ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, May 4, 2022

በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ከሕወሃት ጎን አሰልፈን አንዋጋም በማለታቸው እየታሰሩ መሆኑን ቢቢሲ በዛሬ ዜናው አስታውቋል።

Photo= Mitchellkphotos

Thousands of parents in the Tigray region in Ethiopia are arrested by TPLF for refusing to allow their children to fight against the Federal Government.
BBC Amharic report on May 4,2022 

(Read English translation under Amharic here below)

ቢቢሲ አማርኛ ሚያዝያ 26/2014 ዓም

ከእዚህ በታች ያለው ዘገባ ሙሉው ከቢቢሲ አማርኛ ሚያዝያ 26፣2014 ዓም ከጻፈው ዜና እንዳለ የተወሰደ ነው።

ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ የትግራይ ተወላጅ፤ ልጆች ለመዝመት ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ወላጅ አባቱ እና አጎቱ እንደታሰሩ ገልጿል።ለራሱና ለቤተሰቡ ደኅንነት ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ወጣት፤ "ቢያንስ ከቤተሰብ አንድ ሰው ውድትርና መላክ አለበት። መዋጣት አለበት የሚል ሕግ አለ" ይላል።

ይህ በአሁኑ ወቅት ከትግራይ ክልል ውጪ የሚገኘው ወጣት፤ "አባቴን ልጅህን አምጣህ አሉት። ማምጣት ስላልቻለ ለአንድ ወር አሰሩት። ከዚያ ደግሞ ወንድሜን እንዲያመጣ ብለው ለቀውት ነበር። አሁን ያለበትን ሁኔታ ባላውቅም ለመጨረሻ ጊዜ በስልክ ሳገኛቸው አባቴን አስረውት ነበር" በማለት ይናገራል።

ይህ ወጣት እንደሚለው አዋቂ የሆነው ወንድሙ በዚህ ጦርነት ተሳታፊ የመሆን ፍላጎት የለውም። "ወንድሜ እኮ ትልቅ ነው። ከፈለገ የአባቴን ፍቃድ ሳይጠይቅ ይሄድ ነበር። የያዙት ግን አባቴን ነው" በማለት ይናገራል።ልጆቻቸውን ወደ ጦር ሜዳ ባለመላካቸው አጎቱም ጨምር ለእስር መዳረጋቸውን ይህ ወጣት ይናገራል። "ከሁለት ወር በፊት አጎቴንም ሴት ልጁን አምጣ ብለው አስረውት ነበር። 18 ዓመት እንኳን አይሆናትም" ይላል።

"የደረሱ ልጆች የሉትም። በቤቱ ውስጥ ከትንንሾቹ መካከል ተለቅ ያለችው እሷ ነች። ስልክ ስለሌለ አሁን ያሉበትን ሁኔታ አላውቅም" ይላል።ይህ ወጣት እንደሚለው ከሆነ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የትግራይ ክፍል እያስተዳደረ ያለው ህወሓት ለመዝመት ፍቃደኛ ያልሆኑ ልጆች ወላጆችን ማሰር ከመጀመሩ በፊት ሰዎችን አስገድዶ ወደ ጦር ሜዳ ይልክ ነበር ይላል።

"ከዚህ በፊት በኃይል አስገድዶ የመወስደ ተግባር ነበር። ይሄ ብዙ አላስኬድ አላቸው። ከዚያ 'ወላጆችን ብንይዝ ይገባሉ [ወደ ትግል]' የሚል አካሄደ መጥቷል። ይሄ በትግራይ በጣም ችግር እየሆነ ነው። እንደ ሕግ ነው የወረደው" በማለት ያብራራል። ከዚህ ወጣት በተጨማሪ በጦርነቱ ለመዋጋት ፍላጎት ስለሌላቸው ወላጆቻቸው እንደተሳሩባቸው ከሚናገሩት መካከል በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ክብሮም በርሀ ይገኙበታል።

የባይቶና ዓባይ ትግራይ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ክብሮም በርሀ ታናሽ እህታቸው ለመዝመት ፍላጎት ስለሌላት ወላጅ እናታቸው በህወሓት መታሰራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

"እኛ ቤት ሁሉም ስደት ላይ ናቸው። ከ18 ዓመት በታች የሆነች እህቴ ብቻ አለች [በትግራይ]። እህቴ 'ለምን ትግል አልሄደችም' ብለው ነው እናቴ ያሰሯት" ሲሉ ተናግረዋል።አቶ ክብሮም በርሀ ግን "ትግል መሄድ አለመሄድ የግል ምርጫ ነው፤ ወደ ትግል አልወጣህም ተብሎ ወላጅን ማሰር ግን በዓለም ታይቶ የሚታወቅ ነገር አይደለም" ይላሉ።

"ወላጅ እናቴ እዚጊእምን ተኽለሃይማኖት ትባላለች። በጣም ያሳዝናል። ያልጠበቅኩት ነገር ነው። የእኔ እናት ስለሆነች ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ረሀቡ፣ ችግሩ ሳያንሰው፣ መደፈር ሳያንሰው አሁን ደግሞ የኔ በሚላቸው ካድሬዎች መንገላታቱ ያሳዝናል" ብለዋል።

የባይቶና ዓባይ ትግራይ የውጭ ጉዳይ ኃላፊው የትግራይ ተወላጆች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ፍትሕ ሳያገኙ መታሰራቸውን አውስተው "አሁንም ይህ በትግራይ ሲደገም ያሳዝናል" ሲሉ ተናግረዋል።አቶ ክብሮም ልጅ አልዘምትም ካለ የታመሙ ወላጆች ሳይቀሩ ለእስር እንደሚዳረጉ የገለጹ ሲሆን ፍርድ ቤት የሚቀርቡበት ሁኔታ ሳይኖር በርካታ ሰዎችም ትምህር ቤቶች ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ይናገራሉ።

ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገረው የትግራይ ክልል ነዋሪ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዳሉ ገልጾ ከእነዚህም መካከል አንዱ ወላጆች ልጆቻቸውን ለትግል እንዲልኩ መገደዳቸው አንዱ መሆኑን ይገልጻል።ለደኅንነቱ ሲባል ስሙን የማንጠቅሰው የትግራይ ክልል ነዋሪ፤ "ልጆቻችሁን አዋጡ እየተባልን ነው። መስተዳድር የለንም" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።

=================

==========================

Thousands of parents in the Tigray region in Ethiopia are arrested by TPLF for refusing to allow their children to fight against the Federal Government.

============================
BBC Amharic report on May 4,2022

=============================

A native Tigray region resident interviewed by the BBC: said his parents and uncle were arrested for refusing to allow children for TPLF. The young man who asked not to be named for the safety of himself and his family; "There is a law that says at least one person in the family must send and safety receive."

According to this young man, his older brother did not want to take part in this war. "My brother is big. If he wanted to, he could go without my father's permission. But they arrested my father," he said.

He says that because he (his father) did not send his children to the battlefield, he and his uncle were imprisoned. "Two months ago, my uncle was arrested and told to bring his daughter. She is not even 18 years old," he said.

"He has no grown-up children. She's the biggest one in the house. I don't know where they are now because there is no telephone."

According to the young man, the TPLF, which currently controls most of Tigray, used to send people to the battlefield before they could arrest the parents of children who refused to march.

"In the past, there was rape. This has a lot to do with it. Then came the 'if we take parents, they will [fight].In addition to the young man, Kibrom Berha, a member of the regional opposition party, said his parents had been arrested for refusing to fight in the war against the Federal Government.

The head of foreign affairs of Baito and Abay Tigray, Kibrom Berha, told the BBC that his younger sister had been arrested by the TPLF for refusing to participate in the civil war.

"Everyone in our house is in exile. There is only my sister under the age of 18 [in Tigray]. My sister was arrested for saying, 'Why didn't she go to war?' The TPLF, for its part, says there have been signs of arresting parents in the past, but now it has stopped. "Such things were signs at the cadre level, but there is no way to arrest parents in this way. "Whether or not to go to war is a personal choice; arresting a parent for not going to war is not uncommon in the world," said Kibrom Berha.

"My mother is still called Tehlehaimanot. It is very sad. It is something I did not expect. It is unfortunate that this is being repeated in Tigray," he said. Kibrom said that even if the child is not a child, sick parents will be arrested and many people will be detained in schools without trial. Another resident of Tigray told the BBC that there are currently many problems in the region, one of which is forcing parents to send their children to fight. An unnamed resident of the Tigray region for security reasons; "We are being told to donate your children. We have no government," he told the BBC.

Source = BBC Amharic May 4,2022

Link = https://www.bbc.com/amharic/news-61316845 

===============

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...