Tuesday, December 15, 2015

የህወሃት እና የሱዳን ግንኙነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ያለመ ነው። ''የአገሪቱ በጀት 100% ለመከላከያ ቢውልም አይበቃንም'' አልበሽር ''ሱዳን 70% በጀት ለመከላከያ እና ፀጥታ ታውላለች'' በሱዳን የእንግሊዝ አምባሳደር አሮን (ጉዳያችን ዜና)

Photo :-Sudan Tribune


ከትናንት በስቲያ እሁድ ታህሳስ 3/2008 ዓም  በሱዳን አየር ኃይል ማዘዣ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት አልበሽር ሱዳን ወደ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ መሸጋገር አለባት ብለዋል።ከእዚህ በተጨማሪም እጅግ በፈጣን ሁኔታ የሱዳንን ደህንነት ሊያስከብር የሚችል የአየር ኃይል መገንባት አለብን ብለዋል።የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አገራቸው ለመከላከያ የምታወጣው በጀት በዝቷል የሚሉ ተቺዎቻቸውን በቁጣ ተናግረዋል።በመቀጠልም ''በዙርያችን ያሉ ፀጥታቸው የተናጋ አገሮችን ተመልከቱ። የአገሪቱ በጀት 100% ለመከላከያ ቢውልም አይበቃንም።የእራሳችን የጦር መሳርያ ፋብሪካ ያስፈልገናል....እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ትልቅ አቅም ያለው የአየር ኃይል መገንባት አለብን'' ብለዋል ፕሬዝዳንት አልበሽር።በሌላ በኩል በሱዳን የእንግሊዝ አምባሳደር አሮን ''አሲያስ'' ለተሰኘ ጋዜጣ ሲናገሩ ''የሱዳንን ዕዳ መቀነስ ፈፅሞ አይታሰብም።ምክንያቱም እስከ 70% በጀት ለመከላከያ እና ለፀጥታ ጉዳይ እንጂ ለሌሎች የልማት ዘርፎች እንደ ትምህርት፣ጤና ለመሳሰሉት አታወጣም።'' ብለዋል።

ፕሬዝዳንት አልበሽር ባለፈው ሳምንት ጋምቤላ ኢህአዴግ/ህወሃት ''የብሔር ብሔረሰቦች በዓል'' የብሔር ብሔረሰቦች እስር ቤት ባደረጋት አገር  በከፍተኛ ደረጃ የአገሪቱን ገንዘብ በሚያባክንበት ዝግጅት ላይ ተገኝተው ምሽቱን አዲስ አበባ መመለሳቸው እና ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸውን የሱዳኑ ''ሱዳን ትሪቡን'' መዘገቡ ይታወሳል።በአሁኑ ወቅት ህወሃት እና የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ በሚሰጥ እና ሕዝብን፣አገርንና ታሪክን በሚያዋርድ መልኩ በኢትዮጵያ ላይ በጥምር ሴራ እየሸረቡ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።ህወሃት የኢትዮጵያ ህዝብን አንድነት በሚያናጋ መልኩ ጎሳ ከጎሳ የማጣላት እና ከውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያን የማዳከም ሥራ እየሰራ ለመሆኑን ብዙ እማኞችን መጥቀስ ይቻላል።በአገሪቱ ላይ የታወጀው የጎሳ ፌድራሊዝም ለ25 ዓመታት ያክል  ኢትዮጵያን ሰላም የነሳ መሆኑ እየታወቀ እና ውጤቱም በኦሮምያ እና በሌሎች ቦታዎች የበለጠ ፀጥታ የነሳ መሆኑ እየታየ ለችግሩ የበለጠ ''ቤንዚን የማርከፍከፍ'' ሥራ አሁንም በህወሃት እየተፈፀመ ነው።በሰሜን ጎንደር የ''አማራ እና የቅማንት'' ሕዝብ በሚል ሕዝቡን የመከፋፈል 'መንግስታዊ የዘር ፍጅት' እንዲፈፀም መደረጉን እና እስካሁን ከአንድ መቶ በላይ  ሕዝብ ማለቁን ኢሳት ራድዮ በታህሳስ 4/2008 ዓም ከአካባቢው ያነጋገራቸውን ነዋሪዎች ጠቅሶ ገልጧል። 


የእዚህ የ''አማራ እና የቅማንት'' ሕዝብ በሚል የመከፋፈል ሥራ ላይ የሱዳን የሞራልም ሆነ የገንዘብ ድጋፍ ከወያኔ ጋር ሊኖርበት እንደሚችል የብዙዎች ጥርጣሬ ነው።ሱዳን ሰፊ የሆነውን የኢትዮጵያ ለም መሬት እና ወንዞች ወደ ግዛቷ ለማካለለ ከህወሃት ጋር መስማማቷ እና ሰሞኑን ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል ሲገለጥ ነው የሰነበተው። ዛሬ ታህሳስ 5/2008 ዓም በዋሽንግተን ኢትዮጵያውያን በሱዳን ኢምባሲ በር ላይ የድንበር ውሉን በመቃወም ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ ይታወቃል።


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com 
ታህሳስ 4/2008 ዓም (December 15/2015)

Source:- Sudan Tribune December 13/2015

Monday, December 14, 2015

ኢትዮጵያውያን በሙሉ ኢትዮጵያውያንን አትግደሉ ብለው መቃወም አለባቸው! በኢትዮጵያውያን የተነሳው አመፅ መነሻ ምክንያቶች ምን ምን ናቸው? መፍትሄውንስ ከምን አንፃር መመልከት ይገባል? (የጉዳያችን ማስታወሻ)


በአገራችን ኢትዮጵያ ሰሞኑ በኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የተነሳው አመፅ ችግሩ ምንድነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።የችግሩን ምንጭ አንዳንዶች በእራሳቸው የግንዛቤ ልኬት እንደፈለጋቸው ሊመሩት ይፈልጋሉ።የግለሰብ  እና የአንድ ቡድን የግንዛቤ ልኬት እና የሕዝብ ልኬት የተለያዩ ናቸው።ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው አመፅ በአሁኑ ሰዓት ችግርን በውይይት እና በተጠያቂነት የመፍታት ባህል የሌለው ስርዓት ሰራዊቱን በሙሉ በኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን መንደር አሰማርቶ በመግደል ችግሩን ለመፍታት ይሞክራል።በዛሬው እለት ብቻ ከ25 ኢትዮጵያውያን በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል።ይህ ቁጥር ከሰሞኑ በእጅጉ ሊጨምር ይችላል።ከእዚህ የከፋ ችግር ሳይፈፀም ኢትዮጵያውያን በሙሉ ኢትዮጵያውያንን አትግደሉ ብለው መቃወም አለባቸው።ይህ በእንዲህ እያለ ግን በኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የተነሳው አመፅ መነሻ ምክንያቶች ምን ምን ናቸው?  መፍትሄውንስ ከምን አንፃር መመልከት ይገባል? 

አሁን የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የተነሳው አመፅ የችግሩ ዋና መነሻ:-

1/ የስርዓቱ ዘራፊ ባለስልጣናት ስግብግብነት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ የመሬት ዝርፍያው ቅጥ በማጣቱ እና በእያንዳንዱ ገበሬ ህልውና ላይ በመምጣቱ፣
2/ ስርዓቱ 24 ዓመታት ሲያራግብ የነበረው የጎሳ ፖለቲካ መልሶ እራሱንም የሚያገለው እና የሚገፋውን የባሰ የጎሳ የፖለቲካ ጥያቄ ከሀብት (resource) ጥያቄ ጋር አብሮ ጠንክሮ በመምጣቱ ስርዓቱ እና ስርዓቱ ደግሞ በእርጋት የመፍታት ባህሪ ስለሌለው  በኃይል ለመፍታት መሞከሩ፣
3/ የነፃ ሚድያ መረጃ ስለታፈነ ቀድመው የችግሩን መኖር ደረጃ በደረጃ የሚገልጡ እና ህዝቡ ውስጥ የሚንተከተከውን ስሜት ለሁሉም አካል የሚገልጡ ጋዜጠኞች እንዳይናገሩ እና እንዳይፅፉ መታሰራቸው እና መሰደዳቸው እና
4/  የክልሉ አስተዳዳሪ የነበረው ኦህዴድ በእራሱ የዝርፊያው ተዋናይ ስለነበር ከስርዓቱ መሪዎች ጋር የጥቅም ግጭት መግባቱ የሚሉት ናቸው።

የችግሩ መፍትሄ:-

1/ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች መኖራቸውን ማመን፣

2/ ችግሩን በጊዚያዊነት አለባብሶ ለማለፍ አለመሞከር፣

3/ ይህ የተነሳው ችግር ለጊዜው ይዞት የተነሳው የአዲስ አበባ ፕላን ጉዳይ ይሁን እንጂ በክልሉ የሚነሱ ጥያቄዎች በእየዘመኑ ከአገሪቱ የፖለቲካ ችግሮች ጋር የሚያያዙ ጉዳዮች ከመኖራቸው በላይ ይብሱን ባለፉት 24 ዓመታት  ውስጥ በተለየ መልኩ የክልሉ ተወላጆች በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ከአገሪቱ የስልጣን እርከኖች መራቃቸውን መገንዘብ።
ለምሳሌ ላለፉት 100 ዓመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ ብንመለከት የጦር ኃይሉን ከአፄ ምንሊክ ዘመን ጀምሮ በፍፁም ኢትዮጵያዊነት  በበላይነት ይመራ የነበረው የክልሉ ሕዝብ ምን ያክል ባለፉት 24 ዓመታት እንደተገለለ እና በስርዓቱ ከፍተኛ ንቀት ይፈፀም እንደነበር መገንዘብ።ይህ ለኢትዮጵያ ትልቅ ‘ስብራት’ ነው።በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ ዘመንም ሆነ በደርግ ዘመን በጦር ኃይሉ እና ፖሊስ ሰራዊት ከከፍተኛ መኮንኖች እስከ ታች ባሉ ባለማእረጎች የክልሉ ተወላጆች አገራቸውን አገልግለዋል። ይህ ስርዓት በመንገድ ላይ ለማኝ እንዲሆኑ ያደረጋቸው የቀድሞ ሰራዊት አባላት ውስጥ በርካቶች የኦሮምኛ ተናጋሪ እንደነበሩ ብዙዎቻችን እንረሳለን።

4/ በየትኛውም አቅጣጫ በስርዓቱ የውስጥ ሴራ የሚነሱ የክልሉን ሕዝብ ከሌላው ጋር ለማጋጨት የሚሞከሩ ማናቸውንም ሙከራዎች ማክሸፍ። ለምሳሌ የሱማሌ ክልልን በኦሮሞ ላይ እንዲዘምት፣የአማርኛ ተናጋሪዎችን ከኦሮምኛ ተናጋሪዎች ጋር ለማጋጨት የሚደረገው ሙከራ ነቅቶ መጠበቅ እና እንዲሁም የትግርኛ ተናጋሪውን በሙሉ በጠላትነት የሚመለከቱ የማኅበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻዎች አሁንም የስርዓቱ አቀንቃኞች ሥራ መሆኑን ጠንቅቆ መረዳት፣እንዲሁም  በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በግንፍልተኞች አንዱን በተለየ መልክ ለማጥቃት የሚደረጉ ሙከራዎች ወይንም ድርጊቶችን  የአጠቃላይ ሕዝብ ሥራ አድርጎ ከማቅረብ መጠንቀቅ እና


5/ ይህንን ከፍተኛ የሕዝብ መነሳሳትን ከመላው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጥያቄዎች ጋር ማስተሳሰር እና ከፅንፈኛ የእስልምና አደጋዎች መታደግ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
ታኅሳስ 4/2008 ዓም (December 14/2015)

የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።

======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡  የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ  ወደ  ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...