ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, August 21, 2012

የ ማስታወሻ ደብተሬ ስለ አቶ መለስ


አቶ መለስ ዜናዊ እንደ ኢሳት ቴሌቭዥን ከ አንድ ወር በፊት እንደ ኢቲቪ ደግሞ ትናንት ነሃሴ 14/2004 ዓም ከምሽቱ(5:40) አምስት ሰዓት ከ አርባ ላይ አርፈዋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት መግለጫ ¨በ አቶ መለስ ዜናዊ አለጊዜው መሞት የ ኢፍድሪ መንግስ እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ እጅጉ ያዝናል¨  መግለጫው በመቀጠል ¨ የሃገራችን ህዝቦች የ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቲርን መታመም ከሰሙ በኋላ በ እየእምነታቸው በጸሎት መልካም ምኞታቸውን ሲገልጹ እንደቆዩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና የ ኢፍድሪ መንግስት  በከፍተኛ አድናቆት ተገንዝቧል።¨ ብሏል።

እግዚአብሄር ነፍስ ይማር። ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

አቶ መለስ በ በጎም ሆነ በጎ ባልሆነ መልክ በ ሃገራችን ላይ ብቸኛ ተጽኖ ፈጣሪ(influential) ሰው የነበሩ ለመሆናቸው አሌ የማይባል ሃቅ ነው።

እኔ ከተናገሩዋቸው ንግግሮች ሶስት ንግግሮችን ሳያብራሩልን ማለፋቸው ወይንም በ መጽሃፋቸው ላይ ሳይገልጹልን ማለፍ አልነበረባቸውም   እላለሁ።
እነኚህ ንግግሮች አንድ ቀን ከ ስልጣን ዘመናቸው በኋላ ያስረዳሉ ብየም እጠብቅ ነበር።ምናልባት ያልታተመ መጽሃፍ ካለ አንድ ቀን ታትሞ ለማንበብ ለታሪክ ተመራማሪዎችም የመረጃ ምንጭ ይሆናል ብየ አስባለሁ።
በተለያየ ጊዜ ከተናገሩት:-

፩ ¨እንደ ግለሰብ፣ እንደ መለስ በ አንድ ጉዳይ ላይ የማስበው ሃሳብ አለ ወደ ፓርቲዪ ስመጣ እንደ ኢህአዲግ የማስበው ሃሳብ አለ።''(ለ አዲስ አመት በ አል ላይ ከተናገሩት)
የትኞቹ ይሆኑ የ ፓርቲው ሃሳቦች? የትኞቹስ ይሆኑ የ እሳቸው ሃሳቦች ግን ፓርቲው ያልተቀበላቸው?
፪ ¨ወጣት ሳለሁ ሁሉን ነገር በ አንድ ቀን ካልሆነ፣ ካልተሰራ ብዬ አስብ ነበር። አሁን በ ጉልምስና ዘመኔ ላይ ሆኘ ስመለከተው ግን የተለየ አስተያየት አለኝ። እግዚአብሄርን መፍራት፤ ቆጠብ ማለት ከወጣትነት በኋላ የሚመጣ ስሜት ነው።¨ (በ አፍሪካ ህብረት ከ አፍሪካ ለተሰበሰቡ ወጣቶች በ እንግሊዝኛ  ከተናገሩት)
፫ ¨ አንድ ነገር ስታፈርሱ እያከበራችሁ ማፍረስ አለባችሁ በ አንድ ቀን ሁሉ ካልተቀየረ ማለት የለባችሁም እያከበሩ ማፍረስ ተማሩ!''  (በሚልንየም አዳራሽ ለ ደጋፊዎቻቸው የ ፓርቲው አባላት የተናገሩት)::

ከላይ የተነገሩት ንግ ግሮች አቶ መለስን በ ሚድያ ከምናውቀው ስብዕናቸው በተለየ አንድ ያልተነገረን  ግን በ ተለያዩ ሰዎችም ይሁን ሌሎች ሃይሎች ጣልቃ የገቡበት ጉዳዮች አሉ እንዴ? እላለሁ።
ከ ሶስቱ ያልተብራሩ ንግግሮች በተጨማሪ በደንብ ያልተብራራው እራሱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው።
የ አቶ መለስ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ''አብዮታዊ ዲሞክራሲ¨ እራሱ በደንብ የገባው ሰው ኢህአዲግ ውስጥ ያለ አይመስለኘም። ምክንያት ብዙዎቹ የ ፓርቲው ሰዎች የ እሳቸውን የ መድረክ ንግግር እየመዘዙ ከ ማስተጋባት ያለፈ የ ፖለቲካውን መሰረታዊ ፍልስፍና ስለማያስረዱ። አሁንም የ እሳቸው በበለጠ ሳያብራሩት ቢያንስ በደንብ የሚያብራራ ሰው ሳይተኩ ማረፋቸው እንደገና አሁንም ¨አብዮታዊ ዲሞክራሲ¨ላልገባን በ ሚልዮን ለምንቆጠር ¨ጭቁን ህዝቦች¨ የ ፖለቲካው ፍልስፍና በደንብ እንዲከለስ ለመጠየቅ ግድ ይለናል።
ለ አቶ መለስ እረፍተ ነፍስን፤ ለ ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይስጥልን።
አበቃሁ።

በአማራ ክልል በሚደረገው ጦርነት ሳብያ የአማራ ክልል ህዝብ ላይ እየደረሰ ስላለው ሰቆቃ ያልሰማነው ከሰማነው ይበልጣል።

መከላከያ ክልሉን ለቆ ይውጣ የሚለው  አባባል የአማራ ክልል ጥያቄ ነው? ========== ጉዳያችን ምጥን ========= ወቅታዊው ሁኔታ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ትልቁ አጀንዳ በአማራ ክልል በታጣቂዎች እና በ...