Dr. KETHOSER (ANIU) KEVICHUSA is a speaker and trainer with Ravi Zacharias International Institute in India.
ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Thursday, July 9, 2020
Wednesday, July 8, 2020
ጆሮ ጠገብ ያልሆኑ ኢትዮጵያን የተመለከቱ ዜናዎች
ሐምሌ 2/2012 ዓም (ጁላይ 9/2020)
================
ኢትዮጵያ የዓባይን ግድብ ውሃ መሙላት በሚስጥር ጀምራለች ተባለ።
ኢትዮጵያ በሚስጥር የአባይ ግድብን መሙላት ጀምራለች ሲል ''ግብፅ እንዲፐንዳንትን'' ጠቅሶ ''ኢነርጂ ሚክስ ዶት ኮም'' ገልጧል።እንደ ድረ ገፁ ዘገባ የሱዳን እና የግብፅ ምንጮች እንደገለጡት ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት መጀመሯ ተሰምቷል ብሏል።በሌላ በኩል የግብፅ የውሃ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውሃውን እየሞላች እንደሆነ ተከታታይ መረጃዎች እንደደረሱት ነው ድረ ገፁ የዘገበው።ሆኖም የመስርያቤቱ ቃል አቀባይ መሐመድ አልሰባይ የግብፅ እንዲፐንዳንት ዘገባ አልተረጋገጠም ብለዋል።ይህ በእንዲህ እያለ የካይሮ ዩንቨርስቲ አንድ መምህር ግድቡ እየተሞላ እንደሆነ የሚያሳይ የሳተላይት ፎቶዎች ማሳየታቸውን ዘገባው ያትታል።''ኢነርጂ ሚክስ ዶት ኮም'' በናይጄርያ የነዳጅ እና ሌሎች የኃይል ምንጮች ላይ የሚዘግብ ድረ ገፅ ነው።
ሩስያ ለዓባይ ግድብ ድርድር ቴክኒካል እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኗን ገልጠች
የሩስያ ዜና አገልግሎት ''ታስ'' ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 1/2012 ዓም እንደዘገበው ሩስያ ለዓባይ ግድብ ድርድር ቴክኒካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጠዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌ ላቭሮቭ ይህንን ያሉት ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣የግብፅ እና የደቡብ አፍሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በቪድዮ ከተነጋገሩ በኃላ መሆኑን ታስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሜሪካም ለተደራዳሪዎቹ አገልግሎት መስጠቷን አገራቸው በበጎ እንደምታየው ገልጠው፣ሩስያም አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት እንደምትችል ተደራዳሪዎች ሊያውቁት ይገባል ካሉ በኃላ ሩስያ የግድቡ ጉዳይ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት በቀረበ ጊዜ የሁሉንም ወገኖች የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ስምምነት መደረስ እንደሚገባ መግለጧን አስታውሰዋል።
ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ለሳውዲው የዜና ቻናል ''አል-አረብያ'' ጋር ቃለ መጠይቅ አደረጉ።
''በግድቡ ምክንያት ግብፅ እና ሱዳን ፈፅሞ ውሃ አይጠሙም'' አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
አቶ ገድ በእዚህ መግለጫቸው ሱዳን እና ግብፅ ፈፅሞ በግድቡ ሳብያ ጭንቀት ውስጥ ሊገቡ አይገባም ካሉ በኃላ የግብፅ የተጋነነ እና ትክክል ያልሆነ ጥያቄ መታረም እንዳለበት እና ለችግሩ መፍትሄው መነጋገር ብቻ መሆኑን ገልጠዋል።ይላል የአል-አረብያ'' የእንግሊዝኛ ድረ ገፅ።ድረ ገፁ ሌላውን የቃለ መጠይቅ ይዘት ምንም ሳያቀርብ ወደ ግድቡ ታሪክ ገብቷል።ይሄው ድረ-ገፅ የአቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ያወጣበት ሁኔታ ደረጃውን ያልጠበቀ እና በራሱ ከሚድያ ስነምግባር የራቀ ነው።ቻናሉ የቃለ መጠይቁን ይዘት በገፁ ላይ ይዞ ላይወጣ ቃለ መጠይቅ ያደረገው መረጃ ለማግኘት ነው ወይ? ያስብላል።ድረ ገፁ የአቶ ገዱ ፎቶ በሸራተን ሆቴል ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መግለጫ ሲሰጡ (ከፋይሌ) ብሎ የለጠፈው ፎቶ ከስር ተመልከቱት።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮቪድ -19 በኃላ ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱትን አስታወቀ።አየር መንገዱ ወደ ዱባይ በረራውን ረቡዕ ሐምሌ 1/2012 የጀመረ ሲሆን ወደ ጅቡቲም በመጪው ሳምንት በረራው እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል።አየር መንገዱ አገሮች የአየር ማረፍያቸውን መክፈት መቀጠላቸውን ተከትሎ አገልግሎቱን እንደሚቀጥል ገልጦ፣በረራው በሚደረግባቸው አገሮች ያለውን የጤና መስፈርት እና ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቁ መስፈርቶችን ተከትሎ አገልግሎቱን እንደሚሰጥ እና ደንበኞች ይህንኑ የተመለከተ መረጃ ከአየር መንገዱ ድረ ገፅ ላይ መመልከት እንደሚችሉ አሳስቧል።
=============
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
Gudayachn Multimedia, Kommunikasjon og Konsultent
Monday, July 6, 2020
በምዕራባውያንም ሆነ በግብፅ ትንተና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሸንፈው ወጥተዋል፣በመሆኑም ግብፅ ከሰሞኑ ትለሳለሳለች።የአቶ ኢሳያስ አፈወርቅ የግብፅ ጉብኝት ምንነት?
አቶ ኢሳያስ እና አልሲሲ በካይሮ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ
በእዚህ ፅሁፍ ስር -
>> በምዕራባውያንም ሆነ በግብፅ ትንተና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሸንፈው ወጥተዋል።
>> አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ባሳለፍነው ሳምንት በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ምንነት።
>> ነፍሰ ጡር በምጧ ጊዜ እንድትጨነቅ ሁሉ ኢትዮጵያም የጎሳ ፖለቲካን አሽቀንጥራ ለመጣል የመጨረሻ የመገላገያ ጊዜዋ
ላይ ነች የሚሉ ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።
ከልክ ያለፈው ትዕግስት
ከ1983 ዓም በፊትም ሆነ በኃላ ብዙዎቹ የጮሁለት፣የተሰደዱለት እና የሞቱለት ኢትዮጵያን ከከፋፋይ እና የእልቂት የጎሳ ፖለቲካ የማላቀቅ የመጨረሻው ምዕራፍ ትግል ተጀምሯል።ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ ሁሉን አቃፊ ሆኖ ሰንብቷል።የኦነግ ዓርማ በአዲስ አበባ ሲውለበለብ እና የጎሳ ፖለቲካ ሲሰበክ እንዲሁም ሚድያዎች በአዲስ አበባ ቢሮ ከፍተው በግልጥ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ሲሳደቡ በትግስት ታልፏል።በቦሌ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው አዲስ አበባ እና ሐዋሳ ላይ መከፋፈልን በአደባባይ የሰበኩ፣በሕዝቡ ላይ የዛቱ ለወራት ዝም ተብለው ሰንብተዋል።
ይህ ሁሉ የፈለጉትን የመሆን መብት ግን በራሱ ገደብ አለፈ።ጀዋር መሐመድ ከበቀለ ገርባ ጋር እንዲሁም ልደቱ አያሌው ኃላፊነት በጎደለው መንገድ በዓደባባይ መንግስት ከመስከረም 30 በኃላ አይኖርም ማለት ጀመሩ።ይህ አባባል ቀደም ተብሎ ''ሁለት መንግስት ነው እዚህ ሀገር ያለው'' በማለት ጀዋር ደጋግሞ ከተናገረ በኃላ መሆኑ ነው።ቀደም ብሎ ብዙ ነገሮችን ሲያስታምም እና ሕግ ባለማስከበሩ በከፍተኛ ደረጃ የተወቀሰው መንግስት ከመስከረም 30 በኃላ አናውቀውም የሚል ንግግር ሲነገር፣ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መንግስት ትዕግስቱ እያለቀ መሆኑን በመግለጥ ማስጠንቀቅያ ሰጡ።ሆኖም ከቃላት ዝልፍያ የተጀመረው መንግስትን አናውቅም ስድብ ወደ መሬት የወረደ የሴራ ፖለቲካ ተሸጋግሮ አንድ አመፅ ለማቀጣጠል የሚረዳ አንዳች ምክንያት (Immediate Cause) መፈለግ ተያዘ።ለእዚህም ጉዳይ የድምፃዊ ሃጫሉ ሞት ተመረጠ።ስለሆነም የዛሬ ሳምንት ሰኞ ሰኔ 22/2012 ዓም አዲስ አበባ ላይ ተገደለ።በደቂቃዎች ውስጥ ኦኤምኤን እና የህወሓት ሚድያዎች የጎሳ ግጭት የሚያስነሱ የቅስቀሳ ዘገባዎች ጀመሩ።
በምዕራባውያንም ሆነ በግብፅ ትንተና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሸንፈው ወጥተዋል
የለውጡ ሂደትን በአንክሮ የሚከታተሉ የምዕራባውያንም ሆኑ የኢትዮጵያ ባላንጣ ግብፅ በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ልደናቀፍ የሚችልባቸው ሶስት ምክንያቶች ይኖራሉ ብለው ያስቡ ነበር።እነርሱም -
የመጀመርያው ምክንያት፣ የጦር ኃይሉ በዋናነት በህወሓት አፍቃሪ መኮንኖች የተሞላ ስለሆነ በቀላሉ የጦር ኃይሉን ሊቆጣጠሩ አይችሉም የሚል ግምት ነበር።ሆኖም ግን ይህ ግምት ስህተት መሆኑ ለመጀመርያ ጊዜ ምልክት በማሳየት የታወቀው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ጋር በቤተ መንግስት የጦሩን ኤታማጆር ጀነራል ሳሞራን በክብር ጠርተው እና ሸልመው ሲያሰናብቱ እና በደህንነት መስርያ ቤቱ ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ እየመጣ መሆኑ ሲነገር ነበር።
በሁለተኛ ደረጃ የምዕራባውያንም ሆነ የግብፅ የለውጡ ሂደት ድልድዩን አይሻገርም የሚለው ግምት እና ጥርጣሬ የራሱ የኢሕአዴግ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? የሚል ሲሆን በአጭር ጊዜ ግንባሩ ሊከስም ስለማይችል ኢትዮጵያ ትከፋፈላለች የሚል ዕሳቤ ነበር።በእርግጥም በወቅቱ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት ለሚከታተል ሰው ትልቅ ፈተና እና መውጭያ መንገዱም ድቅድቅ ጨለማ ይመስል ነበር።ለእዚህ መንገድ ግን ቀድመው አቅደው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በለውጡ ሰሞን በሐዋሳ በተደረገው የኢሕአዴግ ጉባኤ ላይ እንደዋዛ ወደ ጉባኤው ማብቅያ ላይ አንዲት ነገር ጣል አደረጉ።ይሄውም ጉባኤው ኢህአዴግ ወደ አንድ የፖለቲካ ኃይል የሚቀየርበትን ሂደት (ከእዚህ በፊትም ተነስቶ ስለነበር) አጥንቶ ለማቅረብ ስልጣን እንዲሰጠው የሚጠይቅ ነበር።እንደዋዛ ቀለል አድርገው ያነሱትን ነገር ጉባኤው በጭብጨባ ተቀበለ። በእዚህ መሰረት ኢህአዴግ ከስሞ ብልፅግና ተመስርቶ ቀድሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሂደት ላይ ፖሊሲ የማውጣት ዕድል ያልነበራቸው ክልሎች እንደ አፋር፣ቤንሻንጉል፣ሱማሌ እና ጋምቤላ በብልፅግና ፓርቲ በአንድ ግንባር ተሰባሰቡ።ይህ ለኢትዮጵያ አንድነት ከሰላሳ ዓመታት በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ አንዱ እና ዓይነተኛ መሰረት የጣለ ሂደት ሆኗል።በእዚህም የምዕራባውያንም ሆነ የግብፅ ግምት ትክክል አለመሆኑን አመኑ።
ሶስተኛው እና የመጨረሻው ጉዳይ በኦሮሞ የፅንፍ ኃይሎች በተለይ በጀዋር እና መሰሎቹ ዙርያ ያለው የኃይል ሚዛን መንግስትን የሚገዳደር ባይሆን አመፅ የመፍጠር እና ወደ አደገኛ መስመር ኢትዮጵያን የመምራት አደጋ አለው።በእዚህ ሳብያ የለውጡ ሂደት ይደናቀፋል የሚል ግምት ነበር።ይህንን ሃሳብ ብዙዎች በስጋት የሚመለከቱት እና ኢትዮጵያን ወደ አላስፈላጊ ኪሳራ እንዳይከት በማለት መንግስት በቶሎ ነገሮችን ማስተካከል እንዳለበት ሲወተውቱ ነበር።ይህ ጉዳይ ግን የድምፃዊ ሃጫሉን የግፍ ግድያ ተከትሎ በተነሳ ግጭት መንግስት ሕግ ለማስከበር በአዲስ መንፈስ እንዲነሳ እና ለሕዝቡም ቃል እንዲገባ ምክንያት ሆነ።በእዚህም መሰረት ጀዋር እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካቶች በአመፅ ሂደት እና ሴራ ውስጥ ገብተው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን በቁጥጥር ስር አዋላቸው።እስሩን ተከትሎ በበርካታ የኦሮምያ ክልሎች የኦሮሞ የፅንፍ ፖለቲካ አራማጆች በንፁሃን ላይ የግፍ ጥፋት ቢያደርሱም መንግስት እንደመንግስት ግን ሁኔታዎችን በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየወሰደ ያለው እርምጃ በራሱ በጣም አበረታች ነው።በእዚህም የምዕራባውያን እና የግብፅ የኢትዮጵያ ለውጥ ሊደናቀፍ ይችላል ያሉት ጉዳይ በመንግስት የበላይነት ቁጥጥር ስር መዋሉ የለውጡ ሂደት በሚገባ እየሄደ ለመሆኑ የማረጋገጫ ማሕተም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ቀደም ብሎ በሱዳን ባሳለፍነው ሳምንት በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ምንነት።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ከሳምንት በፊት ሱዳንን፣ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ደግሞ ግብፅን ጎብኝተዋል።የአቶ ኢሳያስ ጉብኝት በኤርትራ ዜና ማሰራጫዎች እንደተገለጠው በሁለቱ ማለትም ኤርትራ ከሱዳን እና ከግብፅ ጋር ያላት ግንኙነት ዙርያ ተወያዩ ከማለት በቀር ዝርዝር ጉዳይ ያወሩት የለም።በኤርትራ የሚድያ ነፃነት ካለመኖሩ አንፃር ከእዚህ የበለጠ ሊያወሩ አይችሉም።ሚድያዎቹ አይደሉም በአቶ ኢሳያስ የስልጣን ወንበር ላይ ያሉም ዝርዝሩን የማወቅ እድሉ አይኖራቸውም።አቶ ኢሳያስ በሚያደርጉት ጉብኝት ረዳታቸውን አቶ የማነን አስከትለው እንጂ ሌሎች ሚኒስትሮችን አስከትለው አይሄዱም።ሌሎቹን ጉዳዮች አቶ ኢሳያስ ከጉብኝት ወደ አስመራ ሲመጡ መጥነው እስክነግሯቸው መጠበቅ አለባቸው።
የአቶ ኢሳያስ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ግብፅ ያደረጉት ጉብኝት በኤርትራ በኩል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳለህ፣ አቶ የማነ ገብረአብ እና አምባሳደር ፋሲል ገብረስላሴ የተገኙ ሲሆን በግብፅ በኩል ደግሞ የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሽኩሪ፣ የደህንነት ሚኒስትሩ አባስ ከማል እና የእርሻ ሚኒስትሩ መሐመድ ማርዙቅ ተገኝተዋል።የአቶ ኢሳያስ በሱዳንም ሆነ በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት ዓላማዎች ሁለት ናቸው።
የመጀመርያው ዓላማ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ወገን ወግና በግብፅ እና በሱዳን ላይ እያሴረች አለመሆኗን እና እንደ ገለልተኛ ሀገር እንድትታይ ለማድረግ ነው። አቶ ኢሳያስ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረጉት መቀራረብ በግብፅ እና በሱዳን ዘንድ የተገለሉ እንዳይሆኑ ይፈልጋሉ።ስለሆነም አንድ ዓይነት የዲፕሎማሲ ሥራ ማድረግ ነበረባቸው።
ሁለተኛው ዓላማ፣ የግድቡ ጉዳይ የአካባቢው ሀገሮችን የትብብር ዕቅድ እንዳያሰናክል ጉዳዩን ማለሳለስ ነው።እዚህ ላይ አቶ ኢሳያስ አሳማኝ ነጥቦችን ይዘው ካልሄዱ በግድቡ ጉዳይ ያለውን ውጥረት ማለሳለስ አይችሉም።ስለሆነም ሁለት ነጥቦችን ይዘው ነው ወደ ሱዳን እና ግብፅ የሄዱት።አንዱ ለአካባቢው ዋና ስጋት የህወሓት የታጠቀ ኃይል መኖሩ መሆኑን ማስረዳት ሲሆን ሁለተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን በሚገባ አልተረዳችሁትም፣እርሱ ፈፅሞ ግብፅን እና ሱዳንን የሚጎዳ ሥራ አይሰራም።ይልቁንም እርሱ እስካለ ድረስ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ማተኮሩ የተሻለ ነው የሚሉ ሃሳቦች ናቸው።እነኝህ ሃሳቦች ከኤርትራ መምጣታቸው ግብፅን በተወሰነ ደረጃ አያሳምንም ማለት አይቻልም።ባያሳምናትም አሁን ባለችበት ደረጃ ምንም ልታደርግ አትችልም። ሆኖም አቶ ኢሳያስን ''አንተ ካልክ'' በሚል ከኤርትራ ጋር ወዳጅነቷን ለማቆየት ትጠቀምበታለች።አቶ ኢሳያስ ግብፅን ከአልሲስ በላይ ያውቃሉ።የሻብያ እንቅስቃሴ ዋና መነሻ ካፒታል የተፈጠረባት ሃገርን ሊረሱ አይችሉም።በመሆኑም የግብፁን ፕሬዝዳንት በአካባቢው ለረጅም ጊዜ እንደቆየ ሽማግሌ መሪ ፕሬዝዳንት አልሲስን ቆጣ እያሉ እንዴት ነው ዓብይን የማትረዳው? ቢሉ ላያንስባቸው ይችላል።
ይህ በእንዲህ እያለ ግብፅ የኢትዮጵያን የመልማት እና የመብራት የማግኘት መብት በማይቃረን መልኩ አዲስ የስምምነት ፕሮፖዛል አለኝ ማለት መሰማቱ ቀድሞም በውስጥ ኢትዮጵያን ለማበጣበጥ ከመሞከር በላይ ምንም ልታደርግ ያልቻለችው ግብፅ የአቶ ኢሳያስ ጉብኝትን እንደ አንድ ምክንያት ልትጠቀምበት ትችላለች።ግብፅ ከሰሞኑ በዓባይ ጉዳይ ባልተጠበቀ ሁኔታ ልትለሳለስ ትችላለች።የምትለሳለሰው ግን በአቶ ኢሳያስ ጉብኝት አይደለም።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ እና የለውጥ ኃይሉ ለለውጥ ሂደቱ ስጋት የነበረውን የመጨረሻውን የኃይል ሚዛን በአሸናፊነት ስለተወጣው ነው።
ነፍሰ ጡር በምጧ ጊዜ እንድትጨነቅ ሁሉ ኢትዮጵያም የጎሳ ፖለቲካን አሽቀንጥራ ለመጣል የመጨረሻ የመገላገያ ጊዜ ላይ ደርሳለች
ባጠቃላይ አሁን በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ወደ የከፋ መስመር የሄደ ቢመስላቸውም ዕውነታው ግን ተቃራኒ ነው። በእርግጥ ነው ብዙዎች በፅንፈኛ የኦሮሞ አክራሪዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣የንግድ ቤታቸው እና መኖርያቸው ወድሟል።ሆኖም ግን ነፍሰ ጡር በምጧ ጊዜ እንድትጨነቅ ሁሉ ኢትዮጵያም የጎሳ ፖለቲካን አሽቀንጥራ ለመጣል የመጨረሻ የመገላገያ ጊዜዋ ላይ ነች። ስለሆነም ህመም አለው።ህመሙ ግን የአጭር ጊዜ ህመም ነው።ተመልሳ ወደ የጎሳ ፖለቲካ የማትገባበትን የጋራ ቃል ኪዳን የምታፀናበት ብሩህ ጊዜም እየመጣ ነው።መታመማችን ለበጎ ነው።ጎሰኘነትን መልሶ የሚጭን የፖለቲካ ስርዓት ፈፅሞ የማይሸከም ሀገር እና ሕዝብ ከእዚህ ሁሉ ፈተና መሃል ጠንክሮ ይወጣል።
ጉዳያችን
Saturday, July 4, 2020
አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች በሰላማዊው ሕዝብ ባደረሱት ጥቃት የ166 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን መንግስት ገለጠ።ከአስመራ ሲገባ በአቦይ ስብሐት የምሳ ግብዣ የተደረገለት ኦነግ ሸኔ በዓማራ ክልል ላይ የሞከረው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።
በእዚህ ፅሁፍ ስር-
- በሐረር የተፈፀመ አንድ የግፍ ጥቃት የከተማው አምቡላንስ ባለመምጣቱ ከፈረንሳይ በተደወለ ስልክ ህይወቱ የተረፈበትን ታሪክ እና
- ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ በኦሮምያ የንፁሃንን ደም የሚያፈሱትን የመከረችበት ቪድዮ ያገኛሉ።
ባሳለፍነው ሳምንት መጀመርያ ላይ በተወዳጁ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ በግፍ ከተፈፀመው ግድያ ተከትሎ በኦፌኮ አባላት በጀዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ እንዲሁም በኦኤምኤን ቅስቀሳ በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮምያ ክልል እና በአዲስ አበባ የፀጥታ ችግር መፈጠሩ እና በመቀጠልም ጀዋር እና በቀለ ገርባን፣1084 ሰዎች መታሰራቸው እና እስካሁን የ166 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን ኮማንደር ግርማ ገላን የኦሮምያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሰጡት ቃል ገልጠዋል።እንደ ኮማንደሩ ገልጣ 10ሩ ሰላማዊ ሰዎች በአዲስ አበባ የሞቱ ሲሆን፣145ቱ ደግሞ በተለያዩ የኦሮምያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ የፅንፈኞች ጥቃት ሳብያ ህይወታቸውን ያጡ መሆናቸው እና 11 ከፀጥታ ኃይሉ ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጧል።
በሰሞኑ ክስተት በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት በርካታ መረጃዎች ስላልወጡ እንጂ በሐረር፣ዝዋይ፣ሻሸመኔ፣ሞጆ፣ምዕራብ ሸዋ እና አርሲ ውስጥ ምንም ዓይነት ፖለቲካ የማያውቁ ከሁለት ትውልድ በላይ የኖሩበት ከተማ በግፍ የተገደሉት ቁጥር ብዙ እንደሆነ ነው የሚነገረው ። ለምሳሌ የእዚሁ ዜና አዘጋጅ በሐረር የተፈፀመው ግፍ እንደምሳሌ ያቀርባል።በእዚህ በያዝነው ሳምንት ውስጥ በሐረር አራተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ኮንደሚንየም በግል ስራው የሚተዳደረው የቤተሰብ ኃላፊ ላይ የደረሰው ግፍ ጉዳዩን በሚገባ ከሚያውቀው ሰው ሰምቷል።ግለሰቡ በእዚሁ በሐረር ከተማ አራተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያለው ኮንደሚንየም ነዋሪ ነው ።ግለሰቡ ከአዲስ አበባ ሊጠይቁት የመጡትን ዘመዶቹ ጋር ቤቱ ተቀምጦ እያወራ ነበር። ባለፈው ሮብ በድንገት ሁለተኛ ፎቅ የሚገኘው ቤቱ መስኮቱን ሰብረው እቤት ውስጥ ያሉትን ሰዎች ከባለቤቱ ጨምሮ በግፍ ይቀጠቅጧቸዋል።በመሃል ስልክ ወደ አምቡላንስ እና ወደ ፖሊስ ቢደውሉ፣ የሚደርስ የለም።በመሃል ፈረንሳይ ሀገር የምትኖር እህቱ ደውላ አደጋ ላይ መሆናቸውን ሰምታ አዲስ አበባ እና ሌላ ቦታ የሚኖሩ ለምታውቃቸው ደውላ በብዙ ስልክ አምቡላንስ እንደደረሰለት ሰምተናል።አሁን ባለው ሁኔታ አንዳንድ የኦሮምያ ፖሊስ አባላት እና ኃላፊዎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እያዩ እንዳላዩ የሚያዩ እንዳሉ እየተነገረ በመሆኑ የእዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈፅሙትን መንግስት ተከታትሎ ለሕግ ማቅረብ አለበት።
ይህ በእንዲህ እያለ ከሁለት ዓመት በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በአቦይ ስብሐት የምሳ ግብዣ የተደረገለት የኦነግ ሸኔ ቡድን ወደ ዓማራ ክልል በባቲ ከተማ በመግባት በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ሊፈፅም የነበረው ጥቃት በመከላከያ እና በዓማራ ክልል ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የዓማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 27/2012 ዓም ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ገልጠዋል። በእዚሁ መግለጫቸው ላይ አቶ ተመስገን እንዳብራሩት የሽብር ቡድኑ የአዲስ አበባው ጥፋት ቅጣይ መሆኑን እና የቡድኑ መሪ ጨምሮ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን እና የቀረዑት ከሙሉ ትጥቃቸው ጋር መያዛቸውን ነው የገለጡት።በመጨረሻም አቶ ተመስገን መንግስት በቀጣይ የሸረሪት ድሩ ላይ ብቻ ሳይሆን በሸረሪቱ ላይ አትኩሮ እንደሚሰራ ነው የገለጡት።
በመጨረሻም ሰሞኑን በውጭ የሚኖሩ የህወሓት፣ኦነግ ሸኔ እና የጀዋር ደጋፊዎች በአንድነት የተለያዩ የማኅበራዊ ሚድያ ገፆች እየከፈቱ የተለያዩ የጥላቻ ቪድዮዎች እየለቀቁ ሲሆን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ለመንግሥታቱ የጥላቻ ንግግሮች የሚዘሩትን እየጠቆሙ እንደሆነ ነው የተነገረው።ጉዳዩን በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችም በቀጥታ ላሉበት መንግስት የጥላቻ ንግግር የሚዘሩትን ከመጥፎ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማመልከት ይገባቸዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም አዲስ አበባ ያሉትን ኤምባሲዎች በጉዳዩ ዙርያ ቢያነጋግር እና ጉዳዩን ቢከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ በዘረኝነት የጥላቻ ንግግር የሚያልቀውን ሕዝብ ለመታደግ እንደሚጠቅም ማሰብ ተገቢ ነው።
ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ በኦሮምያ የንፁሃንን ደም የሚያፈሱትን የመከረችበት ቪድዮ
Friday, July 3, 2020
በሕወሓት እና በግብፅ መንደር ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ የሚመራው የለውጥ ኃይል በእዚህ ሳምንት በከፍተኛ ደረጃ ወደፊት ተስፈንጥሯል ማለት ይቻላል።ዓርብ ሰኔ 26፣2012 ዓም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፀጥታ እና የፍትህ አካላት ያሉበትን ኮሚቴ ሰብስበው ባደረጉት ውይይት ላይ ሰሞኑን እየተደረገ ያለው ጥፋት ቀደም ብሎ በደህንነት መስርያቤት ተመስርቶ የነበረው የ''ኢኤንኤን'' ቴሌቭዥን ከሁለት ዓመት በፊት የሚያሳየውን የስፖርት ጨዋታ አቁሞ በኦሮሞ እና አማራ መሃል ጠብ እንዳለ ለማስመሰል የነዛው ፕሮፓጋንዳ ቅጥያ ነው ያሉ ሲሆን፣ አንድ ጊዜ ዓቢይ ታፈነ ሌላ ጊዜ ታከል ታፈነ እያሉ የሚያወሩ ከንቱ ምኞታቸውን ነው የሚነግሩን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልፅግና ፓርቲን እና አሁን ያለውን አመራር አስመልክተው ሲናገሩ ባለፉት ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ አሁን ያለነው የብልፅግና አመራር የእዚህን ያህል የጋራ አመለካከት ኖሮን አያውቅም ያሉ ሲሆን መስከረም 30 መንግስት የለም ሲሉ የነበሩ ለመስከረም 30 ያቀዱትን አሁን ለማፍጠን የተገደዱበት ምክንያት ባለን መረጃ መሰረት ባንዳዎቹ ከግድቡ ጋር በተያያዘ አጉራሾቻቸው ለእኛ አሁን ካልሆነ ምን ይሰራልናል ስላሏቸው የእነርሱን ፍላጎት ለማርካት ያደረጉት መሆኑን አብራርተዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ በሰሞኑ የመንግስት ጠንካራ እርምጃዎች ሳብያ በህወሓት መንደር እና በካይሮ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል።በተለይ በአዲስ አበባ በትናንትናው ዕለት ዓርብ ሰኔ 26/2012 ዓም ፖሊስ የጀዋር መሐመድን እና የበቀለ ገርባን ቤት ጨምሮ ሌሎች ስፍራዎች ባደረገው ፍተሻ ከፍተኛ ሰነዶች እንደያዘ ነው የተሰማው።በእዚህ መሰረት ከድርጊቱ ጋር አላቸው የተባሉ መረጃዎች ከህወሓት ጋር እና ከአንዳንድ የግብፅ ንግድ ድርጅቶች ጋር መያያዛቸው ያልተጠበቁ መረጃዎች መንግስት እጅ እንዲወድቁ ማድረጉ ተሰምቷል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በዓርብ ዕለት ማብራርያቸው ላይም ቀድሞ አሸባሪ ይል የነበረው ነው ዛሬ አሸባሪ ሲለው ከነበረው ጋር የገጠመው በማለት የጠቀሱት ይህንኑ የሚስጥር ዕቅድ በተመለከተ ጥቆማ የሚሰጥ ነው።ሃጫሉን በቁሙ ሲያራክሱት የነበሩት ናቸው ዛሬ ለእርሱ የሚቆረቆሩ መስለው ከእኛ በላይ ያዘኑ መስለው የቀረቡት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሁን ሀሳባቸው ሁሉ ጨንግፏል ብለዋል።
ግብፅ የዓባይን ድርድር አስመልክታ ይዛው የነበረው ስልት በሰሞኑ የመንግስት የውስጥ በጥባጮችን በድንገት በመቆጣጠሩ እና ሌላው ቀርቶ ያሏቸውን የውስጥ ደጋፊዎች ለማግኘት እንዳይችሉ የኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ መዘጋት ለካይሮ የስልት መቃወስ ገጥሟታል። በመሆኑም የመረጃ መስመራቸው ሁሉ ጎርፍ እንደበላው አፈር በፍጥነት እንደተሸረሸረባቸው ነው የሚሰማው። በተመሳሳይ መንገድ በህወሓት መንደርም የሆነው ይሄው ነው።ህወሓት ዛሬ ቢጨንቃት ምሽት ላይ መያዣ መጨበጫ የጠፋው መግለጫ አውጥታለች። መግለጫው በራሱ የሚያሳየው ጉዳይ ቢኖር ግራ የተጋባ ሰው ቃላትን ሰብስቦ በአንድ ጆንያ ያጨቀው እንጂ መሰረታዊ የመግለጫው መልዕክት በራሱ መግለጫውን ላወጣው አካልም ግልጥ አይደለም።
አሁን መንግስት ትኩረቱ በህወሓት ቀንደኛ ተጠያቂ ባለስልጣናት ላይ አነጣጥሯል።የመቀሌ ሕዝብም ከምሽት ጀምሮ እንቅስቃሴው ቀንሷል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወታደራዊ ደንብ ልብስ ለብሰው መግለጫ መስጠታቸው በራሱ ለህወሓት መልዕክት ማስተላለፋቸው መሆኑን የተረዳው የመቀሌ ሕዝብ ቁጥሩ ቀላል እንዳልሆነ የሚናገሩ አሉ።
በመጨረሻም ሕዝቡ ህወሓት ሰልችታዋለች።ህወሓት ተወግዳ በነፃነት ከጎንደር እስከ ሞያሌ፣ ከአስመራ እስከ ምፅዋ ተንቀሳቅሶ እና ነግዶ የሚኖርበት ሕይወት ናፍቆታል።ስለሆነም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነፃ እንዲያወጣው በጉጉት እየጠበቀ ነው።በእርግጥ በውጭ ሀገር ያሉ እንደ መቀሌ እና አዲግራት ሕዝብ ውሃ ያልጠማቸው በማኅበራዊ ሚድያ ህዝቡ ከህወሓት ጋር እንደሆነ ጧት ማታ እያወሩ ነው።እነርሱ ይዘውት የወጡትን የህዝቡን ዳቦ መብያ ገንዘብ እየተምነሸነሹ በሕዝቡ ላብ እና ደም የሚቀልዱ ናቸው።ለሁሉም ግን ኢንተርኔት ከመቀሌ ነፃ መሆን በፊት ላይከፈት ይችላል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ስለ ዓባይ ያዜሙት ድንቅ ኢትዮጵያዊ ዜማ ቪድዮ ይመልከቱ
Thursday, July 2, 2020
ሰው ከእንስሳ የሚለየው ማሰብ በመቻሉ ነው - የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ወንድም ሐብታሙ ሁንዴሳ ከወንድሙ ቀብር በኃላ ለቪኦኤ ዛሬ ከሰጠው ቃል (ሙሉውን ቪድዮ ይመልከቱ)
''ስለቀብሩ መጠየቅ ያለበት ቤተሰብ ነው። ሬሳ እንዳይቀበር ፀብ መፍጠር እና ሌላ ሰው እንዲሞት ማድረግ ይሄ ማሰብ አይመስለኝም።ሰው ከእንስሳ የሚለየው በማሰቡ ነው።ማሰብ ደግሞ ትልቅ ነገር ነው።ነገሮችን በስሜት ከመነዳት ወጣቱ እንዲያስብ የሚል መልዕክት አስተላልፋለሁ።''
ሐብታሙ ሁንዴሳ
Video source= VOA Amharic Service July 2,2020
Wednesday, July 1, 2020
ሰበር ዜና - ጀዋር መሐመድ፣በቀለ ገርባ እና ግብረ አበሮቹ በሰኞ ዕለቱ ግድያ ብቻ ሳይሆን ከእዚህ በፊት ባደረጉት ቅስቀሳ እና በጥቅምት ወር ለሞቱት 97 ሰዎች ወንጀል ሁሉ እንደሚከሰሱ የፌድራል ፖሊስ አስታወቀ
>> ከአሁን በኃላ ለሕግ ቀርበው በፍትህ እንጂ በሽምግልና የሚፈታ ምንም ነገር የለም - የፌድራል ፖሊስ
የፌደራል ፖሊስ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኃላፊው በኩል በሰጠው መግለጫ የጀዋር መሐመድ ቡድን በአስከሬን ነጠቃ ብቻ አይደለም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ብሏል ፖሊስ በማብራርያው።ግለሰቦቹ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችን በመግደል በአዲስ አበባ ላይ የሰኔ 15ቱ ዓይነት እልቂት ለመፈፀም ቀደም ብለው አቅደው እንደነበር ነው ከምርመራው ሂደት የተረዳነው እና እየወጡ ያሉት መረጃዎች ያለው የፖሊስ መግለጫ፣በእነ ጀዋር ላይ የሚደረገው ክስ በእዚህ ሳምንት ባደረጉት የመግደል ሙከራ ብቻ ሳይሆን ከእዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሲቀሰቅሱ የነበሩበት ሂደት እና በጥቅምት ወር ላይ ባደረጉት ቅስቅሳ ለጠፋው የ97 ሰው ሞት ጭምር ጉዳዩ ተመርምሮ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተሰጠው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።
የፖሊስ ኮሚሽነሩ መግለጫ በተለይ የእነጀዋርን ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ ከአሁን በኃላ በሽምግልና ወይንም በሌላ መንገድ የሚታይ ምንም ዓይነት ዕድል አለመኖሩን እና ጉዳዩ በአስቸኩአይ አዋጅ ውስጥ ብንሆንም ለሕግ እና ስርዓት መከበር ምርመራው በሚገባ ተፈፅሞ ለፍርድ ይቀርባሉ ብለዋል።የምርመራውን ውጤትም በእየጊዜው ለሕዝብ እንደሚገለጥ ነው የፖሊስ ኮሚሽነሩ ያብራሩት።
"ደወል" በገጣሚት ረድኤት ተረፈ
ከጦብያ ግጥምን በጃዝ የተወሰደ
ግጥሙ ከላይ ከተፃፈው ዜና ጋር አይገናኝም
Subscribe to:
Posts (Atom)
ወቅታዊው እና መጪው የኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ምጣኔሃብታዊ እና ማኅበራዊ ሁኔታ በሶስት ርዕሶች ማጠቃለል ይቻላል።
ፎቶ ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2017 ዓም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ መትከል ብሔራዊ ዘመቻ ሲከፍቱ። ========= ጉዳያችን ምጥን ======== በእዚህ ጽሑፍ ስር ሶስት ምጥን ርዕሶች ያገኛሉ። እነርሱም አ...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...
-
የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉዳያችን/ Gudayachn ሰኔ 2/2011 ዓም (ሰኔ 8/2019 ዓም) ግንቦት 29/2011 ዓም ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በለቀቀው ዜና እንዲህ ይነበባል: - ...
-
Gudayachn Report August 14,2020 Senior Hydrologists and water resource Engineers webinar presentation and discussions on creating awareness ...