Friday, May 31, 2013

በአባይ ግድብ 'ጅኦ-ፖለቲካል' ጉዳይ ተቃዋሚዎች ያላቸው ሃሳብ እና መፍትሄ ሳይሰማ ህዝቡ በመላ ምት ላይ በተመሰረተ አስተሳሰብ ሀገሪቱ ወደ አልተፈለገ መንገድ እንዳትሄድ- የውጭ ፖሊሲያችንን የሚቀይሰው ማነው?((አጭር ማስታወሻ ከአልጀዚራ ቪድዮ ዘገባ ጋር)

ዛሬም የቅኝ ግዛት ውል መጥቀስ ምን ያህል ኃላ ቀርነት ነው? ግብፆች ዛሬም በ 1959 እአኤ  የተፈረመውን ግብፅን እና ሱዳንን የሚጠቅመውን ውል ይጠቅሳሉ።ኢትዮጵያ ግን ከቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዘመን እስካሁን ድረስ ውሉን ተቀብላ አታውቅም። የአባይ ጉዳይ አሁን ላለንበት በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ግብፅን ጨምሮ ከቅኝ ግዛት ተላቀው ነፃ ሀገር መሆን ከጀመሩበት ጊዜ እና የነዳጅ ዘይት ግኝት ማለትም ከ 1950 ዎቹ ወዲህ ለነበረን የሰሜንም ሆነ የሱማሌ ጦርነት ኢትዮጵያ በአቅም እንዳትደረጅ እና የአባይን ውሃ አጠቃቀም ጉዳይ እንዳታነሳ የተሸረቡ ተንኮሎች አካላት ነበሩ ማለት ይቻላል።
በኤርትራ ''ጀብሃን'' ለመርዳት ቀጥሎም ''ሻብያን'' ለማገዝ አንዳንድ የመካከለኛ ምስራቅ ሀገራትን፣ግብፅ እና ሱዳንን ያማለላቸው አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት የተዳከመች ኢትዮጵያን ለማየት ካላቸው ሕልም እና ከእዚሁም በአባይ ላይ እና በቀይባሕር ላይ ያላቸውን የበላይነት የማሳያ አንዱ እና ብቸኛ መንገድ አድርገው ስለሚያስቡ ነበር። በእዚህ ጉዳይ ብዙዎች ብዙ ብለዋል።እኔ የማክልበት የለም።

ሆኖም ግን የውጭው ተፅኖ መንስኤዎችን ብንዘረዝርም ትልቁ ጉዳይ ግን እኛ የውስጥ ጉዳይ አያያዛችን እና የመንግስታቶቻችን ብልህ የሆነ የህዝብ አስተዳደር ዘይቤ ማጣት ብሎም የውጭ ግንኙነቱን ባማከለ መንገድ አለመሆን አንዱ መጤን የሚገባው የነበረ እና አሁንም ያለ የችግሮቻችን ምንጭ ነው።በሌላ አንፃር  በየጊዜው የሚነሳውን ትውልድ ፍላጎት እየተመለክቱ መንግሥታቱ  እራሳቸውን ማስተካከል አለመቻል ከአባይ ጋርም ሆነ ካለንበት 'ጂኦ-ፖለቲካል' አቀማመጥ አንፃር የሚነሱትን ችግሮች በፍጥነት ከህዝብ ጋር ሆነው ለመፍታት ሲሳናቸው እንመለከታለን።

የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም በሃገርውስጥ ባሉ የመንግስት አሰራሮች ላይ ብቻ ሳይሆን በአለምአቀፍ ጉዳዮች በተለይ ኢትዮጵያን በቀጥታ የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የሚይዙትን አቋም በየጊዜው ግልፅ ማድረግ ያለባቸው ይመስለኛል።ይህ ካልሆነ ሕዝብ በፅናት የሚቆምበትን መስመር ሳይመለከት እና ግልፅ የሆነ መንገድ አጥቶ የመዋለል አዝማምያ ለብሔራዊ አንድነትም ሆነ ለሉአላዊነታችን አድገኛ አዝማምያ ይፈጥራል። 

በአንድበኩል ህዝቡ መንግስት  የውጭ ኃይላትን በተመለከተ የሚሰጣቸውን  ማብራርያዎች አለማመን በሌላ በኩል ተቃዋሚዎች ስለጉዳዮች ያላቸው ሃሳብ እና መፍትሄ ሳይሰማ  ህዝቡ በመላ ምት ላይ በተመሰረተ አስተሳሰብ ሀገሪቱ ወደ አልተፈለገ መንገድ እንዳትሄድ ሁሉም ወገኖች ሊያስቡት የሚገባ አንኳር ጉዳይ ነው።

በመጨረሻም የአባይን ግድብ በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ሊኖሩ ይቻላሉ። እኔም አለኝ።ጥያቄዬ ግን በግድቡ ጥቅምና ጉዳት አልያም መዋጮ ወዘተ በሚሉ ዙርያ አይደለም።ባለፈው በግንቦት 20 እለት መንግስት ውሃውን 'የማስቀየር ሥራ' ሰራሁ ብሎ በቀጥታ ለሕዝቡ ባስተላለፈው መልእክት ዙርያ ነው። አንድ ፕሮጀክት ያውም ከሀገር ውስጥ አልፎ የአካባቢ ሃገራትን ብሎም ስሩ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ድረስ የሚዘልቅ ጉዳይ የያዘን ጉዳይ- 'የአባይን ግድብ' ለምን በአደባባይ ውሃውን መንገድ የማስቀየስ ሥራ ሰራሁ ተብሎ ያውም በቀጥታ በኢቲቪ ማስተላለፍ  አስፈለገ? ለምን የበለጠ ለግብፅ እና ሱዳን አስጊ አለመሆኑ ላይ የማሳመን ሥራ አልተደከመም?

እርግጥ ነው የማሳመን ስራው ተሰርቷል የሚል ሃሳብ ሊነሳ ይችላል። ነገር ግን የግብፃውያንን ስሜት ከሞራልም አንፃር ስሜታዊ እንዲሆኑ የታሰብ ካልሆነ በስተቀር የውሃውን መንገድ ማስቀየስ ሥራ በግንቦት 20 እለት ያንን ያክል መለፈፍ አስፈላጊ አይመስለኝም።የግድቡ መኖር በእራሱ ውሃውን መንገድ እንደሚያስቀይረው የታወቀ እስከሆነ ድረስ። ኢህአዲግ ለምን ግንቦት 20 ቀን ይህንን አደረገው?  የውጭ ፖሊሲያችንን እየቀረፀ ያለው ማነው? ኢህአዲግ የሚሰራውን እያወቀ ነው? ጥያቄዬ ነው።የግድቡ ሥራ የበለጠ የዲፕሎማሲ ሥራ በሚጠይቅበት ጊዜ የእዚህ አይነት ግብፅን ለማስደንበር እና ብሔራዊ 'ጀግንነትን' ለማስፈን የታሰበ እስኪመስል ድረስ በግንቦት 20 ቀን ''ውሃውን መንገድ አስቀየስኩት''  ማለት ለግብፅ ሕዝብ  የግብፅን መንግስት ''ጉሮሮህ ታነቀ ብለህ ንገረው'' ይመስላል። አሁንም እጠይቃለሁ የውጭ ፖሊሲያችንን የሚቀይሰው ማነው? 

አልጀዚራ ''inside story'' ፕሮግራም ግንቦት  22፣2005 ዓም (may 30,2013) በአባይ ግድብ ጉዳይ ላይ ከአዲስ አበባ አቶ በረከት ስምዖንን ፣ከለንደን ክሊር ፓስካ በአካባቢ ጥበቃ እና የምግብ ዋስትና  ኤክስፐርት እና ከካይሮ ላማ አልሃታል የአባይ ውሃ ኢንስቲቱት መስራች አባል ውይይት አዘጋጅቶ ነበር።



Inside Story- Death on the Nile

Thursday, May 30, 2013

ሰበር ዜና-የግብፁ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሞርስ ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስትራቸው አብደል ፋታህ አልስሲን ጋር ስብሰባ ተቀምጠው ነበር ፣ኤርትራ በአባይ ግድብ ጉዳይ ከግብፅ ጋር መሰለፏ ይፋ ሆኗል

ሰበር ዜና 
''አህራም ኦን ላይን'' የተሰኘው የግብፅ የድህረ-ገፅ የአንግሊዝኛ ጋዜጣ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 22፣2005 (may 30,2013) ከካይሮ እንደዘገበው የግብፁ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሞርስ ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስትራቸው አብደል ፋታህ አልስሲን፣የሃገር ውስጥ ሚኒስትራቸውን ሙሐመድ እብራሂምን እና የደህንነት ሚንስትር ራፋት ሸሃታን ይዘው ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ስብሰባ አድርገዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ኢሃብ ፋህሚ  ገለፃ ውይይቱ የተደገው ግድቡ በግብፅ ላይ የሚያመጣውን አይነተኛ ተፅዕኖ ላይ መሆኑን ጠቁመው በመቀጠል ''በጉዳዩ ላይ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በጋራ አጠቃቀም ዙርያ ላይ አሁንም ንግግር  እየተደረገ ነው'' ብለዋል።
በመጨረሻም እንደ ጋዜጣው ዘገባ  ፕሬዝዳንቱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ሙሐመድ ከማል ኦመር ጋር እና ከ ውሃ ሀብት ሚኒስትሩ ሞሐመድ በሃ ኤልድን ጋር መመካከራቸውን እና ''በግብፅ የውሃ አቅርቦት ላይ ማንም እንዲያስፈራራን አንፈቅድም'' የሚል መግለጫ ከፕሬዝዳንቱ ቤተመንግስት መሰጠቱን አጥቷል።


ከ''አህራም ኦን ላይን'' ዘገባ  ውጭ ተጨማሪ
 

ኤርትራ ናዋን ለይታለች 

 ባለፈው ወር የአባይን ጉዳይ አስመልክቶ የሱዳኑ ''ሱዳን ትሪቡን'' እንደዘገበው። ኤርትራ ሱዳን እና ግብፅ በቅኝ ግዛት ዘመን ኢትዮጵያን አግልለው ለብቻቸው የአባይን አጠቃቀም በተመለከተ የተፈራረሙትን ውል እንደምትደግፍ መግለጧን ዘግቧል። ለእዚህም ተግባሯ የግብፁ መሪ ሙሐመድ ሞርስ አቶ ኢሳያስን ማሞገሳቸውን እና በቅርቡ ሊያገኛቸው እንደሚሻ መግለጣቸውን ጋዜጣው አትቷል።

ግብፅ የኤርትራን ጦርነት ለማስጀመር ከዛሬ 35 አመት በፊት ለአቶ ኢሳያስ ካይሮ ላይ የነዳጅ ማደያ በመስጠት የሻብያን የመጀመርያ መነሻ ካፒታል ከሰጡት ውስጥ የምትቆጠር መሆኗንየሚገልጡ አሉ።
በ 1990 በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የግብፅ አማካሪ ጀነራሎች አስመራ መታየታቸውን ጠቅሶ አንድ በአዲስ አበባ የሚታተም የግል ጋዜጣ እውነትነቱን እንዲያረጋግጡ ለጠየቃቸው  በአዲስ አበባ የግብፅ  አምባሳደር በሰጡት መልስ ''ጡረታ ከወጡ በኃላ ጀነራሎቻችን ምን እየሰሩ እንደሆነ የማረጋገጥ ግዴታ የለብንም'' ማለታቸው እና ጉዳዩን በተዘዋዋሪ ማረጋገጣቸው ይታወሳል። 

ዛሬ የወጣው የግብፁ ''አህራም ኦን ላይን'' እና ባለፈው ወር በሱዳን የታተመው ''ሱዳን ትሪቡን'' የእንግሊዝኛ ዘገባን ከእዚህ በታች  በተያያዘው የ ''ጉዳያችን ጡመራ'' ላይ ያንብቡ።

1/ ''አህራም ኦን ላይን'

ahramonline

http://english.ahram.org.eg/News/72768.aspx 

Thursday, 30 May 2013
Egypt's Morsi, top officials mull response to Ethiopia dam move
Egyptian officialdom awaits outcome of tripartite commission's report on Ethiopian dam project – expected on Sunday – before deciding on appropriate response
Ahram Online , Thursday 30 May 2013
Share/Bookmark
Views: 283
Morsi
President Morsi and the officials during the meeting (Photo: Presidency Official Facebook Page)
President Mohamed Morsi on Thursday met with Defence Minister Abdel-Fatah El-Sisi, Interior Minister Mohamed Ibrahim and General Intelligence head Rafaat Shehata to discuss recent developments in Sinai and Egypt's position regarding Ethiopian plans to build a series of dams on the Nile.
According to presidential spokesman Ehab Fahmy, meeting attendees discussed the options available to Egypt to deal with Ethiopia's 'Renaissance Dam' project and the project's potential impact on Egypt and its share of Nile water.
Fahmy also stated that talks were ongoing with Ethiopian officials in an effort to reach an agreement to the "mutual benefit" of both countries.
President Morsi, Fahmy said, had also discussed the issue with Foreign Minister Mohamed Kamel Omar and Water Resources Minister Mohamed Bahaa El-Din.
At a press conference held earlier on Thursday at the Presidential Palace in Cairo, Fahmy said that the presidency would "not allow anyone to threaten Egypt's supply of Nile water."
Egypt supports development projects in Africa "as long as they don't affect Egypt's national security," the presidential spokesman stressed. He went on to note that President Morsi was keen to cooperate with "all African states" on water-sharing issues.
At a press conference convened following the meeting with the president, Bahaa El-Din declared that the Egypt had ruled out a military response in the event that Ethiopia insisted on going ahead with its dam project.
The minister added that a report on the dam project by an international tripartite commission – consisting of representatives from Egypt, Sudan and Ethiopia – would be issued on Sunday.
If the report concluded that the Ethiopian dam project would adversely affect Egypt, Bahaa El-Din said that Egypt would prepare "a number of scenarios."  

2/ ''ሱዳን ትሪቡን''


SUDAN TRIBUNE 

FRIDAY 19 APRIL 2013
http://www.sudantribune.com/spip.php?article46276

Eritrea supports Egypt’s position over Nile water dispute

separation
increase
decrease
separation
separation
  • facebook
  • myspace
  • twitter
  • buzzyahoo

By Tesfa-Alem Tekle
April 18, 2013 (ADDIS ABABA) – The Eritrean government said this week that it supports Egypt’s stance over a colonial-era treaty that granted Egypt a right to utilise the lions share of Nile river’s water resources.
The Red Sea nation expressed its support in a message sent from the Eritrean president and delivered to Egypt’s president by Eritrean Foreign Minister Osman Saleh and Presidential Adviser for Political Affairs, Yemane Gebreab.
The Egyptian president, Mohamed Morsi, has highly welcomed Eritrea’s position towards Egypt’s "historic rights" over the sharing of the water of the Nile River.
Morsi said that he looks forward to meeting his Eritrean counterpart.
Although Ethiopia is the source of 85% of the Nile’s water, downriver countries, Egypt and Sudan, use 51 billion and 18 billion square meters a year respectively, around 90% of the Nile’s resources.
In April 2010, Ethiopia, Rwanda, Uganda, Kenya and Tanzania signed a new agreement in Entebbe, Uganda, to overturn a colonial-era treaty seeking a more reasonable and equitable utilisation of the river.
The deal was approved after Burundi later signed the agreement and joined the group in March 2011.
Newly-independent South Sudan has not yet signed the Cooperative Framework Agreement but it has also rejected the 1959 Nile water agreements between Sudan and Egypt.
Downstream countries of Egypt and Sudan have, however, dismissed the deal, saying the agreement is insignificant because it did not include all Nile basin countries.
Egypt has in the past warned against construction of further dams along the Blue or White Nile’s.
One year after the Cooperative Framework Agreement was signed; Ethiopia launched the construction of a massive $4.8 billion dam on the Blue Nile River raising protests from Sudan and Egypt that the dam - Africa’s biggest - would reduce the flow of the water to their territories.
Currently a tripartite committee, which is composed of six experts drawn from Ethiopia, Egypt and Sudan, and four more international experts are assessing the impacts of the project.
The team is expected to announce the final findings and conclusions in May 2013.
(ST)

Wednesday, May 29, 2013

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በ''ቢቢሲ'' ''ሃርድቶክ'' ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቀጥታ ስርጭት (ቪድዮ)

  የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በ''ቢቢሲ''  ''ሃርድቶክ'' ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  ቀጥታ ስርጭት (ቪድዮ) 

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ሳምንት ግንቦት 18፣2005 ዓም ለአፍሪካ ህብረት 50ኛ የወርቅ 
እዮቤልዩ በዓል ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ተገኝተው ነበር።ታዋቂዋ እና  ድምፀ መረዋዋ የ''ቢቢሲ'' ጋዜጠኛ ዘና በዳዊ ታዲያ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ዝነኛውን ''ሃርድቶክ'' ፕሮግራም በመምራት በቀጥታ ለመላው አለም እንዲተላለፍ አድርጋለች። ዘና በዳዊ በአያቷ ኢትዮጵያዊት ስትሆን ሱዳን ውስጥ ስታድግ ስለኢትዮጵያ ብዙ ታሪክ እንደተማረች መናገሯ  ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ተዘግቧል።

ቪድዮውን ይመልከቱት።


Tuesday, May 28, 2013

ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚፈሩበት ጊዜ ነው

ግንቦት 20፣1983 ዓም ታላቁ ቤተመንግስት በር 
ዛሬ ግንቦት 20 ነው።ግንቦት 20 የኢትዮጵያ የፖለቲካ መዘውር የተዘወረበት ለመሆኑ አሌ አይባልም። ዕለቱ እንደ አቶ ሃይለማርያም የመጀመርያ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ እንዳደረጉት ንግግር '' ኢትዮጵያ ልትበታተን ስትል የዳነችበት ቀን'' ነው ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግን ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚፈሩበት ጊዜ ነው።ይህንን ሁለተኛውን ሃሳብ እኔም እጋራዋለሁ። ካለፈው ይልቅ መጪው ይቀርበናል።ያለፈውማ አለፈ።መጪው ግን ቢዘገይም ቢፈጥንም አይቀርም።እና ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ ለመጪዋ ኢትዮጵያ እንዴት አስጊ ያደርገዋል። ይህንን ለማብራራት ግንቦት 20 እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ ይዞት የመጣውን በጥቂቱም መጥቀስ ይፈልጋል።ስለተሰራው የመንገድ እርዝመት፣ህንፃ፣ወዘተ ማተት ይቻላል።እርግጥ ነው መንገድ ተስርቷል።ህንፃ ተገንብቷል።ከተሞች ሰፍተዋል።ይህ ሁሉ  ግን መጪውን አስፈሪ ጊዜ ለሀገር ከመተው አልገታውም።

መጪውን አስፈሪ የሚያደርገው የግንቦት 20 ውጤቶች ምን ምን ናቸው? 

እንድሜ ለግንቦት 20 ብዬ ብጀምርስ-

  • እድሜ ለግንቦት 20 ዛሬ ኢትዮጵያ በአለም ታይቶ በማይታወቅ መልክ በቁጥር ተከልላ ክልሎች ስለ ድንበሮቻቸው ሲደራደሩ አንዳንዴም ሲጋጩ ለማየት በቅተናል።ምሳሌ የአፋር እና ትግራይ፣የሱማሌ እና ኦሮሞ፣የአማራ እና አፋር ወዘተ መጥቀስ ይቻላል።
  • እድሜ ለግንቦት 20 አንድሰው ከአንዱ የሃገሪቱ ክልል ተነስቶ እንበል ደቡብ ወይንም ጅጅጋ  ገብቶ መሬት ገዝቶ ልረስ ወይንም ልነግድ  ቢል እርሱ ከመምጣቱ በፊት ከ 60 እና 70 አመት በፊት የሰፈሩቱ ከጉርዳፈርዳ፣ጋምቤላ፣ጅጅጋ እና አሶሳ ካለምንም ካሳ ሲባረሩ ያያል እና መጪው እያስፈራው አይሞክረውም።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወላጆች ልጆቻቸውን በፈለጉት ቋንቋ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ በታሪካዊ አጋጣሚ የሚኖሩበት ክልል ቋንቋ ውጭ እንዳይስተምሩ ታግደዋል።ለምሳሌ ኦሮምኛ ተናጋሪ ልጁ በአማርኛ እንዲማር ቢፈልግ ግን በኦሮምያ ክልል ቢኖር አማርኛ ወደምነገርበት ክልል መሄድ ብቸኛ አማራጩ ነው።በምዕራቡ አለም የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ግን ልጁን በሀገሩ ቋንቋ እንዲያስተምር ባህሉን እንዲጠብቅ ድጋፍ ይደረግለታል።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሆና የባህር ኃይሏን በትና  30 እና 40 ኪሎሜትር እርቀት የባህሩ ማዕበል ሲማታ እየተሰማ ከ85ሚልዮን በላይ ሕዝብ ወደብ አጥቶ የጅቡቲን እና የሱዳንን ወደቦች በከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍል ተወስኖበታል፣
  • እድሜ ለግንቦት 20  ጦርነት ቆመ በተባለበት ጊዜ በአዲስ አበባ ብቻ ከ 100ሺህ በላይ ''ጎዳና ቤቴ'' ያሉ ሕፃናት መንገድ ላይ ፈሰው ኃላፊነት የሚወስድ መንግስት አጥተው ለማየት የበቃነው በግንቦት 20 ፍሬ ነው። (በቀድሞው መንግስት የተመሰረተው የሕፃናት አንባ እንዴት በአሁኑ መንግስት እንደፈረሰ ይህንን ሊንክ ከፍተው ቪድዮውን ይመልከቱ (http://gudayachn.blogspot.no/2013/05/main-play-list-on-home-page-playlist.html)፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ከሃያ ሁለት አመት በፊት ''የጫት ቤት'' ብሎ በር ላይ መለጠፍ የምያሳፍርባት አዲስ አበባ ዛሬ ጫት በየዘርፉ ''የበለጩ ፣የባህርዳር፣ የወልሶ ጫት ቤት'' ብቻ ተብሎ ሳይሆን የሚለጠፈው ''ጫት እናስቅማለን፣ እንፈርሻለን'' ተብሎ የተፃፈባቸው ባብዛኛው ትምህርት ቤቶች የሚገኙበትን ቦታ ፈልገው የሚከፈቱ የጫት ቤቶች በዝተው ለመታየት በቅተዋል። ምን ይህ ብቻ ዩንቨርስቲዎቻችን በየዶርሙ ጫት ሸጉጠው ሲገቡ- ሲ ቃምባቸው ደጉ መንግስታችን በዝምታ አልፎ ትውልዱን ጫት ቃሚ አድርጎታል። 
  • አድሜ ለ ግንቦት 20 ምሳ ሰዓት ላይ ከቢሮ ወጥተው ጫት ቅመው የሚመለሱ የባንክ ሰራተኞች፣መሀንዲሶች ወዘተ አፍርቷል ግንቦት 20።ከደንበል ህንፃ ጀርባ የሚገኙ የመቃምያ ቦታዎችን ብንመለከት በምሳ ሰዓት ደንበል ህንፃ የሚሰሩ ምሁራን ዩንቨርስቲ ሳሉ በተፈቀደላቸው የመቃም መሰረት ሥራ ከያዙ በኃላም ለመላቀቅ ትቸግረው ይታያል።እረ  እንዲያውም በሥራ ሰዓት ሾለክ ብለው የሚቅሙ ሰራተኞች መኖራቸውን የእዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ እማኝ ነው። እድሜ ለግንቦት 20።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወላጅ አልባ ሕፃናት ጎዳና እንዳይወጡ በሕዝቡ የሚደገፍ እንደ ሕፃናት አምባ መስርቶ ከማሳደግ ይልቅ ለአንድ ሕፃን እስከ 25000 ዶላር መንግስት እየተቀበለ በጉዲፈቻ ስም ለአሜሪካ እና አውሮፓ የተቸበቸቡት እና ብዙዎች በህሊና ስቃይ እና የማንንነት ጥያቄ እንዲሰቃዩ የተደረጉት በግንቦት 20 ፍሬ ነው (ሰኔ 25/2012 እአአቆጣጠር  በቢቢሲ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ አንድ ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በአመት 5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ አሜሪካ  ብቻ እንደሚሄዱ  እና አሜሪካ ከዓለም ላይ በማደጎነት ከምትወስደው ሕፃናት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ከ አምስቱ አንዱ እንደሆኑይገልፃል።(http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474)
  • እድሜ ለግንቦት 20 ሴት እህቶቻችን ተስፋ ቆርጠው ለአረብ ሀገር ባርነት  በአስርሺዎች የተጋዙት በሄዱበት ሀገርም ስበልደሉ የሚሰማቸው አጥተው አሳር ፍዳቸውን የሚያዩት ከግንቦት 20 ፍሬ ወዲህ ነው።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ''የኤርትራ ጥያቄን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት የሚቻለው የ ሻብያን ሃሳብ በመቀበል ነው'' ብለው ስያግባቡን የነበሩት  አቶ መለስ- ጦርነቱ አበቃ ከተባለ ከ ሰባት አመታት በኋላ ለዳግም እልቂት ''ድንበር'' በሚል ሰበብ ዳግም የኢኮኖሚ ፀባቸውን ወደ ወታደራዊ ግጭት ቀይረው በአስር ሺዎች የረገፉት በ ግንቦት ሃያ ውጤት ነው፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ስደት ቀድሞ የነበረ ቢሆንም በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ በባህር፣በእግር ወዘተ ወጣቱ ከሀገር የሚወጣው ከግንቦት 20 ፍሬ ወዲህ ነው (ወደየመን በጀልባ ተሳፍረው ከገቡት ስደተኞች ከ 70%በላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን በዘንድሮው ዘገባው መጥቀሱን ልብ በሉ) ፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወጣቶች ተምረው በእውቀታቸው ሀገርንም መጥቀም ሲገባቸው፣የስራ ዕድል የሚያገኙበት ወይንም  ስነልቦናቸውን የሚጠብቅ ግን ለፈጠራ የሚያዘጋጅ የስራ መስክ ከመፍጠር ይልቅ በምረቃቸው ጊዜ (የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  2004ዓም ምረቃ ላይ አቶ ጁነዲን ለተማሪዎቹ እንደተናገሩት)ከዩንቨርስቲ ሲወጡ  የኮብል ስቶን ሥራን መስራት እንደሚገባ የተነገራቸው በግንቦት 20 ውጤት ነው። 
  • እድሜ ለግንቦት 20 በሚድያውስ ቢሆን (ጎረቤት ኬንያን ለማነፃፀርያ እንጠቀም) ኬንያ የህዝብ ብዛቷ 30 ሚልዮን ሲሆን እኛ 85 ሚልዮን መሆኑን እናስታውስ እና ኬንያ በይዘታቸውም ሆነ በአቀራረባቸው የመንግስት እጅ ያልተጫናቸው 8 የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ 38 ራድዮ ጣብያዎች፣ ከእሩብ ሚልዮን በላይ አንባቢ ያላቸው በየቀኑ የሚታተሙ 4 ጋዜጦች (http://www.pressreference.com/Gu-Ku/Kenya.html#b) ሲኖሩ ሃሳብን የመግለፅ መብት እና በሀገሪቱ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ የመወያየት ነፃነት ከእኛ ጋር ሊወዳደር የማይችል መሆኑን ስናስብ እና ጋዜጠኞች መንግስትን ወቀሱ ተብለው በአሸባሪነት ዘብጥያ መውረዳቸውን ስናስብ እድሜ ለግንቦት 20 እንላለን።
  • እድሜ ለ ግንቦት 20 ጋና ነፃነቷን ስታገኝ የገነባነው ስታድዮም ዛሬ ጋና ከነፃነት አልፋ እስከ መቶ ሺሕዝብ የሚይዝ ስታድዮም ስትገነባ እኛ አሁንም አንድ ለእናቱ በሆነ ስታድዮም መገኘታችን የግንቦት 20 ውጤት ነው።እርግጥ ነው በዛሬው የግንቦት 20 በዓል የስፖርት አካዳሚ ምረቃ በአል እየተከበረ ነው። ስታድዮምስ ?
  • እድሜ ለግንቦት 20 ቀድሞ ጉቦ የሚለው ቃል ሲነሳ ስለ 20 እና 30 ብር ጉቦ እናስብ ነበር። ዛሬ ጉቦ፣ሙስና እና ዝርፍያ ማለት አድገው ተመንድገው  ዝርፍያ ማለት የብሔራዊ ባንክን የወርቅ ክምችት በወርቅ መሰል ነገር መቀየር ሲሆን ጉቦ ማለት ደግሞ የሀገር መሬት እና ውሃን  ለሕንድ እና ለአረብ በርካሽ መቸብቸብ ፣ በባለስልጣናት ቤት እንደባንክ ቤት በኢይሮ ብሉ በዶላር ቢሉ በፈለጉት የገንዘብ አይነት ከቤት ማስቀመጥ ማለት ነው (በቅርቡ የግምሩክ ባለስልጣናት ቤት  ተገኘ የተባለውን ብር ያስታውሱ)።

ይህንን ሁሉ ስናስብ ነው እንግዲህ ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚያስፈራ የሚያደርግብኝ።ከሁሉ የከፋው ግን መንግስት ስለሰራሁት መንገድ እና ድልድይ ስታመሰግኑኝ መስማት ብቻ ነው የምፈልገው ከማለቱም በላይ መሰረታዊ ስህተቶችን ''የጨለምተኞች አመለካከት'፣ የአመለካከት ችግር'' እያለ ማጣጣሉን መቀጠሉ ነው አሳዛኙ።

አበቃሁ 
ጌታቸው 
ኦስሎ 

Sunday, May 26, 2013

አጥንት የሚሰብር ድርጊት (ቪድዮ)

የሕፃናት አምባ እንዴት ተዘጋ? ጉዳያችን ጡመራ በሚያዝያ ወር 2005 ዓም

(http://gudayachn.blogspot.no/2013/04/blog-post_8.html)ወላጅ አልባ ሕፃናትን በተመለከተ ቀረበ ፅሁፍ ''የሕፃናት አምባ'' በቀድሞ መንግስት እንደተመሰረተበአሁኑ መንግስት ደግሞ መዘጋቱን እና በአሁኑም ጊዜ ሕፃናትን በጉድፈቻነት ወደውጭ ከመላክ ይልቅ በአንድ ላይ የማሳደግ በጎ ስራ መስራት የመቻሉን እውነታ ቸል መባሉን የሚያሳስብ   ነበር።
ሆኖም ግን ፅሁፉ   እንዴት በአሁኑ መንግስት እንደተዘጋ በቂ መረጃ አልያዘም ነበር።የኢሳት ቴሌቭዥን ''ምን አለሽ መቲ?'' ፕሮግራም ላይ የአምባው ሕፃናት እንዴት እንደተባረሩ የሚያሳይ ቃለ መጠይቅ ቀርቧል።ጉዳዩ እጅግ አሳዛኝና አጥንት የሚሰብር ድርጊት ነውአሁንም ስላለፈው ጉዳይ በማዘን መቆጨቱ ምንም ላይፈይድ ይችላል።ይልቁንስ አሁንም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አባት እናት የሌላቸው ሕፃናትን እንዴት እንድረስ?መንግስትም ኃላፊነቱን እንዴት ይወጣ? የሚለው ላይ ማተኮር ከዜጎች የሚጠበቅ ግዴታ ነው። 


ኢሳት ''ምን አለሽ መቲ?'' ፕሮግራም

Friday, May 24, 2013

የቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ታሪካዊ ንግግር በ አፍሪካ አንድነት ድርጅት (የሁኑ አፍሪካ ህብረት) የመሪዎች ስብሰባ።


የቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ታሪካዊ ንግግር በ አፍሪካ አንድነት ድርጅት (የሁኑ አፍሪካ  ህብረት) የመሪዎች ስብሰባ።












የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የሰሞኑ ከራሞት ልዩ ሪፖርታዥ

የ2018 ዓም የጥምቀት በዓል አከባባር በአቴንስ ኪዳነምሕረት  በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ፡  በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱን እና ምእመናንን  የሚያምሷት እነማን ናቸው? እራሱን ''የሲ...