ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, January 24, 2022

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በመጪው ሳምንት ከመከፈቱ በፊት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በከፊል ቢነሳ ኢትዮጵያ ብዙ ልታተርፍ ትችላለች።



==============
ጉዳያችን/ Gudayachn
==============
በመጪው ሳምንት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ ይደረጋል።የዘንድሮው ስብሰባ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው እንደሚሆን የወቅታዊውን የዓለማችንን ሁኔታ በመረዳት ለማወቅ ቀላል ነው። አፍሪካ የምስራቁንም ሆነ የምዕራቡን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ብቅ እያሉ ያሉት እንደ ቱርክ እና ብራዚል ሳይቀር ዐይን ውስጥ ገብታለች። አህጉሩ ሲታሰብ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ውሳኔዎች የሚተላለፍበት እና የአፍሪካ መሪዎች በቀላሉ የሚገኙበት የአዲስ አበባው ስብሰባ አንዱ እና ዓለም ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ስብሰባ ነው።ኢትዮጵያ በዘንድሮ በነበረባት ጦርነት አዲስ አበባ የጸጥታ ሁኔታዋ አስጊ ነው በሚል የመነጠል ስራው ከአሜሪካ ኤምባሲ እስከ የተባበሩት መንግስታት ቢሮዎች ርብርብ ተደርጓል። ሆኖም ሁኔታው ተቀልብሷል። 

በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ከመሪዎቹ ጋር ከሚመጡት ልዑካን በተጨማሪ በሺህ የሚቆጠሩ የሚድያ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ይገባሉ።ጋዜጠኞቹ ደግሞ የሚዘግቡት ከስብሰባው ባለፈ በኢትዮጵያ ላይ ሪፖርት ሰርተው መሄድ ይፈልጋሉ። ይህ ስራ ገና ከሃገራቸው ሲነሱ የሚሰጣቸው አንዱ ስራ መሆኑ አይቀርም። በእነኝህ ዘገባዎቻቸው ደግሞ መግቢያ የሚያደርጉት ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ነች የሚለው ነው። ይህ በራሱ ለቱሪዝሙ የሚሰጠው አሉታዊ ገጽታ ይኖራል።

ስለሆነም ቀደም ብላ አዋጁን ኢትዮጵያ ብታነሳው እና ክልሎች ለምሳሌ በኦሮምያ በምዕራብ ወለጋ፣በአማራ እና አፋር በከፊል ከተሞች እየለዩ አዋጁ እንዲጸና ቢደረግ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ጥቅም አለ። እዚህ ላይ አዋጁ በሌለባቸው አካባቢዎችም የጥበቃውም ሆነ አስጊ ለሆኑ እንቅስቃሴዎች የፍተሻ ስራው አዋጁ ባይኖርም አይቀርም።ምክንያቱም ህወሃት እና ሸኔ በሽብርተኝነት መፈረጃቸው እስካለ ድረስ ስራው አይቆምም። ሆኖም ግን የአዋጁ መነሳት የኢትዮጵያን ገጽታ በእጅጉ ማሻሻል ብቻ ሳይሆን የዓለም ዓቀፍ የቱሪስት እና የጉዞ ወኪሎች ወዲያው ለደንበኞቻቸው ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ እና መጎብኘት እንደሚችሉ መረጃ ይልካሉ።ይህ ደግሞ እየመጣ ካለው የፈረንጆቹ የዕረፍት የክረምት ጊዜ አንጻር ከወዲሁ ቀጣይ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያደርጉ ከአሁኑ ለማቀድ ይረዳቸዋል።የምዕራቡ ቱሪስቶች ቀደም ብለው የሚጎበኙትን ሃገር እንደሚወስኑ ይታወቃል።ይህ ወር ደግሞ የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት መጀመርያ ስለሆነ የመጪው ክረምት ጉዞ ማቀጃቸው ጊዜ ነው።

ባጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ኢትዮጵያ በከፊል ማንሳቷ የሚሰጠው ብሄራዊ ጥቅም አለ። እዚህ ላይ ጦርነቱ ገና ሳያልቅ የሚል ሃሳብ ሊነሳ ይችላል።ሆኖም ግን መታየት ያለበት ይህ አዋጅ በመላው ኢትዮጵያ የታወጀው የሽብር ቡድኑ ወደ መሃል ሃገር ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ እንጂ አሁን ያለው በድንበር አካባቢ ያሉ ግጭቶች ለወራት ሊቀጥል ይችላል።ስለሆነም ትርፉ የአዋጁ መኖር እና ውጥረት ያለ አድርጎ በውጭው ዓለም መፍጠር እንጂ ከጥቅም አኳያ ሲታይ አዋጁን በከፊል ማንሳቱ ለኢትዮጵያ ጥቅም አለው።
============////============

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...