ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, December 11, 2013

ዳግማዊ አፄ ምኒልክን ሳስብ የሚገርሙኝ ሶስት አስገራሚ ችሎታዎቻቸው፣የዳግማዊ ምኒልክ እውነተኛ ድምፅ (ኦድዮ) እና አፄ ምኒልክ የነዷት የመጀመርያዋ እውነተኛ መኪና(ቪድዮ)

 ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የጥቁር ህዝቦችን የቅኝ ግዛት ታሪክ ተረት ያደረጉ ብቸኛ የዓለማችን መሪ ናቸው።ያረፉበት 100ኛ ዓመት ታህሳስ 3/2006 ዓም በሰማያዊ ፓርቲ እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ይታሰባል።ዕለቱ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ብቻ ሳይሆን የፊት-አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ 87ኛ እረፍት መታሰብያም ነው።ይህ በዓል ሊከበር የሚገባው በብሔራዊ ደረጃ ነበር።ሆኖም ግን ጉዳዩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ኢትዮጵያ ጀግኖቿን እና ታሪክ የሰሩ እውነተኛ ልጆቿ የሚገፉበት ወቅት ሆነ።ይህንን በዓል ለማክበር ሰማያዊ ፓርቲ በጃን ሜዳ ለመሰብሰብ የጠየቀው ጥያቄ እንዳልተፈቀደ ገልጧል።ፓርቲው ግን ዝግጅቱን ቀጥሏል።

ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት የግራዝያኒን ሃውልት መሰራት ተቃውመው ሲወጡ በፖሊስ ተደበደቡ።በሳውዲ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ግፍ አስመልክተው በሳውዲ ኤምባሲ ለመቃወም ሲሰለፉ እንዲሁ ለፖሊስ ዱላ እና ለእስር  ተዳረጉ።ዘንድሮ ደግሞ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ 100ኛ  እና የፊት-አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ 87ኛ እረፍት መታሰብያ ለማዘጋጀት ጃን ሜዳ እንሰብሰብ ሲሉ አሁንም ተከለከሉ።

የእዚህ አይነቱ ታሪካችንን በአግባቡ እንዳንዘክር የማድረጉ ተግባር ባዕዳንን ሊያስፈነድቅ ይችላል።ለኢትዮጵያውያን ግን በመጪው ታሪካችን ሁሉ በጥቁር ቀለም ተፅፎ የምናነበው አሳዛኝ ታሪክ ነው።ካለፈው ታሪካችን ጋር በእዚህ አይነት ደረጃ የተቃረነ መንግስት ያጋጠመን አይመስለኝም።

እኔ ግን ሁል ጊዜ ዳግማዊ ምኒልክን ሳስብ  የሚገርሙኝ  ሶስት አስገራሚ ችሎታዎቻቸውን መጥቀስ እፈልጋለሁ።

1/ የዲፕሎማሲ ችሎታ

በወቅቱ የነበረው የአውሮፓውያን የቅኝ ግዛት የመስፋፋት ፖሊሲ ከእንግሊዝ ጋር በኬንያ አና ሱዳን በኩል ከኢጣልያን ጋር በሱማሌ እና በኤርትራ በኩል ከፈረንሳይ ጋር በጅቡቲ በኩል የነበሩትን ቁርሾዎች እናስብ።በወቅቱ የነበሩትን ንግግሮች፣ደብዳቤዎች፣ሉዓላዊነትን የማስከበር ሂደቶች ሁሉ ማሰብ ይቻላል።ድንቅ እና ለዘመናዊው ዓለም መማርያ የሚሆኑ ብዙ ትምህርቶች ይገኙበታል።

2/ ዘመናዊ አስተተሳሰብ የመቀበል አቅም 

ከአውሮፓውያን ጋር በነበሩ ግንኙነቶች ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ዘመናዊ አሰራርን የመቀበል ሂደት።የመጀመርያ ዘመናዊ መኪና፣ካቢኔ፣ባቡር፣ስልክ፣ፖስታ፣ሆቴል፣ሲኒማ ቤት ወዘተ የተጀመሩበትን ሂደት እናስብ።በወቅቱ ዘመናዊ አሰራርን ንጉሡ ባይቀበሉ ኖሮ አዲሱ መኪና ላይ እንዳይወጡ ያወገዙ እንደነበሩ አለመዘንጋት ነው።ምኒልክ ግን ዘመናዊ አሰራርን ተቀበሉ።

3/ የአካባቢ ጥበቃ ጠበቃ 

አፄ ምኒልክ ዛሬ የዓለማችን ትልቅ ችግር የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ያሳሰባቸው ገና በጧቱ ነበር።የደን መመናመን ጉዳይን በቤተመንግስታቸው በአጀንዳነት የተወያዩ እና መፍትሄ ያስገኙ ቆይቶም ባህር ዛፍ ከአውስትራሊያ በማስመጣት እንዲተከል ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ነበሩ።

ይህ ሁሉ የሆነው ከአንድ መቶ አመታት በፊት ነው።ይህ ሁሉ የሆነው ዓለም በመረጃ ባልተሳሰረበት እና ዘወትር ለመማር ዝግጁ በሆኑት እለት እለት እራሳቸውን በሚሰሙት፣በሚያነቡት እና በሚያማክሯቸው ሰዎች እራሳቸውን በእውቀት ባበለፀጉት ንጉስ ምኒልክ ነው።

አፄ ምኒልክ የነዷት መኪና(ቪድዮ)



የዳግማዊ ምኒልክ እውነተኛ ድምፅ (ኦድዮ) ድምፁን በሞባይ መስማት ያልቻላችሁ ሞባይላችሁ ላይ የፕሮግራም አለመጫን ስለሚሆን በቤት ኮምፕዩተር ይክፈቱት።


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...