ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, November 16, 2022

አንዳንድ የህወሓት አመራሮች መሳርያ መሸከም በራሱ ለውጥ እንደማያመጣ ቆይቶም የገባቸው ይመስላል።አሳማኝ ምክንያቶቹ ሦስት ናቸው። አሁንም በተለይ የትግራይ ህዝብ በስሙ ከሚንቀሳቀሱ በንቃት ሊጠብቀው የሚገባው አደጋ።


የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ህዝብን በአጨዳ እና እህል መሰብሰብ ሲያግዝ
ህዳር፣2015 ዓም

  • ከጽሑፉ ስር በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያ ፌድራል መንግስት እና በህወሃት መሃል የተደረገው ስምምነት የተፈረመው ሙሉ ሰነድ ያገኛሉ።
(ጉዳያችን ምጥን)

የፕሪቶርያው እና የናይሮቢው በኢትዮጵያ ፌድራል መንግስት እና ህወሃት መሃከል የተደረጉት ስምምነቶች ኢትዮጵያውያንን አስደስቷል።በትግራይ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ዘንድ የዕለት ከዕለት ኑሮ ላይ ቀስ በቀስ ለውጥ እያመጣ ነው። የምግብ ዋጋ አንጻራዊ በሆነ መልኩ መቀነስ አሳይቷል፣ ገበያዎች ከጸጥታ ስጋት ተላቀው መከላከያ በሚያደርገው ጥበቃ ግብይቶች ተጀምረዋል፣የምግብና የመድኃኒት አቅርቦት ተጀምሯል።እርዳታው መቀሌ ድረስ መጓጓዝ መጀመሩን የእራሱ የህወሃት አመራሮችም ሳይክዱ እያረጋገጡ ነው። 

ህወሓት መሳርያ መሸከም በራሱ ለውጥ እንደማያመጣ ቆይቶም የገባው ይመስላል።

ህወሃት በመጀመርያ የነበረው ህልም ኢትዮጵያን አሸንፋለሁ የሚል ቅዠት ላይ ነበር።ይህንን ቅዠቱን ደግሞ በትዕቢት እንዲታጀብ የኢትዮጵያ የቅርብ እና የሩቅ ጠላቶች አይዞህ ባይነት እራሱን ከሚገባው በላይ እንዲኮፍስ አድርጎት ነበር።ቆይቶ ግን ተከትሎ የመጣው አደጋ ለተወሰኑት የገባቸው ይመስላል።እዚህ ላይ ግን ሁሉም ግን ገብቷቸዋል ለማለት ጊዜው አሁን አይደለም። ቀድሞ የሚገባቸው፣ሲያጣጥሙ የሚገባቸው እና ፈጽሞ የማይገባቸው ዛሬም የሉም ማለት ግን አይደለም።

አሳማኝ ምክንያቶቹ ሦስት ናቸው

ህወሃት ወደ ትጥቅ መፍታት ያደረሱት ምክንያቶች ሦስት ናቸው።

1) ግልጽ የሆነው የመከላከያ እና የጥምር ጦሩ አብዛኛዎቹን የትግራይ ከተሞች እና ገጠር ነጻ በማውጣቱ እና በመጨረሻም ህወሃት ሙሉ ህልውናውን ሊያጣ ስለሆነ ነው።

2) ኤርትራን በአጋጣሚው ታጠፋኛለች የሚል ስጋት ነው።ከኤርትራ ጋር ያለውን ድንበር ደግሞ ህወሃት ሊጠብቅ እንደማይችል አውቋል።ይህ ድንበር ሊጠበቅ የሚችለው በመከላከያ እና በመከላከያ ብቻ ነው።የኤርትራ ከኢትዮጵያ ፌድራል መንግስት ጋር ያላት መልካም ግንኙነት ስላሰጋው የመከላከያን ልዕልና ከመቀበል ሌላ አማራጭ የለውም።

3) ሦስተኛው  መሳርያ ይዞ ህዝቡን ሁሉ ወደ ጦርነት መምራት  በእዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን ቢያሸንፍም ባያሸንፍም  ምን ያህል ወደኋላ እንደሚያስቀር ደግሞ በዓይኑ አይቷል። በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገብታ ተጓጉለዋል፣ገበሬው እርሻ ማረስ አልቻለም፣ነጋዴው ሱቁን ዘግቷል። ይህ ሁኔታ ህዝቡ በራሱ ህወሃት ላይ መጠቆም ጀምሯል ብቻ ሳይሆን መከላከያ ወደ ትግራይ ሲገባ በደስታ ከመቀበል አልፎ በሁሉ ነገር ተባባሪ መሆኑ አስደንግጦታል።

አሁንም በተለይ የትግራይ ህዝብ በስሙ ከሚንቀሳቀሱ በንቃት ሊጠብቀው የሚገባው አደጋ

ህወሃት ስለ ትጥቅ መፍታት ቢፈርምም አሁንም ግን በራሱ ውስጥም ሆነ በውጭ ያለ ትግራይን የመገንጠል ዓላማ የያዙ እንቅስቃሴዎች ለትግራይ ህዝብ ሌላ አደጋ አለበት።ይህንን መገንጠል የሚል ሃሳብ በራሱ በህወሃት ውስጥ የሚደግፉም የማይደግፉም አሉ።የሚደግፉት የመከላከያ በትግራይ መኖር በዋናነት ለተገንጣይ ሃሳብ አራጋቢዎች መድኃኒት እንደሆነ ስለሚያስቡ ይህንን ስምምነት ይደግፋሉ።በሌላ በኩል ደግሞ የተገንጣዩ አንጃ የጠነከረ ሲመስላቸው መገንጠል የማይደግፉት አካላት ከተገንጣዮቹ ጋር ለመመሳሰል የሪፈረንደም ጉዳይን በማውራት የተገንጣዩን አንጃ ግልምጫ ለማምለጥ ይሞክራሉ።በሌላ በኩል የመገንጠል እንቅስቃሴ በትግራይ እንዲኖር ከሚገፉት ውስጥ የውጭ ኃይሎች ዋና አቀጣጣዮች ናቸው።እነኝህ ኃይሎች ከመገንጠሉ በላይ የተራዘመ ጦርነት ኢትዮጵያ ላይ እንዲኖር ነው ዋና ግባቸው።በውጤቱም የተዳከመች ኢትዮጵያ ማየት ነው።

በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ነቅቶ መጠበቅ ያለበት ትግራይን ለመገንጠል በህወሃት ውስጥ ባሉ እና በውጭ ከተደራጁት እንደ ባይቶና ያሉት አደረጃጀቶች የአጭር እና የረጅም ጊዜ ግብ ከባዕዳን ጋር እየቀረጹ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።ለእዚህም ግብ መሳካት የዘር ማጥፋት በትግራይ ላይ ተፈጽሟል የሚለውን የሃሰት ትርክት በብዛት በማሰራጨት ነገ ገንጥለው ለባዕዳን ለማስረከብ የሚሞክረው አካል ስልት መሆኑም የትግራይ ህዝብ ሊያውቀው የሚገባ ነው።የትግራይ ህዝብ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ከተገንጣይ እና በመገንጠል ከባዕዳን መተዳደርያቸውን ለመቀበል ከሚቋምጡ በህወሃት ውስጥም ሆነ በውጭ ከተደራጁ ባንዳዎች እራሱን መጠበቅ አለበት። በእዚህ ጉዳይ ላይ የትግራይ ምሑራን ህዝቡን በማንቃት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል።

የኢትዮጵያ ፌድራል መንግስት እና ህወሃት በደቡብ አፍሪካ፣ፕሪቶርያ የተስማሙበት የተፈረመ ሰነድ








=======================///==============


No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)