አስመራ
የህወሓት ስርዓት ጥቃት ፈፀመ
=====================
የህወሓት ስርዓት ዛሬ እሁድ ሰኔ 12/2016 በማዕከላዊ የፆረና ግንባር በኩል ጥቃት ፈፅሟል።የጥቃቱ ዋና አላማ እና ግብ ገና ግልፅ አይደለም።የኤርትራ መንግስት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራርያ ይሰጣል።
የማስታወቂያ ሚኒስቴር
አስመራ
ሰኔ 12/2016
TPLF Regime launches an attack
The TPLF regime has today, Sunday 12 June 2016, unleashed an attack against Eritrea on the Tsorona Central Front. The purpose and ramifications of this attack are not clear. The Government of Eritrea will issue further statements on the unfolding situation.
Ministry of Information
Asmara
12 June 2016
ከላይ እንደተመለከተው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የሰጠው መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ጥቃት ፈፀመብኝ ሳይሆን ህወሓት ጥቃት እንደፈፀመች ነው የሚገልፀው ይህ በእራሱ ከእዚህ በፊት ከነበረው የኤርትራ መንግስት መግለጫ በእጅጉ ይለያል።ከእዚህ በፊት ኢትዮጵያን እንደ አገር ወረረችኝ ይል የነበረው የኤርትራ መንግስት አሁን በእንግሊዝኛ በማስታወቂያ ሚንስቴር በኩል ያወጣው መግለጫ ህወሓት ማለቱ መሰረታዊ የስትራቴጂ ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣቱ እና አቶ ኢሳያስ ከእዚህ በፊት ለኢሳት ከሰጡት ማብራርያ አንፃርም የምታረቅ መሆኑን ያሳያል። ይህ ጦርነት በአጭሩ የማይቆም ከሆነ ህወሓት ጠንክሮ የሚወጣበት ሳይሆን የበለጠ የሚገፋበት እንደሚሆን እሙን ነው።
ከሰው ኃይል እና ትጥቅ አንፃር ለአጭር ጊዜ ለምናልባት ህወሓት ድል ያገኘ ሆኖ ቢታይ በኢትዮጵያውያን እና በኤርትራውያን መካከል የበለጠ የስልት ግንኙነት እና መደጋገፍ ይዞ ስለሚመጣ የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታን የሚቀይር ምናልባትም የተሻለ እና የጠነከረ ዕድል ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ይዞ መምጣቱ አይቀርም።ይህ የሚሆነው ግን የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች እና የኤርትራ የፖለቲካ ተዋናዮች ግንኙነቱን እና ስልቱን ከአፍሪካ ቀንድ አንፃር ብቻ ሳይሆን ከመካከለኛው ምስራቅ በኩል በሁለቱ አገራት ላይ የሚያንዣብበውን አደጋ ወደተረዳ ደረጃ ማሸጋገር ሲችሉ ነው።
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች ለስልጣን እና ለገንዘብ የሚስገበገቡ የህወሓትን የጥቂቶች ቡድን አደገኛነት ማምከን ከቻሉ ከሌሎች አካባቢያዊ ስጋቶች እራሳቸውን ማዳን አይከብዳቸውም።የሁለቱን አገሮች ግንኙነት በስልት ላይ የተመሰረተ እና ከመካከለኛው ምስራቅ በኩል ከሚመጣው ዘመን ተሻጋሪ ስጋት ለመዳን የግድ በአንድነት የጋራ የዕድገት ስልት ከመንደፍ የተሻለ ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የተቃውሞ ኃይሎች እና የኤርትራ የፖለቲካ ተዋናዮች የጋራ የአፍሪካን ቀንድ የጋራ ብልፅግና ያገናዘበ ዕቅድ በሚገባ ነድፈው ሊገፉበት አካባቢያዊ ሁኔታዎች የግድ ይሏቸዋል። ለእዚህም ዋነኛ ምክንያቱ ሁለቱም በመካከለኛው ምስራቅ አጉራ ዘለል መንግሥታት እና ኃይሎች እየተከበቡ መሆኑን ማወቅ ብቻ በቂ ነው።ለእዚህ የጥፋት ተልዕኮ ደግሞ ምንም አይነት አገራዊ ራእይ እና እይታ የሌለው ህወሓትን አንዳንድ አጉራ ዘለል የመካከለኛ ምስራቅ አገሮች እንደ መረማመጃ እና እንደማዳከምያ ኃይል እየተጠቀሙበት ነው።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment