ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Monday, July 31, 2017
Monday, July 17, 2017
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአውሮፓ ለመጀመርያ ጊዜ ሲመተ ጵጵስና አካሄደች።የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የጵጵስና ማዕረግ ተሹመዋል።
ሲመተ ጵጵስና ከተከናወነ በኃላ (ፎቶ ጉዳያችን)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገሮች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ተወላጆች የምትሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።ይህ አገልግሎት በተለይ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለየ መልክ እና እጅግ ወሳኝ የሆነ ገፅታ አለው። ከሀገሩ በርቀት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማለት የመንፈሳዊ ሕይወታቸው መሪ ብቻ ሳትሆን የባህል፣ማንነት እና ስነልቦናዊ ፋይዳ ሁሉ የሚገለጥባት ልዩ አካሉ ነች።ከእዚህ ሁሉ የአገልግሎት ፋይዳ ጋር እንግዲህ የአገልጋይ ካህናት ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም።ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደ አንድ ቁልፍ ተቋም እና የምእመናንን ሕይወት በመንፈሳዊ እና ዓለማዊ ሕይወት ዙርያ የመምራት አቅም፣ አሻጋሪ ርዕይ እና ብቁ ትውልድ የማፍራት ሥራ ሁሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሚኖራት ብቃት ያላቸው አገልጋይ ካህናት ይወሰናል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ካሏት መሰረታዊ ባህርያት ውስጥ አንድነት እና ሐዋርያዊ መሠረትነት ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በፈተና ላይ መውደቃቸው ይታወቃል።ለእዚህም ዋነኛ ምክንያቱ አሁን ስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት የነበሩትን ፓትርያርክ መርቆርዮስ ከሀገር እንዲወጡ ግፊት ካደረገ በኃላ ፓትርያርኩ በሕይወት እያሉ የአቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክነት መሰየም ነው።ችግሩ ከተፈጠረ በኃላም በውጭ እና በሀገር ቤት ያሉ ብፁዓን አባቶች መካከል ንግግር ተደርጎ ችግሩን ለመፍታት የተደረጉ ሙከራዎች የሚፈለገውን ውጤት አላስገኙም።ለእዚህ በዋናነት የሚጠቀሰው ምክንያት ለአንድነቱ በጎ ፍቃድ ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ በታማኝነት ለመስራት ፈፅሞ ምልክትም ያላሳየው በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት አንዱ እና ተጠቃሽ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሀገር በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ብፁዓን አባቶች አህጉረ ስብከቶቹ ከሚያስፈልጋቸው አገልጋይ ጳጳሳት አንፃር ተጨማሪ ጳጳሳትን ከቆሞሳት መካከል እየመረጡ ለጵጵስና ማዕረግ እያበቁ ይገኛሉ።ከአገልግሎቱ አንፃር የቆሞሳት ለጵጵስና ማዕረግ መብቃት ቤተ ክርስቲያን እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ እግዚአብሔር እንደፈቀደ የሚቀጥል መንፈሳዊ ተግባር ነው።የሁሉም ምእመናንም ሆነ የሁሉም ብፁዓን አባቶች ምኞት እና ፀሎት ግን አሁንም ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነቷን መልሳ የምታጠናክርበት ቀን እንዲቀርብ ነው። ይህ እስኪሆን ድረስ ግን በአባቶች መካከል የቀኖና እና ስርዓት ጉዳይ እንጂ የመሰረተ ሃይማኖት (ዶግማዊ) ልዩነት ካለመኖሩ አንፃር ቤተ ክርስቲያን አሁን ያሉባትን ችግሮች የመፍታት አቅሟ አሁንም ትልቅ መሆኑን መረዳት ይቻልል።
በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭም ሆነ በሀገር ቤት የሚገኙ አባቶች በጋራ በመቆም አርአያነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች እየታዩ ናቸው። እነኝህ እንቅስቃሴዎችም በተሃድሶ ጉዳይ ላይ እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ናቸው።በያዝነው ዓመት ብቻ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ያሉ አባቶች በሲኖዶስ ስብሰባዎች ላይ በመግለጫ ደረጃ በጋራ ያስነበቡት ዓቢይ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሰረተ ዕምነት መፃረር ላይ የሚገኘው በተሃድሶ እንቅስቃሴ ላይ ያሳዩት ግልጥ መመሪያ ነው። በስደት የሚገኙ አባቶች በቅርቡ በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይም ሆነ ባሳለፍነው ሳምንት በስዊድን ፣ ስቶኮልም በተደረገው ሃያኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ ፍፃሜ ላይ በወጣ መግለጫ በተሃድሶ እንቅስቃሴ ላይ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት እራሳቸውን መጠበቅ እና ምእመናንን ማስተማር ተገቢ መሆኑን አፅኖት በመስጠት አሳስቧል።
በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭም ሆነ በሀገር ቤት የሚገኙ አባቶች በጋራ በመቆም አርአያነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች እየታዩ ናቸው። እነኝህ እንቅስቃሴዎችም በተሃድሶ ጉዳይ ላይ እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ናቸው።በያዝነው ዓመት ብቻ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ያሉ አባቶች በሲኖዶስ ስብሰባዎች ላይ በመግለጫ ደረጃ በጋራ ያስነበቡት ዓቢይ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሰረተ ዕምነት መፃረር ላይ የሚገኘው በተሃድሶ እንቅስቃሴ ላይ ያሳዩት ግልጥ መመሪያ ነው። በስደት የሚገኙ አባቶች በቅርቡ በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይም ሆነ ባሳለፍነው ሳምንት በስዊድን ፣ ስቶኮልም በተደረገው ሃያኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ ፍፃሜ ላይ በወጣ መግለጫ በተሃድሶ እንቅስቃሴ ላይ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት እራሳቸውን መጠበቅ እና ምእመናንን ማስተማር ተገቢ መሆኑን አፅኖት በመስጠት አሳስቧል።
የመጀመርያው ሲመተ ጵጵስና በአውሮፓ
ከላይ የተጠቀሱት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ነባራዊ እና ወቅታዊ ሁኔታ ለመንደርደርያነት ከቀረበ ባሳለፍነው ሳምንት ማለትም ሐምሌ 9፣2009 ዓም በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመርያ ጊዜ ሲመተ ጵጵስና ማካሄዷን ወደ ሚገልጠው ዜና እንለፍ።በጵጵስና የተሾሙት አባት የቀድሞ ስማቸው መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ ለገሰ ሲሆኑ የጵጵስና ስማቸው አቡነ ሕርያቆስ ተብለው በስደት የሚገኙት ብፁዓን አባቶች በተገኙበት ፀሎት ተሹመዋል።ከእሁዱ የሹመት መርሃግብር በፊት በ2008 ዓም አቡነ ሕርያቆስ የቀደመ አገልግሎት እና ለጵጵስና ማዕረግ ብቁ መሆናቸው በውጭ ለሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በአቡነ መርቆርዮስ ሰብሳቢነት ጉዳዩ የቀረበ እና ብፁዓን አባቶችም ጉዳዩን መርምረው ለጵጵስና ከታጩት ስምንት አባቶች መካከል አንዱ መሆናቸው እና ከስምንቱ መካከል ስድስቱ ጥቅምት 23፣2009 ዓም በኦሀዮ መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን አባቶች ምልዓተ ጉባኤ ሲሾሙ በቪዛ ምክንያት በቦታው ተገኝተው መሾም ያልቻሉት አቡነ ሕርያቆስ (የቀድሞው መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ ለገሰ) ባሉበት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ መልካም ፍቃድ እና ብፁዓን አባቶች ምርጫ ባሉበት እንዲሾሙ ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዓን አባቶችን ልኮ እንዲከናወን ምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፎ ነበር። በእዚሁም መሰረት ቋሚ ሲኖድስ የምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሰረት መጋቢት 5፣ 2009 ዓም ባደረገው ስብሰባ ሿሚ ሊቃነ ጳጳሳትን በመመደብ ሹመቱ ሐምሌ 9፣2009 ዓም በብፁዕ አቡነ ኤልያስ መንበረ ጵጵስና በሚገኝበት በስቶኮልም ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን እንዲከናወን በመጋቢት 20፣ 2009 ዓም ለሿሚ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለአቡነ ኤልያስ እና ስቶኮልም ለሚገኘው ደብረ ሰላም መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በፃፈው ደብዳቤ ማሳወቁን ለማወቅ ተችሏል። በመሆኑም አቡነ ሕርያቆስ መቀመጫቸውን በኦስሎ፣ኖርዌይ አድርገው የአቡነ ኤልያስ ልዩ ረዳት በመሆን ተሹመዋል።
አቡነ ሕርያቆስ ከጵጵስና ሹመት በኃላ ከዲያቆን ናትናኤል እና ዲያቆን ሳሙኤል ጋር
አቡነ ሕርያቆስ (ከጵጵስና በፊት በነበራቸው ስማቸው መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ) ማን ናቸው?
ልደት
ጥቅምት 5፣1968 ዓም ከአባታቸው ከአቶ ለገሰ አዛናው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጥሩ ወርቅ ከበደ በኢትዮጵያ ስማዳ ወረዳ ተወለዱ።
ትምህርት
እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በተወለዱበት በደብረ ቅዱሳን ዱቄ እየሱስ ከአባ ተፈራ ፀጋው ፊደለ ሐዋርያ፣ ውርድ ንባብና አምስቱ አዕማደ ምስጢርን ከአባ አሳየ ጎሹ በቃል ልዑል ሰምራ በዓታ፣ ዳዊት እና ቅዳሴ ከአባ ይሄይስ ካሳ በቅዱስ ወይራዬ ቅዱስ ገብርኤል ተምረዋል።ከእዚህ በተጨማሪ የሚከተሉትን ትምህርቶች በሚገባ አጠናቀዋል።እነርሱም -
1/ ዜማ
ከየኔታ ይትባረክ እና ከየኔታ ኪነ ጥበብ ዓለማየሁ በአንጎት ማርያም ተምረዋል።
2/ ቅኔ
በስማዳ ስመጥር ከሆነው ደብር ቃጨና ኢየሱስ ከየኔታ ዓለሙ፣ እንዲሁም ወደ ምስራቅ ጎጃም ተሻግረው በደጀን ጊዮርጊስ ከየኔታ ናቃቸው ዲበ ኩሉ ተምረዋል።
3/ አቋቋም
በአጋጥ ሩፋኤል ከየኔታ ተመቸ እና በደብረ ኤልያስ ከየኔታ ወልደ ሚካኤል እና የክብረ በዓላትን እና መዝሙራትን አሰላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ከሊቀ ጉባኤ ጽጌ አክሊሉ ተምረዋል።
3/ ትርጓሜ
ውዳሴ ማርያም፣ ቅዳሴ ማርያም፣ኪዳን፣ትምህርተ ኅቡዓት እና ባሕረ ሀሳብ የትርጓሜ መምህር ከነበሩት የኔታ ፍስሃ (አበባው) በመቱ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ተምረዋል።
4/ ኮርሶች
- በመቱ ፈለገ ሕይወት የካህናት ማሰልጠኛ የሶስት ወራት ኮርስ ወስደዋል፣
- አዲስ አበባ በሚገኘው በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአንድ ዓመት ኮርስ ተከታትለዋል።
5/ ማስተርስ፣ ባችለር ዲግሪዎች እና ዲፕሎማ
ደቡብ አፍሪካ፣ ጆሃንስበርግ በሚገኘው ወርልድ ሃርቨስት ቴዎሎጂ ኮሌጅ (World Harvest Theological College _ WHT) የማስተርስ ዲግሪ በክርስቲያን አመራር (Christian leadership)፣ የባችለር ዲግሪ በነገረ መለኮት (Bachelor of Divinity) እና ዲፕሎማ በመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት( Diploma in biblical studies) ተምረው ተመርቀዋል።
6/ክህነት
- በ1983 ዓም ዲቁና ከብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣
- በ1991 ዓም ምንኩስና እና ቁምስና ከአቡነ ፊሊጶስ መቱ፣ኤልባቦር ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል
7/ አገልግሎት
- ከመጋቢት 1989 እስከ የካቲት 1990 ዓም በኢልባቦር ሃገረ ስብከት እና በደሌ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመሪ ጌትነት፣
- ከ1990 እስከ 1993 ዓም ወደ ሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ከፍተኛ ኮሌጅ ለተጨማሪ ትምህርት እስከተላኩበት ድረስ የኢልባቦር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ አቡነ ቀሲስ በመሆን እና በመቱ የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል መንበረ ጵጵስና ረዳት መሪ ጌታ በመሆን አገልግለዋል።
- ከ2001 እስከ 2005 ዓም በአቡነ ኤልያስ መልካም ፍቃድ የዩጋንዳ መካነ ሰላም መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
- ከ2005 እስከ 2015 ዓም በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ፅርሐ አርያም ስላሴ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ሆነው ለአስር አመታት አገልግለዋል።
- ከ2007 ዓም ጀምሮ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው በጵጵስና እስከተሾሙበት ሐምሌ 9፣2009 ዓም ድረስ አስተዳዳሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በጵጵስና ማዕረግ ከተሾሙም በኃላ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነታቸው የሚቀጥሉ መሆናቸው ሲታወቅ በተጨማሪ የአቡነ ኤልያስ ልዩ ረዳት በመሆን ያገለግላሉ።
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ እና በአቡነ መርቆርዮስ ፍቃድ መሰረት በአቡነ ሕርያቆስ ሲመተ ጵጵስና ላይ ስቶኮልም፣ ስዊድን መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ከአቡነ ኤልያስ ጋር በተጨማሪ ተገኝተው ሹመቱን የፈፀሙት ብፁዓን አባቶች የሚከተሉት ናቸው። እነርሱም -
1ኛ/ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የምዕራብ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ዋና ፀሐፊ፣
2ኛ/ አቡነ ዲሜጥሮስ የምስራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣
3ኛ/ አቡነ ቴዎፍሎስ የካሊፎርኒያ ሃገረ ስብከት ረዳት ሊቀጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
4ኛ/ አቡነ ማርቆስ የዋሽንግተን ሲያትል እና የፖርትላንድ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።
ፎቶ - በሃያኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ከብፁአን አባቶች ጋር አቡነ ኤልያስ ሲናገሩ
በመጨረሻም አቡነ ሕርያቆስ ከላይ ቀደም ብሎ ከተጠቀሱት ተግባራት በተጨማሪ በደቡብ አፍሪካ እስከ ክህነት ድረስ ያደረሷቸው ወጣቶችን በማስተማር አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል። በኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንም ማገልገል ከጀመሩ ገና ሁለተኛ አመታቸው ቢሆንም የአብነት ትምህርት መርሃ ግብር በመክፈት፣የቤተ ክርስቲያኗ የአገልግሎት መዋቅር እንዲሰፋ በማድረግ እና ሁሉንም ምእመናን በአባታዊ ፍቅር በማቅረብ እየሰጡት ካለው አገልግሎት በተጨማሪ የአብነት ትምህርት ዘወትር አርብ በአካል እየሰጡ ሲሆን የያይዝነውን ክረምት ሁለት ወሮች ደግሞ በእየቀኑ ለሶስት ሰዓታት እየተገኙ ትምህርት እየሰጡ ሲሆን በእዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥም አራት ዲያቆናትን ኦስሎ ላይ አፍርተዋል። ለአቡነ ሕርያቆስ እረጅም እድሜ እና መልካም የአገልግሎት ዘመን እንመኛለን።
ጉምህርትዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
Wednesday, July 12, 2017
በሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ሥራ፣ሕይወት እና አስተዋፅኦ ዙርያ ልዩ ውይይት
ምንጭ : - አደባባይ (www.adebabay.com) ዩቱዩብ
አወያይ : ዲ/ን ኤፍረም እሸቴ
ተወያይ : መምህር ብርሃኑ አድማስ
ማሳሰቢያ :- የመጀመርያዎቹ ጥቂት ሰኮንዶች ድምፁ ዘግይቶ ስለሚጀምር በትግስት ይጠብቁት
ክፍል አንድ
ክፍል ሁለት
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
አወያይ : ዲ/ን ኤፍረም እሸቴ
ተወያይ : መምህር ብርሃኑ አድማስ
ማሳሰቢያ :- የመጀመርያዎቹ ጥቂት ሰኮንዶች ድምፁ ዘግይቶ ስለሚጀምር በትግስት ይጠብቁት
ክፍል አንድ
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
Thursday, July 6, 2017
Sunday, July 2, 2017
መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ሀብተየሱስ ለገሰ የኦስሎ ቅ/ገብርኤል አቡነ ተ/ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች ዙርያ የሰጡት ቃለ መጠይቅ
ከኢሳት ቴሌቭዥን ሐምሌ 25፣2009 ዓም (ጁን 2፣2017) ላይ የተወሰደ
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
Thursday, June 29, 2017
የተቃወሰ መንግስት ምልክቱ እራሱን ወደ 'አናርኪዝም' ማሸጋገሩ ነው - የኢትዮጵያን የባንክ ኢንዱስትሪ ጉዳይ ይመለከታል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
ጉዳያችን/ Gudayachn
ሰኔ 23/2009 ዓም (ጁን 30/2017 ዓም)
++++++++++++++++++++
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ታሪክ የኢትዮጵያ ባንኮች ከሌሎች የአፍሪካ በተለይ ከሣሃራ በታች ካሉት ሀገሮች በተለየ ጥሩ ተአማኒነትን በሌላው ዓለም አትርፈዋል።ለምሳሌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በደርግ ዘመን ማለትም ኢትዮጵያ ከቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ጋር ወዳጅ ሆና ሳለም ሳይቀር የምዕራብ ባንኮች በ"ሌተር ኦፍ ክረዲት" የላኪ እና የአስመጪ ሰነዶች ላይ በሚፈፀሙ ክፍያዎች ታማኝነቱ የተመሰከረለት ነው።ለምሳሌ የአሜሪካው "ሲቲ ባንክ" እና የእንግሊዙ "ስታንዳርድ ቻርተር" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰነዶች ላይ እምነታቸው ከፍ ያለ ነው።ለእዚህ ደግሞ ምክንያቱ የስርቆት አደጋዎች በብዛት የማይታዩበት፣ለቀረቡለት የክፍያ ሰነዶች በወቅቱ መክፈሉ እና ለእረጅም ጊዜ በባንኩ የዓለም አቀፍ ባንክ አገልግሎት ክፍል (International Banking Division) ላይ የሰሩት ኃላፊዎች የገነቡት ዓለም አቀፍ ስብዕናም ጭምር ነው።ይህ ማለት ታማኝነቱ በአንድ ጀንበር የተገንባ ሳይሆን የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ከቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ጊዜ ጀምሮ የገነባው ብቁ እና ታማኝ የሰው ኃይል ውጤትም ጭምር ነው። በእርግጥ ደርግ የሆነ ወቅት ላይ በሙያው በቂ ስልጠና የሌላቸውን አስገብቶ እንደነበር እና ይህም ለባንኩ የስራ ጥራት ላይ የእራሱን አስተዋፅኦ ማድረጉን የሚናገሩ አሉ። ይህም ሆኖ ግን በታማኝ የሰው ኃይል እና ስራን በማክበር አይታማም።
በእዚህ ፅሁፍ ማንሳት የፈለኩት ግን ይህንን አይደለም።ስለ የባንኮቻችን በቀውስ ላይ ያለው መንግስት አናርክዝም ወይንም ስርዓት አልበኝነት ሰላባ ስለመሆን ነው።በአሁኑ ጊዜ የግል ባንኮችን ጨምሮ 18 ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ።ይህ በራሱ ጥሩ ነገር ነው። ሆኖም ግን የባንክ ቁጥር መደርደሩ ሳይሆን አጠቃላይ የባንክ ኢንዱስትሪው ለኢንዱስትሪው ስነ-ምግባር እና የንግድ ሕግ ተገዢ ነው ወይ? የሚለው ጉዳይ ወሳኝ ነው።አንድ ባንክ ከሁሉም በላይ በገበያው ውስጥ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገር ተመሳሳይ የገንዘብ ድርጅቶች ዘንድም ታማኝ የሚያደርገው ለደንበኞቹ ያለው ዋጋ ነው።ደንበኞቹ ማለት ደግሞ ገንዘብ ያስቀመጡ እና የምበደሩ የሀገር ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ በውጭ ያሉ ባንኮች እራሳቸው ደንበኛ ባንኮች ይባላሉ።ይህ ማለት የውጭ ባንኮችም ደንበኞቻችን ናቸው ማለት ነው።ባንክ ባንክ ለመባል ትንሹ የሚጠበቅበት እና ለምንም ድርድር የማይቀርበው ጉዳይ ደንበኞች ያስቀመጡትን ገንዘብ በፈለጉ ጊዜ መክፈል መቻሉ ነው።ይህ የባንክ ሀ! ሁ! ነው።ይህንን ማድረግ ያልቻለ ባንክ ባንክ አይባልም።ይህ ሃገራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ግዴታ ነው። የብሔራዊ ባንክ ካሉበት ትልልቅ ሃገራዊ ምጣኔ ሃብታዊ ኃላፊነቶች ውስጥ ትንሹ እና ለድርድር የማይቀርበው የቁጥጥር ቀዳሚ ስራው ውስጥ የንግድ ባንኮች ደንበኞቻቸው ገንዘባቸውን ሲፈልጉ መልሰው የመክፈል አቅም ሳይኖራቸው ተበዳሪ አገኘን ብለው ያላቸውን ሁሉ አበድረው ደንበኞች ገንዘባቸውን እንዳያጡ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ ነው። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ታሪክ ውስጥ ጥያቄ ሆኖ አያውቅም። በእዚህ በአሁኑ ዘመን ግን አንድ ሰው በፈለገበት ሰዓት ባንክ ሄዶ ገንዘቡን ለማውጣት ሲፈልግ " ሲስተሙ ችግር አለበት ወይንም ዛሬ ሲስተም የለም" እየተባለ መመለስ የተለመደ ነው። ይህ አይነቱ መልስ በባንኮች ታሪክ በኢትዮጵያ ውስጥ በደርግም ሆነ በሃይለስላሴ ዘመን ተደረገ ሲባል አልሰማሁም።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 'ሲስተሙ አይሰራም' በሚል ምክንያት ደሞዝ ወደ ሂሳባቸው የገባ ሰራተኞች ደሞዛቸውን ሳይወስዱ ከሶስት ቀናት በላይ ይመላለሳሉ።የንግድ ውል ተዋውለው ገንዘቡን መክፈል የሚፈልጉ ነጋዴዎች ባንካቸው ገንዘቡን መክፈል ሳይችል ለሳምንት ልዘገዩ ይችላሉ አልያም ደንበኞች ያስቀመጡትን ገንዘብ ለማውጣት ለቀናት በእዚሁ ሲስተም በሚል ሰበብ ይመላለሳሉ። እዚህ ላይ ሲስተም ተብሎ የሚነገረው በኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ብቸኛ አቅራቢነት የሚሰጠው የኢንተርኔት አገልግሎት ነው።ቴሌን የሚመሩት የኮማንድ ፖስቱም አለቆች ናቸው እና እነርሱ ስለ ንግድ ሕግ፣ ስለ ባንኮች ለደንበኞቻቸው የገቡት ቃልም ሆነ የኢትዮጵያ ባንኮች ለዓለም አቀፍ ባንኮች የገቡት የንግድ ሰነዶች ጉዳይ ሁሉ በወሬ ይሆናል የሚያውቁት። 'ዛሬ ኢንተርነቱን ዝጋው አየሩ ጥሩ አደለም' ካሉ መዝጋት ነው።እዚህ ላይ የባንኮች ለክፍያቸው ታማኝ አለመሆን ያለውን ሌላውን ጣጣ ጉዳያቸው አይደለም። አናርክዝም ወይንም ስርዓት አለበኝነት ማለት ይህ ነው።በሕግ የማይመራ የተቃወሰ መንግስት። በውጪ እና ገቢ ንግዶች ዙርያ ያሉ ክፍያ የሚጠብቁ ዓለም አቀፍ የባንክ የክፍያ መጠየቂያ ሰነዶች ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልጉ እና የክፍያ ሂደቱም ከተባለለት ጊዜ ከፍ ወይም ዝቅ ሳይል መሆን እንዳለበት ይታወቃል።
አንድ አስመጪ ወይንም ላኪ እቃው ወደ ሚላክበት ሀገርም ሆነ እቃው ከሚመጣበት ሀገር ያሉ ባንኮች ገንዘባቸው እንዲከፈላቸው የሚፈልጉበት የጊዜ ገደብ በሌተር ኦፍ ክረዲቱ ላይ የተጠቀሰ እና ገዢ እና ሻጭ በገቡበት የውል ሰነድ መሰረት ነው። በሁለቱ ገዢ እና ሻጭ መካከል ከፍተኛ ታማኝ ተብለው የሚያቀባብሉት ደግሞ ኢትዮጵያ ያለው ባንክ እና ውጭ ሀገር ያለው ባንኮች ናቸው። ልብ በሉ። የኢትዮጵያ ቴሌ ሲስተም መዝጋት ስንት የክፍያ ሰነዶች ለቀናት እንዲቀመጡ እና የውጭ ሀገር ባንኮች በእዚህ ሳብያ ስንት ወለድ እንደጠየቁባቸው በእየባንኩ ቤት ያላችሁ መስክሩ።በእዚህ ሳብያ የሚደርሰው ኪሳራ የወለድ ብቻ አይደለም።ወለዱ ቢደመር ኢትዮጵያ በቴሌ እና የኮማንድ ፖስት አለቆቹ ሳብያ ምን ያህል እንደከሰረች መለስተኛ የዳሰሳ ጥናት ቢደረግ አስደንጋጭ እንደሚሆን ለማወቅ ሊቅ መሆን አይጠበቅም። ከእዚህ ሁሉ በላይ ያለው ኪሳራ ግን የኢትዮጵያን መልካም ስም እንዲጠበቅ አድረገው በዓለም አቀፍ ባንኮች ውስጥ ከሁሉም አፍሪካ ሀገሮች በተሻለ ታማኞች የተባሉት የኢትዮጵያ ባንኮችን ስም እንደሚያጎድፍ እና እየቆየም ወደ ጥቁር ዝርዝር መዝገብ እንደሚያስገባን ማወቅ አለብን።
ለማጠቃለል እነ አባይ ፀሐዬ የቦርድ አባል ሆነው የመሩት የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የስርዓቱ "አናርክዝም" ወይንም ስርዓት አልበኝነት ሰለባ መሆኑ ሌላው የኢትዮጵያ የወቅቱ ህመም ነው።በየትም ሀገር አልፎ አልፎ የሲስተም መቆራረጥ ሊያጋጥም ይችላል። የኢትዮጵያ ግን ኢንተርኔት የሚዘጋው በተደጋጋሚ ያውም በኮማንድ ፖስቱ አለቆች መሆኑን ሲታሰብ እና እያመጣ ያለው ቀውስ ሲታይ የተቃወሰ መንግስት ምልክት መሆኑ በግልፅ አመላካች ነው።በንግዱ ሕግ እና ስነ-ምግባር መሰረት ቴሌ ለባንኮች አገልግሎቱን ሲሰጥ ውል ገብቷል።ባንኮች ደግሞ ለደንበኞቻቸው አገልግሎታቸውን ሲያቀርቡ ውል ገብተዋል።ቴሌ የገባው ውል አገልግሎቱን ሳያቆም ለማቅረብ ሲሆን ባንኮቹም በበኩላቸው ለሚሰጡት አገልግሎት ምንም አይነት መቆራረጥ ሳይኖር ለማገልገል ነው። ስለሆነም በእዚህ የንግድ ትስስር መሃል አንዱ ውሉን ባያሟላ ሌላው ለሚደርስበት ኪሳራ ተጠያቂ ነው።ኪሳራ የደረሰበትም በፍርድ ቤት ቀርቦ ከሶ ካሳ ማግኘት ይችላል። ይህ የአምባገነን መንግስት መኖር እና አለመኖር ጉዳይ አይደለም።በደርግ ዘመን በትክክል ይቻላል።በደርግ ዘመን የነበረው የመብራት ኃይል እና የውሃ ፍሳሽ አገልግሎቶች በእለተ እሁድ የሚሰጡት አገልግሎት የሚቆም ከሆነ ቀድመው ከሶስት ቀናት በፊት በራድዮ እና ቴሌቭዥን እንዲናገሩ የንግድ ውል ሕጉ ያዛቸዋል። ከደንበኛው ጋር ውል ሲገቡ አገልግሎቱን ላያቆሙ ካቆሙ ግን ቀድመው ሊያሳውቁ ነው። ይህ ቀላል የንግድ ውል ሕግ በተቃወሰው የሕውሓት መንግስት ውስጥ አይሰራም። መብራት እና ውሃ እንደሚቆም ሳይነገር ለቀናት መጥፋት የጅመረው በአናኪዝም ወይንም ስርዓት አለበኛው የሕወሓት መንግስት ነው እንጂ በደርግም ሆነ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመን ማስታወቂያ ሳይነገር ውሃ እና መብራት አይቆምም።ምናልባት ከዋናው ጣቢያ ሳይሆን በመንገድ ላይ በደረሰ አደጋ አገልግሎቱ ካልቆመ ማለት ነው።በዘመነ ሕወሓት ግን ውሃ እና መብራት ለሳምንት ሲጠፋ ማስጠንቀቂያ የሚባል ነገር የለም። ይህንን ነው ስርዓት አልበኝነት ወይንም አናርክዝም የነገሰበት መንግስት የምለው። የዶ/ር ደብረፅዮን መስርያቤት ለባንኮች የሚሰጠውን የኢንተርኔት አገልግሎት በማቆሙ መክፈል ያለበት በሚልዮን ምናልባትም በብልዮን የሚቆጠር ብር አለበት።ባንኮችም ለደንበኞቻቸው መስጠት የሚገባቸውን አገልግሎት በወቅቱ ባለመስጠታቸው ደንበኞቻቸው በንግድ ስራቸው ላይ ለደረሰባቸው ኪሳራ በፍርድ ቤት ከሰው የመጠየቅ መብት አለባቸው።ይህንን ስናገር በዛሬዋ የተቃወሰ መንግስት ውስጥ ስለ ሕልም እንደማወራ እንደምትገምቱ አውቃለሁ።እንደዚህ አይነት ግምት ላይ እንድንደርስ ያደረገን ግን እራሱ አናርክዝም የሰፈነበት ስርዓት ነው። ቢያንስ ግን መሆን ያለበትን እያወቅን እየሆነ ባለው መናደድ ከቻልን ለነገ መስተካከል ያለበትን ከአሁኑ እያወቅን መጣን ማለት ነው።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
Tuesday, June 27, 2017
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም አለው! የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የሕወሓት ሀገር ከፋፋይ ቀጣይ አጀንዳ አካል ነው (የጉዳያችን ማስታወሻ)
ጉዳያችን / Gudayacnhn
ሰኔ 21/2009 ዓም (ጁን 28፣2017)
++++++++++++++++++++
ዛሬ ሰኔ 20፣2009 ዓም የሕወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮምያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ የሚኖራት ጥቅም በሚል ርዕስ ውሳኔ ማሳለፉ እና የሕወሓት ኢህአዴግ 99% አሸነፍኩ ወዳለበት ምክር ቤት እንደሚመራ ተነግሯል። ጉዳዩ ልዩ መብት የሰጠ የመሰለው ካለ እርሱ ከ26 አመታት በኃላም ገና ፖለቲካ ሀ ሁ እያለ እንደሆነ መረዳት ያለበት ይመስለኛል።
1/ ልዩ ጥቅም የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?
ልዩ ጥቅም የሚለው አባባል በእራሱ የመከፋፈል አላማ ያነገበ አባባል ነው።አንድ ሰው ልዩ ጥቅም ለማግኘት ዋናው መሰረት ሊሆን የሚገባው በኢትዮጵያዊነቱ ነው እንጂ የታሪክ የበላይነት ወይንም የዘር መሰረቱ ወይንም የተለየ አነጋገር በመናገሩን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ ከሆነ መከፋፈል ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከኢትዮጵያ ምድር በመውጣቱ ነው።ከጃፓን ወይንም ብራዚል የመጣ ሰው የማይኖረው ልዩ ጥቅም ኢትዮጵያዊ ሊኖረው ይገባል።ይህ ማለት ኦሮሞው አዲስ አበባ ላይ በኢትዮጵያዊነቱ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ አዲስ አበቤውም በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ኦሮሞው በመቀሌ ላይ ልዩ ጥቅም እንደሚኖረው ሁሉ የአክሱሙም ሰው በኦሮምያ ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የወለጋው ገበሬ በጎንደር ላይ ልዩ ጥቅም እንዳለው የራስ ዳሽን ገበሬም በነቀምት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።ይህ ሁሉ ልዩ ጥቅም የሚመነጨው እንደ ህወሓት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በከፋፋይ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ሙሉ መብት ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ እና መሬት በሁሉም የኢትዮጵያ መሬት ላይ ልዩ ጥቅም አለው።የኦሮምያ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ የሚለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ በእራሱ ከፋፋይ የሆነው የስርዓቱ አጀንዳ ቀጣይ ምዕራፍ ነው።
2/ የውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሰጥ አገልግሎት አይደለም እንዴ?
"የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት በአዲስ አበባ ዙርያ ላሉ የኦሮምያ ክልሎች ያካተተ ይሆናል" ይላል ከአዋጁ አካል ውስጥ አንዱ።አሁንም ውሃ የማግኘት ልዩ መብት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ነው።ይህ አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያዊነቱ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልሎች የውኃ አገልግሎት ላያገኙ ነበር? የውኃ ፍሳሽ አገልግሎት ለማግኘት የልዩ ጥቅም አዋጅ ባይወጣ ኖሮ በኢትዮጵያውነታቸው የማግኘት መብት የላቸውም ነበር? ይህ በእራሱ ከፋፋይ አቀራረብ ነው።በአዲስ አበባ ዙርያ ያለ የኦሮሞ ሕዝብ ውሃ ለማግኘት ልዩ አዋጅ መጠበቅ ነው ያለበት ወይንስ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያገኘው መብት ነው መሆን ያለበት? ለአዲስ አበባ ውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ወጪ የሚሸፈነው ቀረጥ ከኦሮምያ የሚመጣ ገንዘብም ጭምር መሆኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያረሳሳን ነው ? እናስ የአዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ገና ለገና ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር አብሮ ይነሳብኛል ልከፋፍለው በሚል እሳቤ ውሃ በልዩ ጥቅም አዋጅ መሰረት ይዘረጋልሃል የሚል አዋጅ ረቂቅ አንድ ሐሙስ የቀረው እና የታመመ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካልሆነ ማን ያወጣዋል?
3/ የጤና አገልግሎትስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት አይደለም እንዴ?
በአዋጁ ረቂቅ ላይ "አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ በከተማዋ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙሪያ ያሉ የክልሉ ተወላጆችን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል" ይላል። የጤና አገልግሎት የኢትዮጵያዊነት ልዩ ጥቅም ነው።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍልል ቢኖር የጤና አገልግሎት የማግኘት መብቱ ነው።በእዚህ ረቂቅ ላይ አዲስ አበባ እና ኦሮምያ የተለያዩ ሀገሮች ይመስል በአዲስ አበባ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙርያ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ታሳቢ ያደርጋል ሲል ዛሬ ተነስቶ ልዩ ጥቅም የሰጠ አስመስሎ ሕዝብ የመከፋፈል አላማ ለማሳካት ብቻ የተገለፀ ነው።
4/ የአዲስ አበባ ሕዝብ እና የኦሮምያን ሕዝብ ከህወሓት በበለጠ ይተዋወቃል
በእዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ የአዲስ አበባ ስም በፊንፊኔ፣የከተማዋ አንዳንድ ቦታዎች እና አደባባዮች በኦሮምያ ታሪክ ይቀየራሉ የሚል ሃሳብ የያዙ አረፍተ ነገሮች እንዲሁም ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር የስራ መጠቀምያ ይሆናል ይላል።ኦሮምኛ የስራ መጠቀምያ መሆኑ አማርኛ እስካልገባው ድረስ ኦሮምያ የተወለደ ኢትዮጵያዊ በኦሮምኛ አገልግሎት ማግኘቱ ሙሉ መብቱ ነው።ዛሬ ህወሓት እንደ ልዩ ጥቅም አድርጎ ማቅረቡ ነው የማይመቸው። ይህ እንዴት ልዩ ሆኖ ይቀርባል? ኢትዮጵያዊ መብቱ በሚለው ስር የሚገባ ነው።አንድ የጋምቤላ ተወላጅ አዲስ አበባ መጥቶ አማርኛ ካልገባው በጋምቤላ አነጋገር አገልግሎት የማግኘት መብቱ ኢትዮጵያዊነቱ ያጎናፀፈው መብት ነው እንጂ ልዩ መብት ሊባል ያችልም። ሕወሓት ለመከፋፈል ስትፈልግ ልዩ መብት ብላ ትርክት መጀመሯ አስቂኝ ነው። የአዲስ አበባ ስያሜ መቀየር እና የከተማዋን ታሪካዊ ቦታ ከመቀየር አንፃር የተነሳው አገላለጥ በእራሱ የተደናበሩ ሰዎች ያወጡት ረቂቅ አዋጅ ነው። በመጀመርያ ደረጃ በአዲስ አበባ ውስጥ የተሰጡት ስሞችም ሆኑ የአዲስ አበባ የእራሷ ስያሜ እውን ታሪካዊ አመጣጥ የሌለው ባዶ ትርክት ከነበረ የታሪክ ሰዎች ይንገሩን እና እንመን።በሐሰት ታሪክ ግን የትም ሀገር ስም አይቀየርም። ይህንን ልሞክር የሚል ካለ የመስቀል አደባባይ እና የአብዮት አደባባይ ስያሜን ማስታወስ ነው።በሕልም እና በስሜት ሕዝብ ያጋጭልኛል ከሚል እሳቤ ብቻ ሕወሓት ይህንን ማሰቧን እራሱ የኦሮሞ ሕዝብ እና የአዲስ አበባ ነዋሪ ጠንቅቆ ይረዳል።
ባጠቃላይ ልዩ ጥቅም በሚል ቡልኮ የተሸፈነው የህወሓት ሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ አዲስ አበባ እና ኦሮምያን የተለያዩ ሀገር በማስመስል የአዲስ አበባ እና ዙርያዋን ያሉት የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ግንኙነት ኢትዮጵያዊ የሆነ የጋራ እሴት ሳይሆን የጥቅም ግንኙነት ብቻ ያላቸው አስመስሎ የማቅረብ ሙከራ ነው።መንግስት የተባለ አካል የመጀመርያ ስራው ዜጎቹን በእኩልነት የማስተዳደር፣ሕግ የማውጣት እና የማስፈፀም አቅሙን የማስመስከር መሆን ይገባው ነበር።ከእዚህ ውጭ አንዱን አስነስቶ በእዚህ አካባቢ ልዩ ጥቅም አለህ።አንተኛው ግን በምትኖርበት ከተማ ከእርሱ ያነሰ ጥቅም ነው የምታገኘው የሚሉ አባባሎች በእራሳቸው ህዝብን ለመከፋፈል የሚደረጉ አጀንዳዎች የማስቀጠል ሥራ አካል ካልሆኑ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም። አዲስ አበባ እና ኦሮምኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ ለመከፋፈል አትሞክሩ።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ላይ ልዩ ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ሕዝብ የምታገለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እኩል ልዩ ጥቅም እንዲኖረው ነው።
ይህንን ፅሁፍ የምደመድመው አንድ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አክቲቪስት በተናገረው ንግግር ነው። አባበሉ አሁን ሕወሓት እየዳከረበት ካለው የመከፋፈል ከንቱ ሥራ ፍሬ እንደሌለው በሚገባ ያሳየ ነው። አክትቪስቱ ያለው እንዲህ ነበር
"ሕወሓት የኦሮሞ ማሕበረሰብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ያለውን ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር በመቶዎች በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ ያለፈ እና ጠንካራ የደም ትስስር መሆኑን ህወሓት በደንብ ያወቀው አይመስለኝም።እነርሱ ራቅ ካለ አካባቢ ስለመጡ የእዚህ አይነቱ ጠንካራ ግንኙነት ታሪክ በደንብ የገባቸው አልመሰለኝም።የኦሮሞ ሕብረተስብ አሁን ሕወሓት እለያይበታለሁ እያለ የሚያቀርባቸው አጀንዳዎችን የመለያያ አጀንዳዎች እንደማይሆኑ ጥንት በሰራቸው ስርዓቶች ካፈረሳቸው ቆይቷል።ሕወሓት ትልቅ የመረጃ ክፍተት ላይ እንዳለ መረዳት አለብን" ነበር ያለው።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
Subscribe to:
Posts (Atom)
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.
His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...
-
በቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ፣ ስዊድን (ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አርኪኦሎጂ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና በሉንድ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...
-
አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን =============== ጉዳያችን /Gudayachn =============== ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵ...



