ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 19, 2016

የወጣት ንግሥት ይርጋ ወደ ስቃይ እስር ቤት መግባት ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ውደ ትግሉ ሜዳ ይጠራል !

ንግስት ይርጋ በጎንደር ሰልፍ ላይ 


  • ወጣት ሴቶች ለነፃነት ትግሉ የሚነሱበት አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ። 
  •  የአንዳርጋቸው ፅጌ መታሰር ሚልዮኖችን ወደ ትግሉ ሜዳ እንዳስገባ ሁሉ የንግሥት ወደ መሰቃያ ቦታ መውሰድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያንን ወደ ትግል ሜዳ ያስገባል።
ወጣት ንግስት ይርጋ በጎንደር በተደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ስሜቷ ተነክቶ በሰልፉ መካከል ከእንባ፣እልህ እና ሲቃ ጋር ነበር በሰልፉ የተሳተፈችው።ከኢህአዴግ ሰራዊት ጋር አብሮ ተሰልፎ ደርግን የታገለው በኃላም በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ውስጥ በብቃቱ ተፈልጎ አገሩን የወከለው በመቀጠልም የታገልኩት ትግራይ ሁን ተብዬ እንድገደድ አይደለም ስነ ልቦናዬም፣ባሕሌ እና የአኗኗር ዘይቤዬ የእኔም ሆነ የሕዝቤ የአማራ ነው።የግድ ትግሬ ሁን አትበሉኝ! ብሎ በሕጋዊ መስመር ተከትሎ ከአስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን መብቱ የጠየቀውን ኮ/ል ደመቀ ዘወዱ  ፎቶ ግራፍ በትሸርት አድርጋ ከስር ´´አማራ አሸባሪ አይደለም´´በሚል ፅሁፍ ሰልፉን የተቀላቀለችም ወጣት ታጋይ ንግስት ይርጋ በወያኔ ወታደሮች መታፈኗ እና ወደ አዲስ አበባ መወሰዷን ´´የጥፋት ዘመን´´ መጽሐፍ  ፀሐፊ ሙሉቀን ተስፋው በገፁ ላይ ባሰፈረው ዜና ገልጧል።

የሕወሓት እስር ቤቶች በሴቶች ላይ የሚፈፅሙት ግፍ በሰው ህሊና ከሚታሰበው በላይ ነው።ከእዚህ በፊት በቂልንጦ እስር ቤት ሴት እስረኞች ላይ ምን እንደደረሰ የዞን 9 ታሳሪ ወጣትን ታሪክ ማስታወስ በቂ ነው።በሌሊት እራቁቷን እንድትመጣ እየተደረገ በርካታ በደሎች በማንነት ላይ ያተኮረ ስድብን ሁሉ ጨምሮ ተፈፅሟል።በንግሥት ይርጋ ላይ ደግሞ ምን አይነት ፋሽሽታዊ ሥራ እንደሚሰራ መገመት ይቻላል። ይህ ሁኔታ በእራሱ የኢትዮጵያ ወጣት ሴቶችን በአዲስ መልክ የሚጣራ አዲስ እና ልዩ ለነፃነት የሚደረግ የትግል ጥሪ ነው።በሴትነት እና በማንነት ላይ የተነሱ ፋሽሽቶችን ዝም ብሎ መመልከት አይቻልም።ከአገር ቤት እስከ ውጭ ያሉ ሴቶች የነፃነት ትግሉን በአዲስ መንገድ የሚቀላቀሉበት አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ። ሕወሓት በማሰር እና በማፈን ትግል የምታዳክም ይመስላታል።የአንዳርጋቸው ፅጌ መታሰር ምልዮኖችን ወደ ትግሉ ሜዳ እንዳስገባ ሁሉ የንግሥት ወደ ስቃይ እስር ቤት መግባት ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ውደ ትግሉ ሜዳ ያስገባል።

ከእዚህ በታች የወጣት ንግስት መታፈን አስመልክቶ ሙሉቀን ተስፋው የለቀቀውን ዜና አንብቡት።

ወጣቷ የነጻነት ታጋይ ንግሥት ይርጋ በወያኔ መታፈኗ ተሰማ፥

ወጣት ንግስት ይርጋ፥ አርብ መስከረም 6 ቀን 2009 ዓ.ም ከጎንደር ከተማ ተነስታ፥ በታች አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ ወደ ሚገኘው ቤቷ ስታመራ መንገድ ላይ ታፍና ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ የማሰቃያ ቤት መወሰዷ ታውቋል።
ወጣት ንግስት ይርጋ ተፈራ፥ ሰሞኑን ጎንደር በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ንቅናቄ ላይ ባደረገችው የማስተባበር ተሳትፎ በከተማው ታዋቂነትን ያተረፈች፥ ገና በሃያዎይቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የምትገኝ፥ ምንም ወንጀል የሌለባት ወጣትና ፍትህ ፈላጊ ታዳጊ ዜጋ መሆኗ ነግሯል።

ወጣት ንግስት ወደ ትግሉ የገባችውና በሕዝብ ዓይን ጎልታ መታየት የጀመረችው፥ የወልቃይት ማንነት ኮሚቴዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ዓፍነው ለመውሰድ በመጡ የወያኔ ታጣቂዎችና በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የመከላከል እርምጃ ምክንያት ጎንደር ላይ በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞ፥ ሰልፍ በመምራትና በማስተባበር ባደረገችው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነበር።

ይህች ወጣት ንግስት የአማራ ተጋድሎ በመባል የሚታወቀውን ሕዝባዊ ንቅናቄ የተቀላቀለችው ቂሊንጦና ቃሊቲ እስር ቤት ጓደኛ ለመጠየቅ ሂዳ ባየችው የወጣት ኢትዮጵያውያን እስረኞች ብዛትና የአማራ እስረኞች ስቃይ፥ በተለይም ከገጠሪቱ ጎንደር ባልሰሩት ወንጄል ታፍነው ተወስደው መዳረሻቸው ሳይታወቅ ለእረጅም ጊዜ ያለጠያቂ ሲሰቃዩ ላየቻቸው ወገኖቿ ጩኸትና የመከራ ድምጾች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ያጫወተቻቸው የትግል አጋሮቿ ይናገራሉ።

ምንጭ = ሙሉቀን ተስፋው 
(https://www.facebook.com/muluken.tesfaw?fref=ts) 


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...