ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, June 18, 2022

ህወሓት በእንግሊዝኛ እደራደራለሁ፣በትግርኛ ደግሞ ለትግራይ ህዝብ ''እናንተ ሙቱልኝ እኔ ልኑር'' እያለ ነው።

  •  ''ከመሃል አገር የተወለዱትን የአህያ ልጆች አሉን፣ የመከላከያ አባላት በሲኖ ጨፍልቀው ሲገደሉ አይተናል።የ6ወር ህጻን ልጇን ይዛ ወደ ባሏ የሄደች የትግራይ ተወላጅም ተገድላለች።'' ከጽሑፉ መጨረሻ ላይ ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት የፈጸመውን ግፍ የትግራይ ተወላጅ እናት እና ልጅ የዐይን ምስክርነት ቪድዮ ያገኛሉ።
  • የኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ ወቅታዊ ሁኔታ አጭር ዳሰሳ 
===============
ጉዳያችን / Gudayachn
===============

ጥቂት ወደ ኋላ ስንመለከት 

አዲሱ ምዕተ ዓመት ከተጀመረ በኢትዮጵያ አቆጣጠር አስራ አራት ዓመታት አለፉ። ያለፈው ምዕተ ዓመት ኢትዮጵያ እንዴት አሳለፈችው? ብለን እራሳችንን ብንጠይቅ በሚከተሉት ዐበይት ጉዳዮች ዙርያ መሆኑን መግለጽ ይቻላል። እነርሱም በባዕዳን ቀጥታ ወረራ እና በነጻነት ድል፣መልሰን በመጠኑ በማንሰራራት፣ መልሶ በተነሳ በእርስ በርስ ጦርነት፣ በጎሳ ፖለቲካ የጥፋት ሰደድ እና ከጎሳ ፖለቲካ ለመውጣት እና እራስን ለመመልከት የሚታትር ትውልድ መነሳት በሚሉት ማጠቃለል ይቻላል ብዬ አምናለሁ።

እያንዳንዳቸው ታሪካዊ ሁነቶች በኢትዮጵያ ላይ ባለፈውም ሆነ የአሁኑ ትውልድ ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ አሻራ ጥሏል።በምዕተ ዓመቱ የተደረጉብን ቀጥተኛ የባዕዳን ወረራ ብንመለከት ግብጽ፣ኢጣልያ እና ሱማልያ ያደረጉትን ወረራ ማስታወስ ይቻላል። የጣልያን ወረራ በአባቶቻችን ትውልድ ውስጥ ከፍተኛ የትምሕርት እና የመሰልጠን ጥያቄ ጭሮ ንጉሱ እና በወቅቱ የነበረው ትውልድ በትምሕርት ላይ እና ኢትዮጵያን ከቀረው ዓለም እኩል ለማድረግ ከፍተኛ ትንቅንቅ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። በእዚህም ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለአፍሪካ ነጻነት ፋና ወጊ ከመሆን አልፋ አፍሪካን በራሷ ድርጅት (የአፍሪካ ሕብረት) እንድትሰባሰብ አሻራ ትተው አልፈዋል።

ከባዕዳን የቀጥታ ወረራዎች በተለየ በቀጣይ ጊዜዎች የተነሱት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ክስተቶች ውስጥ የጎላው የእርስ በርስ ጦርነቶች በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እና ኤርትራ የተለኮሰው ጦርነት ነበር።ይህ ጦርነት ውስጣዊ ይምሰል እንጂ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተርገበገበው እና የተደገፈው በኢትዮጵያ የቅርብ እና የውጭ ባዕዳን ነበር። የባዕዳኑ ዋና ፍላጎት ደግሞ ኢትዮጵያ የዓባይ ምንጭ እና የቀይባሕር ላይ ያላት የአንድ ሺህ ኪሎሜትር ቁጥጥር ነው። በተለይ በቀይባሕር ላይ በቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ የነበረው የሁለቱ የወቅቱ ኃያላን የአሜሪካ እና የሩስያ ሹክቻ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የሚንቀሳቀሰው ሻብያ እንደ መልካም ዕድል ተጠቀመበት።ሻብያን ተከትሎ የተመሰረተው የህወሃት ቡድንም እንደፈጣሪው ሻብያ ከአሜሪካ ብቻ ሳይሆን ከመካከለኛው ምሥራቅ አንዳንድ አገሮች ጋር ሳይቀር ያሳደገቻቸውን ኢትዮጵያን ለመውጋት በገፍ የጦር መሳርያ ድጋፍ አግኝተዋል።በኋላ ህወሃት አዲስ አበባ ሲገባ የባዕዳኑን አጀንዳ የጎሳ ፖለቲካ በኢትዮጵያ ላይ ለመትከል ሲታትር ከኖረ በኋላ የራሱን የጥፋት ትውልድ ተክሎ ኢትዮጵያን ወደ የመጨረሻው ውድቀት ለመክተት ሲዘጋጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለለውጥ ተነስቶ ሃገሩን ከውድቀት አፋፍ ታድጎ ትንቅንቁን ቀጠለ።

ያለፈው ምዕተ ዓመት ኢትዮጵያ ብዙ መልካም የሚባሉ ጉዳዮች ቢኖሯትም አጠቃላይ ውጤቱ ግን ኢትዮጵያን እንደ አገር ከጠላቶቿ ተናንቃ ለመቀጠል የቻለችበት፣የማደግ እድሏ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠበት፣ ነገር ግን መድረስ ትችልበት ከነበረበት ደረጃ እንዳትደርስ ተጎትታ የተያዘችበት እና በጎሳ የሚያስብ ትውልድ የተፈጠረባት ጊዜ ሆኗል።

አሁን ያለንበት ዓለም አቀፋዊ እና አገራዊ ሁኔታ  

ይህ በተለይ እያገባደድነው ያለው 2014 ዓ ም  ሆነ መጪው ቅርብ ጊዜ ምን ዓይነት ጊዜ ላይ ነን ብሎ አጠቃላይ ስዕሉን በመጠኑ ማወቅ እጅግ ጠቃሚ ነው።ለእዚህ ደግሞ የአገር ውስጡ እና የዓለም አቀፉ ሁኔታ ብሎ ከፍሎ ማየት ያስፈልጋል።

የዓለም አቀፉ ሁኔታ 

የዓለም አቀፉ ሁኔታ ከኮቪድ 19 በኋላ ያለው ዓለም አንድ ዓይነት ፍትጊያ ውስጥ እንደሚገባ ግልጽ እንደነበር ከሦስት ወራት በፊት ጉዳያችን ላይ ዩክሬን፣ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ እና ወቅቱ የሚጠይቀው ኢትዮጵያን እና መንግስትን የማገዝ ሃገራዊ ፋይዳው በሚል ርዕስ በወጣው ጽሑፍ ላይ እንዲህ የሚል ዓረፍተነገር ተጽፎ ነበር።

 ''የዓለማችን ሁኔታ ከኮቪድ ወረርሽኝ በመጠኑ መቀነስ ተከትሎ እና የዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ገቢ መቀነስ፣የምዕራቡን ዓለም የሚገዳደሩት የቻይና፣ሩስያ እና ቱርክ እንደገና ማንሰራራት ውጥረቶች እየጨመሩ መጥተዋል።ይህም የዓለምን ሥርዓት እንደገና እንዲከለስ ያስገድዳል። ሥርዓቱ ደግሞ በደፈናው አይከለስም።አንድ ዓይነት የጉልበት መፈታተሾች ተካሂደው ወይንም ግልጥ ከሆነ ጦርነት በኋላ የኃይል አሰላለፍ ልዩነት እንደሚኖር አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልጥ እየሆነ መጥቷል።''

ይህ የጉልበት መፈታተሽ በዩክሬን እና ሩስያ ተጀምሯል። ቻይና ታይዋንን በወቅቱ አጋጣሚ ለመቆጣጠር እያኮበኮበች ነው።አሜሪካ በሩቅ ምሥራቅ ያላትን ጥቅም እንዳታጣ ከአውስትራልያ እና በአካባቢው ካሉ ወዳጆቿ ጋር እየመከረች ነው። የዩክሬን ጦርነት በሩስያ እና በዩክሬን መሃከል ብቻ ላለመሆኑ ማሳያው ለዩክሬን መላው የምዕራቡ ዓለም ድጋፍ እያደረገ መሆኑ በራሱ መጪው የዓለም ሂደትን አመላካች ነው። ይህ ሁኔታ ጊዜ በወሰደ ቁጥር አገሮች የአሰላለፍ ለውጥ እያደረጉ ሲመጡ የሚተረተረው የክር እርዝመት የት እንደሚደርስ ለማውቅ አይቻልም። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት በትናንትናው ዕለት እንግሊዝ ገብተው የተደረገላቸው አቀባበል እና የአውሮፓ ሕብረት በጦርነት ላይ ያለችውን ዩክሬንን የያዝነው የአውሮፓውያን ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት በአባልነት ለመቀበል ሽር ጉድ ላይ መሆኑ በራሱ ውጥረቱ የት ድረስ እንደሚሄድ በደንብ አመላካች ነው።ዓለማችን ከጦርነት እንድጸዳ ጸሎት ያስፈልጋታል።

ዓለም አቀፋዊው ውጥረት በዓለም አቀፍ ሕግ የመመራት ቢያንስ በመጠኑ የመሸበብ ዕድሉ ሲላላ ትናንሽ የአካባቢ ጉልቤዎች በመንደራቸው ባሉ አገሮች ላይ ጉልበታቸውን ለማሳየት አጋጣሚ አይፈልጉም ማለት አይቻልም።ከእነኝህ አጉራ ዘለሎች መሃከል አንዳንድ የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ከኢትዮጵያ ጋር ባላንጣ ከሆነችው ከግብፅ ጋር ከእጅ አዙር ውግያ ወደ የቀጥታ ወረራ ሙከራ የሚያኮበኩቡበት ጊዜ አይሆንም ብሎ ማሰብ አይቻልም። ይህ ደግሞ በራሱ የኃያላኑ መፋጠጫ እና ኢከከኝ ልከክህ ሜዳ እንዳትሆን መሰራት ያለበት ጊዜ ነው።

የአገር ውስጡ ሁኔታ 

ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በእዚህ አጭር ጽሑፍ ሙሉ ስዕሉን ማሳየት ከባድ ነው።ሆኖም ግን የ2014 ዓም ኢትዮጵያ ያለፈችበት የፈተና ውጣ ውረድ ውስጣዊ እና ውጫዊ ገጽታውን በማንሳት ብቻ ብዙ ጉዳዮች ግልጽ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል።ይህ ዓመት ኢትዮጵያውያን የውስጣዊ ጉዳያችንን ታከው እነማን በምን ያህል ደረጃ ኢትዮጵያን ሰውተው በእራሷ ላይ ተረማምደው የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ፍላጎት እንዳላቸው የተመለከቱበት ጊዜ ነው። 

ይህም ሆኖ ግን በኢትዮጵያውያን ላይ በህወሃት ፈረስነት በኢትዮጵያ ላይ የተዘራው የጎሳ ፖለቲካ የራሱ የሆነ ግልገል አድናቂዎች ስላሉት እና ከኢትዮጵያዊነት የራቁ ነገር ግን ለገንዘብ ወገናቸውን የሸጠ ትውልድ በየዘርፉ ስለተበተነ የኢትዮጵያ ፖለቲካም ሆነ ሌሎች የማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብት ተቋማት በእዚሁ ረብ የለሽ አስተሳሰብ እና የኢትዮጵያ ነቀርሳ በሆነ አስተሳሰብ የተበከለ አስተሳሰብ አራማጆች ኢትዮጵያን ካለችበት ፈተና እንዳትወጣ ጋሬጣ ሆነውባታል።

ይህ ጋሬጣ በየዘርፉ ቢኖርም በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ እና በተለይ የጎሰኝነት መዘዝን በታላላቆቹ ስቃይ እና በኢትዮጵያ ላይ ያደረሰውን ጥፋት የተረዳ የቀደመውም ሆነ የአሁኑ ትውልድ ኢትዮጵያን ከጎሳ ፖለቲካ ገላግሎ፣የቀደመ ስህተቶችን አርሞ እና የራስን አቅም አዳብሮ ኢትዮጵያን ለማንሳት በከፍተኛ ደረጃ መነሳሳት እና የተግባር ሥራዎች እየታዩ ነው። እዚህ ላይ መንግስት አሁን የሚሰራቸው የአጭር ጊዜ ሳይሆን የረጅም ጊዜ አገር የሚጠቅሙ ስልታዊ ስራዎች ሁሉ በእዚሁ ጥረት ላይ የሚጠቃለሉ ናቸው።መንግስት በራሱ ያሉበት ተግዳሮቶች ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ነጸብራቆች እንጂ ከሌላ ዓለም የመጡ አይደሉም። አገርን እንደ አገር ለማቆም ደግሞ በጎውን የመንግስት ሥራ መደገፍ እና ኢትዮጵያን እንደ አገር ማንሳት የማንም ቅን ዜጋ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው።

በእንግሊዝኛ ሰላም ፈላጊ፣በትግርኛ ጦርነት የሚጎስመው ህወሃት 

አሸባሪው ህወሃት ለትግራይ እንደ አንድ የኢትዮጵያ ክልል እንደ አገር ደግሞ ለመላዋ ኢትዮጵያ መከራ ሆኖባታል።ህወሃት ኢትዮጵያ ልጆቿን በጎሳ ከፋፍሎባታል፣ሃብቷን ለራሱ እና ለባዕዳን ዘርፏል አዘርፏል። ይህ አልበቃ ብሎ ''ኢትዮጵያን በትኜ ሲኦል እገባለሁ'' በሚል በግልጽ ባወጀው አዋጅ አማካይነት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ በከፈተው ጥቃት አብረውት በወደቁ እና በተነሱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ምግብ ላይ መርዝ ከመጨመር እስከ የተኙበት ለመግደል ሞክሯል። ከእዚህ ባለፈ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ገበሬ በአማራ እና በአፋር በሚኖሩ ሰላማዊ ገበሬዎች ላይ በፈጸመው ወረራ ንጹሃንን ገድሏል፣ገበሬውን ዘርፏል፣ሆስፒታል ዘርፏል፣ትምህርት ቤቶች አቃጥሏል፣አብያተ ክርስቲያናት እና አብያተ መስጊዶችን በከባድ መሳርያ ደብድቧል።

ከእዚህ ሁሉ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ተነስቶ የፋሺሽታዊ የህወሃትን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ሆኖ አከሸፈው።በህወሃት የተጫረው ጦርነት ሺዎች የትግራይ ወጣቶችን አስጨርሶ፣ ከስራቸው እና ከኑሯቸው አፈናቅሎ መቀሌ ተመልሶ የትግራይ ህዝብ ላይ ሌላ ዙር ዘመቻ ከፈተ።በውጭ የሚኖረው የህወሃት የጭፍን አምላኪ እና የትግራይ ህዝብ ስቃይ የማይሰማው ስብስብ ደግሞ በህዝብ ስቃይ በየቲክቶኩ በመዝለል ተከታዮቹን ለማደንዘዝ ይጥራል። 

በቅርቡ ለህወሃት የመጨረሻው መጨረሻ ዕድል ተሰጥቶታል። በህወሃት የታገተው የትግራይ ህዝብን ስቃይ ለማሳጠር ከመንግስት በኩልም አዎንታዊ ሂደት መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርቡ በተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ መመስረቱን ቢናገሩም አሁንም ህወሃት የተለመደ የማጭበርበር ሥራውን ቀጥሎበታል። ይህንኑ ሂደት ተከትሎ ህወሃት ለውጪው ማኅበረሰብ በእንግሊዝኛ ለሰላም እንደሚደራደር ተናግሮ ለትግራይ ሕዝብ እና በውጭ ላሉ ደጋፊዎቹ ደግሞ ጦርነት እንደሚቀጥል በትግርኛ ከሰሞኑ ተናግሯል። 

የሽብር ቡድኑ መሪ ደብረጽዮን ከሰሞኑ በትግሪኛ በሰጠው መግለጫ ላይ ሙሉ ትኩረቱ የተለመደው ድንፋታ ላይ ያተኮረ መሆኑ በግልጽ ታውቋል። የቀድሞው የመቀሌ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና አሁን ደግሞ የሽብርተኛው ቡድን የውጭ ግንኙነት ቃል አቀባይ ክንደይ ገብረሕይወት በትዊተር ገጹ ላይ በአንድ አገር ውስጥ ሁሉት ሰራዊት ይኑር፣ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውጭ የትግራይ ሰራዊት የሚባል ይኑር በማለት የሽብር ቡድኑን አቋም በግልጽ አስታውቋል። ይህ ባጭሩ ጦርነት እንቀጥል ነው።

C:\Users\3060\Desktop\kinde.jpg
ህወሃት የትግራይ ተወላጆችን ዳግም እንዳያቄላቸው በእጅጉ ሊጠነቀቁ ይገባል።

ፋሽሽታዊ ድርጅቶች አንዱ የጋራ መለያቸው እያታለሉ የሚነዱትን ሕዝብ እየሞተ ሳለ፣ እየሞትክ አይደለም እያሉ ባፈጠጠ ውሸት መደለል ነው። ህወሃት የትግራይን ህዝብ ስንት ጊዜ እንደዋሸው ለማስታወስ መጀመርያ የትግራይ ህዝብ ከትግራይ ውጭ ያለው በሙሉ በኢትዮጵያ ህዝብ ሊጨፈጨፍ ነው እያለ በካድሪዎቹ የሃሰት ዜና መንዛት ጀመረ። ሁሉ ውሸት መሆኑ በሂደት ታወቀ።በመቀጠል መቶ ሺዎች ተደፈሩ የሚል ውሸት መንዛት ጀመረ፣የዘርማጥፋት ተፈጸመ አለ።የራሱ ደጋፊዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሳይቀሩ ውሸቱን አጋለጡበት። ከእዚህ በኋላ በቅርብ አዲስ አበባን እቆጣጠራልሁ ልጆቻችሁን አምጡ ብሎ መቶ ሺዎችን ህይወት አስቀጠፈ። አዲስ አበባ ቀርቶ ጎንደር እና ደሴ እንደናፈቁት ቀሩ። ተመትቶ ሲወጣም ሽንፈቱን ለመሸፋፈን በህልም እንጀራ የድል ወሬ የትግራይን ህዝብ ማወክ ይዟል።እዚህ ላይ የህወሃት አዲስ ዘፈን ''ሪፈረንደም '' የምትል ሙዚቃ ነች። ሪፈረንደም ለህወሃት ለትግራይ ህዝብ አስቦ ያነሳው ሳይሆን ለስልጣኑ ዋስትና ትግራይን ለባዕዳን አስይዞ ለስልጣኑ ዋስትና የሚሰጠው መንገድ አድርጎ ስለወሰደው ብቻ ነው።

የትግራይ ተወላጆች ህወሃት ዳግም እንዳይቄላቸው መጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን ሙሉ የክልሉ ህዝብ ስደተኛ፣ከስራ የተፈናቀለ፣ እና ተመጽዋች ያደረገው ህወሃት ዛሬም ለሌላ እልቂት ሊዳርገው ሲነሳ መንቃት እና ህወሃት ሳይሆን ቀድሞም የሞተለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መቀሌ እንዲገባ እና በውጤቱም ህዝቡ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር እና ልጆቹም ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለስ ማድረግ ከህዝቡ የሚጠበቅ ወቅታዊ ሥራ መሆን አለበት።ከእዚህ በላይ መታለል እና ህወሃት ለሰላም ቅረብ እየተባለ የተሰጠውን የመጨረሻ ዕድል ከረገጠ ክልሉ ሙሉ በሙሉ ይበትነዋል።

ማጠቃለያ

ህወሃት ካለጦርነት መኖር ይችላል እንዴ? 

የሽብርተኛው የህወሃት የጥፋት ትውልድ እየከሰመ ነው። ጦርነት እና ጎጠኝነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ መስማት የማይፈልገው ጉዳይ ነው። ይህ ማለት ግን በኢትዮጵያዊነት ህልውናው ላይ የሚነሳ ማንንም ይታገሳል ማለት አይደለም።በሌላ በኩል አሁንም ህዝቡ ታጋሽ ብቻ ሳይሆን ድንቅም ህዝብ ነው። ህወሃት የዚያን ያህል መርዘኛ የሆነ የጎሳ ጦርነት የሚያስነሳ ዘርን ማዕከል ያደረገ ቅስቀሳ ብቻ ሳይሆን ግድያ ሲፈጽም በመሃል ሃገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ አንዳች ግጭት ሳይፈጠር ህዝብ ተከባብሮ በሁሉም ማኅበራዊ ተቋማት ውስጥ ተከባብሮ መኖሩ የኢትዮጵያን ህዝብ ድንቅ ህዝብ ያደርገዋል። የህወሃትን ያህል ግፍ የፈጸመ የሽብር ቡድን በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ቢኖር በህዝብ መሃል በምን ያህል ደረጃ ግጭት ይፈጠር እንደነበር ለመገመት ቀላል ነው። ኢትዮጵያ ግን በእውነትም እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰውን የሚያፍር ህዝብ ያለባት አገር ነችና ሌላ ቦታ ህወሃት በጎሳ ስም ለፈጸመው ግድያ ከጎረቤቱ የሚጣላ ኢትዮጵያዊ የለም። ይህ ብስለት እና ማኅበራዊ አንድነትን ለመበጠስ ህወሃት አሁንም ለመጨረሻው መጨረሻ መሞከሩ አይቀርም። በመሆኑም የትግራይ ህዝብ በህወሃት ላይ አለመነሳት ያለውን አደጋ ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለመጪውም ነቀርሳ ማስቀመጥ ነው።
ሽብርተኛው ህወሃት የኢትዮጵያ ህዝብ ተነስቶ ሲይዘው እሪታውን ያቀልጠዋል። ሲለቀው ደግሞ ፉከራው አይጣል ነው።በተመሳሳይ ከውጭ ሆነው የሚያዳንቁትም እንዲሁ ናቸው።ህወሃትን የኢትዮጵያ ህዝብ ሲቀጣው ሻርፕ ለብሰው መቅለስለስ፣ ህዝብ ሲነሳ ደግሞ በየቲክቶኩ መዝለል ሥራቸው ነው። አሁን የሚዘለልበት ጊዜ አይደለም። መቶ ሺዎች ተፈናቅለው፣ አራስ እናት ልጇን እያጠባች የምትበላው ባጣችበት ጊዜ በእርዳታ እህል የተነፋፉ እነ ጌታቸው ረዳን እያዩ መዝለል ምን ዓይነት የአዕምሮ ድህነት ነው?

አሁን ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት ክልል በህወሃት የተቃኙ የጽንፍ ፋሽሽታዊ የጎሳ ስሜታቸው ከሰውነት አስተሳሰብ የባሰባቸው አሉ። የእዚህ ዓይነቶቹ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በኦሮምያም በአማራም በሌሎችም ክልሎች አሉ። እነኝህ ለሠላሳ ዓመታት ውስጥ ተጸንሰው ያደጉ ናቸው። አሁን ጊዜው የህዝብ መሆን አለበት። ህዝብ የጎሳ ጽንፈኞች እንዲመሩት ዕድል ላለመስጠት በሁሉም መስክ መስራት አለበት።ትግራይ ለበቀለው ፋሺዝምም ሆነ በኦሮምያ የሚንቀሳቀሰው ሸኔ እንዲሁም በአማራ ስም የጽንፍ አስተሳሰብ የሚያራምድ ሁሉ በህዝብ መገታት አለባቸው። አስታራቂው መንገድ የኢትዮጵያ መንገድ ነው።በግብጽ ''ኢትዮጵያን እንደ ዩክሬን ካላደረኩ ሰላም 
አላገኝም '' የሚሉ ተናጋሪዎች በሚደነፉበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን ከትግራይ እስከ ጅጅጋ፣ ከኢልባቦር እስከ ሓረር፣ከሞያሌ እስከ ጎንደር ሁሉ መተባበር እና ህወሃትን የመሰሉ የባዕዳን ወኪሎችን ለፍርድ የማቅረብ ሃላፊነት አለበት።ቀድሞም ይጠብቀን የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መቀሌ ይግባልን! ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል እና ለባዕዳን ለማስያዝ የሚሮጠውን ህወሃት ዳግም አይሸጠንም! የሚሉ ድምጾች ከትግራይ መሰማት አለባቸው።

ከኢቢሲ ሰኔ 8/2014 ዓም ካስተላለፈው ልዩ ቃለ መጠይቅ 


No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...