የ ዛሬዋ የ እሁድ ምሽት ከታማኝ የ ኦስሎ የ ኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ጋር ያሳለፍኩት ምሽት ነበር። ምንም እንኳን መርሃግብሩን በሙሉ ለመፈፀም ባልችልም የ አክትቪስት እና አርቲስት ታማኝን በ ቪድዮ የተደገፈ ገለፃ ግን ለመከታተል እድሉ ገጥሞኛል።
ገብስማ ፀጉሩ
ከ ነጭ
ሸሚዝ እና
ሽሮ መልክ
የያዘ ክራቫት
ጋር ታማኝን
ግርማ ሞገስ
አጎናፅፎታል። ታማኝ
ወደ መድረኩ
ሲመጣ ከ
ታላቅ አክብሮት
ጋር ከ
አምስትመቶ በላይ
የሆነው ታዳሚ
ከመቀመጫው ተነስቶ
ተቀበለው። ታማኝ
አፀፋውን እየመለሰ
ምስጋናውን ገለፀ።
ቀደም ብለው
ከጎናቸው ከነበረው
ሰው ጋር
ይነጋገሩ የነበሩ
ሰዎች በፀጥታ
ወደመድረኩ ማስተዋል
ጀመሩ።ታማኝ ሰላምታውን
በ አማርኛ
ብቻ አልነበረም
ያቀረበው ''አሰላም
አለኩም '' በማለት ለ
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን
ያለውን አክብሮት
ሲገልፅ ሞቅ
ያለ ጭብጨባ
ተቸረው። ላፕቶፑን
አስተካክሎ ከ
ጀርባው በኩል
ወዳለው ስክሪን
ተመለከተ ትክክል
ነው። ንግግሩን
ቀጠለ እና
እንዲህ አለ-
''ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው
በ ስቶኮልም
እና በ
ጄኔቭ ከተመለከትቁት
ሕዝብ ኦስሎ
ዛሬ የበላይነቱን
ይዟል።'' ጭብጨባ
አጀበው ቀጠለና :-
''--እኔ አርቲስት
ነኝ በ
አርቲስትነት መኖር
እችል ነበር።
መፅሐፉ የሚለው
ከፊትህ ውሃና
እሳት ቀርቦልሃል
እጅህን ወደወደድከው
ጨምር ነው።እኔ
እጄን ወደ
ውሃ ከትቼ
በ አርቲስትነቴ
እየደነስኩ መኖር
አያቅተኝም ነበር
።ነገር ግን
የ እውነት
ጉዳይስ? የ
ኢትዮጵያ ጉዳይስ?
ዝም ብሎ
የሚኖር ህሊና
አለን? ----እድሜዬ እንደምታዩኝ
ላይሆን ይችላል።
ፖለቲካ ያቃጥላል
፣ያናድዳል። ሆኖም
ግን እስከመጨረሻ
ለመፅናት ነው
ቃል የገባሁት።''
ቀጠለናም የ
ሙስሊም ወንድሞቻችን
ጉዳይ ማንም
ችላ ሊለው
የማይገባ መሆኑን
''በ ሰላማዊ
መንገድ 'ድምፃችን
ይሰማ' ማለታቸው
እንዴት አድርጎ
ነው አሸባሪ
የሚያደርጋቸው? ባለፈው
የቀረበውን ድራማ
አይታችሁታል።አንድ ላይ
እኛም ድምፃችን
ይሰማ! እንበል''
ሲል በ
አዳራሹ የነበረው
ተሰብሳቢ ሁሉ
በአንድ ላይ
''ድምፃችን ይሰማ!
ድምፃችን ይሰማ!''
ሲል አዳራሹን
አናወፀው።
ኦስሎ ለ ኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ መርሃግብር ከተገኘው ሕዝብ በከፊል (photo GUDAYACHN BLOG EXCLUSIVE)
ኦስሎ ለ ኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ መርሃግብር ከተገኘው ሕዝብ በከፊል (photo GUDAYACHN BLOG EXCLUSIVE)
በ
መርሃግብሩ ላይ
በቪድዮ የተደገፈው
የ አቶ ሃይለማርያም
እና የ
አቶ መለስ
ተመሳሳይ ንግግሮች
በጣም አዝናኝም
አስገራሚም ነበሩ።
አቶ መለስ
በ ሕይወት
እያሉ ለ
ፓርላማ ያደረጉት
ንግግር አቶ
ሃይለማርያም እንዴት
ከ አቶ
መለስ እረፍት
በኃላ እንደደገሙት
የሁለቱንም ንግግር
እያሳየ አስገረመን።
ከሁሉ ያሳቀን
ግን '' አቶ ሃይለማርያም
ከ ኢትዮጵያ
ሕዝብ ያገኙት
ስም ምን
እንደሆነ ታውቃላችሁ?''
አለና መልሱን
መለሰልን ።''
ባጃጅ ነው
የሚባሉት ለምን
መሰላችሁ? ባጃጅ
ሶስት እግር
ነው ያለው
አቶ ሃይለማርያምም
በ ሶስት
ምክትል ጠቅላይ
ሚኒስትር ስለሚመሩ
ባጃጅ ተብለዋል
በ ኢትዮጵያ
ሕዝብ ----ወደ ስልጣን
ሲመጡ ተስፋ
ነበረኝ በኃላ
ስመለከት ግን
በጣም ጎበዝ
ኮራጅ ሆኑብኝ
አንዳንድ ተማሪ
አለ አንዴ
አይቶ እጥብ
አድርጎ የሚኮርጅ
አቶ ኃይለማርያምም
አነጋገራቸው፣ውሃ አጠጣጣቸው
፣እጅ አጣጣላቸው
ሁሉ አቶ
መለስን ነው
የሆኑት።'' ሳቅ አጀበው።
አክቲቪስት እና
አርቲስት ታማኝ
በዛሬው መርሃግብር
ብዙ ማለት
እንደማይፈልግ ቶሎ
ወደ እሳት
የገንዘብ ማሰባሰብያ
መርሃግብር እንደሚገባ
ገትልፆ ንግግሩን
ባይገታው ኖሮ
ታዳሚው ገና
እንዳልጠገበ ከፊቱ
ይነበብ ነበር።
በመጨረሻ ግን
ታማኝ ዛሬ
ካሳየን ፎቶዎች
ውስጥ በ
አድዋ ዘመቻ
ጊዜ ዘማች
ኢትዮጵያውያን( ክርስትያን
እና ሙስሊም
ኢትዮጵያውያን) በ
አራዳ ጊዮርጊስ
ፊት ለፊት
ክርስትያኖች ወደ
ቤተክርስቲያን ሙስሊሞች
ወደ መስጊድ አቅጣጫ
ፊታቸውን እንዴት
አዙረው ለሀገራቸው
ለየ አምላኮቻቸው
እንደፀለዩ እና ወደ ውግያው እንደሄዱ በ
ወቅቱ ከነበረው
ፎቶ ጋር
እያመሳከረ ያሳየን
ትእይንት እጅግ
መሳጭ እና
በመርሃግብሩ የተገኙትን
ሙስሊም ወንድሞቻችንን
ብቻ ሳይሆን
የ ክርስቲያን
ኢትዮጵያውያንን ልብ
የገዛ ነበር።
ታማኝ ሲናገር
ኢትዮጵያዊነት ውስጡ
ይንቀለቀላል።አዎን የ
ፖለቲካ ሰው
አይደለም ወይንም
ፖለቲካ ሙያው
አይደለም።ሀገር መውደድ
ግን ሌሎች
ፖለቲካን እሳት ብለው ውሃ
እየተራጩ ከንፈር
ሲመጡ ፣ታማኝ
እውነትን ብሎ
እጁን እሳት
ውስጥ ከቶ
ስለ እውነት
ለመሞት ቆርጦ
የተነሳ ውድ
ኢትዮጵያዊ ነው።
''ወይ እስክንድርን
ሁን።አለበልዝያ ስሜን
መልስ'' ነው
ያለው ታላቁ
እስክንድር አንድ
በፍርሃት ሲርድ
ላገኘው ወታደሩ።
የ ዛሬዋ
የ ታማኝ
ምሽትም ''ወይ
ታማኝን ሁኑ
አለበለዝያ ስሙን
መልሱ'' የምታሰኝ
ነበረች።
ጌታቸው በቀለ
ኦስሎ
ኖርዌይ
ጌታቸው በቀለ
ኦስሎ
ኖርዌይ
2 comments:
you r a true journalist. the way you narrate is fantastic.
grum tihuf new be agerachin lay hasabachinn eygeletn endinnor amlak yrdan yenegewan ethiopia asnafekegn malete hulum hasabun benetanet yemigeltbat malete new endemimeslegn antem yepoletica sew atmeslegnm
Post a Comment