Another savage act of ISIS.
A heart breaking news.
Terrorist Organisation ISIS has released another graphic video showing the mass execution of 30 Ethiopian Christians in Libya.
ልብ የሚሰብር ዜና
እስላማዊ አሸባሪ አይ ኤስ ኤስ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ሊብያ ውስጥ በግፍ አረዳቸው።በጥይት ደበደባቸው። ይሄው ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን ሰልሳ ደቂቃ የፈጀ ኢትዮጵያውያንን ሲቀላ እና በጥይት ሲፈጅ ደማቸው ወደ ባህር ሲቀላቀል አሳይቷል።ይህ በእንግሊዝኛ እና አረብኛ መግለጫ የሰጠው የአሸባሪ ድርጅቱ ቪድዮ ላይ ''የመስቀል ተከታዮች ከጠላታችን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን'' የሚል ለጥፎ ተነቧል።
ከወራት በፊት በግብፅ ክርስቲያኖች ላይ ለተፈፀመው ተግባር ግብፅ ሊብያ የሚገኘውን የአሸባሪውን ይዞታ መደብደቧ እና የሃዘን ቀን ማወጇ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ መንግስት የላትም! አዎን የላትም!!!! አሁን ኢትዮጵያውያን በእራሳችን እኛነታችንን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማስከበር ከመነሳት ሌላ እንጥፍጣፊ የቀረን ተስፋ የለም!
ዛሬ ዕሁድ ሚያዝያ 11/2007 ዓም የዓለም የዜና አውታሮች እግረ መንገዴን ካየሁት ውስጥ -ሲኤን ኤን ፣አልጀዚራ የሩስያው ቲቪ ''አርቲ'' እና የግብፅ ዜና አገልግሎትሰላሳ ''ኢትዮጵያውያን'' ልብ በሉ ሁሉም የጠቀሱት ''ኢ ት ዮ ጵ ያ ው ያ ን'' ተገደሉ እያሉ ነው።አራጁ አሸባሪውም ''ኢትዮጵያውያንን'' ቀላሁ እያለ ነው ያቅራራው።
ይህ ይባል እንጂ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዛሬው እሁድ የምሽት ዜናው ላይ የቀረበው እንዲህ ነበር።በመጀመርያ የኢትዮጵያውያኑ የመቀላት ዜና በቀዳሚ ዜናነት ሳይሆን ከሌላ ዜና በኃላ ዘግይቶ ነበር የተነበበው።
በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች በሰበርነት ከማውራታቸው ጋር ስታነፃፅሩት ልባችሁ አሲድ ሲረጭ ይሰማችኃል። ቀጥሎ የቀረበው ዜና ላይ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ተገደሉ ሳይል ''የተደረገውን ግድያ የኢትዮጵያ መንግስት ያወግዛል'' ይልና ''የሞቱት ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አላረጋገጠም'' በሚል ስሜት አልባ ዜና የአንድ
ደቂቃው ወሬ ያበቃል።
ይህ እንግዲህ -
1ኛ/ ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎችም ዓለም ዓቀፍ የዜና አውታሮች ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን እየተናገሩ፣
2ኛ/ ገዳዩ አሸባሪ ድርጅት እራሱ ኢትዮጵያውያንን ገደልኩ እያለ ያቅራራበትን የ30 ደቂቃ
ፊልም በአረብኛ እና እንግሊዝኛ የለቀቀው ቪድዮ ኢህአዴግ/ወያኔ እጅ ገብቶ እያለ፣
3ኛ/ ሰማዕትነት የተቀበሉት ወጣቶች አንዳንዶቹን በአይን የምናውቃቸው እስኪመስለን
ድረስ አይናቸው ሲንከራተት እና የፊት ገፅታቸው ኢትዮጵያዊነታቸውን በግልፅ እያሳየ ነው እንግዲህ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ኢትዮጵያዊነታቸው ሊረጋገጥ ነው የሚለን።
ግን ኢህአዴግ/ወያኔ ለምንድነው በኢትዮጵያውያን ደም የምትቀልዱት????
ኢትዮጵያ እኮ ለግብፅ ክርስቲያኖች ለመሰዋት የዘመቱ መሪ የነበራት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ እኮ በየመን ለነበሩ ለናግራን ክርስቲያኖች የዘመቱ መሪዎች የነበሯት ሀገር ነች።
ኢህአዲግ/ወያኔዎች ኢትዮጵያን በእዚህ አይነት ጭካኔ ለምን ታደሟታላችሁ?
ደግሞስ ለእዚህ አይነቱ ሀገራችንን በመላው ዓለም ላስጠራ እኩይ ተግባር በመንግስት ፕሮቶኮል ደረጃስ በቃል አቀባይ ነው የሚነገረው ወይንስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ (ስልጣናቸው ባይጣራም) ደረጃ ነው ለኢትዮጵያ ሕዝብ መገለፅ ያለበት?
እነዚህ ወገኖች እኮ በሀገራቸው እና በወገናቸው መሃል ሆነው መስራት ቢችሉ ባልተሰደዱ ነበር።እንደሚለፈፍልን አድገን ቢሆን ኖሮ ባልተሰደዱ ነበር።ለሞታቸው ተጠያቂነት ፈፅሞ ንፁህ ነው የሚል አንድም ሰው አይገኝም።
የኢትዮጵያ ህዝብስ ውሳኔህ ምንድነው? ልጆችህን የመጠየቅ ቢያንስ አደባባይ ወጥተህ ስለልጆችህ እና ስለጠፋችው ፈፅማም ልትከስም ስለምታጣጥረው ኢትዮጵያ ማልቀስም አቃተህ?እሪ መንግስት የለንም!!! ማለት አቃተህ??? ምነው አስከሬን ከቤልጅየም በምሽት ተቀብለህ በቦሌ መንገድ አላለቀስቅም ነበር እንዴ? እንደ በግ ለታረዱ ልጆችህ ኡ ኡ ታ! ደረቀብህ? ለምትፈራው ሰው ብቻ ነው የምታለቅሰው?
ኢትዮጵያውያን ሁሉ እግዚአብሔር ያፅናን።