ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረብያ ስደት ላይ
ጉዳያችን/ Gudayachn
''ኢትዮጵያዊቷ ሴት ለየት ያሉ ባህርያት አላት። በቅዱሱ መፅሐፍ ላይ ሙሴ ህዝበ አስራኤልን ይዞ ከግብፅ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲገባ በስራው ሁሉ የምትረዳው እና ለትዳሩ አጋር ያደረገው ኢትዮጵያዊቷን መሆኑን በቅዱስ መፅሐፍ ውስጥ ማንበቤን አስታውሳለሁ።'በምድር ከሚነሱት ነገስታት ማንም ያንተን ያህል ጥበብም ሆነ ሀብት አይኖረውም' የተባለው ንጉስ ሰለሞን ልቡን ከፍቶ የሆዱን ያወራው ከኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ (አዜብ) ጋር ነው።ኢትዮጵያውያን ሴቶችልዩ ናቸው።ክብራቸው፣ዝምታቸው፣እርጋታቸው እና አስተዋይነታቸው ሁሉ የተለየ ድባብ ያላብሳቸዋል ።አዲስ አበባ ለስብሰባም ሆነ ለተመሳሳይ ሥራ ስሄድ ከምገባበት ኬክ ቤት ጀምሮ አስከ አየር መንገዳችሁ አስተናጋጆች ድረስ ያሉት ሴቶችሁ ልዩ፣አስተዋይ እና ብሩህ አእምሮ አላቸው።'' ይህንን ያሉት ከአመታት በፊት ካምፓላ ውስጥ በሚገኘው ማካራሬ ዩንቨርስቲ ውስጥ የልማት ጥናት ፕሮፌሰር ዩጋንዳዊው ማተምቤ ለክፍል ተማሪዎቻቸው ነበር።
አዎን! ከተናገሩት ውስጥ አንድም የሚጣል እንደሌለው አውቃለሁ። ያንን ንግግር ዛሬ ላይ ሆኘ ሳየው በተለይ'' ማርች 8 የሴቶች ቀን ታስቦ ዋለ'' የሚለው ከኮሚንስቶች ፕሮፓጋንዳ ያላለፈ፣ የወረቀት እና ንግግር ማሳመርያ ዜና መሰል ነገር ከወደ ሀገር ቤት ስሰማ ያስገርመኛል።ይህ ማለት ግን ''ማርች'' ስምንት የሴቶች ቀን መከበር የለበትም የሚል ሃሳብ የለለኝ መሆኑን እንዳትዘነጉብኝ።አከባበሩ አንዳች የረባ የሴት እህቶቻችንን ሕይወት የሚያሻሻል ሥራ ተሰርቶ ቢሆን ጥሩ ነበር።ሁኔታው ተቃራኒ ሆኖ ሳለ ስለ በዓሉ ማውራት በራሱ በሴት እህቶቻችን ላይ ከመቀለድ አይተናነስም።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ( UNHCR) ሰኔ 27/2011 አንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ''በ2011 የሰዎች ዝውውር በኢትዮጵያ'' በሚል ርእስ ባወጣው ሪፖርት ላይ አንዲህ የሚል ሰፍሮ ይገኛል።
''Young women, most with only three to four years of primary education, from various parts of Ethiopia are subjected to domestic servitude throughout the Middle East, as well as in Sudan, and many transit through Djibouti, Egypt, Libya, Somalia, Sudan, or Yemen as they emigrate seeking work. Some women become stranded and exploited in these transit countries, unable to reach their intended destinations. Many Ethiopian women working in domestic service in the Middle East face severe abuses indicative of forced labor, including physical and sexual assault, denial of salary, sleep deprivation, and confinement. Many are driven to despair and mental illness, with some committing suicide.....''
''ከሦስተኛና አራተኛ ክፍል ያልዘለሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መጥተው ጅቡትን፣ግብፅን ፣ሊብያን፣ሶማልያን፣ሱዳንን ወይንም የመንን አቋርጠው ወደ መካከለኛው ምስራቅ አረብ ሃገራት ለመሄድ ይሞክራሉ።ብዙዎች ገና እነኝህን ሃገራት ሳይሻገሩ እዝያው ጉልበታቸውን ሸጠው እንድያድሩ ያረጋቸዋል....በመካከለኛው ምስራቅ በሥራ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን በከባድ የጉልበት ሥራ፣የአካልና የፆታ ጥቃት፣የለፉበትን የመነጠቅ ወዘተ ይፈፀምባቸዋል።በእዚህም ምክንያት ብዙዎች የአአምሮ ህመም ደርሶባቸው እራሳቸው ያጠፋሉ....''
''እማዬ ለምን ወለድሽኝ ?''
ዛሬ በሺህ የሚቆጠሩ እህቶቻችን በሊባኖስ፣ሳዑድአረብያ፣የተባበረው አረብ አምረት፣ኩዌት፣ወዘተ በቤት ውስጥ ሥራ እና በተለያዩ አስከፊ ተግባራት ተሰማርተው ይገኛሉ።አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሄዱ በሺህ የሚቆጠሩ እህቶቻችን ለአረብ ሀገር እንግልት ሲሳፈሩ ያገኛሉ። ይህ ብቻ አደለም በቅርቡ በአዲስ አበባው ራድዮ እንደተገለፀው ወደ አረብ ሀገር የሚያሰድዱት ደላሎች ከከተሞች ይበልጥ ሰፊ የመገናኛ መረባቸው በገጠር ውስጥ መሆኑ እና ለምሳሌ በወሎ ውስጥ በምትገኝ የአንድ ገበሬ ማህበር መንደር ውስጥ ለማህበራዊ ጉዳይ ከተሰበሰቡት ገበሬዎች ለናሙና በተወሰደ መረጃ ከሃምሳ ገበሬዎች ውስጥ ሰላሳ ሁለቱ ልጆቻቸውን ለአረብ ሀገር እንግልት መላካቸውን ገልፀዋል። ከእዚህ ሁሉ አሳዛኙ ነገር ደግሞ ሁሉም የሴት ልጆቻቸውን ወሬ ሰምተው የማያውቁ መሆናቸውንና ግራ መጋባታቸውን በለቅሶ መግለፃቸው ነው ። የእህቶቻችን ጉዞ በአየርመንገድ ብቻ የምመስለን ካለን በጣም ተሳስተናል። በ እዚሁ የራድዮ ዘገባ መሰረት ባለፉት አምስት ወራት ብቻ በሱዳን በኩል የወጡት እህቶቻችን ብዛት በብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠር መሆኑም ተነግሯል።
በአረብ ሀገር ያሉት እህቶቻችንን መከራ ና ስቃይ መተንተን በቃላት መቀለድ ሆነብኝ።ከፎቅ ላይ እራሳቸውን የወረወሩትን፣መርዝ የጠጡትን፣የፈላ ውሃ የተደፋባቸውን፣ምግብ ሳይበሉ በረሃብ ጠኔ ሕይወታቸው ያለፈውን፣እስር ቤት ተወርውረው ተረስተው የሞቱትን፣ ኩላሊታቸው የቀዶ ጥገና ሕክምና አዋቂ ባልሆኑ ሰዎች ወጥቶ የተወሰደባቸውን (ከዓመት በፊት 'ሲ ኤን ኤን' የተሰኘውን የ አሜሪካ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያውያን እህቶቻችን የኩላሊት መወሰድ ላይ ያሳየውን ዘገባ ልብ በሉ) እህቶቻችን ዛሬም ''እማዬ ለምን ወለድሺኝ?'' እያሉ ነው።መከራን የምንረዳው እኛ በዝያ መከራ ውስጥ ተገብተን አልያም በእህታችን ወይንም በሴት ልጃችን ላይ ደርሶ ቢሆንስ? ብለን ስናስብ ብቻ ሊሆን ይችላል።
ኢትዮጵያዊት ሴት በአረብ ሃገራት ውስጥ የተዋረደችውን ያህል በታሪካችን ኢትዮጵያ የተዋረደችበት (ውርደቱ የአኔም፣የናንተም፣የሁላችንም መሆኑን ሳንዘነጋ) ጊዜ ነበር ለማለት አያስደፍርም ።በአረባውያኑ ምድር ኢትዮጵያውቷን ሴት አይዞሽ ባይ ማጣት፣ግራ መጋባት፣ተስፋ መቁረጥ፣ግፍ እና መከራው አንገላተዋት ባዶ አውላላ ሜዳ ላይ የቀረች ብቸኛ ፍጥረት የሆነች ያህል እየተሰማት ያለችበት ጊዜ ነው። ሀገሮች በድንበር መካለል ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በመካከላቸው የሚኖረውን ግንኙነት ከንግዱ ዘርፍ ባለፈ የ ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወር ሌላው የሚያገናኛቸው ጉዳይ ነው። ይህ ግንኙነት ደግሞ ዲፕሎማስያዊ ግኑኝነት እንድያዳብሩ ትልቅ በር ከፍቷል ።
ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት በ ዘመናት ውስጥ የራሱን አድገት አያሳየ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሰናል።የ ዲፕሎማሲ ግንኙነት አጅግ ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ሲሰራበት የነበረውን ዘመን አልፎ ዛሬ ''public diplomacy'' ''ግልፅና ሕዝቡን መሰረት ያደረገ'' የዲፕሎማሲ ዘመን ላይ እንገናኛለን። የሀገሮችን የዲፕሎማሲ ግንኙነት መልክ ለማስያዝና ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በሁዋላ በሀገሮች መካከል የነበረውን ግንኙነት መልክ ያስያዘው ብሎም የዓለም አቀፍ ሕግን ቅርፅ የሰጠው አሁንም ድረስ በሥራ ላይ የሚገኘው የዲፕሎማሲ ሕግ የ'' ቬና ኮንቬንሺን''(የቬና ውል) ይባላል። ይህ ውል በሚያዝያ 18/1961 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ወጥቶ በሚያዝያ 24/1964 አሁንም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ሥራ ላይ ዋለ።በአውሮፓውቷ ሀገር ኦስትርያ ዋና ከትማ ቬና ውሉ ሲፈረም ከፈረሙት ሀገሮች አንዷ በወቅቱ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች በቅኝ ግዛት ስር በሆኑበት ዘመን ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን የ ውሉ ቀዳሚ ፈራሚ ብቻ ሳትሆን በማርቀቅ ሂደቱም ሁሉ ተሳታፊ ነበረች።ዛሬ ግን የእዚህን ውል ዋና አካል የሆነውን አንቀፅ ሶስት የ አትዮጵያ መንግስት ከነመኖሩም የዘነጋው ይመስላል።
የ ቬና ውል አንቀፅ ሶስት ''b'' አንዲህ ይላል : -
Article 3 1.The functions of a diplomatic mission consist, inter alia, in: (a) Representing the sending State in the receiving State; (b) Protecting in the receiving State the interests of the sending State and of its nationals, within the limits permitted by international law; 2
''የአንድ ሀገር የዲፕሎማሲ ሉዑክ አንዱ ተግባር በተቀበለው ሀገር ውስጥ የሃገሩን ጥቅሞችና የዜጎቹን ጥቅሞች የአለማቀፍ ሕግ ማቀፍን በተከተለ መንገድ ማስከበር ነው” ይላል።
የሀገራችን የወቅቱ የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስት አባልነትን መሰረት ያደረገ እና ቅድምያ ለመንግስት ታማኘትን ማእከል ያደረገው የሀገራችን ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ስርዓት በመካከለኛው ምስራቅ ለሚሰቃዩት እህቶቻች በቁስል ላይ ቁስል ሆኖባቸዋል።
ዛሬ ለእህቶቻችን በሄዱበት ሀገር መብታቸውን ለማስከበር ኃላፊነት ያለበት መንግስት መሆኑን የሚዘነጋው አይኖርም ።ይህ ደግሞ በአለማቀፍ ሕግ እንደ መንግስት ተቁአምነት ግዴታው ነው።የአንድ መንግስት ቀዳሚ ተግባር የሃገሩን ሉዓላዊነት ከማስከበር ጀምሮ የ ዜጎቹን ደህንነት (ዜጎቹ በየትኛውም የ ምድር ማአዘን ቢኖሩ) ማስጠበቅ ነው። አሁንም ይህ ኃላፊነት በቀጥታ የሚመለከተው መንግስትን ነው።መንግስት በአረብ ሀገር እንባዋን የምታፈሰውን ኢትዮጵያዊት ሴት ለመርዳት የወሰደው አርምጃ ትንሿ ጅቡቲ በዲፕሎማሲ ተልኮዋ ከምትሰራው ሥራ ያነሰ ነው ሲሉ ብዙዎች ይተቻሉ።ይህም ተራ በስሜታዊነት የተሞላ ነቀፋ ሳይሆን በገሃድ የታየ እውነታ ነው።
በሶርያ፣ሊባኖስ፣ሳዑድ አረብያ፣ሱዳን የነበረውን ሁኔታ የሚያውቁና በሃገራቱ ውስጥ ያሉትንም ሆነ በአካባቢው ሃገራት ያሉትን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ በሮች ሲማፀኑ የነበሩት እህቶቻችን ቢናገሩት ይቀላል። የኢትዮጵያውቷ ሴት እሮሮም ይሄው ነው። እንዴት ሀገር እንደለለኝ፣ወገን እንደለለኝ፣የተከራከርልኝ አጣሁ? ለምን በ አረብ ምድር ተገፋሁ? ዛሬም የሚሰማ ድምፅ ነው።
''ማርች ስምንት'' የሴቶች ቀን በዓል በአረብ ሀገር የመከራ ቀን ለምትገፋው ለኢትዮጵያውቷ ሴት የመራር ፌዝ ያህል ሆኖ ቢሰማት አይፈረደም።የዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት የ''ቬናን'' ስምምነት የፈረመችው ሀገር ዜጎች ዛሬም መረር ያለ ዲፕሎማስያዊ እርምጃ ወስዶ'' ዘጎቼ ተሰቃዩ'' ብሎ የሚናገርላቸው መንግስት አጥተው ያለቅሳሉ።