Saturday, January 26, 2013

ጀግንነት ፈፅሞ አለመሸነፍ አይደለም። ተሸንፎ መነሳት ነው-ለ ብሔራዊ ቡድናችን ፣ለ አሰልጣኞች እና ለደጋፊዎች ሁሉ

ፎቶ ከ ድሬ ዩቱብ (ለ ናይጀርያው ግጥምያ ዝግጅት ላይ)
 
 
ትናንት አርብ ጥር 17/ 2005 ዓም ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ የተላለፈው ኢትዮጵያ እና ቡኪናፋሶ እግር ኳስ ውድድር ኳስን መሰረታዊ ባህሪ በያዘ መልኩ ማለትም ማሸነፍ ወይንም መሸነፍ አንዱን መርጦ አብቅቷል። አዎን ኢትዮጵያ በኩል አራት ጎሎች ተቆጥረዋል። ጫወታው እንዳበቃ በመጀመርያ በጣም ተናደድኩ ትንሽ ቆይቼ ነገሩ አለመሞቱ ግን ቡድኑ ሞራል ምን ያህል ይሆን? የሚለው ብቻ አሳሰበኝ።ዛሬ ቅዳሜ ጫወታውን ደግሜ አየሁት።በ እውነት ትናንት ያልታዩኝ የተጫዋቾቻችን ድንቅ ጥበብ ታየኝ።ሰው አንድን ነገር ለመመልከት የረጋ ልቦና ይሻል የሚባለው ልክ ነው።ዛሬ ከስሜት ውጭ ሆኘ ስመከት ቡድናችንን የሚያስደንቁ ጥበቦቹ ታዩኝ።እናም የሚከበር ቡድን ግን አኛ ተመልካቾች ልናከብረው እና ልናደንቀው የሚገባ ነው ብዬ አሰብኩ።
አንድ ወቅት አስራዎች አመታት በፊት ግብፅ ውስጥ ብሔራዊ ቡድናችን (ለማጣርያ ይመስለኛል)ሲጫወት ቡድኑን ለማዋከብ የነበረው ተመልካች ዘዴ በጣም መጮህ እና እዚህ በፊት ሰማንያ አና ዘጠና ሕዝብ የተሞላ ስታድዮም ውስጥ ተጫውቶ የማያውቀውን ተጫዋች ማዋከብ ነበር። በወቅቱ ቡድናችን አለም አቀፍ ጫወታ ተሞክሮ ስሌለው እና ሰላሳ ሕዝብ የሚይዝ አዲስ አበባውን ስታድዮም ብቻ ስለሚያውቅ ትልቅ ችግር ፈጥሮ ነበር። አሁን አቅም ተፈጥሮ ጫወታው ቴክኒክ ሁሉ ጥሮ መስመር ላይ ነው ያለው። የተሞከሩት ጎል ሙከራዎች ዕድል ጉዳይ እንጂ ምርጥ ተጫዋቾች እንዳሉን ለመረዳት አይናችንን የሚከፍቱ ናቸው።አሁን የቀረን አንዲት ነገር ነች። ጀግንነት፣እራስን ማወቅ፣ካለምንም ጉራ ታላቅ ተጫዋቾች እንዳሉን ማወቅ፣ይህንንም ለቡድኑ መንገር።ሽንፈት የሚጀምረው እራስን ዝቅ አድርጎ ማየት ሲጀመር ነው።ቡክናፋሶች ጎል ዕድል ቢያገኙም፣በ ጫወታ ቢገዳደሩንም፣ አሁንም የማሸነፍ እድላችን እጃችን ውስጥ መሆኗን ማወቅ አለብን። መሸነፍ፣ፈተና፣ተስፋ መቁረጥ አንዳንዴ ተደጋግመው የተጫኑ የሚመስሉበት ጊዜ አለ። እዚህ ላይ ነው ጀግና የሚያስፈልገው። ''ቁርጥ ቀን ባይመጣ ሁሉም ጀግና ነበር'' የሚባለው እዚህ ቀን ነው። ቡድናችን አሰልጣኞቻችን ሁሉ በአንድ መንፈስ ቀጣዩን ጫወታ እንደሚያሸንፉ ሙሉ ልብ እራሳቸውን ከማወቅ እና ከማክበር ጋር ይጫወቱ ይመኑ ታምር ይሰራሉ።

እዚህ ላይ በቡድናችን የሞራል መጠበቅ ላይ እክል ፈጥረዋል የተባሉ ወደፊት ጥብቅ ምርመራ የሚፈልጉ እና በቀላሉ የማይታዩ ጉዳዮች እንደነበሩ ይወራሉ። ይህንን በተለይ አስልጣኝ ሰውነትም ሆኑ ምክትላቸው ተመሳሳይ ስህተት እንዳይሰሩ ለ ፖለቲካው አካላት ም ሆነ ለሕዝቡ በድፍረት እንዲነግሩልን እንጠብቃለን። በ እዚህ ዘመን ''የተሰወረ የማይታይ ያልታወቅ የማይገልጥ'' የለምና። ለሁሉም ግን አሁን መደረግ ያለበት  ቢያንስ ቀጣዩ ጫወታዎች እስከሚጠናቀቁ በ ትዕግስት የ ቡድኑንም ሆነ የደጋፊውን ህብረት እንዲጠበቅ ማድረግ ይመስለኛል።

ጀግንነት ፈፅሞ አለመሸነፍ አይደለም። ተሸንፎ መነሳት ነው። ጀግናን ጀግና የሚያሰኘው ፈፅሞ የማይሸነፍ ምትሃታዊ ፍጥረት ስለሆነ አይደለም ዕድል ወይንም ትንሽ ስህተት አልያም ችላ ብሎት ጀግና የመጀመርያ ሽንፈት ይሸነፋል። ሁለተኛ እና ሶስተኛ ላይ ግን የሚያስደነግጥ ብቻ ሳይሆን የሚያርበደብድ ይሆናል።የዓለማችን ጀግኖች ተሸነፉ ሲባሉ እንደገና ተነስተው ስለሚያሸንፉ ያለፈውን ሽንፈታቸው ከቶ ማን ሊያስበው ይቻላል? እንግሊዝን እስኪ አለም ዋንጫ ላይ የሚደርስባትን እንመልከት።እንዲያ ድንቅ ክለቦች ያላት ሀገር በዓለም ዋንጫ ላይ ግማሽ መድረስ ሲያቅታት እንግሊዝ ሕዝብ እና መንግስት ሰቀቀን የማይሆን ይመስለናል ? ግን እንግሊዞች ኳስ ስለማይችሉ ነው የተሸነፉት? አይደለም። ኳስ እንዲህ ስለሆነች ነው። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጫወታ ዛሬ አለፍ አለፍ እያልኩ ቡክናፋሶ ጋር ያደረገውን ጫወታ ስመለከት እጅግ ድንቅ ተጫዋቾች እንዳሉን ግን እኛ ልናከብራቸው፣ልናደንቃቸው፣ ታላቅ ችሎታ እንዳላቸው አንዳንድ ቴክኒካዊ ስራዎችን እያስተካከሉ እንዲሄዱ እራሳቸውን ዝቅ እንዳያደርጉ መንገር ባለዑያዎች ብቻ እንደሚገባ አመንኩ። ይህ ደግሞ ለሽንገላ ሳይሆን ቀድሞ የነበረው ''እኛ ኳስ አይሆንልንም'' የሚባልበት ጊዜ ላይ ላለመሆናችን ችሎታቸውን ልዩ አቀራረብ ያሳዩን ተጫዋቾች ምስክር ናቸው። ዛሬ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ደረጃዋ አለም አይደለም እኛ ኢትዮጵያውያንም ያስደነቀን ጉዳይ ነው። ወደ ኋላ ፈፅሞ መመለስ የለም!

በመጪው ማክሰኞ ናይጄርያ ጋር በሚኖረው ውድድር ተአምር የመስራት ብቃቱም ሆነ አቅሙ አላችሁ።በ አንድ በኩል ናይጀርያ በትናንትናው ቡክናፋሶ ጋር በተደረገው ጫወታ ቡድናችንን ዝቅ አድርጎ የማየት ሁኔታ ሊኖር እንድሚችል ይገመታል።ይህ ጥሩ ዕድል ነው።

እርግጥም ቡክናፋሶ ጋር የሆነ አምላክ እኛ ጋርም አለ። ናይጄርያ ጋር ያለ አምላክ እኛ ጋርም አለ። ቀጣዩን ናይጄርያ ጋርም ሆነ ቀጥለው በሚከፈቱት ዕድሎች ቡድናችን እንዲያሸንፍ እኛ ተመልካቾች የምናደርገው ሁለት ነገር ነው። አንድ ስታድዮም ተገኝቶ መደገፍ ሁለተኛው እና ዋናው ማንም ችላ ሊለው ወይንም ሊረሳው የማይገባው ከልብ የሆነ ቢያንስ ጥቂት ደቂቃዎች ልመና ወደ እግዚአብሔር ማቅረብን ነው። ያኔ ሁሉም ግዴታውን ተወጣ ማለት ይቻላል።የ ኢትዮጵያን ቡድን ያወደሱ ብእሮች እንደገና ይቀረፃሉ።ዋልያዎች በርቱ!

ጀግንነት ፈፅሞ አለመሸነፍ አይደለም። ተሸንፎ መነሳት ነው። ጀግናን ጀግና የሚያሰኘው ፈፅሞ የማይሸነፍ ምትሃታዊ ፍጥረት ስለሆነ አይደለም ዕድል ወይንም ትንሽ ስህተት አልያም ችላ ብሎት ጀግና የመጀመርያ ሽንፈት ይሸነፋል። ሁለተኛ እና ሶስተኛ ላይ ግን የሚያስደነግጥ ብቻ ሳይሆን የሚያርበደብድ ይሆናል።

ኢትዮጵያ ዘላለም ትኑር!

ጌታቸው  

ኦስሎ

Thursday, January 24, 2013

ለንደን የሚገኘው የ ኤርትራ ኤምባሲ ታግቶ ዋለ። የ አቶ ኢሳያስ ፎቶ ወርዶ በ ወጣቶቹ ተረጋገጠ (ቪድዮ)

ለንደን እንግሊዝየሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲበ ኤርትራውያንወጣቶች መታገቱንየተለያዩ የዜና ዘገባዎችበ ዛሬውእለት ዘግበዋል።የ 'ኢትዮጵያሪቪውን' ጨምሮበተለያዩ ብሎጎችሙሉ ፊልሙንአስደግፈው ዘግበውታል።'ጉዳያችን' የጡመራ መድረክባለፈው አመትመጋቢት ወርላይ የኤርትራን የፖለቲካ አቅጣጫእና በግብፅ አዲሱ' እስላምወንድማማቾች ህብረት'ስልጣን ከመያዙጋር እናበ ኢትዮጵያበወቅቱ ከነበሩትጠቅላይ ሚኒስትርአስተሳሰብ አንፃር'' ኤርትራ ጉዳይ ሃያ አንደኛው /ዘመን ልጆች አስተሳሰብ'' በሚልአርዕስት ስርአንድ ዘገባአቅርባ ነበር።ዘገባውን ይህንበመጫን ያንብቡ-(http://gudayachn.blogspot.no/2012/03/blog-post.html)

በኤርትራ የፖለቲካትኩሳቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረለመሄዱ የሚያሳዩሁለት ክስተቶችበያዝነው ሳምንትታይቷል። የመጀመርያውባለፈው ጥር14/2005 የተሞከረው የማስታወቅያ ሚኒስትርመስርያቤትን በታንክየታገዙ ወታደሮች
ለመቆጣጠር ያደረጉትጥረት(የቪድዮዘገባዎችንይህንበመጫንይመልከቱ)(http://gudayachn.blogspot.no/2013/01/142005.html)ሲሆን ዛሬደግሞ ለንደንየሚገኘውን ኤምባሲ ከሃያ በላይ ወጣቶች ተቆጣጥረው መዋላቸውነው። ከእዚህ በታች ቪድዮው ላይ እንደምትመለከቱት ወጣቶቹ አቶ ኢሳያስን ፎቶ ሰብረው በእግራቸው ሲረግጡት ከመታየቱም በላይ ኢምባሲው ግድግዳ ላይ ቀይ ኤክስ የተሰረዘ አቶኢሳያስን ምስል መልሰው ሰቅለዋል።ሙሉ ቪድዮውን እዚህ በታች ይመልከቱ።



 
 
 
 

Tuesday, January 22, 2013

በ አስመራ ኤርትራ በ ጥር 14/2005 ዓም የተከሰተው የ ወታደሩ አመፅ በተለያዩ የ አለም የ ቴሌቭዥን ጣብያዎች ሲዘገብ (ቪድዮ)

በ ኤርትራ አስመራ ትናንት ጥር 14/2005 ዓም ከ ሁለትመቶ የማያንሱ ወታደሮች የ ቴሌቭዥን እና ራድዮ ጣቢያውን ተቆጣጥረው የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱ እና የ 1990 ዓም  ህገ መንግስት እንዲከበር ጠይቀዋል። ይህንኑ  ዜና ሮይተር፣ኤ ኤፍ ፒ እና ኤሮ ኒውስን  ጨምሮ በ አጭሩ ዘግበውታል።
 ከምሽቱ 4 ሰዓት አልፎ የተላለፈው የ ኤርትራየ እንግሊዝኛው የ ቴሌቭዥን ፕሮግራም ምንም ነገር እንዳልሆነ ቀጥታ ሌሎች ዜናዎችን  ማስተላለፉ እና አለም ስለሚያወራው ጉዳይ ምንም አለማውራቱ አስገራሚ ትዕይንት ነበር። 
ጉዳዩ ግን ተለያዩ የ ዜና ዘገባዎች እንዲህ ቀርቧል።

1/ ኤሮ  ኒውስ 

 
 
 
 

2/ አልጀዝራ 
 
3/ ቴክ ኔትዎርክ ኒውስ 
 
 
 

Wednesday, January 16, 2013

ቤተክርስቲያንን ለሚሰቅሏት እና ለሚያሰቅሏት ወዮላቸው!

አዲስ አበባ ስብሰባ የተቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 እስከ ጥር 8/2005 ዓም ያደረገው ስብሰባ ዝርዝር ጉዳዩ ባይገለፅም ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አቡነ አብርሃም የተነበበው የውሳኔ መግለጫ ሕዝበ ክርስቲያንን ያሳዘነ ቤተክርስቲያንን ሌላ የመከራ እና የመከፋፈል ዘመን ፊቷ የደቀነ ሆኗል  ዛሬው ጥር 8/2005 ዓም 'ኢሳት ' አጭር ሞገድ ራድዮ ስርጭቱ ላይ 'ዘግይቶ የደረሰን ዜና' ብሎ ባቀረበው ዜና '' አቡነ አብርሃም የተነበበውም ሆነ ለጋዜጠኞች የተበተነው ወረቀት የደብዳቤ ቁጥር እና ማህተም የሌለው መሆኑ ታወቀ '' ካለ በኋላ ቀጠለና ''አቡነ ሕዝቅኤል አብዛኛው አባቶች ባላመኑበት ሁኔታ ማህተም አላሳርፍም ማለታቸው እና ስብሰባውን እረግጠው መውጣታቸውም ተስምቷል '' በማለት ዘግቧል

ቤተክርስቲያን ሕይወቷ መስቀል ላይ ነው። ለሚሰቅሏት እና ለሚያሰቅሏት ወዮላቸው።

ቤተክርስቲያንን ለሚሰቅሏት

ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እጅግ የሚያሳዝን ወቅት ላይ ነች። አስተዳደራዊ ጉዳይዋን ሳትፈታው፣የ ፓትርያርክ ጉዳይ፣ይህን ፓትሪያርክ ጉዳይ ሳትፈታው የዋልድባው እያለ ይሄው ዛሬ ደግሞ ሁለት አስርተ አመታት የተለያዩባት አባቶቿ በአለፈው ወር ዳላስ አሜሪካ እንደተመለከትነው አባቶች አንድ ላይ ኪዳን ሲያደርሱ ደስ ያለንን ያህል ዛሬ ዳግም አዘንን።መንግስት እርቀ ሰላሙ ሂደት ጀመሮ እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ በግልፅ ያሳያቸው ጣልቃ ገብነት ስራዎች ነበሩ። እነዚህም ውስጥ ፕሬዝዳንት ግርማ 'ብፁዕ አቡነ መርቆርዮስን ወደመንበራቸው እንዲመለሱ ቢደረግ'' በሚል የፃፉትን ደብዳቤ 'መንግስት በቤተክርስቲያን ጉዳይ አይገባም' በሚል እንዲነሳ ማድረጉ፣ አስታራቂ ኮሚቴ አባላት በፀጥታ ኃይላት እንዲዋከቡ እና ተገፍተው ሀገር እንዲወጡ መደረጉ፣እርቀ ሰላሙ እየተካሂያደ ' ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ' እንዲዋቀር በመግፋት፣በመጨረሻም ጥር 6 እስከ 8 በተደረገው ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አባቶችን በማስፈራራት አዲስ ፓትርያርክ ምርጫው እንዲከወን በመጣደፍ ላይ መሆኑ ሁሉ ጉልህ ማስረጃዎች ነበሩ እናም ቤተክርስቲያንን እየሰቀላት ያለው መንግስት ቤተክርስቲያንን ቁስል ከማድረቅ ይልቅ ሌላ መለያየት እነሆ አዲስ ምዕራፍ ከፈተባት።

ቤተክርስቲያንን ለሚያሰቅሏት

''እናንተንጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ እኔ በኋላ ለመንጋይቱ የማይራሩ ነጣቂዎች ተኩላዎች እንደሚመጡ እኔ አውቃለሁ '' ሐዋርያት ሥራ 2028-30

ቤተክርስቲያን ጉዳይ አባቶች የመምራት፣የማስተማር እና እስከ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ጉዳይ ቢኖር ግንባር ቀደምትነት እንዲቆሙ ለአባቶቻችን አደራ መሰጠቱን መፅሐፍ ቅዱስ የሚያረጋግጥልን እውነታ ነው።ዛሬ ግን ቤተክርስቲያንን መስቀል ባይችሉ በመከራ መስቀል ላይ ሊሰቅላት ከሚታትሩ ጋር ጮማ እየቆረጡ የሚያሰቅሏት አንዳንድ አባቶች አልጠፉም። ''በአንድ ገበታ ተቀምጠው ሐሰት ይናገራሉ'' የተባለለት ዘመንን ደረስንበት ማለት ይሆን? ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታላቁ ገዳም ዋልድባ እየታመሰ ምንድነው የሆነው? ብለው ችግሩን ማዳመጥም ሆነ መፍትሄው ላይ ታች ማለት ያለባቸው አባቶች አዲስ አበባ ላይ ሲንሸራሸሩ መታየታቸው  ሌላው ቀርቶ የገዳሙን ችግር እንወያይ ብለው ምእመናንን ለማናገር መንግስት ሹመኞችን ግልምጫ እና እስር የፈሩ መሆናቸው፣ ይህ ሁሉ ባይሆንላቸው ባለፈው ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አጀንዳ አስይዞ ለመወያየት ቅምጥል መንግስት ሹማምንትን ፊት የሚመለከቱ አንዳንድ አባቶች  ቤተክርስቲያንን ከሚያሳቅሏት ወገን ናቸው።

ዛሬ ከወደ አዲስ አበባ የተሰማው ወሬ ቤተክርስቲያንን የሰቀሏት እና የሚያሰቅሏት ተባብረው ላለፉት ሁለት አስርተ-አመታት የነበረባትን ሲኖዶስ ክፍፍል ሌላ አዲስ ምዕራፍ ሊያራዝሙባት ሽር ጉድ ማለታቸውን ነው።

ጥያቄው እኛ ከየት ወገን ነን? ከሚሰቅሉት ወይስ ከሚያሰቅሉት?

ቤተክርስቲያን ችግር ውስጣችን የደማ ሁሉ እና በሚሰራው ማባርያ የሌለው ጥፋት ያዘንን ሁሉ ዝምታችን ከከንፈር መምጠጥ ባላለፈ ተግባር ላይ መሆናችን ከሚሰቅሏት ወይንም ከሚያሰቅሏት ወገን ላለመሆናችን ከቶ ምን አይነት መረጃ ይኖረን ይሆን? ኑሮዬ፣ጨርቄን፣ ወዘተ እያልን በመስቀል አልያም በማሰቀል ላይ መሆናችንን ልብ ብለነው ይሆን?ጌታችን ቀራንዮ ሲሰቀል ሰፍነግ ያቀበሉም ሆኑ ከመስቀሉ ስር ገበጣ የሚጫወቱ- ሁለቱም በሰቃይነትም ሆነ አሰቃይነት ተፈርጀዋል።ቤተክርስቲያንን ለሚሰቅሏት እና ለሚያሰቅሏት ወዮላቸው! ዝምታ የሚሰበርበት ''የቤተክርስትያኔ ጉዳይ ያገባኛል'' የምንልበት እውነተኛው ጊዜ ነው እና 


ይቆየን

ጌታቸው
ኦስሎ 

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...