ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, June 22, 2022

በምዕራብ ወለጋ በሸኔ ፊታውራሪነት፣በህወሃት አቀናባሪነት እና ድጋፍ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በንጹሃን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ከሞቱት ውስጥ ከአንድ ቤተሰብ 12 ሰዎች የሞቱበት ሁኔታ አለ።የጭፍጨፋው ስልት ያልታየበት አቅጣጫ አለ።

ህወሃት በአቦይስብሃት ተወክላ አክራሪውን የሸኔ ቡድን ትግራይ ላይ ስትቀበል

========
ጉዳያችን
========

የጨፌው ስብሰባ 

ከወራት በፊት የኦሮምያ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ከቦረና የመጡ ዕድሜ የጠገቡ አዛውንት እጃቸውን አወጡ።ሽማግሌው የክልሉ ፕሬዝዳንት ያቀረቡት ሪፖርት ላይ ዋናው እና አንገብጋቢው ጉዳይ በሚገባ አለመወሳቱ አናዷቸዋል። አዛውንቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ የክልሉ ህዝብ ራስ ምታት የሆነው የፋሺሽቱ ሸኔ ጉዳይ በሚገባ አለመነሳቱን ተናገሩ። በመቀጠል የተናገሩ ተሳታፊዎችም ሸኔን ማጥፋት የሚለው አጀንዳ ዋና መሆን እንዳለበት ደጋግመው ተናገሩ።ይልቁንም እኛ ህዝቡን ወክለን እዚህ እንደመቀመጣችን ህዝብ የነገረን የጸጥታው ጉዳይ ቅድምያ ይሰጥ የሚል ነው በሚል ደጋግመው ተናገሩ። በመቀጠል የክልሉ ስብሰባ አቅጣጫ ወደ ሸኔ ጉዳይ ላይ ዞረ። አቶ ሽመልስም በጥቂት ወራት ሸኔን እናጠፋለን የሚል ዕቅድ መያዙን አስታወቁ።

የህወሃት የሽብር ጥቃት እና የወለጋ ጭፍጨፋ ፊትና ኋላ ናቸው።

አክራሪ እና አሸባሪው የኦነግ ክንፍ በህወሃት ዘመን በኦህዴድ ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ ብቻ ሳይሆን ወደ ስልጣን እርከኑ እንዲወጣ የተደረገው በህወሃት ምስጢራዊ ስብሰባ ነው።ከጅማ በሸሻ ጭፍጨፋ ጀምሮ የቀድሞው የጅማ ከተማ በጽንፈኛ የተሞላው አስተዳደር ጨምሮ አክራሪዎቹ ወደ ኦህዴድ የስልጣን መሰላል ሲንጠላጠሉ ህወሃት ያውቃቸው ነበር።ይህንንም እያወቀ የለቀቃቸው ስለ ሁለት ዓላማ ነበር። አንዱ ምክንያት በኦሮምያ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን እንዲያሳድዱ ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በራሱ በኦሮምያ ክልል ውስጥ በለዘብተኛው እና አክራሪው መሃከል ግጭት እንዲፈጠር እና ህወሃት በመሃል የክልሉን ሃብት እንደፈለገ መጠቀም እና መዝረፍ ስለፈለገ ነበር።

የዛሬ ሦስት ዓመት በፊት የኦነግ አክራሪ አንጃ በኤርትራ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገባውን ቡድን አቦይ ስብሃት ዓርማውን ጉልበታቸው ላይ አስደግፈው ምሳ የጋበዟቸው ቀድመውም ውስጡን የሚያውቁትን ቡድን ተጨማሪ የሎጀስቲክ ድጋፍ ከደጎሙት ኢትዮጵያን ያተራምስልኛል የሚለውን የህወሃት የነበረ ዕቅድ እያሰላሰሉ ነበር።ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሽብርተኛው ህወሃት በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ ከመፈጸሙ በፊት በምዕራብ ወለጋ የንጹሃን ህይወት ሲቀጠፍ በተከታታይ ታይቷል።በመሃል ከተፈጸሙት ጥቃቶች ውስጥ ለምሳሌ የጥቅምት 24ቱ የሽብርተኛው ህወሃት ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት በምዕራብ ወለጋ በአንድ ምሽት ከሁለት መቶ በላይ ንጹሃን ተገደለው ነበር።ህወሃት እና ሸኔ የተለያዩ አድርጎ ማየት አይቻልም።እነርሱም የተለያየን ነን አላሉም።የዛሬ ዓመት ላይም በጋራ ግንባር ፈጥረናል ብለው እንደነገሩን ብቻ ሳይሆን በከሚሴ ከተማ ጭምር በጋራ ሲገድሉ እና ሲዘርፉ እንደነበር እናስታውሳለን።በቅርቡ የተደረገው ጭፍጨፋም ላይ ህወሃት በሎጀስቲክ ብቻ ሳይሆን በስልጠናም አልተሳተፈም ማለት ሞኝነት ነው። ህወሃት በወለጋው ጭፍጨፋ ውስጥ እጁ እንዳለበት ለመረዳት ብዙ የምትቸገሩ አንዳንድ የዋሆች የጀርባ ታሪኩን ባታምኑ በሰሞኑ የህወሃት የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ለወለጋው ጭፍጨፋ ኦነግ ሸኔ አይደለም በሚል ሲለፍፉ መመልከት ብቻ በቂ ማስረጃ ነው።

የጭፍጨፋው ስልት ያልታየበት አቅጣጫ አለ።

እንደ መቀሌው ሁሉ በካምፓላ፣ጁባእና ናይሮቢ የሚርመሰመሱት የሸኔን እና ህወሃትን የተናበበ ጭፍጨፋ አቀናባሪዎች እና የውስኪ ብርጭቆዎቻቸው

የወለጋው ጭፍጨፋ አፈጻጸም ስንመለከት በአፍሪካ በተለይ በኮንጎ፣ናይጀርያ እና ሴራልዮን ውስጥ ይፈጸሙ የነበሩት ዓይነት ጭፍጨፋዎች ናቸው።እነኝህ ጭፍጨፋዎች የጠነከረ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ክርክሮች አይደሉም። ይጭፍጨፋዎቹ ዋና መሰረቶች ገንዘብ፣ኢትዮጵያን በጎሳ ፖለቲካ ለማተራመስ እና መንግስትን ውጥረት ውስጥ መክተት የሚሉት ናቸው።የግድያው ድርድር የሚደረጉት እና በሟቾቹ የደም ፍሳሽ ልክ ከባዕዳን ገንዘብ የሚቀበሉት ሰው በላ ቡድን አስተባባሪዎች የሚተራመሱት እና በፈሰሰው ደም ልክ ውስኪ የሚራጩት የሚተራመሱት ኝ መቀሌ፣ካምፓላ እና ናይሮቢ ናቸው። ወለጋ የማዕድን ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኩባንያዎች አሉ። በተመሳሳይ በናይጄርያ፣ሴራልዮን እና ኮንጎ ይፈጸሙ የነበሩ ጭፍጨፋዎች የሚመሩት በፈጻሚዎቹ ብቻ ሳይሆን በማዕድናት ላይ ፍላጎት ያላቸው አንዳንድ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጭምር በጓሮ በር ይደገፉ ነበር።ኩባንያዎቹ የእዚህ ዓይነት የቆ ሸሸ ሥራ ላይ ይሰማራሉ ብሎ የሚያስብ ማን አለ?

ከላ።ይ በጥቂቱ የጭፍጨፋው ሂደት የምናይበት አቅጣጫ አንጻርየወለጋው ጭፍጨፋ በተመለከተ መደረግ ያለባቸው ሦስት ጉዳዮች አሉ። እነርሱም  

  1. የኦነግ ሸኔ ዋና ደጋፊ ህወሃት አሁንም ለፍርድ መቅረብ አለበት። የኦነግ ሸኔ አስተሳስብንም ሆነ ቡድኑን መግቦ ያሳደገው እራሱ ህወሃት ነው።
  2. ከመቀሌ በተጨማሪ በናይሮቢ፣ካምፓላ እና ጁባ የሚተራመሱት የሸኔ የውስኪ ቅምጥሎች አድኖ ለፍርድ ማቅረብ ያስፈልጋል።እነኝህ በህወሃት እና በኦነግ ሸኔ መሃል አገናኝ መኮንኖች እነኝህ ናቸው።
  3. ለኦነግ ሸኔ የሳሳ ልብ ያላቸው ቀድሞ ህወሃት ወደ ኦህዴድ አውቆ ያስጠጋቸው ጽንፈኞች ከኦሮምያ ክልል የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ መንጥሮ ማውጣት ያስፈልጋል።
  4. ወለጋ ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና ከአማራ''ማጽዳት'' ወለጋ የኦሮምያ ብቻ ትሆናለች ብለው እያሰቡ የሚጃጃሉ የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ዛሬም አሉ። ሆኖም ግን ወለጋን ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና አማራ ማጽዳት የማዕድኑን ሃብት ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን የተራዘመ ጦርነት በመክፈት ኢትዮጵያን እናዳክም ብለው የሚያስቡ መኖራቸው የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው። 
 ባጠቃላይበምዕራብ ወለጋ በሸኔ ፊታውራሪነት፣በህወሃት አቀናባሪነት እና ድጋፍ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በንጹሃን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ከሞቱት ውስጥ ከአንድ ቤተሰብ 12 ሰዎች የሞቱበት ሁኔታ አለ።የጭፍጨፋው ስልት ያልታየበት አቅጣጫ አለ። የወለጋ የንጹሃን ኢትዮጵያውያን ግድያ ከዘር ጭፍጨፋ ባለፈ በአፍሪካ የማተራመሻ መንገድ ሆኖ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ላይ ተፈጽሟል።በኦሮምያ ክልል ያሉ ጽንፈኞች የአማራ ተወላጅ ወጥቶ ሰላም የሚያገኙ መስሏቸዋል።ይህ ግን ፈጽሞ አይሆንም።ድርጊቱን ባዕዳን የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚደግፉት ቦታውን ካለተከላካይ አመናምኖ እና አተራምሶ በቀጣይ ለውጭ ኩባንያዎች ባርያ የሆኑ የመንደር ቡድኖች መመስረት እና መበዝበዝ ቀጣዩ ሥራ መሆኑ ካልገባቸው ሊገባቸው ይገባል።ባጭሩ በወለጋው እልቂት ከኦነግ ሸኔ በላይ ህወሃት በንጹሃን ደም ጨፍሯል።ባዕዳኑ የማተራመሻ አጀንዳ ለመፍጠር አቀጣጣይ ክብሪት ይሆናል ብለው ይጠብቃሉ። ከሁሉም ከሁሉም ግን መንግስት የጸጥታ አጠባበቅ መንገዱን መከለስ እንዳለበት ብቻ ሳይሆን የደህንነቱ መዋቅር ቀድሞ የመከላከል አቅሙን ማዳበር ይገባዋል።
==========////============

No comments:

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...