Thursday, October 16, 2014

''ነፃነት ከመዋለ ንዋይ በፊት!'' ''Freedom before investment!'' ኢትዮጵያውያን ዛሬ በከፍተኛ ቁጥር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን በኦስሎ መገኘት በመቃወም ያሰሙት ድምፅ።

























ዛሬ ጥቅምት 6/2007 ዓም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የኖርወጅያን-አፍሪካ የንግድ ማህበር (Norwegian-African Trade Association) ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ ለመገኘት ኦስሎ፣ኖርዌይ  በተገኙበት ወቅት ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ ''Freedom before investment!''  ''ነፃነት ከመዋለ ንዋይ በፊት!'' በሚል ተቃውሞ አሰምቷል።

የተቃውሞ ሰልፉን ያዘጋጀው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ  ድርጅት በኖርዋይ ሲሆን ድርጅቱ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚገልፅ እና ኖርዌይ በኢትዮጵያ ካለው አምባገነን ስርዓት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ላይ በሚገባ ልታስብበት እንደሚገባ የሚያሳስብ ደብዳቤ ሰጥቷል።

በከፍተኛ ደረጃ ቁጣቸውን የገለጡት ኢትዮጵያውያን ከተቃውሞ ድምፅ በተጨማሪ እንቁላል በልዑኩ  መኪና ላይ በመወርወር ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን የኖርዌይ ታዋቂ የቴሌቭዥን ጣብያ NRK ''Kastet egg på stats minister'' ( ''የእንቁላል ውርወራ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ'' ) በሚል አርዕስት ስር የኖርዌይ ፖሊሶች ሲያስተናብሩ አሳይቷል።አንዳንዶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ''ጠቅላይ ሚኒስትር'' ተብለው መጠራታቸው የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቦታ በዶ/ር ቴዎድሮስ ተተካ እንዴ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

ኖርዌይ ለኢትዮጵያ ከምትሰጣቸው ርዳታዎች አንዱ በ''ኖርወጅያን ቤተክርስቲያን'' በኩል መሆኑ እና አዲስ አበባ አይቤክስ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው የኖርዌጅያን ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ስራውን የጀመረበትን አርባኛ ዓመት ባለፈው ግንቦት ወር አዲስ አበባ ላይ ማክበሩ ይታወቃል።

ጉዳያችን
ጥቅምት 7/2007 ዓም (ኦክቶበር 17/2014)


Sunday, October 12, 2014

ከሐይማኖታዊ ይዘቱ ይልቅ ፖለቲካ ለሚሸተው የቤተ ክህነቱ ስብሰባ የትውልዱ ፖለቲካዊ ምላሽም ያስፈልገዋል።


ቅዱስ ላሊበላ ቤተ ክርስቲያን 

የሰሞኑ በቤተክህነት በአቡነ ማትያስ ሰብሳቢነት የተደረገው ጉባኤ እና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረው የፈጠራ ክስ፣በመቀጠልም በኢቲቪ ዜና ላይ የተላለፈው ስብሰባውን አስታኮ ''ምዕመናን ነቅታችሁ ጠብቁ'' መሰል ዜና ሁሉ አንድ ነገር ያሳያል - በቤተ ክርስቲያን ላይ አንድ የአደጋ ደወል ከቅርበት እየተሰማ መሆኑን።

ስብሰባው ላይ ወቀሳ የሰነዘሩት እና የፈጠራ ክሶችን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያወረዱቱ  ባብዛኛው የሚጠቅሱት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሳይሆን የአቶ መለስን ንግግርን እና በዓለም ላይ አሉ የተባሉ የፅንፈኛ አሸባሪ ድርጅቶች ስምን መሆኑን ስንመለከት ጉዳዩ ፖለቲካዊ መሆኑን እና ፖለቲካዊ ምላሽ የሚሻ መሆኑንም ጭምር ያመላክታል።

ስብሰባው ቤተክርስቲያንን የተዳፈረ ነው 

ከሁሉ በፊት ስብሰባው የቤተ ክርስቲያንን  ሕጋዊ መስመር ተከትሎ አለመደረጉ ቤተ ክርስቲያንን የተዳፈረ ነው።የቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል መንፈስ ቅዱስ ነው።በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እስኪሰበሰብ የሚከናወኑ ተግባራት በቋሚ ሲኖዶስ ስር የሚታዩ መሆናቸው ይታወቃል።ይህ ስብሰባ ግን ቋሚ ሲኖዶስንም አላማከረም።አዲስ አድማስ ቅዳሜ ጥቅምት 1/2007 ዓም ስብሰባውን አስመልክቶ ''የጠቅ/ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፓትርያርኩን ተቃወሙ'' በሚል ርዕስ ስር እንዲህ የሚል አስነብቧል ''ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ÷ ‹‹አኹን ወደ ስብሰባው ስገባ ነው መልእክቱን የሰማኹት፤ አጀንዳውም ከመቅረቡ በፊት ከቋሚ ሲኖዶሱ ወይም ከእኔ ጋራ ምክክር አልተደረገበትም፤›› በማለት ስብሰባው ከመዋቅሩና ከዕውቅናቸው ውጭ የተጠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡'' ይላል።

በአቡነ ማትያስ የተመራው ስብሰባ ከተለቀቁት ተንቀሳቃሽ ስዕሎች እና ተከትሎም በኢቲቪ ከቀረበው ዜና አንፃር አጠቃላይ ሂደቱ  ሁለት ዋነኛ ዓላማዎች እና ሶስት የማስፈፀምያ ስልቶች ይታዩበታል።እነርሱም - 

1/ የቤተ ክርስቲያን ሕግ አውጭ እና ውሳኔ ሰጭ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስን በሕገወጥ እና የካድሬ ስብስብ ውሳኔዎች የመተካት፣ የማለማመድ፣ ብሎም የመቀየር ሂደት

በስብሰባው ላይ የተሰጡት አስተያየቶች፣ አቡነ ማትያስን የመጨረሻው የውሳኔ ሰጪ እያደረጉ የተሰጡ ነበሩ።በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ግን የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው።በስብሰባው ላይ የተነገረን ግን አቡነ ማትያስ እንደሆኑ ተደርጎ ነው።መንግስት በአቡነ ጳውሎስ ፕትርክና ዘመንም ሆነ ከዝያ ወዲህ  በፈለገው (እሱ ያረካኛል ባለበት)  ደረጃ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን ለመቆጣጠር ብዙ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።ይህ ማለት ግን ላለፉት ሃያ-ሶስት ዓመታት አልተቆጣጠረም ለማለት አይደለም።ቁጥጥሩ አርክቶታል ወይንስ አላረካውም ነው ጥያቄው።

2/ የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ፣ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት  በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋል 
በእዚህ ስር አሁንም በግለሰቦች እና በሙሰኛ ባለስልጣናት ጭምር የምመዘበረውን የቤተክርስቲያንን ንብረት እና ገንዘብ ስልታዊ በሆነ መንገድ ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ማድረግ ሲሆን ይህም ቤተ ክርስቲያን በቀጥታ የስርዓቱ ርዕዮተ ዓለም አስፈፃሚ ለማድረግ የታለመ ነው።
እዚህ ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት ተግባራት ለማከናወን ሶስት የማስፈፀምያ ስልቶችን መከተል አስፈልጎታል።እንደርሱም -
ሀ/ እንቅፋት ይሆንብኛል ወይንም በከፍተኛ ደረጃ ይቃወመኛል ያለውን፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ከወዲሁ ሰበብ አስባብ ፈልጎ ማስወገድ ወይንም (ለናሙና የተቀመጠ የተግባር ቤት ያልሆነ) ማኅበር ማድረግ
ለ/ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከውስጧ በሚነሱ የዶግማ እና የቀኖና ቀሳጮች እንድትታመስ ማድረግ እና ቤተክርስቲያንን ለሚገዳዳደሩ በእምነት የማይመስሏት በቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ  የወሳኝነት ሚና እንዲኖራቸው ማድረግ። ነገር ግን ይህ የሚሆነው  በኢህአዲግ የጎሳ ፖለቲካ የተጠመቁ እስከሆኑ ድረስ ብቻ ማድረግ እና 
ሐ/ ቤተ ክርስቲያን የሰው ኃይል እና የገንዘብ አቅሟን ሊያጎለብቱ ይችላሉ የሚባሉ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች፣ማሻሻያዎች ወዘተ የኢህአዲግን ርዕዮተ ዓለም እስካላራመዱ ወይንም በሚያራምዱት እጅ ሙሉ በሙሉ እስካልተዛወረ ድረስ ከወዲሁ ማክሸፍ የሚሉት ዋነኞቹ ስልቶች ናቸው።
ለእዚህ ነው እንግዲህ  ማኅበረ ቅዱሳንን አይን ባፈጠጡ እና የተናጋሪዎቹ ህሊና ከሃይማኖታዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ሽታው በሚሰነፍጥ ደረጃ  ባልዋለበት ውሎ ሲወቅሱ የተሰሙት።

የችግሩ መፍትሄ ከእግዚአብሔር በታች በእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን ልጅ እና እንደሀገር በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ አርፏል።

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው እርምጃዎቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን የህልውና ጉዳይ የሆኑትን ዋና ዋና ምሰሶዎችን የሚነካ ምናልባትም እንደ ሀገርም ለመቀጠል የሚያሰጋን አደገኛ ሂደቶች በስርዓቱ እየተፈፀመ መሆኑን አመላካች ነው።የችግሩ መፍትሄም ከእግዚአብሔር በታች በእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን ልጅ እና እንደሀገር ደግሞ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ አርፏል።እንደትናንት በቸልታ የሚታለፍበት ጊዜ ግን አብቅቷል።
በመሆኑም አሁን እያንዳንዱ ሰው ከእራሱ ጋር የሚማከርበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነው ።በመፍትሄነትም መታሰብ ከሚገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ከእዚህ በታች የተጠቀሱት አምስት ነጥቦችን ላቅርብ።እነርሱም - 

1/ቤተክርስቲያንን የሚያውካትን (ከሃይማኖት ቀሳጮች) በተጨማሪ የኢህአዲግን ተግባር አንጠርጥሮ መለየት፣
2/  ከሃይማኖታዊው መንገድ ባልተለየ ፖለቲካዊ ምላሽ መስጠት፣ 
3/ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የሁሉም ሳትሆን በጎጥ እና በመንደር በሚያስቡ ፖለቲከኞች ስር የከፋ ሁኔታ ወደ ፊትም እንደሚፈጠር  ጠንቅቆ መረዳት እና ከጊዜያዊ ተግባር እና ብስጭት ይልቅ ተከታታይ እና ዘለቄታነት ያለው ተግባር ላይ ማተኮር፣  
4/ በስልጣን ላይ ባለው መንግስት ፖሊሲ ሳብያ ቤተክርስቲያ የገጠማትን ችግር ለሁሉም አካላት ማስረዳት እና በቂ የቅስቀሳ ሥራ መስራት እና 
5/ እናት ቤተ ክርስቲያናችን  እና  ኢትዮጵያ ሀገራችንን አይናችን እያየን ስትጠፋ ዝም የማለትን ውርስ አባቶቻችን እንዳላወረሱን እና  የውዴታ ግዴታችን እንደሆነ ጠንቅቆ መረዳት የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ጉዳያችን 
ሰኞ ጥቅምት 3/2007 ዓም (ኦክቶበር 13/2014)
  




Saturday, October 11, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ይፈርሳል ? ይህን ማኅበር ሚገዳደሩት እነማን ናቸው? በካሌብ ብርሃኑ /ግላዊ እይታ/



(ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍ ካሌብ ብርሃኑ ከተሰኘ ግለሰብ  በማህበራዊ ድረ-ገፅ (ፌስ ቡክ) ላይ ከፃፈው የተገኘ ፅሁፍ ነው)

የብዙ ወንድሞች እና እህቶች ጥያቄ ነው፤ እስኪ የኔን አስተያየት ላቅርብ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደተነገረው (አንዳንዶች ሰምተው እንዳልሰሙ ፤ አንብበው እንዳላነበቡ ፤ አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም ብለው ተርተው አልሰማንም አሉ እንጂ) የቅዱሳን ስብስብ ሳይሆን ቅዱሳን ተጋድሎአቸው የሚዘከርበት ፤ የመንፈስ ልጆቻቸውም አሰረ ፍኖታቸውን የሚከተሉበት የአገልግሎት ማኅበር ነው፡፡ ቢሆንም ቅሉ ብዙ ሰዎች እዚህ ማኅበር ላይ ቂማቸው እና ጥላቻቸው እየጨመረ መሄዱ የእለት ተእለት ተግባራቸው ለአንዳንዶችም መተዳደሪያ ስራቸው ሆኗል ፡፡ እኔ በግሌ ማኅበሩን ለምን ጠሉት አልልም መውደድና መጥላት የነሱ ነፃ ፈቃድ ነው፤ (እስከማውቀውም ድረስ ማኅበሩ ለመወደድ ብሎ ሲሰራ አላጋጠመኝም )፡፡ በመሆኑም የነዚህ ሰዎች ጥላቻ ማኅበሩን ያፈርሰዋል ወይ ወደሚለው የብዙዎች ጥያቄ ላምራ፤ ይህን ጥያቄ ለመመለስ መጀመሪያ ማኅበሩ ምንድነው ፤ የመጨረሻ ግቡስ የሚሉትን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ምንድን ነው? 

ይህን ለመመለስ ከተመሰረተ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰራ የለውን ሥራ በተጨባጭ መረጃ መገምገም ቀላሉ መፍትሔ ነው፡፡ በብዙ ቦታዎች እንደተገለፀው ማኅበሩ ሲቋቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ተማሪዎችን በመንፈሳዊ ህይወት አንፆ ማሳደግ በዓለማዊውም ትምህርታቸው ጠንካራ ኦርቶዶክሶችን ማፍራት በዚህም በስነ ምግባር የታነፁ ዜጎችን ለ ኢትዮጵያና ለ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ማበርከት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተማሩ ሰዎች ስብስብ እንደመሆኑም መጠን ቤተ-ክርስቲያኗ በተለይም ገዳማቶቿ የእውቀት እና የነገ ቤተ-ክርስቲያን መሪዎች መፍለቂያ እንደመሆናቸው መጠን ከ እርዳታ እና ከ ጥገኝነት ተላቀው እራሳቸውን የሚችሉባቸውን ፕሮጀክቶች በመንደፍ እና ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም የተዘጉና የተዳከሙ የ አብነት ትምህርት ቤቶችን በማጠናገር እና በማስከፈት መምህራንና ተማሪዎችንም ስፓንሰር በማድረግ ለተፈለገው የቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት እንዲበቁ የማድረግን ስራ መስራት ነው፡፡ ማኅበሩ ሲቋቋም እንደ ሌሎች ማኅበራት በሰዎች ስምምነት ብቻ ሳይሆን በቤተ-ክርስቲያኗን ከ አምላክ ቀጥሎ የመጨረሻ አዛዥ በሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ መተዳደሪያ ደንብ እና ቡራኬ የተሠጠው ፤ ለዚህ አገልግሎቱም ከቤተ-ክርስቲያኗ መዋቅር ስር ሆኖ የሚያገለግል የ አገልጋዮች ማኅበር ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ግን ይህ ከላይ የተገለፀው ብቻ አይደለም ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ እንደመሆኑ አንፃር በብዙ አባቶች እንዲሁም አገልግሎቱን ቀና እንነት በተገነዘቡ ሰዎች “የቤተ-ክርስቲያን የችግር ጊዜ ልጅ” የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል፡፡ ይህ የተባለበት ምክንያት ደሞ አጽራረ ቤተ-ክርስቲያኖች የመነኩሴ ቆብ ለብሰው ህዝቡን ሊያወናብዱ “ቤተ-ክርስቲያኗ አርጅታለች እናድሳታለን” እያሉ በየአዳራሹ በሚበጠብጡበት ጊዜ ተከታትሎ ጉዳዩን ለቤተ-ክርስቲያኗ የበላይ አካላት (ቅዱስ ሴኖዶስ) በማስረጃ በማቅረብ አባቶች ውሳኔ እንዲሰጡ በማድረጉ እና አለማዊውን ትምህርት በከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያጠናቀቁ ክህናት ሙህራንን ለ ቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎት በማቅረቡ ነው ፡፡ ይህ ደሞ ኢንጅነሮቻችን በነፃ ዲዛይን በሚያደርጓቸው ቤተ-ክርስቲያኖች ፤ ሙህራኖቻችን በሚያቀርቧ ቸው የጥናት እና ምርምር ስራዎች ውስጥ የሚታይ መሬት ላይ የወረደ እውነት ነው፡፡
በአሁኑ ስዓት ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ይህ ማለት ብቻ አይደለም ምክንያቱ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ከ አገልጋዮች ስብስብነት ወደ እሳቤ (ideology) አዊነት ስለተሸጋገረ ነው፡፡

ይህን ስል ምን ለማለት ፈልጌ እንደሆነ በምሳሌ ልግለፅ ፡-
ከጥቂት ወራቶች በፊት እንዲህ ሆነ በአውሮፓ ሀገር የምትኖር እህት በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ከ ኦርቶዶክሳዊ ስርአት ውጪ የሆነ ስራ ሲሰራ አይታ “ለምንድነው እንደዚህ ሚሰራው ከ አባቶች ያልወረስነው በመፅሐፍም ያልተፃፈ ከ ቤተ-ክርስቲያናችንም ትውፊት ውጪ የሆነ ሥራ ለምን ይሰራል ብላ ትጠይቃለች” በዚህ ሰዓት ይህቺ እህት አንቺ እማ ማኅበረ ቅዱሳን ነሽ ሚል ታፔላ ይለጥፉባታል ፤ ማኅበሩ ከነመፈጠሩ የማታውቀው እህት ይህ የተሰደብኩበት ማኅበር ማን ነው ብላ ማፈላለግ ትጀምራለች በመጨረሻም ወደ ኢትዮጵያ በምትመጣበት ወቅት ብዙ ጥናቶችን በማኅበሩ ላይ ካደረገች በኋላ ወደ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቀርባ የታማሁባችሁ እናንተ የቤተ-ክርስቲያን ተስፋ ናችሁ በማለት ቤተ-ክርስቲያን ሥርዓት ሚፈፀምባቸውን መንገዶች እንድ ማሳያ ፕሮጀክት በመንደፍ የፕሮጀክቱን ማስፈፀሚያም አስተዋፅኦ በማድረግ ወደ አገልግሎቱ ገባች፡፡ ከዚህ ታሪክ የምንረዳው ነገር ስርዓት ሲጣስ የሚጠይቅ ፤ ስለቤተ-ክርስቲያን ፍቅር ልቡ የሚነድ እና ሲለሚፈፀምባት በደል የሚታመም መፍትሄም የሚፈልግ ሰው እሱ ማኅበረ ቅዱሳናዊ ነው ወደሚል መደምደሚያ እየተዞረ መሆኑን ማሳየት ነው ይህ ደሞ በማኅበሩ አባላቶች የተገለፀ ሳይሆን ፤ በግልባጩ ቤተ-ክርስቲያኒቷን ለማውደም ከሚንቀሳቀሱ አካላት የመጣ እውነታ ነው፡፡

 የማኅበሩ የመጨረሻ ግብ፡-

የማኅበሩ የመጨረሻ ግብ ምንድነው? ወደሚለው ጥያቄ እንዙር፤ ማኅበሩ በግልፅ እንዳስቀመጠው “ቤተ-ክርስቲያን የመሪነት ቦታዋን ማስመለስ” ነው፡፡ ይህ ምን ማለት ነው ብዙ ሰዎች ይህን ሲሰሙ ሊደናገጡ ይችላሉ ፤ አንዳንዶችም በስልጣናቸው የተመጣባቸው ሰለሚመስላቸው ማኅበሩን ለማጥፋት ጉድጓድ ሲቆፍሩ ይታያሉ (አጥልቃችሁ አትቆፍሩት ….) ፤ ቤተ-ክርስቲያንን የመሪነት ቦታዋን ማስመለስ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባጭሩ ላቅርብ፡፡
ቤተ-ክርስቲያን በቀደምት ዘመናት የነበራት ቦታ አለ ይህም የተሰሚነት ፤ አገርን የማገልገል ፤ “በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርቴ አድርጓቸው” የሚለውን የአምላኳን ትእዛዝ መፈፀም ፤ በልማትና እርዳታ ከፍተኛ ቦታ ላይ መድረስ ወደምትችልበት ቦታ ማድረስ መቻል ማለት ነው፡፡
ታዲያ ይህን ማኅበር ሚገዳደሩት እነማን ናቸው?

1. መንግሥት ፡- 

መንግሥት እንደ አስተዳዳሪነቱ ሁሉም ነገሮች (በተለይም የምሁራን ስብስብ) ያስፈራዋል በተለይ ደግሞ ብሔር ተኮር ለሆነ የገዢ ስርዓት ስለ አንድነት የምታስተምር ቤተ-ክርስቲያን ፈተናው ነች፡፡ ለዚህም ማሳያው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእስራኤላውያን ዘር ቢመጣም በፊቱ ቀለም ሳይሆን ባፈሰሰው ደም አለምን አድኗል፡፡ መልካችን ቢለያይም ደማችን ግን አንድ ነው ብላ ማስተማሯ መንግስት ከ በረሃ ጀምሮ ጥርሱ ውስጥ እንድትገባ አደርጓታል፡፡ ይህን አስተምህሮቷን ለማዳከም በሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ ደሞ ቤተ-ክርስቲያኒቷን ሊያጠናክሩ የሚችሉ አካላትን ማጥፋት ካልተቻለ ማዳከም ሁነኛ መፍትሔው ነው፡፡

2. አፅራረ ቤተ-ክርስቲያናት፡- 

እነዚህ አካላት ደሞ ቤተ-ክርስቲያኗን ለማፍረስ ምእመናኖቿንም ለመረከብ ብዙ የሚለፉ የእምነት ድርጅቶች ናቸው፡፡ በተለይም በቤተ-ክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ በመግባት ተሐድሶን እናደርጋለን የሚሉ ቅጥር ፕሮቴስታንቶች ሲሆኑ በኦርቶዶክስ ማልያ ለሌላ ቡድን ሚጫወቱ ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት የሉም እያሉ በየቦታው ቢያስነግሩም በየእጆቻችን ያሉት መረጃዎች ይህን አያመላክቱም፡፡ ይባስ ብለው እነዚህ ሰዎች መፃህፍትን እና ቪዲዮችን በመልቀቅ አለን እናድሳታለንም እያሉ ሲፎክሩ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደነበራቸው እቅድ በ ሚሊኒየሙ (2000 ዓ.ም) ሙሉ በሙሉ ቤተ ክርስቲያኗን እንረከባታለን ብለው እቅድ ቢያወጡም ሊሳካላቸው አልቻለም ፡፡የዚህን ምክንያትም ሲናገሩ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል የወጣት ሙህራኖች ስብስብ እንቅፋት እንደሆነባቸው ያስረዳሉ በመሆኑም በሚቀጥለው ስትራቴጂያቸው በቻሉት አቅም ቤተ-ክርስቲያኗን ለመረከብ ማኅበሩን ማጥፋት ካልቻሉ ደግሞ ማዳከም ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡

3. ጥቅማቸው የተነካ የቤተ-ክርስቲያኒቷ አካላት ፡- 

እነዚህ አካላት ቤተ-ክርስቲያኒቷ ላይ ኑራቸውን ጥገኛ ያደረጉ ነገር ግን ከሚገባቸው በላይ የቤተ-ክርስቲያኒቷን ንብረት ለመቀራመት የሚተጉ ፤ ምንኩስናን እና ቅስናን ክፍት የስሥራ ማስታወቂያ ያደረጉ የቤተ-ክርስቲያኗ አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት ከ ሰበካ ጉባኤ አባልነት እስከ ቤተ-ክርስቲያኗ ከፍተኛ የስራ አመራር ደረስ የተሰገሰጉ ቡድኖች ሲሆኑ ፤ ማኅበሩ እያደረገ ያለው አገልግሎት የነሱን ጥቅም የነካ (የሚነካ) የመሰላቸው (የነካባቸው) አካላት ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የማኅበሩን አገልጋዮች ባዩ ቁጥር “ባለ ድግሪው ሊቀድስ መጣ” እያሉ ሚጨነቁት ምክንያቱ ደሞ የማኅበሩ አገልግሎት መርህ ቤተ-ክርስቲያንን በ ገንዘብ በጉልበት እና በእውቀት ማገልገል በመሆኑ ሚሰራቸው እያንዳንዳቸው አገልግሎቶች ለቤተ-ክርስቲያን በነፃ ሚደረጉ ሲሆን እነዚህ አካላት ደሞ በቤተ-ክርስቲያኗ ተከፋይ (ሊያውም ከሚገባቸው በላይ) በመሆናቸው ነው፡፡ ተከፋይ ስል በቤተ-ክርስቲያን በ አገልግሎት ለሚሳተፉ መደበኛ አገልጋዮች ሚከፈላቸውን ደሞዝተኞች አለመሆኑ ይተወቅልኝ፡፡ ይልቅስ አንዲት ፕሮጀክት ለመተግበር የ አስር ፕሮጀክት ብር የሚበሉትን ለማጠየቅ ነው፡፡ እናም እነዚህ አካላት ተደላድለው የቤተ-ክርስቲያኒቷን ሃብት ለመብላት ማኅበሩን ማጥፋት ካልቻሉ ደግሞ ማዳከም ሁነኛ መፍትሔአቸው ነው፡፡

4. ማኅበሩን ባለማወቅ እንቅፋት የሚሆኑ፡- 


እነዚህ አካላት ስለማኅበሩ ምንም ባለማወቅ ወይም ከላይ የተገለፁትን አካላት እንደ መረጃ ምንጭ በመውስድ ለማኅበሩ እንቅፋት የሚሆኑ አካላት ናቸው፤ በዚህ ምክንያትም አንዳንዶች ማኅበሩን የተሐድሶ መነሻና መድረሻ አድርገው የሚያስቡ ሆነዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ማኅበሩ ከ ሰንበት ት/ቤቶች ጋር ፉክክር የገባ የሰንበት ት/ቤቶችን ለመብለጥ (ለማዘዝ) የተቋቋመ እየመሰላቸው ማኅበሩን ለመጣል ብዙ ሲለፉ እናያቸዋለን፡፡ እነዚህ ወገኖች ሁላችንም አንዲት ቤተ-ክርስቲያን ለመገንባት የምንጥር መሆናችንን አልተረዱም፡፡ ይልቅም ማኅበሩ ከብዙ ሰንበት ት/ቤቶች ጋር በ ጋራ ስለሚሰራቸው ስራዎችም እንዲሁም ሰንበት ት/ቤቶችን ለማጠናከር የሚሰራውን ስራ አልተገነዘቡም፡፡ የዚህም ማሳያው የሰንበት ት/ቤቶችን መጠናከር ሲመለከቱ “እሰይ ከማኅበሩ ቅዱሳን እየበለጡ ነው” እያሉ በየመድረኩ የሚሰጡት ያላዋቂ አስተያየት ነው፡፡
ይህን ያህል ማኅበሩን ሊያጠፉት (በማወቅም ሆነ ባለማወቅ) ስለ ሚጥሩት አካላት ከገለፅን እውን ማኅበሩን ማጥፋት ይችላሉ ወይ? ወደሚለው የመጨረሻ ጉዳይ እንሂድ፡፡
ማኅበሩን ሊያጠፉት አይችሉም!!!፡፡ እንደምን እንደማይችሉ በትንሹ ልግለፅ ፤ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ማኅበሩ አሁን የአገልጋዮች ስብስብ ብቻ ከመሆን ዘሎ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤ (ideology) ወደ መሆን ተሻግሯል፡፡ እነዚህ ሰዎች ማኅበረ ቅዱሳናውያን ብለው ሚያስቡት በአባልነት የተመዘገቡትን ከ 60,000 በላይ አባላት ሊሆን ይችል ይሆናል ነገር ግን አሁን ከዛም አልፏል ፤ ማኅበረ ቅዱሳናዊነት በያንዳንዱ ለቤተ-ክርስቲያን ይገባኛል በሚል ኦርቶዶክሳዊ ውስጥ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡ ቤተ-ክርስቲያኔን ባለኝ ነገር ሁሉ ላገልግል በሚል ኦርቶዶክሳዊ ውስጥ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህን ደሞ ተቋሙን በማፍረስ ማጥፋት የሚቻል አይደለም ፤ ብዙዎች ማኅበሩ አሁን ካለበት የአደረጃጀት ስርአት ቢበተን የልባቸው ሚሳካ ይመስላቸዋል፡፡ በጣም ትልቅ ስህተት ነው ምክንያቱም አሁን እንደሚታየው ማኅበሩ ላይ ያሉት አባላት በአንድ መዋቅር ስር የተሰበሰቡ ናቸው ይህ ደሞ ተወደደም ተጠላም ለነዚህ አገልጋዮች የሚያስቀምጥባቸው ድንበር (limitation) አለ፤ ይህን መዋቅር መበተን ግን እነዛን ሰዎች ያለ ምንም ድንበር አገልግሎት ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል ሌላ ትልቅ የአገልግሎት በር መክፈት ነው፤ ይህ ደሞ እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ወደ ቤተ-ክርስቲያን እንዲመለስ እና በትጋት እንዲያገለግል የሚያደርግ ጥይት መተኮስ ነው፡፡ በዚህ ሰዓት ሊፈፀም የሚችለው አንድ እና አንድ ነገር ብቻ ነው እያንዳንዱ ሰንበት ት/ቤት እና ሰበካ ጉባኤ ማኅበረ ቅዱሳናዊ እሳቤን ወደመያዝ ይዞራል ያኔ “በተንን” የሚሉት መዋቅር ሺ ጊዜ ጠንክሮ እና አብቦ ይመጣል፡፡ it’s just a win win scenario.


Friday, October 10, 2014

የዶ/ር ሽፈራው ''የአንገታችሁን ማዕተብ እንዲወልቅ ይደረጋል'' ንግግር ላይ የአይን እና የጆሮ እማኝ ቃሉን ሰጠ፣የፈድራል ጉዳዮች ቃል አቀባይ እና ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በጉዳዩ ላይ የሰጡት ቃል (የጉዳያችን አጭር ጥንቅር)



ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 24/2007 ዓም ሐራዘተዋህዶ በድረ-ገፁ ላይ የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‹መንግሥታችን ሴኩላር ነው›› ሲሉ በጠያቂዋ የተጠቀሰውን ዐይነት አለባበስ የተቹት ሚኒስትሩ፣ ‹‹እርሱም [ማተቡም] ቢኾን የጊዜ ጉዳይ ነው፤ እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢኾን መውለቁ አይቀርም፤›› የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተገልጧል፡፡'' ሲል ሰፊ ዘገባ አስነበበ።ዘገባውን ተከትሎ በርካቶች ሃሳባቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።ጉዳዩን አስመልክቶ ማክሰኞ መስከረም 27/2007 ዓም ኢሳት ራድዮ ሶስት ግለሰቦችን አነጋግሯል።የአይን እና ጆሮ እማኝ፣ዶ/ር አረጋዊ በርሄ እና አቶ አበበ ወርቁን።

1ኛ/ የአይን እና የጆሮ እማኝ 

ከሀገር ቤት በስብሰባው ላይ የነበረ ተሳታፊ በስልክ የሚከተለውን ተናግሯል።ግለሰቡ በሰጠው ቃል ''ነገሩ እውነት ነው የተሰበሰብንበት ርዕስ 'ልማታዊ ዲሞክራስያዊ መንግስት ግንባታ' የሚል ሲሆን ወደ 800 ይምንጠጋ የመካከለኛ አመራር አካላት የተሳተፍንበት ነው።የነገሩ መነሻ ጥያቄ ነበር .....ጥያቄው ለዶ/ር ሽፈራው የቀረበ ነበር እና እሳቸው በምላሻቸው 'የጊዜ ጉዳይ ነው፤ እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢኾን መውለቁ አይቀርም፤' ነበር ያሉት እና በወቅቱ በጣም አሳዛኝ ጉዳይ ፈጥሯል.....እኔ እንደማስበው በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚያደርጉት ነው የማስበው።''
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን -'' ቀደም ብዬ የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስትር ቃል አቀባይን አነጋግሬ ነበር እና እሳቸው 'በሬ ወለደ' ነው ያሉት እስኪ ያሉትን ቃል በቃል ተናገር''
የስብሰባው ተሳታፊ '' ይህንን ነገር ቃል በቃል ብለውታል በትክክል ብለውታል ! እየተሰራበት ነው መመርያውን እያዘጋጁ ነው ----በትክክል የምነግርህ ነገር በቅርብ ጊዜ በቅርብ ጊዜ ምናልባት ምርጫውን ይጠብቁ ይሆናል ---ዕውነትን ተናግሬ መሞት ስለምፈልግ ነው ---ለእናንተማ መረጃ ይሰጣሉ ብዬ አላስብም ----''
ጋዜጠኛ መሳይ -''በቃል ነው እንጂ በወረቀት ደረጃ የተቀመጠ አለ?"
የስብሰባው ተሳታፊ - ''በፓወር ፖይንት የታገዘ ነው ከእዝያ ላይ ሲያብራሩ ነው የተጠየቁት''


2ኛ/ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የመጀመርያው የህወሓት ሊቀመንበር እና መስራች 


ዶ/ር አረጋዊ በርሄ   ''መንግስት የእዚህ አይነት እርምጃ ሊወስድ ይችላል ብለው ያስባሉ ወይ ?'' ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ - ''ይሄ መንግስት በጠበንጃ የመጣ መንግስት ነው የተለያየ ሕዝቡን የሚቆጣጠርበት መዋቅር መመስረት አለበት----አሁን አስር እና አስራ አምስት እያደራጀ ለመቆጣጠር ይፈልጋል።ሃይማኖትን ከፋፍሎ አክራሪ እንዲፈጠር እያረገ ነው----ይህ እራሱ መንግስት የሚፈጥረው ሕዝብ ከህዝብ በማጋጨት የሚኖር ነው----የማዕተቡን ጉዳይ ሊያደርገው ይችላል።ሕዝቡን አፍኖ ለመያዝ እንደ ስልት የሚጠቀምበት ነው።ይህም አንዱን በአንዱ ላይ ለማነሳሳት ይች ለበሰች ያች አለበሰችም እያለ ለመክፈል ነው።---ፖሊሲው አይታወቅም ተገላባባጭ ፖሊሲ ነው ያለው የሃይማኖት ድርጅቶችን በሙሉ መቆጣጠርይፈልጋል።ይህ ሕዝብ ድሮ ተቻችሎ የኖረ ሕዝብ ነበር።ይህ መንግስት ለመቆጣጠር የሚሰራው ነው።ይህ መንግስት አይታመንም።የስለላ መዋቅሩን ብትመለከት የሃይማኖት ድርጅቶች ውስጥ እየገባ ነው የሚሰራው----ሃይማኖቶችን ለመቆጣጠር እስከ ማሰር፣መግደል የሚደርስ ነው እነ አስገደ የትኛውን ጥይት ተኩሰው ነው የታሰሩት? ይህ በወታደር እና በስለላ መቆጣጠር ስለሚፈልግ ነው ይህንን ጠንቅቀን ድሮም እናውቀዋለን'' ብለዋል።በመጨረሻም ዶ/ር አረጋዊ ሃይማኖትን በተመለከተ እንዲህ አሉ '' አፄ ኃይለ ስላሴ ያሉት አንድ ነገር አለ።ኃይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው -----የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግሩን የጋራ ስርዓት ፈጥረን ለመፍታት ሜዳ ላይ ወርደን መፍታት አለብን'' ብለዋል፣

3ኛ/ የፌድራል ጉዳዮች ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ አበበ ወርቁ 

አቶ አበበ  ''ጉዳዩ የፈጠራ ነው።የግለሰብ መብት ጉዳይ ነው።መስራበታችን ሴራ ነው የሚለው''
ጋዜጠኛ መሳይ - '' ወሬው ከምን መነሻነት ነው የተነገረው።አልተናገሩም ከተባለ።ጉዳዩ በቀጥታ ተወስኗል ሳይሆን ወደፊት ሊተገበር ይችላል ነው።''
አቶ አበበ ''መነሻው የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ነው።ስለዚህ አነሳሱ የተለያየ አቅጣጫ ይኖረዋል።መስራቤታችን ግን ይህንን አልወሰነም----
የሙስሊሞች ሂጃብም አልተከለከለም።ሙሉ በሙሉ ሰውነትን የሚሸፍነው አለባበስ ነው የተከለከለው'' 
ጋዜጠኛ መሳይ -''ማዕተብ በጥሱ የሚለው ጉዳይ እራሳቸው የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ሁሉ ስብሰባው ላይ እንደተከራከሩ እኛም ለመረዳት ችለናል።ነገር ግን ጉዳዩ የመንግስት አቅዋም አለመሆኑን ነበር ለማወቅ የጠየኩት እርስዎ ደግሞ የመንግስት ውሳኔ አደለም የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።የፌድራል ጉዳዮች ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ አበበ ወርቁ ስለሰጡኝ ጊዜ አመሰግናለሁ።''


በእዚህ አጋጣሚ ኢሳት ይህን የመሰለ ሚዛናዊ ዘገባ በማቅረቡ ትልቅ ምስጋና ሊቸረው ይገባል።የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስትር ቃል አቀባይን አቅርቦ ማናገሩ በራሱ ሚዛናዊ እና ዘመናዊ የጋዜጠኝነት ሙያ ነው።ኢቲቪ ለምሳሌ ዋሽግተን ደውሎ አንዳንድ ዜና ቀጥታ ባለጉዳዮችን እያናገረ ለሕዝብ መዘገብ መቼ ይለምዳል? ምኞት አይከለከልም።

ጉዳያችን
መስከረም 30/2007 ዓም (ኦክቶበር 10/2014)


Thursday, October 9, 2014

''ሀገሪቷን ለመምታት ሲሉ መጀመርያ ቤተ ክርስቲያኗን መምታት አለባቸው ይሄ ነው ዓላማው ለእዚህም ከውስጡ ሊገዙ ይፈልጋሉ'' አቡነ ኤልያስ (ቪድዮ)

አቡነ ኤልያስ -
        - በአቡነ ተክለሃይማኖት ፕትርክና ዘመን የፓትራሪኩ ልዩ ፀሐፊ ሆነው አገልግለዋል፣
        - በኬንያ፣ዑጋንዳ፣ጅቡቲ እና በበርካታ የዓለም ክፍሎች የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን ተክለዋል፣እንድትስፋፋ ደክመዋል፣
         - በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘመን ጀምረው እስካሁን በሕይወት ላይ ካሉት አባቶች ውስጥ የቀሩት ናቸው፣
         - በሀገር ቤት አሁንም በጵጵስና ማዕረግ ካሉት እንደ አቡነ ገሪማ ያሉትን ምንኩስና የሰጡ እሳቸው ናቸው።

አቡነ ኤልያስ ከሉሲ ራድዮ አዘጋጅ ዘውዱ መንግስቱ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ -


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...