Tuesday, February 5, 2013

ወንድምህን አታባረው


በቅድምያ ይህንን ግጥም ጉዳያችን ጡመራ (GUDAYACHN BLOG) ላይ እንዲለጠፍለት ለላከልኝ ማኔክስ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።

የግጥሙ ደራሲ ማኔክስ 
ከሀገረ ስዊድን
FACE BOOK link- https://www.facebook.com/manex.yonis


ወንድምህን አታባረው
አንድ ቤት ነበረ
በደም ነው አሉ የተመሰረተ። የልጅ ልጆች በዙ
ባለቤት ነን አሉ።
ብለውም አልቀሩ
ድንበር ተካለሉ።
እንዲህ ተባሉ በአበው ሊያዳምጡ ተሰባስበው። ስትፈጠር በባርኮት

ከቀኖች ሁሉ በዚያ ቀን ለከት ያጣ ውበቷ
አማለለ ጎበዞችን። እናም. . . አሉ
ሽማግሌዎቹ አበው ሲያወሩ ታሪኳን
በትዝታ ሰጥመው። እናም. . .
ብዙ ሆነው መጡ
ከውበቷ ሊቋደሱ አባትነትን ሊያገኙ
ድንግልናዋን ሊወርሱ። ያቺ የውበት ማማ
ስንዱ እመቤት በጥበቧ የጉብሎቹን ማማር አይታ የቤቷን ክፍል አብዝታ ስታበቃ አምራ ተሰናድታ
ተቀበለቻቸው በዕልፍኟ ሊደሰቱ በድንግል ውበቷ ዘር ሊሆኑ ከአብራኳ።
ዘመናት ተሻግሮ ትውልድ
በአንድ ጉድጓድ ተቀብሮ እትብት

የብዙ አባት ልጆች የአንድ እናት ፍጡሮች
ይኖሩ ነበር በዚያች ቤት
በአንድነት ሆነው ባለቤት ሲጣሉ ተኳርፈው
ሲፋቀሩ ተጋብተው

ተናክሰው ተቃቅፈው በአንድነት
ዘምረው ነበረ በሲቃ ውበት ነው ብለው ልዩነት። ዘመኑን አበው ሲዋጁት
አፋቸው ሞላ በምሬት
እንዲህም አሉ
. . . በእሳት ላንቃ አንደበት የአባቶቻቸውን ታሪክ ለረሱት
አንገታቸውን ቀና ላደረጉት ላሰከራቸው እኔነት
አዎ
! ቤቱ የናተው ነው ውርሳችሁ!
ቅርሳችሁ!
ዝክራችሁ!
ግና ያስጨንቃል
ጥፋትን አርግዟል
ጥቁር ደመና አዝሏል
ነጎድጓድ አይሎአል
ተከባብሮ መኖር አንገሽግሿችኃል
ደም እንደጠማው ውሻ አክለፍልፏችኃል
የጥላቻ ዝማሬአችሁ ምድሪቷን ከድኗታል።
.. .
ለተሰበሰቡት ልጆቿ ለደም አጥንት ክፋዯቿ
እንዲህ አሉ አበው
አንገታቸውን አቀርቅርው ሰማይ ላይታረስ
ደመና ላይዘገን

አትዘምሩ ለማይበጀው ወንድምህን አታባረው።

ማኔክስ

ምንም በማያቁት የአባቶቻቸው ቋንቋ እየታየ እትብታቸውን ከቀበሩባት አፈር፣ጭቃ አቡክተው ካደጉባት ምድር ፣በልጅነት አንደበት ፊደልን ከቆጠሩባት ት/ቤት እና በግዳጅ ከማንኛውም ቦታ ለሚፈናቀሉ እና ለተፈናቀሉ ወገኖቼ መታሰቢያ ትሆን ዘንድ ፃፍኳት። በተለይ የሚነገራቸው ታሪክ ለሚያስጨንቀኝ በቅርቡ ከቤኒሻንጉል ለተፈናቀሉት ህፃናት መታሰቢያ ትሁንልኝ። 
Post a Comment

GUDAYACHN BLOG started on August 28/2011 ኢሜይል አድራሻዎን በመሙላት ጽሁፎቹን መከታተል ይችላሉ/Follow by Email

በብዛት የተነበቡ/Popular Posts

ጉዳያችን በፌስ ቡክ ገፅ / GUDAYACHN ON FACE BOOK

https://www.facebook.com/gudayachn/?pnref=story