርታ እንዲኖራት እንደሚያደርግ አብራርተዋል።ዶ/ር ዳዊት በመቀጠል የስልታዊ እቅድ ዝግጅቱ የመረጃ ምንጮቹ የተለያዩ ዶክመንቶችን ማለትም የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓመታዊ ዕቅዶች እና ሪፖርቶች ከመገምገሙም በላይ በውጭያዊ ተፅኖ ዙርያ የኖርዌይ መንግስት የፖሊሲ ዶክመንቶችን በመመርመር በግብዓትነት መጠቀሙን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል የአዘጋጅ ኮሚቴው ጸሃፊ ዶ/ር ታጠቅ ፍቃዱ የስልታዊ እቅዱ ዝግጅት  በአገልግሎት ላይ ካሉ የተለያዩ ንዑስ የአገልግሎት ክፍሎች እና ምዕመናን በተሰበሰበ መጠይቅ መሰረት አስፈላጊው ግብዓት መሰብሰቡን፣በአጥብያው የጥንካሬ፣ድክመት፣ዕድል እና ስጋት ትንተና መካሄዱን፣የስልታዊ ዕቅዱ ወሳኝ ጉዳዮች እና በስራቸው ያሉትን ዓላማዎች ላይ በዝርዝር አብራርተዋል።

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ኖርዌይ ለተወለዱ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች የአብነት ትምህርት ሲያስተምሩ  
(ኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ)
ይህ ፎቶ ከኮሮና ወረርሽኝ በፊት የተነሳ ሲሆን አሁንም አገልግሎቱ በቪድዮ መገናኛ ቀጥሏል


በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የኢጣልያን እና አካባቢው  ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ የበላይ ጠባቂ በመካነ ቅዱሳን የኦስሎ  ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለመጪዎቹ ስድስት ዓመታት ማለትም ከ2013 ዓም እስከ 2018 ዓም የሚተገበረው ስልታዊ ዕቅድ ከያዝነው አዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት  2021 ዓም ጀምሮ ቤተክርስቲያኒቱ ሥራ ላይ ከምታውለው ዕቅድ ጋር ተግባራዊነቱ እንደሚጀምር ከገለጡ በኃላ በእዚህ ዓይነቱ አሰራር ቤተክርስቲያን ካልተራመደች በሌሎች እየተቀደመች የመሄድ ዕጣ ስለሚገጥማት  ምዕመናን ለስልታዊ ዕቅዱ መሳካት በአገልግሎት በንቃት መሳተፍ እንደሚገባቸው አባታዊ ምክር እና ማሳሰቢያ ሰጥተው መርሃግብሩ ተፈፅሟል።

ይህ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ስልታዊ ዕቅድ ለቤተ ክርስቲያን መልካም አርአያነት ያለው እና ሁሉም አጥብያዎች እና ሀገረ ስብከቶች ሊከተሉት የሚገባ ውጤታማ የአሰራር መንገድ ነው።የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር አስተባባሪነት እና በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የቅርብ ክትትል፣በዓመት ሁለት ጊዜ ማለትም በእየስድስት ወሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አጠቃላይ የአገልግሎት ክፍሎች ሪፖርት ለምእመናን የምታቀርብ እና ሃሳብ የምትቀበል ስትሆን ዓመታዊ ዕቅዶችም በመጀመርያ በአገልግሎት ንዑስ ክፍሎች ደረጃ እንዲታቀድ አድርጋ እና ተወያይታ ለጠቅላላ ምዕመናኑ በማቅረብ በሥርዓት በማስተቸት፣ሃሳብ በመቀበል እና በሃሳቦቹ መሰረት ማሻሻያ በማድረግ ሥራ ላይ የምታውል አጥብያ ቤተ ክርስቲያን ነች።በእዚህም መሰረት በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከማዕከላዊ የኦስሎ ከተማ በቅርብ እርቀት የሚገኝ የራሷ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን መግዛት፣በአሁኑ ጊዜ በአገልግሎት ላይ ያሉ በኖርዌይ ተወልደው ያደጉ 12 ዲያቆናትን ያፈራች ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው ታዳጊ ሕፃናት የአብነት ትምህርት በመስጠት ላይ ትገኛለች።
===========================
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Friday, January 8, 2021

ትናንት የተለቀቀው የኢቢኤስ ጋዜጠኛ ይድነቃቸዉ ብርሀኑ "ሲያስባት" የተሰኘው ስለ ኢትዮጵያ ያዜመው አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ 

ምንጭ - ኢቢኤስ ቲቪ (EBS TV)

=====================================
ማስታወቂያ
=======
የላኩትን ካርድ እጥፍ ሆኖ ለተቀባይ ቤተሰብ ይደርሰዋል!
----------------
ሀገር ቤት ለወዳጅ፣ዘመድ፣ጓደኛ የሞባይል ካርዳቸውን ሲሞሉ የሞሉት ገንዘብ 100% እጥፍ ሆኖ ለላኩለት ሰው ይደርሰዋል::
ዕድሉ እስከ ጃንዋሪ 9 ብቻ የሚቆይ ነው::ይፍጠኑ!
==========
አገልግሎቱን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ -

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...