ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, June 21, 2021

ኢትዮጵያ ላትመለስ አንድ እርምጃ ወደፊት ሄዳለች።

ከጽሁፉ ስር የሚያገኙት ቪድዮ - 
           የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዶ/ር አብርሃም በላይ በርሔ በተገኙበት የቀረበው የጦብያ ኪነጥበብ ምሽት  
           ላይ የቀረበ ግጥም እና ዜማ ያገኛሉ።

ጉዳያችን/Gudayachn

ኢትዮጵያውያን ተሸማቀው የሚኖሩበት አስከፊ ዘመን ከዓመታት ውጣ ውረድ በኃላ፣ከተከታታይ ትውልድ መገበር በኃላ፣ከመቶ ሺዎች ስደት መንከራተት በኃላ፣ለአሥርተ ዓመታት የልጆቿ መውደቅ መነሳት በኃላ ዛሬ ሰኔ 14፣2013 ዓም ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪክዋ የመጀመርያ የተባለ ማንንም ሳይሸማቀቅባት እና ሳይገደድባት ሕዝቡ ተወካዮቹን ለመምረጥ ወደ ምርጫ ጣብያዎች ከ37 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ለሀገር አቀፍ እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚያገለግሏቸውን እንደራሴዎች ሲመርጡ ውለዋል። በእዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት ብቻ ለኢትዮያ ተውካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች የ445 ወንበሮች መቀመጫ ሕዝብ የመረጠ ሲሆን በመጪው ጳጉሜ 1 ደግሞ የ64 መቀመጫዎች ምርጫ ላልተደረገባቸው ጥቂት ቦታዎች ማለትም ለሱማሌ እና ሐረር የተቀመጡ ናቸው።የቀረው 38 ወንበር በትግራይ ክልል የሚደረግ ሲሆን በትግራይ የሚደረገው የምርጫ ሰሌዳ ወደፊት የሚገለጥ መሆኑን የምርጫ ቦርድ ገልጧል።

የምርጫ ቦርድ ይህንን ሥራ ለመስራት ግዙፍ የሰው ኃይል አንቀሳቅሷል።በእዚህም መሰረት ቦርዱ ከዛሬው ምርጫ ቀን በፊት ለምዝገባ  በመላው ሀገሪቱ በመሰረታቸው 48 ሺህ የምርጫ ጣብያዎች 152ሺህ700 የሰው ኃይል አሰማርቶ ምዝገባ ያደረገ ሲሆን፣በዛሬው ዕለት ብቻ 240ሺህ የምርጫ አስፈፃሚዎች አሰማርቶ ነበር።በእዚህ መሰረት ለዛሬው ምርጫ እስከ ምርጫ ድረስ 392 ሺህ 700 የሰው ኃይል ለምርጫ አስፈፃሚነት ምርጫ ቦርድ አንቀሳቅሷል።ከእዚህ በተጨማሪ 207 ሺህ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ሳጥኖች ጨምሮ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች በሁሉም የምርጫ ቦታዎች አድርሷል።

የምርጫውን ሽፋን በተመለከተ ጉዳያችን በፐርሰንት ለመለካት እንደሞከረችው በዛሬው ሰኔ 14 ቀን ብቻ ከተወካዮች ምክር ቤት (የፈድራል ፓርላማ ወንበሮች) 81.35% የሚሆነው የተመረጠ ሲሆን ጳጉሜ 1 የ64 ወንበሮች ምርጫ ሲጨመር 93% የፓርላማው ወንበር ምርጫ ይሸፈናል ማለት ነው።በቀጣይ የትግራይ ክልል ተወካዮች የ38 ወንበር (7%) ሲጨመር  የፓርላማው ሙሉ 547 ወንበሮች ይሸፈናሉ ማለት ነው።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ፓርላማ ስብሰባ ከመከፈቱ በፊት 93% የፓርላማው አባላት ስለሚሟሉ አዲሱ መንግስት የመመስረት ስልጣን ይኖረዋል።ምናልባትም በያዝነው ክረምት የትግራይ ሁኔታ ተሻሽሎ የምርጫ ሰሌዳው ሊወጣ ይችላል።ይህ ግን የትግራይ ሕዝብም በህወሓት የደረሰበትን የአዙሪት የግጭት ድግስ ሰብሮ በቃኝ ልጆቼን ከአሁን በኃላ ሕዝብ ከህዝብ ለሚያባሉ የቀድሞ ህወሓት ርዝራዦች አልገብርም የሚል ቆራጥ እርምጃ ይፈልጋል።በምንም መለኪያ ብንመለከተው ግን ኢትዮጵያ ላትመለስ አንድ እርምጃ ወደፊት ሄዳለች።

በጦብያ የጥበብ ምሽት ላይ የቀረበ ግጥምና ዜማ
ዜማ - የድምፃዊ አብርሃም ገብረመድህን ዜማ በዕንቁ ዜማ ባንድ  ተቀናብሮ የቀረበ 
(በዝግጅቱ ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሊቀመንበር ዶ/ር አብርሃም በላይ በርሔ የተገኙበት ነው) 
ምንጭ - አርት ቲቪ 

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)