================
ጉዳያችን እናስተዋውቃችሁ
================
1/ ዶ/ር ፍቅርተ አረጋ
ዶ/ር ፍቅርተ አረጋ ብልኋ ጦጢት በሚል ርዕስ የተረት መጽሓፍ ክፍል አንድ ይዛ ቀርባለች። መጽሓፏ በአሁን ጊዜ በአማዞን እየተሸጠ
ይገኛል።
የዶ/ር ፍቅርተ መጽሓፍ በእንግሊዝኛ፣በአማርኛ እና በኦሮምኛ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን የትግርኛ ትርጉሙ በቅርቡ እንደሚደርስ ገልጻለች።አማዞን ላይ ለመክፈት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። መጽሓፎቹን በሦስቱም ቋንቋዎች የሚያገኙበትሊንክ ከእዚህ በታች ያገኛሉ።
ብልኋ ጦጢት (Kindle edition only)
Totit the Baby Monkey & Her Wise Family
Qamalee Qarute (Afaan Oromo version) - (Kindle edition only)
2/ የጋዜጠኛ ማኅሌት ሊባኖስ ሚድያ
በዩቱብ ትውልዱ የጎደለበትን የማንበብ ባሕል እንዲያድግ የተለያዩ መጽሓፎችን እያስተዋወቀች የምትገኝ ወጣት ነች። ከመጽሓፎቹ ውስጥ አጓጊ ክፍሎቹን እየመዘዘች ትውልዱ እንዲያነብ እያበረታታች ነው። ብዙዎች እንዲህ ዓይነት የቁም ነገር ዩቱቦችን ሳይሆን የፌዝ እና ቧልት ሲሆን ብዙ ተከታይ እና ተመልካች አለው። ይህ በራሱ የስብራታችን ማሳያ ነው። የማኅሌት የመጽሃፍ ዳሰሳዎች ግን አስተማሪዎች ናቸው።
የሊባኖስ ሚድያ ሊንክ ከእዚህ በታች ያገኛሉ።
3/ የእንግዳወርቅ Engida Vlogs ዩቱብ
እንግዳወርቅ ከምትኖርበት ኬንያ ባላት ጊዜ ወገኖቿን ለማስተማር፣ያገኘችውን ለማካፈል ትተጋለች።ኬንያ ውስጥ ያሉ ልምዶች፣የህይወት ተሞክሮ፣የቤት አያያዝ፣የምግብ አዘገጃጀት ወዘተ ለወገኖቿ ለማካፈል ትተጋለች። አሁንም ግን የቧልት ዩቱበሮች ይሰማሉ እንጂ ቁምነገር የያዙትን የሚከታተለው ጥቂት ነው።
የእንግዳ ወርቅ ዩቱብ ሊንክ ከእዚህ በታች ያገኛሉ።
ባጠቃላይ ሴት ጸሓፊዎች፣የቁምነገር ዩቱብ አቅራቢዎች ብዙ የሉንም።ብዙ የቧልት ዩቱቦች እና ጽሑፎች ግን ሞልተዋል። ብዙው የሚከታተለው የቧልቱን ነው። የቁም ነገር ጸሓፊዎችን የሚከታተል ብዙም የለም። በመሆኑም ቁም ነገር ይዘው ብቅ የሚሉትን ማበረታታት አስፈላጊ ነው።ጉዳያችን ዛሬ ለጅማሮ ለመጠቆም ሞክራለች።ሌሎች ሚድያዎችም ሊቀጥሉበት የሚገባ ነው።
=================///፟=============
No comments:
Post a Comment