አንዳንድ ጊዜ ትምህርት ሰውን አይቀይርምን? የሚል ጥያቄ ብጠይቅ ከሞኝ እንዳትቆጥሩኝ ስጋት አለኝ።ምክንያቱም ትምህርት ሰውን ማነፁ ብቻ ሳይሆን የማመዛዘን እና ትክክለኛውን ነገር ከበቂ ማስረጃ ጋር የማቅረብ ብሎም ሃሳብን እገሌን ላስደስት ከሚል ከንቱ አስተሳሰብ የማራቅ ሁሉ ክህሎትን ያላብሳልና።አሁን ያለንበት ዘመን የመረጃ ዘመን ነው። አሁን ያለው ትውልድ ደግሞ መረጃ የማግኘት ውሱንነት ቢገጥመው መረጃን ሙሉ በሙሉ ማፈን የማይቻልበት ጊዜ ነውና ቢያንስ የተጋነነ መረጃን ከትክክለኛው ለመለየት ችግር የለበትም።
ይህንን ለማለት ያነሳሳኝ ጉዳይ በአቶ መለስ ላይ የሃገር ቤት የመገናኛ ብዙሃን እና እጅግ ጥቂት ምሁራን የሚነግሩን ፈፅሞ ከእውነታው የራቁ ጉዳዮች ናቸው። አንዳንዶቹን ጉዳዮች እንድያውም እራሳቸው አቶ መለስ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ የማይቀበሉት ሊሆን ይችላል።በእዚህ ፅሁፍ ላይ ላነሳው የፈለኩት ጉዳይ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ደጋግሞ የሚነገረው ''አቶ መለስ የአረንጓዴ ልማት እና የልማታዊ መንግስት መርህ አመንጪ ናቸው'' የሚለውን ንግግር ነው።አቶ መለስ ግን የሁለቱም ፅንሰ ሃሳቦች አመንጪ ወይም ፈጣሪ አይደሉም።የእዚህ አይነቱ አባባል ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶችን መነሻቸውን ያደርጋሉ።አንደኛው የአቶ መለስን ስብዕና ከሚገባው በላይ ለመካብ ከሚደረግ ጉጉት ሲሆን ሁለተኛው ግን ''ነገር ሲደጋገም ወደ መታመንነት ይቀየራል'' ከሚል አስተሳሰብ ለመረጃ የራቀው ሕዝብ አምኖ ይቀበላል ከሚል አስተሳሰብ ነው።ሆኖም ግን ማናቸውም የስብዕና ግንባታ ሥራ ሚዛናዊ ቢሆን ምን ያህል ባማረበት ነበር።
አቶ መለስ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ''ግኝት'' ተብለው የቀረቡት ''የአረንጓዴ ልማት እና የልማታዊ መንግስት መርህ'' አግኚ ሆነው ቢሆን ኖሮ እንደ ኢትዮጵያዊነት ሁላችንም ደስ ባለን ነበር።ኢቲቪ እንደሚነግረን አለመሆናቸው ግን የሚታይ ሀቅ ነው።አለማችን በልማት ዙርያ ያጠነጠኑ ጥናቶች ላይ ማተኮር ከጀመረች ሰነባብታለች።ልማት ከሚለው ፅንሰ ሃሳብ በፊት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጡት የምጣኔ ሀብት እድገት(growth) ከቁጥር አንፃር መለካት የሚቻል ብቻ ነበር። ይህም የአንዲት ሀገር ማደግ የሚለካው ከአጠቃላይ አመታዊ ምርት አንፃር ብቻ ነበር።ሆኖም በተለይ ከ1970ዎቹ ወዲህ የልማት ፅንሰ ሃሳብ ብዙ ትኩረትን እየያዘ መጣ።በተለይ የሀገሮች አጠቃላይ ምርትን በማሳየት ብቻ የሀገርን እድገት አለማመላከቱ ከተረጋገጠበትመንገዶች ውስጥ አንዳድንዶቹ አጠቃላይ ምርቱን ማን አመረተው? ምን ያክሉ ሕዝብ ከምርቱ ተጠቃሚ ነው? የእያንዳንዱ ግለሰብ የዓመት ገቢ ስንት ነው? የጤና፣የትምህርት፣የገበያ ወዘተ ዕድል የሚያገኘው ሕዝብ ስንት ነው? ሃሳብን የመግለፅ የነፃነት ደረጃ ምን ያህል ነው? ወዘተ የሚሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች መመለስ ያለመቻሉ እውነታ ነው።
አቶ መለስ በምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ በአብዛኛው እድገትን የሚተረጉሙት ከአጠቃላይ ምርት አንፃር ብቻ መሆኑ እራሱ በዘመኑ የልማት ጠበብት አንፃርም ትልቅ ተግዳሮት እንዳለበት ልብ ለማለት ይቻላል።የሀገሪቱን የንግድ ዘርፍ እንደ ኢፈርት የመሳሰሉ የኢህአዲግ ድርጅቶች የአንበሳውን ድርሻ ይዘው ባለበት ምጣኔ ሀብት ውስጥ የአጠቃላይ ሃገራዊ ምርትን በማውሳት የሀገሪቱን ዜጋ አጠቃላይ እድገት እና ልማት ያሳያል ማለት በእራሱ በስህተት የተሞላ መሆኑን ለመገንዘብ ብዙም ምርምር አይጠይቅም።
በተለያየ ጊዜ በዘርፉ ባለሙያዎችም ሆነ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምርምር ከተደረገበት በኃላ አዳዲሶቹ የልማት ፅንሰ ሃሳቦች ወደ አለምአቀፍ መርህነት የመቀየራቸው ዕድል ከፍተኛ ነው።ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የአንዲት ሃገርን መሻሻል በትክክል የሚለካው የእድገት (growth) አስተሳሰብን በልማት (development) አስተሳሰብ መቀየሩ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ካስተዋወቁት ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ድርጅት(UNDP) አንዱ እና ዋናው ነው።የአረንጓዴ ልማት የወቅቱ የአለማችን የልማት ችግር መፍትሄ መሆኑ በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ እና ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ደረጃ የታመነበት ግኝት ለመሆኑ የተባበሩት መንግሥታት አካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር (UNEP) በድህረ-ገፁ ላይ እንዲህ ይገልፀዋል-
''Designed as a timely and appropriate policy response to the economic crisis, the (Global Green New Deal)
GGND proposal was an early output from the United Nations’ Green Economy Initiative. This initiative, coordinated by UNEP, was one of the nine Joint Crisis Initiatives undertaken by the Secretary-General of the UN and his Chief Executives Board in response to the 2008 economic and financial crisis.''www.unep.org/greeneconomy/Portals/88/documents/ger/GER_1_Introduction.pdf,page 15.
የአቶ መለስ ግኝት ነው የተባለው ''የአረንጓዴ ልማት እና የልማታዊ መንግስት መርህ'' አቶ መለስ ስለጉዳዩ ሳያወሱ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ብዙ የለፉበት እና በመጨረሻም በአለም አቀፍ ድርጅቶችም ሆነ በከፍተኛ የምርምር ተቋማት እውቅና የተቸራቸው ሃሳቦች ናቸው። ስለእዚህ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ከተቻለ ''አቶ መለስ የአረንጓዴ ልማት እና የልማታዊ መንግስት መርሆዎችን ይደግፉ ነበር'' ማለት ማንን ገደለ? ''የመርሆዎቹ አስገኚ እና ለአፍሪካ ያስተዋወቁ ናቸው'' ማለት ግን ገሃዱ አለም የደከመበትን ሥራ ማጣጣል አይደለም ወይ?
በመጨረሻም ለናሙናነት የአረንጓዴ ልማት እና የልማታዊ መንግስት ሃሳቦች በተባበሩት መንግሥታት አካባቢ ጥበቃ መርሃግብር (United Nations Environment Programme) ''በአረንጓዴ ልማት'' ላይ የማንቸስተር ዩንቨርስቲ ደግሞ በ''ልማታዊ መንግስት'' ምንነት እና የት-መጣነት ላይ የሰጡትን ማብራርያ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።
የአረንጓዴ ልማትን በተመለከተ
''የአረንጓዴ ልማት የምጣኔ ሀብት ሽግግር ደረጃዎች'' በሚል አርእስት ስር የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር (United Nations Environment Programme) 2011 ሪፖርት የአረንጓዴ ልማት ፅንሰ ሃሳብ ብቸኛ የአለማችን አማራጭ የእድገት መንገድ መሆኑን ምሁራኑ ማሳሰባቸውን ያመላክታል። http://www.unep.org/greeneconomy/Portals/88/documents/ger/GER_1_Introduction.pdf, page 14
''....This recent interest in a green economy has been
intensified by widespread disillusionment with our
prevailing economic paradigm, emanating from the
many concurrent and recent crises – particularly the
recession of 2008-2009. At the same time, increasing
evidence is pointing to an alternative paradigm, in
which increased wealth does not lead to growing
environmental risks, ecological scarcities and social
disparities.
Transitioning to a green economy has sound economic
and social justification. As this report demonstrates,
there is a strong case for governments as well as the
private sector to engage in this economic transformation.
For governments, this transition would involve leveling
the playing field for greener products by phasing out
harmful subsidies, reforming policies and incentives,
strengthening market infrastructure, introducing
new market-based mechanisms, redirecting public
investment, and greening public procurement. For the
private sector, this transition would involve responding
to these policy reforms and incentives through increased
financing and investment, as well as building skills and
innovation capacities to take advantage of opportunities
arising from a green economy. ''
page 15 '' ....UNEP’s green economy report, Towards a Green Economy,aims to debunk several myths and misconceptions about
“greening” the global economy, and provides timely and
practical guidance to policy makers on what reforms
they need to unlock the productive and employment potential of a green economy.Perhaps the most prevalent myth is that there is
an inescapable trade-off between environmental
sustainability and economic progress. There is now
substantial evidence that the greening of economies
neither inhibits wealth creation nor employment
opportunities. To the contrary, many green sectors
provide significant opportunities for investment, growth,
and jobs. For this to occur, however, new enabling
conditions are required to promote such investments in
the transition to a green economy, which in turn calls for
urgent action by policy makers.
A second myth is that a green economy is a luxury only
wealthy countries can afford, or worse, a ruse to restrain
development and perpetuate poverty in developing
countries. Contrary to this perception, numerous
examples of greening transitions can be found in the
developing world, which should be replicated elsewhere.
Towards a Green Economy brings some of these
examples to light and highlights their scope for wider
application.
UNEP’s work on the green economy raised the
visibility of this concept in 2008, particularly through
a call for a Global Green New Deal (GGND). The GGND
recommended a package of public investments and
complementary policy and pricing reforms aimed at kick-starting a transition to a green economy, while
reinvigorating economies and jobs and addressing
persistent poverty (Barbier 2010a). Designed as a timely
and appropriate policy response to the economic
crisis, the GGND proposal was an early output from the
United Nations’ Green Economy Initiative. This initiative,
coordinated by UNEP, was one of the nine Joint Crisis
Initiatives undertaken by the Secretary-General of the
UN and his Chief Executives Board in response to the
2008 economic and financial crisis.''
ልማታዊ መንግስትን በተመለከተ
''ልማታዊ መንግሥታት'' በሚል ርዕስ ስር በየካቲት 2012 በማንቸስተር ዩንቨርስቲ በሚታገዘው (ESID) የምርምር ማዕከል ''ሊትረቸር ሪቪው'' ላይ ፅንሰ ሃሳቡ ቀደም ብሎ በተለያየ ምሁራን ሲጠና የነበረ መሆኑን ይጠቁማል።
''....One of the central debates around developmental states has focused on the controversy
over how and, indeed if, states should intervene in the market, and what role the state
should play in development (White and Wade 1988). Johnson (1999) recalls the hostility
with which his notion of a developmental state was received by Anglo-American economists
(p.34) and discusses how the Japanese experience he described was ‘inconvenient’ for both
sides of the ideological cold war divide (p.49). These debates have gradually shifted to an
acceptance of the significance of the states’ role, but the nature of this role continues to be
argued over (Kohli 1994, p.1269). ''
ኦስሎ
1 comment:
Great great point!!!!
Post a Comment