ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, May 16, 2022

የክረምቱ ወራት ሳይመጣ በሽብርተኛው ህወሃት እና ሸኔ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያንን ከበለጠ ፈተና እናድናቸው።

በሽብርተኛው ህወሃት የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን 
ፎቶ =አል ዐይን
==============
ጉዳያችን / Gudayachn
==============

በሽብርተኛው ህወሃት እና ሸኔ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን በመቶ ሺዎች ይቆጠራሉ። ተፈናቃዮቹ እስካሁን ከሕዝብ በሚያገኙት ድጎማ፣በመንግስት እርዳታ እና ከውጭ የተገኘ መጠነኛ ድጋፍ ህይወታቸውን ለመግፋት ሞክረዋል።ሁኔታው በተለይ ለወለዱ እናቶች፣ለሴቶች እና ለህጻናት የበለጠ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳሉ በተደጋጋሚ ተገልጧል።ወደ ቀደመ ቦታቸው መመለስ ወይንም በጊዜያዊነት ባሉበት መጠለያቸው መስተካከል አለበት።

ዛሬ ግንቦት 8/2014 ዓም በርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮንን በሰጡት መግለጫ አሸባሪው ህወሓት (የትግራይ ወራሪ ቡድን) በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ማድረሱን ዩንቨርሲዎች፣የክልሉ መንግሥትና የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ለአምስት ወራት ባጠኑት ጥናት መረጋገጡን ገልጠዋል።

በእዚህም መሰረት በአማራ ክልል ብቻ ከ828 ሺህ ሕዝብ በላይ ላይ ቀጥተኛ ጉዳት መድረሱን እና ከ288 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳዊ ውድመት እንደደረሰ ጥናቱ ማሳየቱን አቶ ስዩም መኮንን አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፋርም በተመሳሳይ በሽብርተኛው ህወሃት የእብሪት ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር ከ300 ሺህ በላይ እንደሆነ ከሳምንታት በፊት ክልሉ ማስታወቁን ዲደብሊው ራድዮ መዘገቡ ይታወሳል። በተለይ በአፋር የተፈናቀሉት ተሰደው ለመኖር የተገደዱት ለሰው ልጅ አደገኛ በሚባሉ እንደ አድፌራ የተባሉ ቦታዎች መሆኑ ጉዳዩ አደገኛ ያደርገዋል።

በአማራ ክልል በአሁኑ ጊዜ ተፈናቅለው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሽብርተኛው ህወሃት ብቻ ሳይሆን የእርሱ ተቀጥላ አሸባሪ ሸኔ ከወለጋ እና የተለያዩ የኦሮምያ ክልል አካባቢዎች የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በደብረብርሃን፣ደብረ ታቦር እና በጎጃም የተለያዩ ቦታዎች በጊዜያዊ መጠለያዎች ይገኛሉ።

ባጠቃላይ ወቅቱ በተለያዩ ቦታዎች ተሰደው እና በሜዳ ካለመጠለያ የወደቁ ኢትዮጵያውያንን የክረምቱ ወራት ከመምጣቱ በፊት ከተቻለ ከመለስተኛ ማቋቋሚያ ጋር ወደ ቦታቸው በፍጥነት የሚመለሱበት ወይንም ባሉበት ጊዜያዊ መጠለያ ቦታ የክረምቱን ወራት የሚቋቋሙበት ጊዜያዊ ዳስ በፍጥነት ሊያገኙ የሚችልበት ሁኔታ ካልተመቻቸ ለባሰ አደጋ ይጋለጣሉ።ለእዚህም ተግባር ህዝብ፣ድርጅቶች እና የሃይማኖት ተቋማት በፍጥነት ሊንቀሳቀሱ ይገባል።ሌላው የፕላስቲክ እና ላስቲክ ኢንዱስትሪዎች በቀላሉ ሊንቀሳቀስ እና ሊተከሉ የሚችሉ ድንኳኖች ባጭር ጊዜ ፈጠራም ማዘጋጀት እና ወደቀያቸው በቅርብ መመለስል ላልቻሉ የሚዳረስበትን መንገድ መፈለግ አለባቸው። መንግስትም ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ የማስተባበር ስራውን ለክልሎች ብቻ መስጠት ሳይሆን የፌድራል መስርያቤቶች የተግባር ሥራ እንዲሰሩ ማድረግ እና መቆጣጠር ይገባዋል። በመጨረሻም የመገናኛ ብዙኃን ይህንኑ ችግር ለሕዝብ በማድረስ ከክረምቱ በፊት ጉዳዩ አፋጣኝ ትኩረት እንዲያገኝ የማድረግ ሥራ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

=============///===========

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...